አንድ አካልና #አንድ መንፈስ አለ።


ከውይይት የተጠቀሰ፤ Ayu Wendimu ክፍል 1፤ ሰላም ለአንተ ይሁን ወንድም አዩ። እኔ መቸም በጥቅስ መወራወር አይሆንልኝም ዕንባቆም እግዚአብሔርም መለሰልኝ እንዲህም አለ አንባቢው ይፈጥን ዘንድ ጻፈው አለኝ አይደል ያለው። ውስጤ ካመጣው መጻፍ ደስ ይለኛል። ተባረክ። ትንቢተ ዕንባቆም 2፡2 እግዚአብሔርም መለሰልኝ እንዲህም አለ፦ አንባቢው ይፈጥን ዘንድ ራእዩን ጻፍ፥ በጽላትም ላይ ግለጠው። እግዚአብሔር[አብ] መንፈስ ነው። ጌታ ኢየሱስም መንፈስ ነው። መንፈስ ደግሞ አንድ ነው። ኢየሱስ እኔና አብ[መንፈስ] #አንድ ነን ማለቱ ግልጽ ነው። የኢየሱስ መንፈስ የአባቱ መንፈስ ነው።
የዮሐንስ ወንጌል 4:24 እግዚአብሔር[አብ] መንፈስ ነው። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3:17 ጌታ ግን መንፈስ ነው[ኢየሱስ]፤ 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:45 ኋለኛው አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ [ኢየሱስ] ወዘተ…. 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12፡4 መንፈስ #አንድ ነው። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:4 #አንድ አካልና #አንድ መንፈስ አለ። ለምሳሌ ለማየት ያህል። ወደ አባቴ እመለሳለሁ ሲል አባት መንፈስ ነው በክርስቶስ አእምሮ እናስተውለው ወደ አባቴ ማለቱ ወደ መንፈሴ እመለሳለሁ ማለቱ ነው። ቀድሞ በመንፈስ ክቡር ነበር። ከአብ ወይም ከአባት ወጥቼ መጥቻለሁ ሲል ከመንፈስ ወጥቼ መጥቻለሁ ማለቱ ነው። በመጀመሪያው ቃል ወይም መንፈስ ነበረ፥ ቃልም መንፈስም እግዚአብሔር ነበረ። ቃልም ወይም መንፈስም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ ። ስሙንም #አማኑኤል ይሉታል ትርጓሜውም። #እግዚአብሔር #ከእኛ #ጋር የሚል ነው።
ኢየሱስ በራእይ 3/1 …ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት..ያሉት ሲል ሰባት መንፈስ አለ ማለት አይደለም መንፈስ አንድ ነው። ሰባት የመንፈስ ስራ መገለጦች ግን አሉ። ለምሳሌ ለልጅነት ክብር እግዚአብሔር መንፈሱን ሰፍሮ ለልጁ አይሰጥምና የልጁ መልክ ይዞ መገለጥ ማለት አንዱና ዋንኛው በሰባቱም የእግዚአብሔር መናፍስት አሰራር እንደ እየሱስ ክርስቶስ ይዞ መገለጥ ነው። በኢየሱስ ውስጥ የእግዚአብሔር መንፈስ፥ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፥ የምክርና የኃይል መንፈስ፥ የእውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል። እግዚአብሔርን በመፍራት ደስታውን ያያል። ዓይኑም እንደምታይ አይፈርድም፥ ጆሮውም እንደምትሰማ አይበይንም፤ትንቢተ ኢሳይያስ 11/2 የዮሐንስ ራእይ 3/1 …ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት..ያሉት እንዲህ ይላል።
ይህም አንዱ መንፈስ በብዙ ክብር ተገልጦ ታይተዋል። ለምሳሌ የእግዚአብሔር መንፈስ ወይም የመንፈስ ቅዱስን አንድ ቢሆንም ለማስተዋል ያህል ስያሜውና አንዳንድ ባህሪያቱን በመጽሃፍ በጥልቀት እንመልከታቸው ብንል እርሱ “የእግዚአብሔር መንፈስ The Spirit of God” “የክርስቶስ መንፈስ The Spirit of Christ” “የቅድስና መንፈስ The Spirit of Holiness”, “የእውነት መንፈስ The Spirit of Truth”, “የጤናማ አእምሮ መንፈስ The Spirit of a Sound Mind”, “የነጻነት[የአርነት] መንፈስ The Spirit of Liberty”, ” “የሚያቃጥል መንፈስ The Spirit of Burning”, “የአብ[አባት] መንፈስ The Spirit of the Father” “ወልድ[የልጁ] መንፈስ The Spirit of the Son”, “የ ቃል ኪዳኑ[የተስፋው] መንፈስ The Spirit of Promise” “የየዋህነት መንፈስ The Spirit of Meekness” “የመረዳት[የማስተዋል] መንፈስ The Spirit of Understanding” “የጉዲፈቻ መንፈስ The Spirit of Adoption “” የትንቢት መንፈስ The Spirit of Prophecy “” የክብር መንፈስ The Spirit of Glory “” የምክር መንፈስ The Spirit of Counsel “” የጸጋው መንፈስ The Spirit of Grace “” የጌታ መንፈስ The Spirit of the Lord “ወዘተ … ወዘተ … ወዘተ. ..።ክፍል2 ቢኒ።

ክፍል 2፤ የዮሐንስ ወንጌል 4:24 እግዚአብሔር[አብ] መንፈስ ነው። አብ ሙላት የሚኖርበት በልጁ በክርስቶስ ውስጥ ይኖራል (ቆላ. 1 19; 2 9) እና በልጁ በኩል የማይታየውን ማንነቱን ገልጦታል (ዮሐንስ 1፡18) The Father is Spirit, He is source of all things, and He is embodied in the Son የማይታየው እግዚአብሔር በክርስቶስ ተገልጧል ክርስቶስ የእግዚአብሔር መልክ the invisible God is revealed in Christ, Christ is the IMAGE of God (ቆላ 1:15). ስለዚህም ወልድ እና አብ አንድ ናቸው (ዮሐ 10 30) ወልድ ደግሞ አባት ተብሎ ተጠርተዋል (ኢሳ 9: 6). እንዲገባን በዚህ መልኩ እናስቀምጠውና ፊልጶስ ጠየቀ. ጌታ ሆይ: አብን አሳየንና ይበቃናል አለው. ኢየሱስም አለው: አንተ ፊልጶስ: ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቶአል; እንዴትስ አንተ አብን[መንፈስን] አሳየን ትላለህ? እኔ በአብ[በመንፈስ] እንዳለሁ አብም[መንፈስም] በእኔ እንዳለ አታምንምን? አብ[መንፈሴ] በእኔ ውስጥ ነው? እኔ የምነግራችሁን ቃል ከራሴ አልናገረውም ነገር ግን በእኔ የሚኖረው አብ[መንፈሴ] እርሱ ሥራውን ይሠራል. እኔ በአባቴ እንዳለሁ እና በእርሱ ውስጥ እንዳለሁ አምነኝ »ብሎ መለሰ (ዮሐ 14 8-11). ምን ምን አለ? የተጠየቀው ስለአብ የመለሰው ስለራሱ ነው። ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? ማ? አብ! ደስ ይላል። አብ የተባለው መንፈስ በሱ ውስጥ ነው እሺ እሱ በአብ ውስጥ መሆኑ ምን ይባላል። እየሱስ እውነት ነው አይዋሽም የመነ ብጹ[ደስተኛ] ነው። Believe Me that I AM IN THE FATHER, AND THE FATHER IN ME።እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን?
‘የመለኮት ሙላት ሁሉ በአካል በእርሱ ይኖራልና፤ ‘ቈላስይስ 2:9 “For in Him dwelleth all the fullness of the Divinity bodily” (Col. 2:9 አስተውሉ በዚህ አውድ! በመሎኮት አካል ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስ አለ እያለን ሳይሆን ፡ በተቃራኒው ልክ የወይን መጥመቂያ በርሚል ወይም በአቅማዳም ውስጥ አዲስ የወይን ጠጅ ቲፍ ብሎ እንደሚሞላ በኢየሱስ ክርስቶስ አካል ውስጡ መሎኮት በሙላት ቲፍ ብሎ ታጭቆ ይኖራልና! እያለን ነው። ሃሌሉያ!…።ክፍል 3 ቢኒ።

ክፍል 3፤ እውነት ወይም ምስክርነት የሚፀናው ወይም የሚመሰረተው በሁለት ወይም በሰዎስት ነውና ተጨማሪ የእ/ር ቃል ያስፈልገናል። የዮሐንስ ወንጌል 8:17
ጌታ ምን እንዳለ አስተውሉ። ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ። መጣ እሺ ከዛስ በኋላስ መንፈስ ስለሆነ ምን አለ? ዓለም አያየኝም፤እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤ በዚያን ግዜ ምን ይከሰታ? ማወቅ ይከሰታል። ‘እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ።’ ሃይሉ ያለው ማወቁ ላይ ነው ዓለም አያየኝም፤እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤’ ቅኔውን ሲፈታው ስለራሱ እንጂ ስሌላ እያወራ እንዳልሆነ አስተዋላችሁ? ።
የዮሐንስ ወንጌል 14/18 ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ። 19ገና ጥቂት ዘመን አለ ከዚህም በኋላ ዓለም አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤ እኔ ሕያው ነኝና እናንተ ደግሞ ሕያዋን ትሆናላችሁ። 20እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ።
“I will NOT leave you abandoned[comfortless], or send you off as orphaned ones. I am repeatedly (habitually) and progressively coming toward you [in the form of the comforter and spirit of truth] men. (Jn 14:18Open in Logos Bible Software (if available)
ጌታችን ምን እንዳለ በግማሽ ሳይሆ በሙሉ ትኩራታቹሁ አሁን አስተውሉ። መንፈስ ማን እንደሆነ መንፈስ ቅዱስ ምን እንደሆነ ግልጽ ያደርግልናል። የስላሴ 3ኛ አካል ነው ?ጌታ እራሱ ይናገር።
20እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን[አጽናኙ በሚመጣበት ቀን] ታውቃላችሁ።
“IN THAT DAY [the day when the comforter comes] you shall know that I am in My Father, and you in Me, and I IN YOU” (Jn 14:20Open in Logos Bible Software (if available)
“John 14/28 Ye have heard how I said unto you, I am going, and I AM COMING TO YOU” የዮሐንስ ወንጌል 14/28 እኔ እሄዳለሁ ወደ እናንተም እመጣለሁ እንዳልኋችሁ ሰማችሁ።
አስተዋላችሁ ጌታ ምን አለ ? I am going, and I AM COMING TO YOU! እኔ እሄዳለሁ ወደ እናንተም እመጣለሁ!
አሁን እየሱስ ክርስቶስ እራሱ ጳራቂላጦስ ተብሎ መጠራቱን በእ/ር ቃል እናረጋግጥ። nother Comforter[ጳራቂላጦስ] ሌላ አጽናኝ[ጳራቂላጦስ] ይሰጣችኋል ያለው ጳራቂላጦሱ ማን እንደሆነ እናያለን።
የዮሐንስ ወንጌል 14/15-16 ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ[ pray] ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ[ጳራቂላጦስ፤ parakletos par-ak’-lay-tosan intercessor, consoler:–advocate, comforter.] ይሰጣችኋል፤
John 14/15 If ye love me, keep my commandments.16 And I will pray the Father, and he shall give you another Comforter[ጳራቂላጦስ፤ parakletos par-ak’-lay-tosan intercessor, consoler:–advocate, comforter.], that he may abide with you for ever;
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 2
1 ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ[ጳራቂላጦስ፤ parakletos par-ak’-lay-tosan intercessor, consoler:–advocate, comforter.] አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
1John 2/1 My little children, these things write I unto you, that ye sin not. And if any man sin, we have an advocate[ጳራቂላጦስ፤ parakletos par-ak’-lay-tosan intercessor, consoler:–advocate, comforter.] with the Father, Jesus Christ the righteous: ያውላቹ እንግዲህ ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ጳራቂላጦስ አጽናኙ እራሱ ነው። በተረፈ በጌታ ፍቅር ሰላም ለአንተ ይሁን። የመለካከት ልዩነት በሃዋርያትም ዘመን ንርበረ ሁሉም የእ/ር ልጆች ናቸው። በመጨረሻ ደስ የሚለው እ/ር የሚያመጣን ቦታ አለ እሱም ሁላችንም የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ስራውን እየሰራ ነው ለክርስቶስ መንፈሳዊ አካል ሕንጻ ፍጹማን ያደርገናል። ክብር ለቅዱስ ስሙ ይሁን። ወንድም ቢኒ።

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal