
ከጥያቄና/መልስ የተወሰደ Binyam TA Israel Samuel Heaven ወንድም ቢንያም ኣንድ ጥያቔ ኣለኝ፡ከዚህ የምትለው ትምህርት ጋር ትገናኛለች፡፡በዘፍጥረት ያህዌ ከማን ጋራ ነበር የሚናገረው”ብምስላችን ሰው እንፍጠር”ብሃላም” ኣዳም ኣንድ እንደኛ ሁነዋልና”ይላል ክተሳሳተ በሃላ፡ይህ ቃል ከድሮ የስላሴ መገለጫ ስንጠቀምበት የነበረ ቀዳሚ ቃል ነው፡፡በእርግጥ የሰሶት መገለጫ ኣይደለም፡ብዙነት ስለሚናገር ግን ካለው ሶስትነት ልምምዶች ጋር ኣገናኝተን ይዘንዋል፡፡ለዚህ ሃሳብህ ምን ይሆናል?ተባርከሃል
ዘፍጥረት 1:26 እኛ ሲል ስላሴን አያሳይም ባይ ነኝ። የቃሉ ፍቺ ለተፈጥራዊው አእምሮ ስሜት ስለማይሰጠው አይቀበለውም ስሜቱን ያለመኮርኮሩ ትክክል ነው ይህ መንፈሳዊ እንጂ 5ቱ የስሜት ህዋሳት ሰፈር ዘንድ ስፍራ የለውምና። መንፈሳዊውን ነገር በመንፈስ ይምንረዳው ነውና። ብዙ ሰዎች በመቆጣትም በድንጋጤም እኛ ሲል ስላሴን አይደል እንዴ የሚያሳየው ብለውኛል እንደደረሱበት ነው እንግዲህ? ጥሩ ጥያቄ ነው እኛ የሚለው ቃል 3ቱ ሥላሴን እግዚያብሄሮች ለማሳየቱ በምን እርግጠኛ ይኮናል ትሆናለህ/ሽ? እኛ 2ለትም 3ትም 4ትም 5ትም ከዛም በላይ የሚያሳይ ሊሆን ይችላልና።
በቤተክርስቲያን ውስጥ ስለ ሥላሴ በአብያተ-ክርስቲያናት ክርክር ውስጥ ዋናው ነጥቡ ተደርጎ ይነሳል። አንድ ጊዜ አምላክ ሥላሴ እንደሆነ አድርገው ከተረዱና ካወቁ በኋላ እንደገና በእግ/ር ቃል ለመታረም ለብዙዎች ጭንቅ ነው። በውኑ እነሱ በትክክል 3 እግዚአብሔር ሲሉ እንደ ቃሉ ተረድተዋልን? ለራስህ/ሽ ቃሉን መመርመር መልካም ነው።
ይልቁኑ ይህ ቃል የእግዚአብሔርን ሙሉነት የሚያስረዳ በድርብ ክብሩ እራሱን የገለጠበት ነው እላለሁ።
የእግዚአብሔር አምሳያ ጣእም ድርብ ስለሆነ ወንዶችና ሴቶች መፍጠሩ የሱ መልክ ነው። የጥንት የስነ-መለኮት ምሁራን በስላሴ ላይ በጣም ትኩረት ስላደረጉበት በዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ለይ የእግዚአብሔርን ቃልን ዋናን ሃሳብ ሳያስተውሉት ቀርተዋል። “ከዚያም እግዚአብሔር አለ ሰውን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር አለ. እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፡ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፡ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ።
ሀይማኖት ያጔሯ : የእግዚአብሔር መንፈሳዊ መልክ ወንድና ሴት ነው ማለትም ማንም ሳያግዘው በራሱ ሊያዘጋጅ ይችላል። ይህን ለማለት ለሰው የሚቸግረው የሰው አእምሮ ከሥጋ ፍትወት ጋር የተቆራኘ ስለሆነ ግልፅ ነው። እግዚአብሔርን መንፈስ እንጂ ስጋ ስላልሆነ ፍትወተ ሥጋ አይመለከተውም። እርሱ ልእለ ተፈጥሮና ልእለ ፍጡራን ነውና ። የእግዚአብሔር ክብር ሌላ ነው የሰው ክብር ሌላ ነው የመንፈስ ክብር ሌላ ነው የሥጋ ክብር ሌላ ነው።
የቃሉ ፍቺ ያበራል።
“እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፡ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፡ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ።”
እንደምናስተውለው የእግዚአብሔር መልክ አምሳል እና አምሳያ በዚህ ቃል መሰረት የወንድን እና የሴትን ገጽታ ያካትታል። ይህ ባይሆን ኖሮ ምድራዊው የእግዚአብሔር አምሳያ ተብሎ የፈጠረው ሰው አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት የያዘ ባለ አንድ ፆታ ብቻ ሆኖ ይፈጥረው ነበረ። ሲፈጥራቸው ግን በአንድ አዳም ውስጥ ሁለት ፆታ ነበር እግዚአብሔር ግን ቡሃላ ለሁለት ከፈላቸው።
እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፡ በመልኩ? በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፡ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ;;
በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፡ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ? ግልጽ ነው። ።Gen 1 verse 27, “And God created man in His own image, in the image of God He created him; male and female He created them.” The #image and #likeness of #God, then, #includes #male and #female #aspects of #God. If this were not so, then the #earthly #image of God would #express just #one #sex, either male or female. ወንድም ቢኒ።
በእርግጥ የጥንት የነገረ-መለኮት ምሁራኑ አምላክን በአዎንታዊነት ለመግለጽ እውነትን ለማሳየት አልቻሉም። እግዚአብሔር በራሱ ሙሉ ስለሆነ ማንም ሳያግዘው መለኮታዊ ሙልአቱን ተጠቅሞ ማዘጋጀት እንደሚችል ከገለፁት እየተገዘቱ መገለል እንዳይደርስባቸው እውነትን መቅበር ይመረጣሉ።ሌላው ችግር ብዙዎቹ የጣዖት አምልኮ አምላኪዎችና አማልክቶች የሴት አገላለጾች ስለሚጨምሩ ሁሉ እርስ በራሱ እየተፈራራ ችግር ነበረ። ወንድም ቢኒ።