
Binyam TA
Discussion Quotes: Lidiya Eyesus ሰላም ለአንቺ ይሁን እህታችን፡ መልካም ጥያቄ ነው እኔ አመጣጤ ከኦርቶዶክስ ቤተሰብ ስለሆነ ሃይማኖት ስለሚለው ቃል አክራሪ ነበርኩ እንደምታውቂው ክራር እንካ ስታከሪው ችንጋው ይበጠሳል ሁሉም ነገር ሚዛኑን ከጠበቀ ብቻ ነው መልካም የሚሆነው። እንደ ቃሉ ስፈትሸው ግ ን እንደምታውቂው የቀድሞው ኪዳን የተጻፈው በእብራይስጥ አዲሱ ኪዳን ዳግሞ በግሪክ ስለሆነ አማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ ሆነ ሌሎች ቃንቃዎች ሁሉ ትርጉም ናቸው። ሃይማኖት ቃል እምነት ተብሎ መተርጎም ሲገባው አባቶቻችን ሲተረጉሙት እምነቴን እንደማለት ፈንታ ሃይማኖቴን እያሉ ተርጉመውታል። በተለይም የኦርቶዶክስ ሃይማኖት በኢትዮጵያ ውስጥ ክርስትና ተጠብቆ ከባእድ ሃይማኖት አገሪቱን ለመጠበቅ ትልቅ አስተዋጻኦ በማድረግዋ በትርጉሞች ላይ በጊዜው የአገሪቱ ሁኔታ ያማከለ ቃላት መጠቀም የተለመደ አካሄድ ነበረ። ለምሳሌ እነሆ፤ ዘንዳ፤ ወዘተ… ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:5 አንድ ጌታ #አንድ #ሃይማኖት[አንድ እምነት] አንዲት ጥምቀት፤
Eph 4:5 One Lord, #one #faith, one baptism, እንደሚታወቀው በአጠቃላይ ሃይማኖት ማለት ሰው ወደ እግዚአብሄር ለመድረስ የዘረጋው የፈረሰ መንፈሳዊ ድልድይ ነው። ብቸኛው መንፈሳዊ ድልድይ ሆነ መሰላሉ መንገዱም መድሃኒአለም ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። እ/ር ለያቆብ ራእይን አሳየው ይህም ራእይ ስለ ጌታ ነበር። ኦሪት ዘፍጥረት 28፡12 ሕልምም አለመ፤ እነሆም #መሰላል #በምድር ላይ ተተክሎ፥ ራሱም #ወደ ሰማይ ደርሶ፥ እነሆም የእግዚአብሔር መላእክት[መልክተኞች] ይወጡበት ይወርዱበት ነበር። ጌታ እየሱስ ይህ ሰማይና ምድርን ወይም ተፈጥራዊውን ጉኡዙን አለምና መንፈሳዊውን አለም የሚያገኛኘው መሰላል እሱ በሆኑን ደጋግሞ አስረድቶናል። የዮሐንስ ወንጌል 1፡52 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይ ሲከፈት የእግዚአብሔርም መላእክት[መልክተኞች] #በሰው ልጅ ላይ #ሲወጡና #ሲወርዱ ታያላችሁ አለው። እምነት ደግሞ የእ/ርን ድምጽ ወይም ቃል ከመስማት የሚመጣ ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 10፡17 እንግዲያስ #እምነት #ከመስማት ነው #መስማትም #በእግዚአብሔር #ቃል ነው። ሃይማኖት ከሰው የተዘጋጀ ለተፈጥራዊው ሰው ብቻ ደስ የሚያሰኝ ስርአት ሲሆን እምነት ግን ምንጩ እ/ር እራሱ ነው። ስለዚህ ሃይማኖት የሚለውን ሁሉ እምነት በሚለው ተክተሽ ካነበብሽው የአምላክሽ እውቀት ሳይበረዝ ህይወት ይሆንሻል። ለምሳሌ፤ የይሁዳ መልእክት 1፡3 ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ #ሃይማኖት[ #እምነት #faith] እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።
Jude 1፡3 Beloved, when I gave all diligence to write unto you of the common salvation, it was needful for me to write unto you, and exhort you that ye should earnestly contend for the #faith which was once delivered unto the saints.
የማቴዎስ ወንጌል 4፥4 እርሱም መልሶ፦ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው።
የሉቃስ ወንጌል 4፥4 ኢየሱስም፦ ሰው በእግዚአብሔር ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል ብሎ መለሰለት። የዮሐንስ ወንጌል 14
6 ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። እኔ መንፈሳዊው መንገድ ነኝ ካለ ሌላው ሁሉ መንፈሳዊ ገደል ነው። እኔ መንፈሳዊው ህይወት ነኝ ካለ ሌላው ሁሉ መንፈሳዊ ሞት ነው። እኔ መንፈሳዊው እውነት ነኝ ካለ ሌላው ሁሉ መንፈሳዊ ውሸት ነው። ወንድም ቢኒ።5Mulugeta Shiferaw, Alem Wenji and 3 others1 Comment3 SharesLikeCommentShare
Comments
- Mulatu Ye Eyesus ጌታ ኢየሱስ ይባርክህ።