ማሪያም የዳዊት ዘር አንዳልሆነች እወቅ በወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ ሲል ምን ማለቱ አንደሆነ በእ/ር ቃል አሳይካለሁ።


ከውይይት የተጠቀሰ፤ Christo Light ክፍል 1፤ ሰላም፤ ኢየሱስ የዳዊት ዘር እንዳልሆነ እወቅ ከዳዊት ዘር እንደተወለደ ተቆጠረለት እንጂ። ዳዊትስ ጌታ ብሎ ከጠራው:? #እንዴት#ልጁ#ይሆናል? ብሎ ኢየሱስ የጠየቃቸው ትርጉሙ ገብቶሃል? ማሪያም የዳዊት ዘር አንዳልሆነች እወቅ በወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ ሲል ምን ማለቱ አንደሆነ በእ/ር ቃል አሳይካለሁ። ሮሜ1፡”3-4 ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው። እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ተወለደ። በስጋ ከዳዊት ዘር ሳይወለድ ለምን በስጋ ከዳዊት ዘር እንደተወለደ ተቆጠረለት? በቃሉ እንየው። በቅድሚያ የሰው ልጅ አባት ማን ይመስላችሀል? ጌታ እየሱስ ክርስቶስ በብፅዕት ድንግል ማርያም ማህፀን #የተረገዘው( CONCEIVED by the Holy Spirit.) በመንፈስ ቅዱስ መፅለል ነበር። እንደምናስተውለው መንፈስ ቅዱስ ለእርግዝናዋ ምክንያት ነው። እየሱስም ተወለደ ያስረገዛት መንፈስ ቅዱስ ቢሆንም የመንፈስ ቅዱስ ልጅ ግን አልተባለም አልነበረምም ነገር ግን የአባት(አብ) ልጅ ነው።”the Son of the FATHER” (II John 2:3 ያስረገዛት መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር መንፈስ ነው እንጂ ከ3ቱ ስላሴዋች አንዱ አይደለም ቢሆን ኖሮ እርሱ ባስረገዘ ሌላ አባት ባልተባለ። እንደ የስላሴ አፈ ታሪክ ቲፎዞዋች አባባል መንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ ስብእና ለብቻው ያለው ቢሆን ኖሮ ወይም ከ3ቱ ስላሴዋች አንዱ ቢሆን ኖሮ መንፈስ ቅዱስ አባቱ በተባለ ነበር እንጂ ሌላ ጣልቃ የገባ መለኮት አብ የተባለ በጉልበት አባቱ ባልሆነ። Even any simple minded person can understand that whoever conceives a child in a mother’s womb is the biological F-A-T-H-E-R OF THAT CHILD when it is born, NOT SOME OTHER PERSON or member of Trinity….።ክፍል 2 ወንድም ቢኒ።
ክፍል 2፤ ትንቢተ ኢሳይያስ 11 ፡1 ከእሴይ (ከዳዊት አባት) ግንድ በትር ይወጣል: ከሥሩም ቍጥቋጥ ያፈራል.2 የእግዚአብሔር መንፈስ: የጥበብና የማስተዋል መንፈስ: የምክርና የኃይል መንፈስ: የእውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል. 3 እግዚአብሔርን በመፍራት ደስታውን ያያል. ዓይኑም እንደምታይ አይፈርድም: ጆሮውም እንደምትሰማ አይበይንም 4 ነገር ግን ለድሆች በጽድቅ ይፈርዳል: ለምድርም የዋሆች በቅንነት ይበይናል በአፉም በትር ምድርን ይመታል: በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል. 5 የወገቡ መታጠቂያ ጽድቅ: የጎኑም መቀነት ታማኝነት ይሆናል.
በትረ መንግሥቱ ከይሁዳ እንደ ሚመትጣ ከዳዊት ዘርም እንደሆነ ከኦሪት ጀምሮ እ / ር ሲናገር ነበረ :: “ኦሪት ዘፍጥረት 49 10 በትረ መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም: የገዥም ዘንግ ከእግሮቹ መካከል:. ገዥ የሆነው እስኪመጣ ድረስ የአሕዛብ መታዘዝም ለእርሱ ይሆናል” ከዳዊት ግንድ እንደ ሚመጣ ደግሞ “መዝሙ 89 29 ዘሩንም ለዓለምና ለዘላለም:. ዙፋኑንም እንደ ሰማይ ዘመን አደርጋለሁ “ሲል ለባሪያው ለዳዊት ቃል ገብቶለት ነበረ :: የጌታ እየሱስ እናት ማሪያም በዮሴፍ በኩል በጋብቻ የዳዊት ዘር አድርጎ እ / ር ይቆጥራታል :: መጽሐፍ ዮሴፍ የዳዊት ዘር እደሆነ ያስረዳናል ::” ሉቃ 1 27 ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ:. የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ “ስለ የጌታ እየሱስ እናት ማሪያም ትውልድ ከይሁዳ ነገድ መሆንዋን ምንም አይናገርም ::” ሉቃ 1 27 ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ: የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ. “ሲል ብቻ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ብሎ በእጮኛዋን ነገድ ብቻ ያስተዋውቃታል ::
ከየት ነገድ እንደ ሆነች ፍንጭ የምናገኘው መላኩ ገብርኤል ለማሪያም የእ / ርን ቃል ሲያቀብላት ከአሮን ወገን የሆነችውን ኤልሳቤጥን ዘመድሽ ብሎ የጠራትን እናስተውላለን :: የመጥምቁ ዮሃንስ እናትን ከከአሮን ወገን እንደሆነች መጽሐፍ ይናገራል በዚህም የጌታ እየሱስ እናት ማሪያም እንደ ዘመድዋ ኤልሳቤት ከአሮን ወገን እንደሆነች ግልጽ ነው :: “ሉቃ 1 36 እነሆም ዘመድሽ ኤልሳቤጥ: እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች: ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው; “መላኩ ገብርኤል ለማሪም የእ / ርን ቃል ሲያቀብላት ዘመድሽ ኤልሳቤጥ ብሎ ያረጋግጣል ከዛም ማሪያም ለወራት ከኤልሳቤት ዘመድዋ ዘን ተጠልላለች “ሉቃ 1 5 በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ; ሚስቱም ከአሮን ልጆች ነበረች: ስምዋም ኤልሳቤጥ ነበረ.” ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ; ሲል ሚስቱም ከአሮን ልጆች ነበረች:. ስምዋም ኤልሳቤጥ ነበረ “ይለናል እንደ ምናስተውለው የማሪም ዘመድ ከአሮን ወገን መሆንዋ ብቻ ሳይሆን ከተለያየ ነገድ ጋብቻ ያደርጉ እንደ ነበር እናስተውላለን :: ዘካሪያስ ከአብያ ክፍል ሲሆን ሚስቱም ኤልሳቤጥ ከአሮን ልጆች ነበረች :…. 3ክፍል። ወንድም ቢኒ።
ክፍል 3፤ በዚህም ከይሁዳ ነገድ የሆነው የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ከአሮን ነገድ የሆነችውን የጌታ እየሱስ እናት ማሪያም መታጨቱ በዛ ዘመን እንግዳ ነገር እንዳልሆነ እናስተውላለን :: ስለዚህ ጌታ ከይሁዳ ነገድ የዳዊት ዘር የተባለው በዮሴፍ በኩል ነው የዳዊት ልጅ የተባለው እንጂ ከአሮን ወገን ከሆነችው ከናቱ ከማሪም በኩል እይደለም :: ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ ብሎ እንደ ተነገረ እ / ር ዮሴፍንና ማሪያምን አንድ ስጋ አድርጎ ስለ ሚቆጥር ከይሁዳ ነገድ አድርጎ ይቆጥራታል በዚህም ጌታ የዳዊት ልጅ ተብሎ ተጠራ :: በጋብቻ ያለው ውህደት በጌታ ፊት ምንኛ ክቡር እንደሆነ ስናስተውል ትህትናን ያስይዛል በአመለካከታችንም ንስሃ ያመጣብናል :: እዚህ ላይ እ / ር ስለ ጋብቻ ያለው አመለካከት እጅግ ጥብቅና ሰማይ ከምድር እንደ ሚርቅ ከሰው እመለካከት የራቀ እደሆነ እንረዳለን ::….
ጌታ በ “ዘፍ 2 24 ጠቅሶ ሲናገር በ” ማቲ 19 5 አለም. ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል: ከሚስቱም ጋር ይተባበራል:? ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ የሚለውን ቃል አላነበባችሁምን 6 ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም. እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው “ለዚህም ነው ጌታ ፈሪሳውያንን እንዴት የዳዊት ልጅ ልሆን እችላለሁ ሲል መለኮታዊ ምንጩን እንዲያስተውሉ በማድረግ ዝም ያሰኛቸው ::” የማቴዎስ ወንጌል 22 41-42 ፈሪሳውያንም ተሰብስበው ሳሉ:. ኢየሱስ: ስለ ክርስቶስ ምን ይመስላችኋል? የማንስ ልጅ ነው? ብሎ ጠየቃቸው. የዳዊት ልጅ ነው አሉት.43-44 እርሱም: እንኪያስ ዳዊት: ጌታ ጌታዬን. ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው ሲል እንዴት በመንፈስ ጌታ ብሎ ይጠራዋል 45 ዳዊትስ ጌታ ብሎ ከጠራው:? #እንዴት #ልጁ #ይሆናል? አላቸው .46 አንድም ቃል ስንኳ ይመልስለት ዘንድ የተቻለው የለም:. ከዚያ ቀንም ጀምሮ ወደ ፊት ማንም ሊጠይቀው አልደፈረም “አሜን. ሰላም ለአንተ ይሁን። ወንድም ቢኒ።

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal