መዝሙረ ዳዊት 110:1 እግዚአብሔር[ያህዌ] ጌታዬን[አዲኒን]፦ ጠላቶችህን ለእግርህ መቀመጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው።


ከውይይት የተወሰደ፤ Wahid Omar Negash ክፍል 1፤ ሰላም ዋሂድ፤ ይህን ቃል ለማስተዋል አውዱ የተነገረበትና አንዴት ሆኖ መንፈሳዊ አመልካችነት ሊይዝ እንደቻለ ማየት ያስፈልጋል። ለጌታዬ (አዶዶኒ la•ḏō•nî)’to my lord’ (የቃሉ ስር 113. Adon፣ adown aw-done’ or (shortened) adon {aw-done’}; from an unused root (meaning to rule); sovereign, i.e. controller (human or divine):–lord, master, owner. Compare also names beginning with “Adoni-“.) የሚለው አገላለጽ የኮዴክስ ወይም ጥንታዊ የእጅ ጽሑፍ לימיני adoni ማለት ጌታዬ my lord ወይም ዋና አዛዤ ማለት ነው። ይህም ሰዋዊ የመአረግ መጠርያ ነው። ለምድራዊ የበላይ ገዢዎች የሚውል የማእረግ መግለጫ ንው። ላአዶኒ l’adoni ማለት ‘ለጌታዬ to my lord’ ማለት ነው። ይበልጥ ግልጽ እንዲሆን በእ/ር ቃል በደንብ ማስተዋል አለብን። አዶን እና አዶናይ ያለ ማሻማት መለኮትን የሚያመለክቱ ሲሆን ሁለቱም አምላክን ለማመልከት ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ። አዶኒ ሊቃውንት ምሁራን በእነዚህ ቃላት መካከል ያለውን ልዩነት ለይተው ማወቅ መልካም ይመስለኛል። ለምሳሌ ያህል ዚ ኢንተርናሽናል ስታንዳርድ መጽሐፍ ቅዱስ ኢንሳይክሎፒድያ እንዲህ በማለት እንዳይምታታብን በጥቆማ መልክ ያሳስበናል: – ‘አዶኒ’ (‘ጌታዬ’ADONI (‘my lord’) የሚለው ንጉሣዊ ማዕረግ ሲሆን(1 ሳሙኤል 29 8) ይህ ቃል አዶናይ ADONAI ከሚለው መለኮታዊ አመልካች ለያህዌ Yahweh ነው። (አዶናይ)ADONAI (‘my Lord’)) ከመለኮት ክብር ጋር የተያዛዘ ክብር የምንጠቀምበት መሆኑንን አንዳንረሳ ያሳስበናል። አዶናይ ሲነበብ ‘adon-eye’; ሲሆን adoni የሚነበበው ‘adon-ee’, ነው። በዚህ ልዩነት መሰረት አዶኒ ‘my lord’; or ‘my master’ የሰው ክብርን ገላጭ የመአረግ ስም ሲሆን መለኮትን ለመግለጥ በመጽሓፍ ጥቅም ላይ በየትም ቦታ ላይ አልዋለም።
ይህ ከሆነ እውነቱ ከተለመደው የምድር እይታ ከፍ ብለን በንስር አይን እንደገና በቃሉ ውስጥ አይተን እውነቱን ልንረዳው ተገቢ ነው። መዝሙረ ዳዊት 110:1 እግዚአብሔር[ያህዌ] ጌታዬን[አዲኒን]፦ ጠላቶችህን ለእግርህ መቀመጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው።
የማቴዎስ ወንጌል 22:43-44 እርሱም፦ እንኪያስ ዳዊት፦ ጌታ ጌታዬን፦ ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው ሲል እንዴት በመንፈስ ጌታ ብሎ ይጠራዋል?
ወደ ዕብራውያን 1: 13 ነገር ግን ከመላእክት፦ ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ ከቶ ለማን ብሎአል?
የሐዋርያት ሥራ 2:34-35 ዳዊት ወደ ሰማያት አልወጣምና፥ ነገር ግን እርሱ፦ ጌታ ጌታዬን፦ ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው አለ። 36 እንግዲህ ይህን እናንተ የሰቀላችሁትን ኢየሱስን እግዚአብሔር ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ።
አሁን ጥያቄው ዳዊት ይህን ሲናገረው ጌታየ የሚለው ማንን ነው? በመዝ፤ 110፡1 እና ማቴ፡ 22:44 እና ዕብ፤ 1:13? …2 ውንድም ቢኒ።

ክፍል 2፤ “ያህዊው Yehovah” የሚለው ማንን እንደሆነ በመዝሙር 110፡1 በዕብራይስጥ ስሙ በግልጽ እንደ ተጠቀመ እናውቃለን። ነገር ግን ማንን ነው? “ጌታዬ MY Lord?” ብሎ የሚጠራው። አዶን ወይም አዶኒ ለሰው የሚሰጥ የመአረግ ስም እስከሆነ ድረስ ዳዊት እሱ ራሱ ለራሱ መሆን አለበት የሚለው ሃሳብ ይጭራል ይህ ግን ከተለመደው እይታ ውጭ በመሆኑ በእ/ር ቃል መረጋገጥ አለበት። በዚህ በዳዊት መዝሙር ውስጥ እየተናገረ ያለው ያህዌ THE LORD እራሱ ነው። እግዚአብሔር አብ በማንኛውም ጊዜ ለማንም ሰው በቀጥታ አልተናገረም (ድምፁን ከቶ አልሰማችሁም፥ መልኩንም አላያችሁም፤ ዮሐንስ 5:37), አባት ከያህዌ/ኢየሱስ ልጁ ልጁ ዘንድ ትእዛዝ አይወስድም። ኢየሱስ በአጭሩ የአብ ፈቃድ፤ የአብ[የመንፈስ] ቃል፤ የአብ[የመንፈስ] ሃሳብ፤ የአብ ፤ ትበብ፤ የአብ ሃይል፤ የአብ ክብር ክርስቶስ መሆኑ ግልጽ ነው። ወይም የመናፍስት አባት የአብ ሁለንተና ለፍጥረታዊው አእምሮ ይታይ ዘንድ የመንፈስ ወይም የማይታየው ሃይል ሙሉ ክብር መገለጥ ነውና። እውነቱ የማቴዎስ ወንጌል 11፡27 ከአብ[ከመንፈስ] በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፥ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም። ወልድም ሊገለጥለት ለፈቀደው ይህን ያስተውል ዘንድ መንፈሱ ለነቃው በሰማያት ያለው አባት[መንፈስ] እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ[ደስተኛ] ነህ ልንለው እንችላለን። ለባለአእምሮው ደግሞ እንዲህ ነው “1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2፡14 ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም።” በመንፈስ ካለማወቅ ካለ መቀበል የለም።
“Adonay” # 136 “ከአዶን adon” የተወሰደ ሲሆን በዶክተር ስትሮንግም ጭምር Dr. Strong እንደተገለጸው ” ጌታ the Lord (ለእግዚአብሔር ብቻ የሚሆን ትክክለኛ ስም ሆኖ ያገለግላል ብለውናል)” እናም ከሁለት መቶ ጊዜ በላይ “አዶናይ Adonay” ተጽፈዋል። ዘጸአት 4፡10- “..ሙሴም ለያህዌ፦ አዶናይ ሆይ፥ the LORD O my Lord” (Yahweh O my Adonay) ..
ጥንት በመጽሃፍ ቅዱስ ዘመን መንፈሳዊ ቅኔ መቀኘት በዛ ውስጥ ድርብ መለክት መተንበይ የተለመደ ነው። በመዝሙር 110 ፡1 ላይ በእርግጠኝነት ያህዌ[እግዚአብሔር] ሌላ ጌታዬን እያናገረ አይደለም። ያህዌ[እግዚአብሔር] ይልቅ እየተናገረ ያለው ከስልጣን ከእርሱ በታች less authority ለሆነ ጌታ ለሆነ ሰው ነው። በበመዝሙር 110 ፡1 ያለው ያህዌ[እግዚአብሔር] Yahweh was Jesus ኢየሱስ, ስለዚህ ያህዌ Yahweh [LORD/ኢየሱስ Jesus] እየተናገረ ያለው ለአዶን ወይም በተሳቢ ቃሉ ለአዶኒ adon [ለምድራዊ ጌታው ለዳዊት Lord David] ነው። ይህንን የሚፈታልን የእ/ር ቃል ማየት የግድ ነው። We all know the Bible is a book of definition.
እውነት ነው አዶ Adon ለኢየሱስ ለመሲሁ ትንቢታዊ መንፈሳዊ አመልካች ማጣቀሻ አለው። ግን በብሉይ ኪዳን የአውዱ ዋና መንፈስ አይደለም። በብሉይ ዳዊትና ሌሎችም ጨምሮ ራሳቸውን በቅኔ በሦስተኛ ሰው ገጸ ባህርይ ትራኬ ራሳቸውን ይጠቅሳሉ። ለምሳሌ ለመጥቀስ ያክል።
ዳዊትም እግዚአብሔር ከሳኦል እጅና ከጠላቶቹ እጅ ሁሉ ባዳነው ቀን የዚህን ቅኔ ቃል ለእግዚአብሔር ተናገረ። እንዲህም አለ፦ እግዚአብሔር ዓለቴ አምባዬ መድኃኒቴ ነው፤ 51 የንጉሡን [ለራሱ ለንጉሥ ዳዊት የመዳን ግንብ ግንብ] መድኃኒት ታላቅ ያደርጋል፤ ቸርነቱንም ለቀባው፥ ለዳዊትና ለዘሩ፥ ለዘላለም ይሰጣል።” (2 ኛሳሙ 22 1 እና 51). እናም መዝሙር 144 ቀዳማዊ ቁጥር 1 እና 10 ” 1 እግዚአብሔር አምላኬ ይባረክ፥ ለእጆቼ ሰልፍን፥ ለጣቶቼም ዘመቻን የሚያስተምር…..10 #ለነገሥታት መድኃኒትን የሚሰጥ፥ ባሪያውን #ዳዊትን ከክፉ ሰይፍ የሚያድነው እርሱ ነው። እንዳትረሱ ዳዊት በመንፈስ መነሳሳት እንደተናገረው ጭምር። የማርቆስ ወንጌል 12፡36 ዳዊት ራሱ በመንፈስ ቅዱስ፦ ጌታ ጌታዬን….. ክፍል3 ወንድም ቢኒ።

ክፍል3፤ ይሁን እንጂ “ጌታ” በእርግጥ የዳዊት ጠላቶችን በሙሉ የእግሩ መረገጫ[ሁሉን ከስልጣኑ ስር] አድርገዋል? አላደረገም የዚህ ልዩ ተስፋ ሙላት ለእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ የተጠበቀ ነውና(ዕብ 10:12 እርሱ ግን ስለ ኃጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፥13 ጠላቶቹም #የእግሩ #መረገጫ እስኪደረጉ #ድረስ ወደ ፊት ይጠብቃል።
ወደ ዕብራውያን 1፡1 ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ፥2 ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን[Gk: ‘ዘመን ages’] በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤….13 ነገር ግን ከመላእክት፦ ጠላቶችህን[ለክርስቶስ እንጂ ለዳዊት አይደለም Christ, not David] የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ[ክርስቶስ Christ’s] ድረስ በቀኜ ተቀመጥ ከቶ ለማን ብሎአል? (ዕብ 1: 1 – 2, 8, 13)።
ስለዚህ እዚህ ጋር ግልጽ ሆኖ እንደሚታየው ክርስቶስ “የዳዊት ልጅ” (ከትውልድ ሃረግ) እንዴት እንደሚሆን የተገለጠበትን ነገር ዳዊት “ጌታ” ብሎ ሊጠራው እንደቻለ ፍንጭ ሊሰጠን ይችላል። ከመንፈሳዊ ትርጉሙ አንጻር ጌታዬ ብሎ ኢየሱስን እንደጠራው ግልጽው ነው። እንዳስተዋልነው ጌታ ኢየሱስ ነው ጠላቶቹ ሁሉ ከእግሩ ሥር[ከስልጣኑ ስር ወይም #የእግሩ #መረገጫ footstool] የሚሆኑለት ። (1 ኛ ቆሮ 15 25)። እ/ር አሰበ ማለት የፈለገው የአእምሮ የሃይማኖት ኦሎምፒክ ጅምናስቲክ ብትሰራ እ/ር አሰበ ማለት ሆነ ማለት እንደሆነ ግልጽ ነው። በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው እቅዱና አጀንዳው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን #ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1፡10 ይህም በዘመን ፍጻሜ አሁን በዚህ ገጽ የሚያቃልሉት ወንድሞችና እህቶች ወገኖች ሆኑ ሃይማኖቶችም ሆኑ ነብዮቻቸው ሁሉ በክርስቶስ ስልጣን ስር ለመጠቅለል የተወሰነ ነው ይህም በአገራችን አበላል የተበላ እቁብ ነው! ። ፍጹም የሆነ ሲመጣ ሌላው ትንንሽ ሃይል ሁሉ ይሻራል። አለም ሁሉ፤ ሃይምኖቶች ሁሉ፤ የባሃኢ፤ ቡድሂዝም፤ ክርስትና፤ ኮንፊሺያኒዝም፤ዩኒተሬያን፤ የሂንዱ፤ የእስልምና፤ የአይሁድ፤ የሺንቶ፤ የታኦ፤ ታኦይዝም ወዘተ…. አሁን ጠላቶቹ የሚመስልሉ ሁሉ ከእግሩ ሥር[ማለትም ከስልጣኑ ስር ወይም #የእግሩ #መረገጫ footstool] ይሆናሉ። በመንፈስ ቅዱስ ኅይል ፍጥረት ሁሉ ኢየሱስ ጌታ ነው ብሎ ይድናል። “1ኛ ወደ ቆ ሮንቶስ ሰዎች 12/3 ….በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር፦ ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ። 1Cor 12/3 ….that no man can say that Jesus is the Lord, but by the Holy Ghost” እናስተውል በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር፦ ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቆናል አሁን ጠላቶቹ የሆኑት አድስዋቸው ከክርስቶስ ስልጣን ስር ሲጠቀለሉ ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ሆነው ኢየሱስ ጌታ ነው እያሉ ለበጉ ክብርን ተንበርክከው ይሰጣሉ። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2/10ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥11መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።
በትንቢቱ የዳዊት ዙፋን የክርስቶስን ዙፋን የሚሆነው እንዴት ነው? “ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል … ሉቃስ 1፡32″ የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ” ማቴ 1፡1. ኢየሱስ ሁለቱንም ማንነት የያዘ ልጅ እና ጌታ መሆኑ ግልጽ ነው።
ስለዚህም ያህዌ በራሱ ላይ ትንቢት መጀመሪያውን ባቻ ሳይሆን መጨረሻውንም ተናገረ። የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ እንደሚመጣና ጠላቶቹ ሁሉ ከእግሩ ስር እንዲገዙለት አወጀ። መጀመሪያውን ብቻ ሳይሆን መጨረሻውን የሚናገር ብቸኛው ሃይል ነውና። ትንቢተ ኢሳይያስ 46፡9 እኔ አምላክ ነኝና፥ ሌላም የለምና የቀድሞውን የጥንቱን ነገር አስቡ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም።10 #በመጀመሪያ #መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን እነግራለሁ፤ ምክሬ ትጸናለች ፈቃዴንም ሁሉ እፈጽማለሁ እላለሁ። ወንድም ቢኒ።

Ahmad Diddat አዶናይ ለኢየሱስ የዋለበት ጥቅስ አለ?

መልስ፤ በቡልይ ኪዳን[ከኦሪት ዘፍጥረ እስከ ትንቢተ ሚልክያስ] “(የአብን …#ድምፁንም #ከቶ #አልሰማችሁም፥ #መልኩንም #አላያችሁም፤ ዮሐንስ 5:37)”

http://wongelradio.org/archives/2195
  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal