
ከውይይት የተጠቀሰ፣ Bizuneh Bekele የዮሐንስ ወንጌል 5:39 እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፤ የዮሐንስ ወንጌል 7:15 አይሁድም፦ ይህ ሰው ሳይማር መጻሕፍትን እንዴት ያውቃል? ብለው ይደነቁ ነበር።
ጌታ እንዳለው ከሙሴ ዘንድ ስለሱ ተጽፈዋል እስቲ ይህን የሚደንቅ ምጢር እንመልከት። ‘ እግዚአብሔር (ያህዌ) ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም[ደህንነቴም yashua: እያሱ በእብራይስጥ እየሱስ በግሪክ] ሆነልኝ፤ እርሱ አምላኬ ነው፤ አመሰግነዋለሁ፤ የአባቴ አምላክ (ኤሎሂም) ነው፤ እኔም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ። እግዚአብሔር (ያህዌ) ተዋጊ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር (ያህዌ) ነው። ‘ ዘፀአት 15:2-3 አስተዋላችሁትን ቢቱን እግዚአብሔር (በያህዌ) ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም[ደህንነቴም yashua: እያሱ በእብራይስጥ እየሱሴም በግሪክ] ሆነልኝ። እንዲገባን በግልጽ አማርኛ እንየው “ያህዌ ደህንነቴ ወይም እየሱሴ ሆነልኝ[“ያህዌ እየሱሴ ሆነልኝ”]”
ይህ የእየሱስ ስጋ የመልበሱ ትንቢት ነው። የአሮጌው ኪዳን እ/ር በአዲስ ኪዳን ሰው ሆኖ ስለመገለጡ ነው። ይህም በኢሳያስ 12:2-3 ‘እነሆ፣ እግዚአብሔር ድነቴ[እየሱሴ] ነው፤ እታመናለሁ፣ ደግሞም አልፈራም፤ ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም [እየሱሴም]ሆኖአል።” ከድነቴ[እየሱሴ] ምንጮች ውሃ በደስታ ትቀዳላችሁ። ‘ ኢሳይያስ 12:2-3 እንደምናስተውለው ኢሳያስ በሙሴ መጽሐፍ በዘፅአት የተፃፈውን ደግሞ ሲጠቅስ እናስተውላለን። በዚህ አያበቃም እየሱስ ይህን በመጥቀስ አጽንቶታል።
ጌታ እየሱስ ይህን ትንቢት ግልጽ አድርጎ ፈቶታል። ‘የበዓሉ መጨረሻ በሆነው በታላቁ ቀን፣ ኢየሱስ ቆሞ ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ አለ፤ “ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ፤ በእኔ የሚያምን፣ መጽሐፍ እንዳለ የሕይወት ውሃ ምንጭ ከውስጡ ይፈልቃል።” ‘ ዮሐንስ 7:37-38 በሌላ የእንግሊዝኛ ትርጉም ማንም ከተጠማ ከደህንነት ምንጭ ዉሃ ይጣጣ ይላል።
ይህ ግልጽ ቃል የሚያስረዳን በአሮጌው ኪዳን እየሱስ [በእብራይስጥ እያሱ] ስለ ድነት ወይም ደህንነት ተደብቆ የነበረው ሚስጥር እንደሆነ ነው። ጌታ እየሱስ ስጋ የለበሰው ያህዌ ነው። “ያህዌ እየሱሴ ሆነልኝ” በቀድሞው ኤልሻዳይ ብሎ እራሱን የጠራው በራእይ[በእየሱስ ክርስቶስ መገለጥ መጽሐፍ] እራሱን በድጋሚ ሲያረጋግጥ ሁሉን ቻይ ብለዋል። ጌታ እየሱስ ክርስቶስ በአዲስ ኪዳን አስር ቦታ ላይ (ኤልሻዳይ ‘el ale Shadday shad-dah’-ee) ተብሎ ተጠርተዋል። ልናየው ያልቻልነው ተርጋሚዎቹ ኤልሻዳይ እንደማለት ፈንታ በአማርኛችን ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ በእንግሊዝኛ Almighty ብለው ስለተረጎሙት ነው ። የፃድቅ ሃብቱ ትጋቱ ነውና ማጥናት ትችላላችሁ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:18 , የዮሐንስ ራእይ 1:8, 4:8, 11:17, 15:3, 16:7, 16:14, 19:6, 19:15, 21:22 ወንድም ቢኒ።