በቡልይ ኪዳን[ከኦሪት ዘፍጥረ እስከ ትንቢተ ሚልክያስ] “(የአብን …#ድምፁንም #ከቶ #አልሰማችሁም፥ #መልኩንም #አላያችሁም፤ ዮሐንስ 5:37)” አገኘከው? Did You observe it Bro.?


ከውይይት የተጠቀሰ፤ Mulugeta Shiferaw ወንድም ቢኒ። 6/04/2019 ሰላም ሙሌ፤ የሚገርመው ይህ እይታ ከተወሰኑት ትንታኔዎችህ በቀር በአብዛኛው እኔም በሆነ ወቅት ላይ ከሞላ ጎደል እይታየ ነበር። ያህዌን አብ አድርጎ ማየት ላይ ካለ ወገን ሁሉ አሁን ያነሳካቸው ሃሳቦች ሁሉም ባይባሉም አብዛኛዎቹ ማለትም ኢየሱስ የመለኮትና የሰው ባህርይ ይዞ እስከተገለጠ ድረስ ምንም የሚቃረን ሃሳብ የለውም በእርግጥ እራሱን ባዶ አድርጎ ያዋረደበትን የሃጥያኛ ሰው ምስል ተመስሎ የተገኘበት ላይ ምንም ብታተኩርም ያም የመጣበት አላማ መካከል አንዱ ነውና ሚዛኑን እስከጠበቀ ድረስ ችግር የለውም። አንድ እውነት ከተረዳን ግን እይታችን 360 ዲግሪ ይቀየራል። ጌታ በቅርብ አንዱን ቃሉን እስካስረዳኝ ድረስ የእኔም እይታ ዘወር አሉ አልሸሹም ነበር። ይህን ቃል በቃል ደረጃ እንጂ የቃሉ መንፈሳዊ ፍቺ ከጥቂት ወንድሞች በተለይም አንድ የማከብረው የእ/ር ሰው ወደ ጌታ ሊሄድ ጥቂት ወራት እንደቀረው ጌታ እንደገለትጠለት ከመጨረሻ ጹሁፉ ማንበቤ ትዝ ይለኛል። ይህ እይታ አንተም ወገኖችም እንዲታያችሁ ጸሎቴ ነው። ቃሉ እያለ ከሁሉም የተሰወረው ሃሳብ እንደሆነ ተረድቻለሁና። ይህን ቃል ስናስተውል ግን እይታችንን እንደገና ልናጤነው እንገደዳለን። ማለትም ለወራጅ ውሃዎች ማለቴ ነው እቃሪ ውሃ ባለበት ይረጋል አይፈወስም ወራጅ ውሃ ግን ስለሚንቀሳቀስ ይፈወሳል በሌላ አነጋገር በመንፈስ በጉ ወደ እውነት ሁሉ ወደሚመራቸው ወደ ሚሄድበት ለሚከተሉት ማለቴ ነው።
“አንድ” የሚለውን መንፈሳዊ እይታ ከማግኘታችን በፊት ማለትም እ/ር አንድ ነው፤እግዚአብሔር ግን አንድ ነው።፤አንድ እግዚአብሔር አለና፤ሕግን የሚሰጥና የሚፈርድ አንድ ነው፤ እኔና አብ አንድ ነን።፤ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው፤ ሌላ ሊበራል የተገባ ቃል አለ። ባለፈው የተወሰኑ ዩኒቴሬያኒዝም፤ የጆቫ፤ የስልምና፤ ቡዱኖች ከምን መነሻ ነጥብ ከጌታ ጋር እንደተላለፉ ሳስብ ነበር በእ/ር ፊትም በውስጤ ስቃትት ነበር። እኔ ለማመን ብዘገይም ጌታ የአንድን ቃል ፍቺ በዘልማድ ከማስተውለው ባሻገር ደጋግሞ ያስረዳኝ ነበር። ወዲያው አላስተዋልኩትም ጌታ ግን ውጤታማ አስተማሪ ነው ማንካካቱን ቀጠለ። አስተውለው ዘንድ አእምሮየን ከፈተለኝ። በመጨረሻ የማይታየው አብ በብሉይ ኪዳንም ቢሆን አንድም ቦታ እንዳልተገለጠ አስተዋልኩ። በብሉይም ሆነ በአዲስ ያህዌም ሆነ ኢየሱሱ የአብ ብቸኛው የመጨረጫው ልናየው የምንችልበት የመገለጥ መንገድ እንደሆነ ፍንትው ብሎ ገባኝ። አብ አይታይም። አብ ድምፁ ከቶ አይሰማም፥ መልኩም አይታይም፤ የአብ ድምፁ የሚሰማው፥ መልኩም የሚታየው በቡሉይ በያህዌ አዶናይ ወዘተ.. ሲሆን በአዲስ በኢየሱስ ክርስቶስ ነው[በአካሉ በክርስቶስም አክልበት]፤ ኢየሱስ በድፍረት መጽሃፍት ሁሉ ስለኔ ተጽፈዋል ሲል ምን ማለት ነው? መቼም ከሱ ይልቅ እውነት ለአሳር ነውና። ከአብርሃም በፊት እኔ ነኝ ምን ማለት ነው? ኢየሱስ ክርስቶስ ትላንትናም ዛሬም ነገም ህያው ነው ማለት ምን ማለት ነው? ወዘተ … መቼም እውነት ኢየሱስ ነው አይደል? ይህን እውነት አስተውል። በቡልይ ኪዳን[ከኦሪት ዘፍጥረ እስከ ትንቢተ ሚልክያስ] “(የአብን …#ድምፁንም #ከቶ #አልሰማችሁም#መልኩንም #አላያችሁም፤ ዮሐንስ 5:37)” አገኘከው? Did You observe it Bro.? ተጨማሪ በመጀመሪያው ቃል ከነበረው ኢየሱስ ምን እንዳለ እናስተውል፤ የዮሐንስ ወንጌል 1፡18 “#መቼም #ቢሆን #[አብን፤ መንፈስን]እግዚአብሔርን #ያየው #አንድ ስንኳ #የለም፤” ።ማለትም በቡልይ ኪዳን[ከኦሪት ዘፍጥረ እስከ ትንቢተ ሚልክያስ] አብ አልታየም። በመረዳት እየተነጠክ ነው? ፡) ቃሉም እግዚአብሔር አብ በማንኛውም ጊዜ ለማንም ሰው በቀጥታ አልተናገረም (ድምፁን ከቶ አልሰማችሁም፥ መልኩንም አላያችሁም፤ ዮሐንስ 5:37), እነ ሙሴ፤ አብርሃም ወዘተ የተገለጠላቸው የማይታየው የአብ መገለጥ ያህዌ ነው። አባት ከያህዌ/ኢየሱስ ልጁ ዘንድ ትእዛዝ አይወስድም እውነት ነው። ኢየሱስ በአጭሩ የአብ ፍጹም ፈቃድ ነውና፤ የአብ[የመንፈስ] ቃል፤ የአብ[የመንፈስ] ሃሳብ፤ የአብ ጥበብ፤ የአብ ሃይል፤ የአብ ክብር ክርስቶስ መሆኑ ግልጽ ነው። ክርስቶስ ኢየሱስ መንፈስ የሆነው የመናፍስት አባት የአብ ሁለንተና ለፍጥረታዊው አእምሮ ይታይ ዘንድ የመንፈስ ወይም የማይታየው ሃይል ሙሉ ክብር መገለጥ ነውና። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1፡24 የአብ ኃይልና የአብ ጥበብ ክርስቶስ ነው። የአብን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ? ምን ማለቱ ነው? መጻሕፍት ስለማን ይናገራሉ
*መጻሕፍትንና [የዮሐንስ ወንጌል 5፡39 በመጻሕፍት … ስለ እኔ(ኢየሱስ ክርስቶስ ) የሚመሰክሩ ናቸው።
*የአብን ኃይል[የአብ ኃይል ኢየሱስ ክርስቶስ ነው] አታውቁምና ትስታላችሁ።የማቴዎስ ወንጌል 22፡29
እውነቱ የማቴዎስ ወንጌል 11፡27 ከአብ[ከመንፈስ] በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፥ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን[መንፈስን] የሚያውቅ የለም። ወልድም ሊገለጥለት ለፈቀደው ይህን ያስተውል ዘንድ መንፈሱ ለነቃው በሰማያት ያለው አባት[መንፈስ] እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ[ደስተኛ] ነህ ልንለው እንችላለን። ለባለአእምሮው ደግሞ እንዲህ ነው “1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2፡14 ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም።” በመንፈስ ካለማወቅ ካለ መቀበል የለም። ይህን እንዳንረሳ አብ በራሱ ተገልጦ አያውቅም። የአብ[የማይታይ] እንዲገባን የመታየቱ መገለጦች እዚህ መልክ እናስቀምጣውና በአሮጌው ኪዳን ብዙ ቢሆንም ከብዙ በጥቂቱ አዶናይ: ጌታ እግዚአብሔር Adonai: Lord God፤ በያህዌ Yōd, Hē, Vav, Yahweh: God፤ አዶናይ፤ ኤልሻዳይ ሁሉን ቻይ አምላክ El Shaddai: God Almigh[The all sufficient God of the Mighty #Breasted One] ። ኤል ሮይ: የሚያየኝ አምላክ፤ ያህዌ: እግዚአብሔር ያዘጋጀል Yahweh Yireh: God Provides፤ ወዘተ….. “(የአብን …#ድምፁንም #ከቶ #አልሰማችሁም፥ #መልኩንም #አላያችሁም፤ ዮሐንስ 5:37)”…. ክፍል 2 ወንድም ቢኒ።

ክፍል 2 ፤ ልጆቹ ሁሉ በቅዱስ ቃሉ ውስጥ ልናውቃቸው ከሚገቡ እጅግ በጣም ጠቃሚና ከፍተኛ የሆኑ ነገሮች አንዱ ማንም ሰው እግዚአብሔርን አይቶት ወይም ድምፁን ሰምቶት አያውቅም የሚለው እውነት ነው። No man has ever seen God or heard His voice. ሁላችንም ይህንን እውነት በቀላሉ ገና ማመን አልችልም ሆኖም እሱም ደጋግሞ መናገሩን አላቆመም በቃሉ እንደሚናገረው አሁን ልታምኑት የሚገባ ከባድ ሚዛን ያለው እውነት ነው። If you don’t believe No man has ever seen God or heard His voice, well then you will keep having big problem you will keep think Yehovah or Jehovah is God the Father and you will have all these crazy spiritual Babylonian understanding and all it’s things, that aren’t true at all. It’s a major spiritual truth. We have to find out the truth who the God of the Bible is. “No man hath seen God at any time (John 1:18).” that is clear to the one with quick understanding in the fear of the Lord to get this great understanding! በቀላሉ አብ ታይቶ አያውቅም ይህን ካላስተዋልክ ያህዌ አብ እንደሆነ ብታስብ አይደንቅም፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ከንቱ ነገሮች ታከማቻለ። ይህም ከእውነት አይደለም። ይህ የአብን ድምፁን በማንኛውም ጊዜ አልሰማችሁም፤ የእሱን መልክ[ቅርጽን] አይታችሁት አታውቁም የሚለው የኢየሱስ ቃል ብዙ ነገር ወለል ብሎ እንዲታየን አይነተኛ ቁልፍና ዋነኛው እውነት ነው። በታላቅ ክብር የተገለጠው የመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ ማን እንደሆነ ማወቅ አለብን የግዴታ ማወቅ አለብን። ምን ለማለት ነው በየትኛውም ጊዜ ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው ማንም የለም ማለት? “መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ (ዮሐ 1:18).” በማስተዋለ ፈጣን ለሆነና ለማመን ለማይዘገይ ይህ እውነት ግልጽ ነው! “1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4፡12 እግዚአብሔርን ማንም ከቶ አላየውም፤”
“የዮሐንስ ወንጌል 5፡37 የላከኝ አብም እርሱ ስለ እኔ መስክሮአል፡፡ ድምፁን ከቶ አልሰማችሁም፥ መልኩንም አላያችሁም፤” ስለዚህ አብርሃም ሶስቱን ሰዎች ሲያዝናና እና ያዕቆብ በለሊት ከአንድ ሰው ጋር ሲታገል “ኦሪት ዘፍጥረት 32፡30 ያዕቆብም፦ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፥ ሰውነቴም ድና ቀረች ሲል የዚያን ቦታ ስም ጵኒኤል ብሎ ጠራው።” አብርሃምም ያቆብም እግዚአብሔር አብን አላዩትም። እንዳውም ኢየሱስ ክርስቶስን እንዳየ ሆኖ አይሰማኝምና እሱንም አላምንም። እግዚአብሔር የላከውን አንድ ሰው በእግዚአብሔር መልክ አየ ብዮ ነው የማምነው። I think he is representative from God himself, probably in the form of a man. እርሱ ሰው ነበር ና ከላከው ከእግዚአብሔር ተልኳል እናም ብቃቱ ድንቅ ነበር ሀይለኛ እና ጉልበታም ነገር ነበር እውነት ነው። ነገር ግን ግልጽ በሆነ ሁኔታ መጽሃፍ ሰው ነበር ይለናል።
አንዴ መንፈሳዊ እውነትን ከተማራቹ በፍጹም ከእውነት ጋር እንዳትፋቱ አጥብቃቹ ተዋሃዱ። God willing if once you learn a spiritual truth from the Lord, don’t ever let it go. Matt 11:27 ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል። ይህ በጣም ኃይለኛ መንፈሳዊ መግለጫ እዚህ ላይ ለጌታ የሰጠው ማነው?። ክርስቶስ ሁሉን ከየት ነው ያገኘው? ቅልብጭ ባለ ቃንቃ ከአባቱ። አንዳንድ ሰው እሱ ግን ከእግዚአብሔር ጋር እኩል ነበረ ከሦስቱ የሥላሴ አንዱ ክፍል ነው ይላል። ጥያቄው ‘ ከየት ነው ሁሉን ያገኘው? ከአባቱ! አባት ከልጅ ይበልጣል ብቻ ሳይሆን ሰጪው ከተቀባዩ ይበልጣል!
“እሱ ከአባት ተልኳል” ስለ ተለኮ ደግሞ ቅዱሳት መጻህፍ “መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም። (ዮሐንስ 13 16).” ይላል።
እስከ ሚገባኝ ቅዱሳት መጻህፍትን ማመን ነው የሚያዋጣው። ያ ነው በቃ እውነቱ በትክክለኛው መንገድ ተረድተህ ካስተዋልክ ከዚያም እውነተኛውን ለውጥ በራስህ ውስጥ ማየት ትጀምራላችሁ። አዲስ የሆነ አዲስ ነገር ከጌታህ ትንማራለህ።
እዚህ በሌላ ብዙ ጥቅስ ሌላ ተጨማሪ ጥቅስ ይኖራል። ይህን ሃሳብ ገና አሁን በሰፊው እያጠናሁት ነው።
የዮሐንስ ወንጌል 6:45 ሁሉም ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ ተብሎ በነቢያት ተጽፎአል፤ እንግዲህ ከአብ የሰማ የተማረም ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል።46 አብን ያየ ማንም የለም፤ ከእግዚአብሔር ከሆነ በቀር፥ እርሱ አብን አይቶአል።
ታዲያ አብን ያየ አንድም ሰው አለን? የለም! የእሱን መልኩን ወይም ቅርጹን ማየት የቻለ አለ? የለም! ድምፁንስ ሰምቶ ማንም ሰው ያውቃል? በጭራሽ! በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔርን ድምጽ ሰምተዋል? «እህ?» አዎ አዎን ድምጹን ሰምተዋል። የእሱን ቅርጽ ማየት ችለዋል? አዎን ። “ኦሪት ዘጸአት 33፡23 ጀርባዬንም ታያለህ፤ ፊቴ ግን ቆይ ቆይ እ/ርን ያየ የሰማም አንድም የለም አልተባለም እንዴ? ምድነው ነገሩ? በብሉይ ኪዳን ውስጥ “ኦሪት ዘዳግም 4፡33 አንተ ከእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር የእግዚአብሔርን ድምፅ እንደ ሰማህ፥ ሌላ ሕዝብ ሰምቶ በሕይወት ይኖራልን?” የእግዚአብሔርን ድምፅ እንደ ሰማህ? እሺ፤ ይህ ግራ ሊያጋባ ይችላል። ይህን እንፈታው እንደሆን እስቲ እንመልከተው።
በመጀመሪያ እንድናየው የፈለኩት ኢየሱስ ክርስቶስ ወይም ቃል ስጋ ከመሆኑ ወይም ከሰብዓዊ ቅርጽነቱ በፊት ህያው ነበር ወይም የነበረ መሆኑን ነው። ይሄንን ለማረጋገጥ እሞክራለሁ፤ ወደ 18 ገደማ ማረጋገጫዎች አሉኝ።
[1] “አሜን የሆነው [ኢየሱስ] የታመነና እውነተኛ [ኢየሱስ] የእግዚአብሔር ፍጥረት መጀመሪያ[746 arche ar-khay’፤ አለቃ፤ምንጭ፤መገኛ፤ሉኡል][the chief of the creation of God or the originator of God’s creation]” ይላል (ራዕ 3፡ 14).
ክርስቶስ እንዴት እንደመጣ ሦስት ጽንሰ-ሐሳቦች theories አሉ።
1) ከሰው ልጅ የወሰደው ሥጋዊነት ማንነት ያለው ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ሆኖ ተከሰተ በናቱ ማህጸን ክርስቶስ ለመጀመሪያ ጊዜ የተወለደ ሰው ብቻ ነው። የሚሉ አሉ።
2) ከእዚያ ቀደም ብሎ የተፈጠረ ፉጡር ሆኖ ወደ እናቱ ማህጸን የገባ ነው። የሚሉ አሉ።
3) ከዚያም ሌሎች እሱ ዘላለማዊ ማንነት ያለው ነው እርሱ ሁል ጊዜ ይኖር ነበር። የሚሉ ናቸው። ወዘተ….
ለመጀመሪያ ጊዜ የተወለደ ሰው ነው እንደ ሰው አካል ሆኖ ወደ ሕልውና እንደመጣ የሚያምኑት ብዙ አይደሉም በጣም ጥቂቶች
ብዙ ሰዎች የክርስትናን ባሕል ይከተላሉ በቁ 3, ላይ እንደተጠቀሰው ክርስቶስ ዘላለማዊ ነው። እርሱ የስላሴ አካልና ዘወትር በሕይወት የኖረ ነው። 2, ኢየሱስ ክርስቶስ የተፈጠረ ነው የሚሉም አሉ።
– “የእግዚአብሔር ፍጥረት ምንጭ[Origin” (የጄምስ ሞፋት ትርጉም)
– “የእግዚአብሔር የፍጥረት መጀመሪያ[Original]” (የኮንኮርዳት ሊትራል ኒው ቴስታመንት).
– “የእግዚአብሔር ፍጥረት አለቃ[Chief ]” (ያንግስ ትርጉም).
– “የእግዚአብሔር ፍጥረት ምንጭ፤ እና መጀመርያ፤ ደራሲ፤ the Origin, and Beginning, and Author of God’s creation” [ዘ አፕሊፋይድ ኒው ቴጽመንት]
ከቃሉ እንደምንረዳው በዚህ አንድ ቃል ላይ ሁለት አይነት እይታ የተለመደ ነው። አንዱ የእ/ር ፍጥረት መጀመርያ ነው በሚለው ትርጉም ያየዋል። ሌላው የትርጉም ዝንፈት ነው የእ/ር ፍጥረት ምንጭ፤ደራሲ፤አለቃ ነው ብሎ ያየዋል። በዚህ ላይ ለአሁን አናተኩርም ሆኖም አንድ ነገር የምናውቀው ሰው ከመሆኑ በፊት እዛው ነበረ። ስጋ ከመልበሱ በፊት ከጥንት ከመጀመርያው የነበረ እንደሆነ እናውቃለን።
[2] #አልፋና #ዖሜጋ#መጀመሪያውና #መጨረሻው እኔ ነኝ። ያለው ለተጠማ ከሕይወት ውኃ ምንጭ እንዲያው እኔ እሰጣለሁ ደግሞ ብለዋል ያ ደግሞ የኢየሱስ ቃል ነው። አብ መቼም የከሕይወት ውኃ ምንጭ እሰጣለሁ ሲል አልታየም በኢየሱስ ቃል በቀር። አብ ነው ካልን ሁለት #አልፋና #ዖሜጋ፥ #መጀመሪያውና #መጨረሻው እኔ ነኝ። አሉን ማለት ነው።
“አለኝም፦ ተፈጽሞአል። #አልፋና #ዖሜጋ፥ #መጀመሪያውና #መጨረሻው እኔ ነኝ። ለተጠማ ከሕይወት ውኃ ምንጭ እንዲያው እኔ እሰጣለሁ። And he said unto me, It is done. I am Alpha and Omega, the beginning and the end. I will give unto him that is athirst of the fountain of the water of life freely” (የዮሐንስ ራእይ Rev. 21:6).
[የተጠማ ወሃ የሚሰጠው ኢየሱስ ነው።] የዮሐንስ ወንጌል 4፥14 እኔ[ኢየሱስ] ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው #ውኃዘላለም #ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ አላት። 7፥38 በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ፥ #የሕይወት #ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል ብሎ ጮኸ። የዮሐንስ ራእይ 22:1 በአደባባይዋም መካከል ከእግዚአብሔር እርሱም[καὶ] ከበጉ ዙፋን የሚወጣውን እንደ ብርሌ የሚያንጸባርቀውን የሕይወትን ውኃ ወንዝ አሳየኝ። 1. And he showed (points out to) me a river of “water of life,” bright (resplendent, glistening, clear, sparkling) as crystal (clear ice), continuously flowing (issuing) forth from out of God’s namely[καὶ] the little Lamb’s throne!
καὶ ፍቺ እና አጠቃቀም Definition & Usage: and[ም፣ ና፣ እና፣ ደግሞ], even[ደልዳላ፣ ሙሉ፣ እኩል፣ ትክክል፣ እንኳ፣ ም እንኳ፣ እንኳን ሳይቀር፣ እንደዲያውም], also[እንዲሁም፤ደግሞ], namely[ማለትም፤ እርሱም፣ ይኸውም፣ ማለት]#አልፋና #ዖሜጋ፥ #መጀመሪያውና #መጨረሻው እኔ ነኝ። ያለው ለተጠማ ከሕይወት ውኃ ምንጭ እንዲያው እኔ እሰጣለሁ ብለዋል ያ ደግሞ የኢየሱስ ቃል ነው። አብ መቼም የከሕይወት ውኃ ምንጭ እሰጣለሁ ሲል አልታየም በኢየሱስ ቃል በቀር።
[3] የዮሐንስ ራእይ 1፡8 ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፦ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።
“ሁሉን ቻይ” “Almighty”ስትሮንግስ # G3841 “pantokrator፤ የሁሉ ገዢው the all ruling, that is, God (ፍፁም እና ጽንፈተ፟ ፟- ሁለንተናዊ ሉዓላዊነት): – ሁሉን ቻይ, ሁሉን ቻይ; ያልተገደበ ኃይል ያለው ማንኛውንም ነገር ማድረግ የሚችል Almighty, Omnipotent” Walaa… Well here you go it sounds pretty absolute Godly to me and it sounds like He is contributing all that to Jesus Christ. በተጨማሪም መጅርምርያውና መጨረሻውን ይነግረናል። ግን ዘላለማዊ ነው ወይስ ተፈጥረዋል? ገና አላወቅንም። …..ክፍል 3 ወንድም ቢኒ።

ክፍል 3፤ ይህ ሁሉን ቻይ እንደሆነ የሚያረጋግጥ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ጥያቄ የሚፈጥርብን ነገር አለ ሌላ ነገርም እንማራለን ይህ አባባሉ ስለ አብ[አባት] እየተናገረ እንዳልሆነ እናያለን። ቆይ ግን አብ[አባት] እና ክርስቶስ በእውነት እኩል አንድ ከሆኑ በእርግጥ ዘላለማዊ ስለሆኑ አሁንም መልሱን ለማወቅ ችግር አለን ትንሽ ቀጥለን በቃሉ እንየው።
ይህ “ሁሉን ቻይ” ማለት “አልፋ እና ኦሜጋ” ነው። ይህ “አልፋ እና ኦሜጋ” በ 1፡ 17 ላይ “የመጀመሪያ እና የመጨረሻው” ተብለዋል። በ 1፡ 17 ውስጥ “የመጀመሪያ እና የመጨረሻው” ተብሏል። ግን እስካሁን ድረስ እሱ እዚያ እንደነበረ ያንን ማረጋገጥ አልቻልንም። ነገር ግን በቁጥር 18 ላይ ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ። “ሞቼም ነበርሁ” አሁን ነገሩ እግዚአብሔር ይሞታልን? ክርስቶስ ለዘላለም ከአባቱ ጋር ከነበረ። ለዘለዓለማዊ ማንነት እንዴት ሊሞት ይችላል? ዘላለማዊ እግዚአብሔር ይሞታልን?
በዚህ ክፍል ውስጥ በቅዱስ መጻህፍት እናስተውል።
1 ” ካለውና ከነበረው ከሚመጣውም” (ራዕ 1፡4).
2. “ያለውና የነበረው የሚመጣውም ፤ ….. አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ” (ራ 1: 8).
3. “አልፋና ኦሜጋ፤ ፊተኛውና ኋለኛው” (ራዕ 1:11).
4. “እኔ ፊተኛው ነኝ እኔም ኋለኛው ነኝ” (ራዕ 1 17)
5. ” #ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ” (ራዕ 1:18). [እኔ ሕያው ነኝ, ሞቼም ነኝ, እኔም በሕይወት እኖራለሁ። ትክክለኛው ወደዚህ ይጠጋል [እኔ የሚኖረው ነኝ፤ ሞቼ ነበር እነሆ ህያው ነኝ፤ I am He that lives, and was DEAD; and, behold, I am alive, KJV፤] 18. even The LIVING ONE (or: the One continuously living), I also brought Myself to be (birthed Myself) a dead one [or: I also came by Myself to be dead], and Behold! I am living into the ages of the ages, and I constantly hold (have) the keys of Death and of the Unseen (Hades).”JMT
ያው አንዱ እራሱ ነው። አንድ አይነት አልፋ እና ኦሜጋው፤ መጀመርያውና እና መጨረሻው, የሚመጣውም “ሞቼም ነበርሁ እነሆም እኔ ህያው ነኝ”
6. ” ሞቶ የነበረው ሕያውም የሆነው ፊተኛውና መጨረሻው ” (ራዕይ 2፡ 8).
7. ” ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ” (ራዕይ 4፡8).
8. ” ያለህና የነበርህ ሁሉን የምትገዛ ጌታ እግዚአብሔር[አምላክ] ሆይ” (ራዕይ 11፡17).
9. ” ያለህና የነበርህ ጌታ ሆይ፥ ቅዱስ ሆይ” (ራዕ 16: 5).
10. ” አለኝም፦ ተፈጽሞአል። አልፋና ዖሜጋ፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ። ለተጠማ ከሕይወት ውኃ ምንጭ እንዲያው እኔ እሰጣለሁ።”(ራዕ 21: 6)”
11. ” አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።” (ራዕይ 22፡ 13).
እናም ይህ “አልፋና ኦሜጋ” “መጀመሪያ እና መጨረሻ” “ፊተኛውና ኋለኛው,” የሆነው እና የሚመጣው. ” ሞቶ የነበረው ነው Was DEAD.
ይህ እግዚአብሔር አብ አይደለም! እግዚአብሔር አብን አይቶት ወይም ድምፁን ሰምቶት አያውቅም የለም No man has ever seen God or heard His voice እግዚአብሔር አብ አይሞትም እናም እግዚአብሔር አብ ሊሞት አይችልም። እውነቱን እናየው ዘንድ ከሁሉም መአዘን ማየቱ መልካም ነው። ….ክፍል 4 ወንድም ቢኒ።

ክፍል 4፤ ሌላው አንተ ካልካቸው የተወሰኑት ከእ/ር ሃሳብ ጋር ስለሚጋጭ የማልስማማው ለምሳሌ “የሹዋ[አዳኝ] ማለት በግዜው ለሆነው የእዚአብሔር ማዳን በዝማሬ የተጠቀሙት ቃል ነው ። መልክቱ መድኅን ሆነኝ ነው።” በማለት ለኢየሱስ የተነገረ ትንቢት አንዳልሆነ ነገር ግን በግዜው ለሆነው የእዚአብሔር ማዳን በዝማሬ የተጠቀሙት ቃል ነው ብለህ አስቀምጠከዋል። በአንተ አካሄድ ከዚህ ቃል ጋር እንደ መላተም እንዳይሆን ደግመን ብናየው መልካም ነው። “ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1፡21”
አንተ በግዜው ለሆነው የእዚአብሔር ማዳን በዝማሬ የተጠቀሙት ቃል ነው ያልከው በወቅቱ መነገሩ እውነት ቢሆንም እውነቱ በዛ አይገታም ይህንኑ ዝማሬ ጌታ ኢየሱስ ለኔ የተነገረ ትንቢት ነው ብሎ ለራሱ ጠቅሶታል። ይህም የአሮጌው ኪዳን ያህዌ በአዲስ ኪዳን ሰው ሆኖ ስለመገለጡ የተነገረ ትንቢት ነው። ይህም በኢሳያስ 12:2-3 ‘እነሆ፣ እግዚአብሔር[ ሁሉን ቻይ አምላክ Almighty God] ድነቴም (እብራይስጥ፤3091 Yhowshuwa` yeh-ho-shoo’-ah፣ yshuw`ah የሽዋ አዳኝ፤ አዳኜም [ክሪክ፤2424 Iesous ee-ay-sooce’ of Hebrew origin (3091); Jesus (i.e. Jehoshua)አዳኝ እየሱሴም]) ነው፤ እታመናለሁ፣ ደግሞም አልፈራም፤ ጌታ እግዚአብሔር[ያህዌ Yhovah] ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም (አዳኜም [እየሱሴም]) ሆኖአል።” ከድነቴ[እየሱሴ] #ምንጮች #ውሃ በደስታ ትቀዳላችሁ። ‘ ኢሳይያስ 12:2-3 እንደምናስተውለው ኢሳያስ በሙሴ መጽሐፍ በዘፅአት የተፃፈውን ደግሞ ሲጠቅስ እናስተውላለን። በዚህ አያበቃም እየሱስ ይህን በመጥቀስ አጽንቶታል። የማቴዎስ ወንጌል 1፡21 ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን #ኢየሱስ[ክሪክ፤2424 Iesous ee-ay-sooce’ of Hebrew origin (3091); Jesus (i.e. Jehoshua)አዳኝ እየሱሴም]) ትለዋለህ።
ጌታ እየሱስ ይህን ትንቢት ግልጽ አድርጎ ፈቶታል። ‘የበዓሉ መጨረሻ በሆነው በታላቁ ቀን፣ ኢየሱስ ቆሞ ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ አለ፤ “ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ፤ በእኔ የሚያምን፣ መጽሐፍ እንዳለ የሕይወት #ውሃ #ምንጭ ከውስጡ ይፈልቃል።” ‘ ዮሐንስ 7:37-38 በሌላ የእንግሊዝኛ ትርጉም ማንም ከተጠማ ከደህንነት ምንጭ ዉሃ ይጣጣ ይላል።
‘እግዚአብሔር (ያህዌ) ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም[ደህንነቴም yashua: እያሱ በእብራይስጥ እየሱስ በግሪክ] ሆነልኝ፤ እርሱ አምላኬ ነው፤ አመሰግነዋለሁ፤ የአባቴ አምላክ (ኤሎሂም) ነው፤ እኔም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ። እግዚአብሔር (ያህዌ) ተዋጊ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር (ያህዌ) ነው። ‘ ዘፀአት 15:2-3 አስተዋላችሁትን ትንቢቱን እግዚአብሔር (በያህዌ) ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም[ደህንነቴም yashua: እያሱ በእብራይስጥ እየሱሴም በግሪክ] ሆነልኝ። እንዲገባን በግልጽ አማርኛ እንየው “ያህዌ ደህንነቴ ወይም እየሱሴ ሆነልኝ[“ያህዌ እየሱሴ ሆነልኝ”]” ይህ የእየሱስ ስጋ የመልበሱ ትንቢት ነው። ይህ ግልጽ ቃል የሚያስረዳን በአሮጌው ኪዳን እየሱስ [በእብራይስጥ እያሱ] ስለ ድነት ወይም ደህንነት ተደብቆ የነበረው ሚስጥር እንደሆነ ነው። ጌታ እየሱስ ስጋ የለበሰው ያህዌ ነው። “ያህዌ እየሱሴ ሆነልኝ”…. ክፍል 5 ወንድም ቢኒ።
ክፍል 5 ፤ ከሙታን ስለመነሳቱ። ነፍሴን ደግሞ አነሣት [እኔ እየሱስ] ዘንድ አኖራለሁና …. ላነሣት[እኔ እየሱስ] ሥልጣን አለኝ። እኔ አነሣት እኔ ላነሳት ካለ እንደማይዋሽ እናውቃለን ቅኔው ታላቅ ነው። እርሱ እራሱ #ትንሣኤ መሆኑን አትዘንጋ። የዮሐንስ ወንጌል 11፡25 ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ። የሞተው የተዘጋጀለት ስጋ እንጂ በመንፈስ እንዳልሞተ አትርሳ። በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ስለሆነ ስላልሞተ እርሱ ወንጌልን ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው።
18 ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፥19 በእርሱም ደግሞ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት[መናፍስት spirits] ሰበከላቸው፤1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3
የእ/ር መንፈስና ኢየሱስ የተለያዩ ከሆኑ ኢየሱስ ቀጥፈዋል እያልክ ነው? ወይስ በሁለቱም ገጽታ ማየት ይኖርብናል ። ላነሣት[እኔ እየሱስ] ሥልጣን አለኝ
የዮሐንስ ወንጌል 10፡17 ነፍሴን ደግሞ አነሣት ዘንድ አኖራለሁና ስለዚህ አብ ይወደኛል።18 እኔ[እየሱስ] በፈቃዴ[እየሱስ] አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ[እየሱስ] ማንም አይወስዳትም። ላኖራት[እየሱስ] ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት[እየሱስ] ሥልጣን አለኝ ይህችን ትእዛዝ ከአባቴ[አብ መንፈስ ነው፤ ከመንፈሴ] ተቀበልሁ። ላነሣት[እየሱስ] ሥልጣን አለኝ። ስለዚህ ከአብ ሁሉን ተሰጥቶት የተገለጠው ማን መሆኑ ግልጽ ነው አብ የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ በያህዌ ሆነ ኢየሱስ እንዲሁም ከተሠሩት ከተፈጠሩት ሁሉ ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያል። ያህዌም ሆነ ኢየሱስ በከፊልም በሙላትም ታይተዋል አብ ግን የማይታየው መለኮታዊ ባሕርይ ነው። አብ አይታይም። አብ ድምፁ ከቶ አይሰማም፥ መልኩም አይታይም፤ የአብ ድምፁ የሚሰማው፥ መልኩም የሚታየው በቡሉይ በያህዌ አዶናይ ወዘተ.. ሲሆን በአዲስ በኢየሱስ ክርስቶስ ነው[በአካሉ በክርስቶስም አክልበት] ጌታ ኢየሱስ ሲዘጋው በቡልይ ኪዳን[ከኦሪት ዘፍጥረ እስከ ትንቢተ ሚልክያስ] “(የአብን …#ድምፁንም #ከቶ #አልሰማችሁም፥ #መልኩንም #አላያችሁም፤ ዮሐንስ 5:37)” አሜን። ወንድም ቢኒ። 6/04/2019

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal