አባ ጥያቄ አለኝ? ልጄ መልስ አለኝ!


አባ ጥያቄ አለኝ ልጄ መልስ  አለኝ

አባ ጥያቄ አለኝ? ልጄ መልስ አለኝ!

1 ኛ፣አባት፡ እግዚአብሔርም በሰላም ውስጥ ሆኖ ለልጁ መለሰ እንዲህም አለ፦

ልጄ ያለ እውቀት በሚነገር ቃል ምክርን የምታጨልም አንተ ማን መሆንክን አላስተዋልክምን? ወደ ልጅነት ክብርህ መመለስህንስ ገና ተሰውሮብሃልን?  እንግዲህ እንደ ሰው ወገብህን ታጠቅ እጠይቅሃለሁ፥
አንተም ተናገረኝ። በውኑ የሚከራከር ሰው
ሁሉን ከሚችል አምላክ ጋር ይከራከራልን?ከእግዚአብሔር ጋር የሚዋቀስ እርሱ ይመልስለት።

ልጅ:እነሆ፥ እኔ ወራዳ ሰው ነኝ፤ የምመልስልህ ምንድር ነው?

እጄን በአፌ ላይ እድታስጭነኝ አውቃለሁና አልከራከርም። አባት ሆይ ልጅህም መለሰ እግዚአብሔርንም እንዲህ አለው፦ ከአንተ ልማር እወዳለሁና ብትወድስ እንድጠይቅ ፈቀድልኝ

2 ኛ፣አባት፡ እወዳለሁ ጠይቅ ልጄ

ልጅ:ጌታየና አባቴ ሆይ ለምን ብዙ ጊዜ የምናምናቸው ሰዎሽ ሳይቀሩ እውነት ያልሆኑ ነገሮች ለምን ይነግሩናል?

3 ኛ፣አባት:ሁለት ምክንያቶች አሉ ልጄ ፤ አንዱ የተነገራቸውን እንደ ቁራና እንደ ፓሮት ይደግሙታል ይህም የሚሆነው ሃይሌንና መጽሓፍትን ስለ ማያውቁ ለስተት የተጋለጡ ናቸውና። አብዛኛውን ጊዜ ዘየዎችን ለመደገፍ አብዛኛውን ታዋቂ ነገሮችን ለማመን ይቀላቸዋልና። ሌላው ምክንያት ነቢያቱ በውሸት በስሜ ትንቢት ይናገራሉ፤
አላልክኋቸውም፥አላዘዝኋቸውም፥ አልተናገርኋቸውም፤ የውሸቱን ራእይ ምዋርትን ምከንቱንም ነገር የልባቸውንም ሽንገላ ይሰብኩላችኋል።ትንቢተ ኤርምያስ14/14

ልጅ፤ ታዲያ ከእውነት ወይም ከውሸት ዘንድ እንደሆኑ ነብያትን እንዴት እንለያለን?

4 ኛ፣አባት፤ በቃሌ ስታስተውል ጥሩ ምሳሌዎችን ለትምህርትህ ታገኛለህ። ለምሳሌ ሉቃ1፡76/79 ስለ ነብዩ ዮሃንስ ስናገር ያልኩት እንዲህ ነበር።
76ደግሞም አንተ ሕፃን ሆይ፤ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፤

የጌታን መንገድ ለማዘጋጀት በፊቱ ትሄዳለህና፤

77የኀጢአታቸውን ስርየት ከማግኘታቸው የተነሣ፤

ለሕዝቡ የመዳንን ዕውቀት ትሰጥ ዘንድ፣

78ከአምላካችንም በጎ ምሕረት የተነሣ፣

የንጋት ፀሓይ ከሰማይ ወጣችልን፤

79ይኸውም በጨለማ ለሚኖሩት፣

በሞት ጥላ ውስጥም ላሉት እንዲያበራና፣

እግሮቻችንንም ወደ ሰላም መንገድ እንዲመራ ነው።”

ልጅ፡ ድንቅ ነው ጌታዮ ። አሁን ከዚህ ሳስተውል ነብይ ለህዝቡ የሚሰጠው የመዳንን ዕውቀት፤ የኀጢአታቸውን ስርየት ማግኘታቸውን፤

ይህም ከአምላካችንም በጎ ምሕረት የተነሣ፣ መሆኑን ለህዝቡ ማስረዳት፤ እንዲሁ ነብይ እግሮቻችንንም ወደ ብርሃንና ወደ ሰላም መንገድ እንዲመራና የሚመራም ነው። ይኸውም በጨለማ ለሚኖሩት፣ በሞት ጥላ ውስጥም ላሉት የሚያበራ ነው፣

5 ኛ፣ አባት፡ አዎን በቀላሉ ነብያቶቼ ያነሳሳሉ ያንፃሉ የእየሱስ መንፈስ የትንቢት መንፈስ ነውና።

ልጅ፡ ታዲያ እኮ በድሮው ጊዜ ነብያቶች ግን መጥፎ ዜና ይዘው መጥተው ነበር እኮ።

6ኛአባት፡ ያ የሚወስነው መጥፎ የሚባለው ነገሩን ከምታይበት መአዝን ነው። በንስር በእንቁራሬት እይታ ምሳሌ ላስረዳህ አንድ ትልቅ ህንፃ አለ እንበል እንቁራሪቱ ከአንድ ጥግ ሆኖ ሊያይ የሚችለው የተወሰነ የህንፃውን ጥግ ነው ለእሱ እውነት ያ የሚያየው ወስን እይታው ነው ንስር ከሰው 50 እጥፍ አይኖቸ አጉልተው ያያሉና ከፍ ካለው በላይ ከፍ ብሎ ህንፃውን ብቻ ሳይሆን በዙርያው ያለውን ሁሉ በአንድ ግዜ ማየት ይችላል።  የእግዚአብሄር አይኖች በምድር ሁሉ ላይ ናቸው የሚል ቃሌን አስተውለሃልን ? ስለ ዚህ የነገሮችን እውነተኛ ተፈጥሮ ከኔ ከማየው ማለትም በክርስቶስ በቀኜ ከተቀመትክበት ካየከው ሁሉ ለበጎ እንደሆነ ማስተዋል ትችላለህ ከአንድ ጥግ ካየከው ግን ይለያል ውስንም እይታ ይኖርሀል።

ልጅ፡ አሃ …እኔ እንካን የድሮ ጊዜ የጥፋት ትንቢቶቹ መጥፎ ስለ ሚመስሉኝ ነበር

6 -1ኛ፣ አባት፡ ለመጠገን መስበር ሲቀድም ማለትህ ነውን?፡ ለመገንባት ማፍረስ ሲቀድም? ጆሮን ለመክፈት መከራ ወይም ውጥረት ሲቀድም?፡ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድድ ቀን ሳመጣ፤ ትዕቢተኞችና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ እንደ ገለባ ገለባ ሲሆኑ ማለትህ ነው?

እኔ እንደ አንጥረኛ እሳትና እንደ አጣቢ ሳሙና ተምሳሌት የምመጣበትን ቀን ማንም መታገሥ ማንም የማይችልበትን
ነው? እኔ በተገለጠ ጊዜ የሚቆም የማይኖርበትን ነው?እንደ ባርያየ ዳዊት ሥርዓትህን እማር ዘንድ ያስጨነቅኸኝ መልካም ሆነልኝ። ሳስብላቸው?

እኔ ብርን እንደ ሚያነጥርና እንደ ሚያጠራ ሰው ስቀመጥ፥ ካህናትና ልጆችን ሳጠራ፥ እንደ ወርቅና እንደ ብርም
ሳነጥራቸው፤ እነርሱም ለእግዚአብሔር በጽድቅ ምስጋናየንና በጎነቴን እንዲያውጁ ሳደርጋቸው ማለትህ ነው? እኔ የምባላ እሳት ነኝና ሰውን ሁሉ በመንፈሴ እሳት ስቀምመው ማለትህ ነውን?

ልጅ፡ የሚገርም ነው አባት ሆይ። ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሃለች፤መንፈሴም በውስጤ ትፈልግሃለች። ፍርድህን ወደ ምድር በመጣ ጊዜ፣

የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ጽድቅን ይማራሉ ያልከውን ቃልህን አስታወስኩ። ክፉዎች ርኅራኄ ቢደረግላቸው እንኳ፣ ጽድቅን አይማሩም፤

በቅንነት ምድር እንኳ ክፋትን ያደርጋሉ፤
የእግዚአብሔርንም ግርማ አያስተውሉም። ሃጥእን እሽሩሩ ብትለው ሞገስንም ብታደርግለት እንካ ጽድቅን እንደ ማይማር የተናገርከውን አስታወስኩ ፍርድህ ወደ ምድር በመጣ ጊዜ፣ግን ሁሉ ጽድቅን ይማራሉ።

7ኛ፣ አባት፡ ልጄ ብዙዎች እውነትን ለመገናኘት መጽሐፍትን ይመረምራሉ አንተ ግን አስተውል መጽሐፍት ሁሉ ወደ እኔ ወደ እውነት ይጦቁሙሃል እንጂ ፊደሉ ላይ እንድትታቆር አይሉሁም ህይወት እንዲ ሆንልህና እንዲ በዛልህ ወደኔ ወደ ህይወት ተጣበቅ።

ልጅ፡ ጌታ ሆይ ስለ አንተ ከመጀመርያው፡ንገረኝ

8ኛ፣ አባት፡ ከሁሉ በፊት እኔ እ/ር እንደ ነበርኩ ታውቃለህ ? በቃ እኔ እግዚአብሔር መጀመሪያ ነኝ!ኦሪት ዘፍጥረት 1/1 በመጀመሪያ እግዚአብሔር። በቃ እኔ እግዚአብሔር መጀመሪያ ነኝ!

‘ገና ተራሮች ሳይወለዱ፣ ምድርንና ዓለምን
ከመፍጠሬ በፊት፣ እኔ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላክ ነኝ።
መዝሙር 90:2

‘ይህን የሠራና ያደረገ፣ ትውልድን ከጥንት የጠራ ማን ነው? እኔ እግዚአብሔር  ከፊተኛው፣ ከኋለኛውም ጋር፤ እኔው ነኝ።”   ‘ኢሳይያስ 41:4

ትንቢተ ኢሳይያስ 41/4 ይህን የሠራና ያደረገ፥ ትውልድንምከጥንት የጠራ ማን ነው? እኔ እግዚአብሔር፥ ፊተኛውበኋለኞችም ዘንድ የምኖር እኔ ነኝ።

10 ደግሞ፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ሰማዮችም የእጆችህ ሥራ ናቸው፤ 11 እነርሱም ይጠፋሉ አንተግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፥ 12 እንደመጎናጸፊያም ትጠቀልላቸዋለህ ይለወጡማል፤ አንተ ግን አንተነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም ይላል።ወደ ዕብራውያን 1

የዮሐንስ ራእይ 22/13 አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።

9ኛ,አባት፡ ልጄ ሁሉ ነገር ከኔ እንደ ወጣ ታስተውላለህን?
የእግዚአብሔር የጥበቡና የዕውቀቱ ባለጠግነት ወይም ጥበቡና እውቀቱ እንዴት ጥልቅ ነው!

ፍርዱ አይመረመርም፤

ለመንገዱም ፈለግ የለው …

34“የጌታን ልብ ያወቀ ማነው?

አማካሪውስ የነበረ ማን ነው?”

35“እግዚአብሔር መልሶ እንዲሰጠው፣

ለእግዚአብሔር ያበደረ ከቶ ማን ነው?”

36ሁሉም ከእርሱ፣ በእርሱ፣ ለእርሱ ነውና፤

ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።11/34

34.  For who knows (knew by intimate experience) the Lord’s [= Yahweh’s] mind? Or, who becomes (came to be) His planning adviser (His design counselor; the one who makes determinations with Him)? 35.  Or, who gives to Him first, and it will be repaid to him? 36.  Because, forth from out of the midst of Him, and through the midst of Him (or: through means of Him), and into the midst of Him, [is] the whole (everything; [are] all things)! By Him (In Him; To Him; For Him) [is] the glory (the manifestation of that which calls forth praise; the reputation; the notion; the opinion; the credit; the splendor) into the ages.  It is so (Amen; So be it)! Romans 11:34

10ኛ፣አባት፡ ክርስቶስ የፍጥረት በኩራት እንደሆነ ታስተውላለህን?

ቆላስያስ1/13 እርሱ ከጨለማ አገዛዝ ታደገን፤ ወደሚወደው ልጁ መንግሥትም አሻገረን፤ 14በእርሱም መዋጀትን በደሙ1፥14 አንዳንድ ቅጆች በደሙ የሚለው ቃል የላቸውም አግኝተናል፤ ይህም የኀጢአት ይቅርታ ነው።15እርሱ የማይታየው አምላክ አምሳል ነው፤ ከፍጥረት ሁሉ በፊት1፥15 ወይም በላይ በኵር ነው፤ 16ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል፤ በሰማይና በምድር ያሉ፣ የሚታዩና የማይታዩ፣ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ኀይላት፣ ገዦች ቢሆኑ ወይም ባለ ሥልጣናት፣ ሁሉም ነገር በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል። 17እርሱ ከሁሉ በፊት ነው፤ ሁሉም ነገር በአንድ ላይ ተያይዞ የጸናው በእርሱ ነው።

‘  “…..አሜን የሆነው፣ ደግሞም ታማኝና እውነተኛ ምስክር የሆነው፣ የእግዚአብሔርም ፍጥረት ገዥ የሆነው እንዲህ ይላል፤ ራእይ 3:14

Colossians1/13.  Who drags us out of danger (or: rescued us) forth from out of the midst of the authority of the Darkness (Darkness’s jurisdiction and right), and changes [our] position (transports {or: transferred} [us]; gave [us] a change of standing) into the kingdom of the Son of His love (of the Son Who has the characteristics and qualities of His love; the Son Whose origin is His love),

14.  in Whom we continuously hold (have) the redemption (the release and liberation procured by payment of a ransom): the sending away (the dismissal; the divorce) of the failures (of the errors pertaining to falling short and straying to the side of the target; of the sins; of the mistakes),15.  Who is the Image (the Exact Formed Likeness; the Figure and Representation; visible likeness) of the not-seen God (the unable to be seen God; the invisible God), the Firstborn of all creation (or: of every creature; of every framing and founding; of every act of reducing from a state of disorder and wildness) [= the Inheritor of all creation; the One who will assume authority over every creature],

11ኛ፤ አባት፡ ልጄ ይህንንስ ታስተውላለህ?ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል፤ በሰማይና በምድር ያሉ፣ የሚታዩና የማይታዩ፣ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ኀይላት፣ ገዦች ቢሆኑ ወይም ባለ ሥልጣናት፣ ሁሉም ነገር በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል። 17እርሱ ከሁሉ በፊት ነው፤ ሁሉም ነገር በአንድ ላይ ተያይዞ የጸናው በእርሱ ነው።

ዮሐንስ 1/1በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። 2እርሱም በመጀመሪያ ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ። 3ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል፤ ከተፈጠረው ሁሉ ያለ እርሱ የተፈጠረ ምንም የለም። 4ሕይወት በእርሱ ነበረች፤ ይህች ሕይወት የሰው ብርሃን ነበረች።

ቆላ1/12በቅዱሳን ርስት በብርሃን ተካፋዮች ለመሆን ያበቃንን1፥12 ወይም ያበቃችሁን አብን እንድታመሰግኑ ነው። 13እርሱ ከጨለማ አገዛዝ ታደገን፤ ወደሚወደው ልጁ መንግሥትም አሻገረን፤ 14በእርሱም መዋጀትን በደሙ1፥14 አንዳንድ ቅጆች በደሙ የሚለው ቃል የላቸውም አግኝተናል፤ ይህም የኀጢአት ይቅርታ ነው። ክርስቶስ ከሁሉ በላይ15እርሱ የማይታየው አምላክ አምሳል ነው፤ ከፍጥረት ሁሉ በፊት1፥15 ወይም በላይ በኵር ነው፤ 16ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል፤ በሰማይና በምድር ያሉ፣ የሚታዩና የማይታዩ፣ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ኀይላት፣ ገዦች ቢሆኑ ወይም ባለ ሥልጣናት፣ ሁሉም ነገር በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል። 17እርሱ ከሁሉ በፊት ነው፤ ሁሉም ነገር በአንድ ላይ ተያይዞ የጸናው በእርሱ ነው።

12ኛ፡ አባት፡ የፈቃዴን ምስጢር እንደ በጎ ሐሳቤ ሁሉን በዘመን ፍጻሜ ይሆን ዘንድ ያለው ሐሳቤ በሰማይም በምድርም ያሉትን ነገሮች ሁሉ ራስ በሆነው በክርስቶስ ሥር እንደ ምጠቀልለው ታውቃለህ? ከአፌ ቃል ከወጣስ ሆነ ማለት እንደሆነ ታስተውላለህ?የነገር ጅማሪ ብቻ ሳይሆን ፍፃሜውንም እንደ ተናገርኩ ታስተውላለህን?

ኤፌ1/9በክርስቶስ ያቀደውንም የፈቃዱን ምስጢር እንደ በጎ ሐሳቡ እንድናውቅ1፥8-9 ወይም ጸጋውን አበዛልን በጥበብና በአእምሮ ሁሉ፣ 9… አሳወቀን አደረገ። 10በዘመን ፍጻሜ ይሆን ዘንድ ያለው ሐሳቡ በሰማይም በምድርም ያሉትን ነገሮች ሁሉ ራስ በሆነው በክርስቶስ ሥር ለመጠቅለል ነው።

13ኛ፡ አባት፡ እኔ እግዚአብሔር ለሁሉም ምሕረት አደርግ ዘንድ ሰውን ሁሉ ባለመታዘዝ እንደ ዘጋሁት ታስተውላለህን?

‘እግዚአብሔር ለሁሉም ምሕረት ያደርግ ዘንድ ሰውን ሁሉ ባለመታዘዝ ዘግቶታልና።  ‘ሮሜ 11:32

‘መጽሐፍ ግን ዓለም ሁሉ የኀጢአት እስረኛ መሆኑን ያውጃል፤ ይኸውም በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው ተስፋ ለሚያምኑት ሁሉ ይሰጥ ዘንድ ነው።  ‘ገላትያ 3:22

14ኛ፡ አባት፡ ሁሉ በፀጋ ይሆን ዘንድ ለሕይወት የሚሆን ንስሐን እና እምነትን የምሰጥ እኔው እንደ ሆንኩና እኔ ካልሳብኩት በቀር ማንም ሰው ወደ ክርስቶስ ሊመጣ እንዳይችላ ታስተውላለህን?

የሐዋርያት ሥራ 11/18 ይህን በሰሙ ጊዜም ዝም አሉና፦እንኪያስ እግዚአብሔር ለአሕዛብ ደግሞ ለሕይወት የሚሆንንስሐን ሰጣቸው
እያሉ እግዚአብሔርን አከበሩ።

ወደ ሮሜ ሰዎች 12/3 እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ የእምነትንመጠን እንዳካፈለው

‘ወዳጆች ሆይ፤…. ነገር ግን ለቅዱሳን አንዴና ለመጨረሻ ስለተሰጠው እምነት(Greek 4102 pistis pis’-tis, Faith) ….’ይሁዳ 1:3

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12/9 ለአንዱም በዚያው መንፈስ እምነት….ይሰጠዋል።

የዮሐንስ ወንጌል 6/44 የላከኝ አብ ከሳበው በቀር ወደ እኔሊመጣ የሚችል የለም፥

15ኛ፡ አባት፡ ፍጥረት ሁሉ ለከንቱነት እንዳስገዛሁት፤ ይኸውም በራሱ ምርጫ ሳይሆን፣ ለተስፋ እንዲገዛ ካደረግሁት ከእኔ የተነሣ እደሆነ ታስተውላለህ?

ሮሜ8/20 ፍጥረት ሁሉ ለከንቱነት ተዳርጎአል፤ ይኸውም በራሱ ምርጫ ሳይሆን፣ ለተስፋ እንዲገዛ ካደረገው ከፈቃዱ የተነሣ ነው።8፥20-21 ወይም በተስፋ አስገዝቶታል። 21ይህም ፍጥረት ራሱ ከመበስበስ ባርነት ነጻ ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደ ሆነው ወደ ከበረው ነጻነት እንዲደርስ ነው።

Romans 8/20.  For the creation (that which was framed and founded) was placed and arranged under, in emptiness (was subordinated to vanity; was subjected by futility; was arranged under, in unprofitableness for frivolous idleness), not voluntarily (willingly), but rather because of (on account of; for the sake of) the one (or: the One) placing [it] under and arranging [it] in subordinated subjection upon an expectation (a hope)

Rom 8/20 For the creature was made subject to vanity, not willingly, but by reason of him(God) who hath subjected the same in hope,

16ኛ፡ አባት፡ ፍጥረትን ራሱ ከመበስበስ ባርነት ነጻ አውጥቼ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደ ሆነው ወደ ከበረው ነጻነት እንደ ማመጣው ታውቃለህ?

ሮሜ8/22 ‘ይህም ፍጥረት ራሱ ከመበስበስ ባርነት ነጻ ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደ ሆነው ወደ ከበረው ነጻነት እንዲደርስ ነው። እስከ አሁን ድረስ ፍጥረት ሁሉ በምጥ ጊዜ እንዳለው ሥቃይ በመቃተት ላይ እንደሚገኝ እናውቃለን። 23እርሱ ብቻ ሳይሆን፣ የመጀመሪያውን የመንፈስ ፍሬ ያገኘን እኛ ራሳችን የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን ልጅነታችንን በናፍቆት እየተጠባበቅን በውስጣችን እንቃትታለን።

17ኛ፡ አባት፡ እኔ ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነትን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ እንደምፈልግ በአንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን።

‘እርሱ ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነትን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ ይፈልጋል። ‘1 ጢሞቴዎስ 2:4

‘አንዳንድ ሰዎች የዘገየ እንደሚመስላቸው ጌታ የተስፋ ቃሉን ለመፈጸም አይዘገይም፤ ነገር ግን ማንም እንዳይጠፋ ፈልጎ፣ ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃ ስለ እናንተ ይታገሣል።  ‘2 ጴጥሮስ 3:9

18ኛ፡ አባት፡ ሁሉን በፈቃዴ ምክር መሠረት እንደሚሠራው እንደ እራሴ ዕቅድ እንደምሰራ ታስተውላለህን?

”ሁሉን በፈቃዱ ምክር መሠረት እንደሚሠራው እንደ እርሱ ዕቅድ አስቀድሞ የተወሰንን እኛ ደግሞ በእርሱ ተመርጠናል፤  ‘ኤፌሶን 1:11

መዝ33/8 ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን ትፍራው፤ በዓለም የሚኖር ሕዝብ ሁሉ በፊቱ ይንቀጥቀጥ።

9እርሱ ተናግሮአልና ሆኑ፤ አዞአልና ጸኑም። 10 እግዚአብሔር የሕዝቦችን ምክክር ከንቱ ያደርጋል፤

የሕዝብንም ዕቅድ ያጨናግፋል። 11 የእግዚአብሔር ሐሳብ ግን ለዘላለም ይጸናል፤ የልቡም ሐሳብ ለትውልድ ሁሉ ነው።

‘ዕጣ በጒያ ውስጥ ይጣላል፤ ውሳኔው በሙሉ ግን ከእግዚአብሔር  ዘንድ ነው።’ምሳሌ 16:33

‘የሰው አካሄዱ በእግዚአብሔር  ይመራል፤ ሰውስ የገዛ መንገዱን እንዴት ማስተዋል ይችላል?’ ምሳሌ 20:24

19ኛ፡ አባት፡ ለሰዎች ሁሉ በተለይም ለሚያምኑት አዳኝ እንደ ሆንኩ ታውቃለህ?

‘ይህ ቃል የታመነና ሙሉ ለሙሉ ሊቀበሉት የሚገባ ነው፤ ለዚህ ብለን እንጥራለን፤ እንደክማለንም፤ ይኸውም ለሰዎች ሁሉ በተለይም ለሚያምኑት አዳኝ በሆነው በሕያው እግዚአብሔር ተስፋ ስለምናደርግ ነው። ‘1 ጢሞቴዎስ 4:9-10

20ኛ፡ አባት፡ ሁሉ በአዳም እንደሞቱ እንደዲሁ ሁሉም በክርስቶስ ሕያዋን እንደሚሆኑ ።ነገር ግን ለእያንዳንዱ ሰው በራሱ ተራ እንደማደርገው እቅዴን ታውቃለህ?

ሁሉ በአዳም እንደሞቱ እንደዲሁ ሁሉም በክርስቶስ ሕያዋን ይሆናሉ።ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው በራሱ ተራ ይሆናል። 1ቆሮ 15/22

21ኛ፡ አባት፡ አዳም ሁሉን ወደ ሃጥያት ይዞ ለመውደቅ አቅም እንደ ነበረው ሁሉ ክርስቶስም ይበልጡኑ ሁሉን ወደ ጽድቅ ይዞ ሊነሳ የበለጠ ሃይል እንዳለው በአንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን።

‘እኔ ግንከምድር ከፍ ከፍ ባልሁ ጊዜ ሰውን ሁሉ ወደ ራሴ እስባለሁ።” ዮሐንስ12:32

ከአእምሮ ውጪ ብንሆን ለእግዚአብሔር ብለን ነው፤ ባለ አእምሮም ብንሆን ለእናንተ ነው። 14የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናልና፤ ምክንያቱም አንዱ ስለ ሁሉ እንደ ሞተ እርግጠኞች ሆነናል፣ ከዚህም የተነሣ ሁሉ ሞተዋል። 15በሕይወት ያሉትም ለሞተላቸውና ከሙታን ለተነሣላቸው እንጂ ከእንግዲህ ለራሳቸው እንዳይኖሩ እርሱ ስለ ሁሉ ሞተ።2 ቆሮንቶስ 5/13

22ኛ፡ አባት፡ ከአፌ የሚወጣውም ቃሌ፣ በከንቱ ወደ እኔ እንደማይመለስ፤ ነገር ግን የምሻውን እንደ ሚያከናውን የተላከበትንም ዐላማ እንደሚፈጽም። በአንተ ዘንድ ማስተዋል ይሁን።

ኢሳይያስ 55/8“ሐሳቤ እንደ ሐሳባችሁ፣ መንገዴ እንደ መንገዳችሁ አይደለምና” ይላል እግዚአብሔር።

9“ሰማያት ከምድር ከፍ እንደሚሉ፣መንገዴ ከመንገዳችሁ፣ሐሳቤም ከሐሳባችሁ እንዲሁ ከፍ ያለ ነው።

10ዝናምና በረዶ ከሰማይ ወርዶ፣ምድርን በማራስ፣እንድታበቅልና እንድታፈራ

ለዘሪው ዘር፣ለበላተኛም እንጀራ እንድትሰጥ ሳያደርግ፣ወደ ላይ እንደማይመለስ ሁሉ፣

11ከአፌ የሚወጣውም ቃሌ፣በከንቱ ወደ እኔ አይመለስም፤

ነገር ግን የምሻውን ያከናውናል፤የተላከበትንም ዐላማ ይፈጽማል።

23ኛ፡ አባት፡ በመስቀሉ ላይ በፈሰሰው ደም ሰላምን በማድረግ በምድርም ሆነ በሰማይ ያለውን ነገር ሁሉ ከራሴ ጋር እንዳስታረቅኩትና በሰማይና በምድር ያሉ፣ የሚታዩና የማይታዩ፣ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ኀይላት፣ ገዦች ቢሆኑ ወይም ባለ ሥልጣናት፣ ሁሉም ነገር በእኔና ለእኔ ለደስታየ እንደፈጠርካቸው ታውቃለህን?

ቈላስይስ 1/16- ‘ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል፤ በሰማይና በምድር ያሉ፣ የሚታዩና የማይታዩ፣ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ኀይላት፣ ገዦች ቢሆኑ ወይም ባለ ሥልጣናት፣ ሁሉም ነገር በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል። ..19እግዚአብሔርም ሙላቱ ሁሉ በእርሱ ይሆን ዘንድ ወዶአልና፤ 20በመስቀሉ ላይ በፈሰሰው ደሙ ሰላምን በማድረግ በምድርም ሆነ በሰማይ ያለውን ነገር ሁሉ በእርሱ በኩል ከራሱ ጋር አስታረቀ።21ከክፉ ባሕርያችሁ የተነሣ1፥21 ወይም በክፉ ባሕርያችሁ እንደሚታየው ቀድሞ ከእግዚአብሔር የተለያችሁ በአሳባችሁም ጠላቶች ነበራችሁ። 22አሁን ግን ነውርና ነቀፋ የሌለባችሁ ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ሊያቀርባችሁ፣ በክርስቶስ ሥጋ በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ፤

የዮሐንስ ራእይ 4/10-11 ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይበተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወትለሚኖረው እየሰገዱ፦ ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ አንተ ሁሉንፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም (ለደስታህም for thy pleasure they are and were created ) ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብርውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል እያሉ በዙፋኑ ፊትአክሊላቸውን ያኖራሉ።

Rev 4 /11 Thou art worthy, O Lord, to receive glory and honour and power: for thou hast created all things, and for thy pleasure they are and were created.

24ኛ፡ አባት፡ በፍፁም መለኮትነቴ በክርስቶስ ተገልጬ ዓለምን ከራሴ ጋር ሳስታርቅ የሰዎችን በደል ሳልቆጥርባቸው ለእናተም ልጆቼ ደግሞ የማስታረቅ ቃል መስጠቴን በሙልአት ታስተውላለህን?

‘እግዚአብሔር በክርስቶስ ዓለምን ከራሱ ጋር ሲያስታርቅ የሰዎችን በደል አይቈጥርባቸውም ነበር፤ ለእኛም ደግሞ የማስታረቅ ቃል ሰጠን። ‘2 ቆሮንቶስ 5:19

25ኛ፡ አባት፡ ፍቅር ማለትም እኔ ለዘወትር እንደ ማልወድቅ ታውቃለህ?

‘ፍቅር ከቶ አይወድቅም፤ ‘1 ቆሮንቶስ 13:8

ኛ የዮሐንስ መልእክት 4/8 ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና።

ሮሜ8/35ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን ማን ነው? ችግር ነው ወይስሥቃይ፣ ወይስ ስደት፣ ወይስ ረሀብ፣ ወይስ ዕራቍትነት፣ ወይስአደጋ ወይስ ሰይፍ? 36ይህም፣

“ስለ አንተ ቀኑን ሙሉ ከሞት ጋር እንጋፈጣለን፤

እንደሚታረዱ በጎች ተቈጠርን”

ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።

37ምንም አይለየንም፤ በዚህ ሁሉ በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎችእንበልጣለን። 38ይህን ተረድቻለሁ፤ ሞትም ይሁን ሕይወት፣መላእክትም ይሁኑ አጋንንት፣8፥38 ወይም በሰማይ ያሉ አለቆችያለውም ይሁን የሚመጣው፣ ወይም ማንኛውም ኀይል፣39ከፍታም ይሁን ጥልቀት፣ ወይም የትኛውም ፍጥረት፣በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካለው ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየንአይችልም።

26ኛ፡ አባት፡ በአንድ ሰው መተላለፍ የተነሣ ኵነኔ በሁሉ ሰው ላይ እንደ መጣ፣ እንዲሁም በአንዱ የጽድቅ ሥራ ለሰው ሁሉ ሕይወትን የሚሰጥ ጽድቅ እንደተገኘ እና በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኀጢአተኞች እንደሆኑ፣ በአንዱ ሰው መታዘዝ ደግሞ ብዙዎች ጻድቃን እንዲሆኑ በቃሌ አስተውለሃልን?

‘ከእንግዲህ በአንድ ሰው መተላለፍ የተነሣ ኵነኔ በሁሉ ሰው ላይ እንደ መጣ፣ እንዲሁም በአንዱ የጽድቅ ሥራ ለሰው ሁሉ ሕይወትን የሚሰጥ ጽድቅ ተገኘ። በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኀጢአተኞች እንደሆኑ፣ በአንዱ ሰው መታዘዝ ደግሞ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ።  ‘ሮሜ 5:18-19

27ኛ፡ አባት፡  ኢየሱስ ክርስቶስን እጅግ ከፍ እንደ ተደረገ፤ ከስምም ሁሉ በላይ የሆነውን ስም እንደ ተሰጠው፤   ይኸውም በሰማይና በምድር፣ ከምድርም በታች፣ ጒልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይንበረከክ ዘንድ፣  ምላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።  ደግሞስ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ ካልሆነ በቀር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ ነው ሊል እንዳይችል ታውቃለህ?

‘ስለዚህ እግዚአብሔር እጅግ ከፍ አደረገው፤ ከስምም ሁሉ በላይ የሆነውን ስም ሰጠው፤   ይኸውም በሰማይና በምድር፣ ከምድርም በታች፣ ጒልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይንበረከክ ዘንድ፣    ምላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።  ‘ፊልጵስዩስ 2:9-11

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12/3 ስለዚህ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ ሲናገር፦ ኢየሱስ የተረገመ ነው የሚል እንደሌለ፥ በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር፦ ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ

‘ጒልበት ሁሉ በእኔ ፊት ይንበረከካል፤ አንደበትም ሁሉ በእኔ ይምላል፤ ብዬ በራሴ ምያለሁ፤ የማይታጠፍ ቃል፣ ከአፌ በጽድቅ ወጥቶአል።   ስለ እኔም ሲናገሩ፣ ‘ጽድቅና ኀይል፣    በእግዚአብሔር  ብቻ ነው’ ይላሉ።” በእርሱ ላይ በቍጣ የተነሡ ሁሉ፣ ወደ እርሱ መጥተው ያፍራሉ።    ነገር ግን የእስራኤል ዘር ሁሉ፣    በእግዚአብሔር  ይጸድቃሉ፤ ሞገስንም ያገኛሉ።’ኢሳይያስ 45:23-25

28ኛ፡ አባት፡  ትንንሽ የሚመስሉ እንደ “ኢየሱስ ጌታ ነው” ብለህ በአፍህ ብትመሰክር፣ እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን፣ ትድናለህ እንደሚል ማንም በዚህ መልኩ ሊድን እንዲችል ታውቃለህ ?

‘ከእምነት የሆነው ጽድቅ ግን እንዲህ ይላል፤ “ ‘በልብህ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል?’ አትበል”፤ ይህ ክርስቶስን ለማውረድ ነው፤ “ወይም ‘ወደ ጥልቁስ ማን ይወርዳል?’ አትበል”፤ ይህም ክርስቶስን ከሙታን ለማውጣት ነው።  ነገር ግን ምን ይላል? “ቃሉ በአጠገብህ ነው፤ በአፍህና በልብህም ውስጥ ነው፤” የምንሰብከውም የእምነት ቃል ይህ ነው፤  “ኢየሱስ ጌታ ነው” ብለህ በአፍህ ብትመሰክር፣ እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን፣ ትድናለህ።  የምትጸድቀው በልብህ አምነህ ነው፤ የምትድነውም በአፍህ መስክረህ ነውና። ‘ሮሜ 10:6-10

29ኛ፡ አባት፡  ኢየሱስ ክርስቶስ ነው የኀጢአት ሁሉ ማስተስረያ እንደሆነ፤ ይኸውም  ለዓለም ሁሉ ኀጢአት እንጂ ለልጆች ብቻ እንዳይደለ ታውቃለህ?

‘ልጆቼ ሆይ፤ ይህን የምጽፍላችሁ ኀጢአት እንዳትሠሩ ነው፤ ነገር ግን ማንም ኀጢአት ቢሠራ፣ በአብ ዘንድ ጠበቃ አለን፤ እርሱም ጻድቁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱም የኀጢአታችን ማስተስረያ ነው፤ ይኸውም  ለዓለም ሁሉ ኀጢአት እንጂ ለእኛ ብቻ አይደለም። ‘1 ዮሐንስ 2:1-2

‘ምክንያቱም ሁሉም ኀጢአትን ሠርተዋል፤ የእግዚአብሔርም ክብር ጐድሎአቸዋል፤ በኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ቤዛነት እንዲያው በጸጋው ጸድቀዋል፤  በደሙም በሆነው እምነት፣ እግዚአብሔር የማስተስረያ መሥዋዕት አድርጎ አቅርቦታል፤  ይህንም ያደረገው ቀድሞ የተፈጸመውን ኀጢአት ሳይቀጣ በትዕግሥት በማለፍ ጽድቁን ለማሳየት ነው፤ ‘ሮሜ 3:23-25

‘እግዚአብሔር ፍቅሩን በመካከላችን የገለጠው እንዲህ ነው፤ እኛ በእርሱ አማካይነት በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ወደ ዓለም ላከ። ፍቅር ይህ ነው፤ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው ሳይሆን እርሱ እንደ ወደደንና ስለ ኀጢአታችን ማስተስረያ  ይሆን ዘንድ ልጁን መላኩ ነው። ‘1 ዮሐንስ 4:9-10

30ኛ፡ አባት፡ በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል አንድ አስታራቂ እንዳአለ፤ እርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ እንደሆነ፤ ራሱንም ለሰዎች ሁሉ ቤዛ አድርጎ ሰጠ፤ ታውቃለህ?ብዙ የምነገርህ ነገር አለ ሁሉን ግን አሁሉን ልትሸከመው አትችልም። እኔን አውቀከኝ አትጨርስምና ለዛም ነው ለዘልአለም ከኔ ጋር ያለከው ለዘልኧለም እኔን እተርክልህሃለሁ።

‘አንድ እግዚአብሔር አለና፤ ደግሞም በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል አንድ አስታራቂ አለ፤ እርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ ራሱንም ለሰዎች ሁሉ ቤዛ አድርጎ ሰጠ፤ ይህም በትክክለኛው ጊዜ ተመስክሮለታል። ‘1 ጢሞቴዎስ 2:5-6

ልጅ፤ በመንፈስ ቅዱስ ሐሤት አደረገኩኝ፦ የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግናለሁ፤ አዎን አባት ሆይ፥ ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአልና። አሜን!

BROTHER BINYAM T. ALEMAYEHU 12/07/2017

http://wongelinlove.com/

http://wongelradio.org/


  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal