
ከውይይት የተጠቀሰ፤ ያነሳችሁት ለእኔ በፊት ከሚቸግረኝ ቃል አንዱ ነበር። የቸገረኝ ግን ጊዜ ከተባለ ሃይል ስር ሆኜ ስለማየው ነበር ለብዙ ግዜ ያልገባኝ ከእ/ር ከመንፈስ ግዛት ጊዜ አይሰለጥንም ሁሉም አሁን ነው። ትላንትም ዛሬም ነገም ለእ/ር አሁን ነው። የደም ስርየት ሳይካሄድ እነዚህ ሁሉ መንፈሳቸው ውደ እ/ር ተመልሶ ለእ/ር ህያዋን መሆናቸውና ይገርመኝ ነበር። ቡሃላ ሲገባኝ ግን በመንፈሳዊው አለም ጊዜ የለም አለም ሳይፈጠር በፊት በጉ ታርዶላቸዋል የትረካው መገለጥ በጊዜ ውስጥ ታየ እንጂ አለም ሳይፈጠር በፊት በጉ እስከታረዳላቸው ድረስ በመንፈሳዊው አለምም ቢሆን ኢየሱስ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ሊቀ ካህናት ሆኖ፥ ስለ እኛ[ሁሉ] ቀዳሚ ሆኖ ለእነ አብርሃም መንገዱን አጽድቶት ነበረ። ስለዚህ በጊዜ ግዛት አለም ከተፈጠረ ቡሃላ ከአፈር የተሰራው ስጋቸው ወደ እፈር ሲመለስ ከእ/ር ያመጣው መንፈሳቸው ወደ እ/ር መመለሱና ለሱ ህያዋን መሆናቸው ለምን እንደሆነ አሁን ገባኝ።
የሉቃስ ወንጌል 20፡38 ሁሉ ለእርሱ ሕያዋን ስለ ሆኑ፥ የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም ይለናል። ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆኑት በኖህ ዘመን የነበሩት የማይታዘዙት ነፍሳት[መናፍስት፤ መንፈሶች] እ/ር 120 አመት የታገሳቸው እና በስጋ የፈረደባቸው ፍጻሚያቸውን በቃሉ አይተን እናስተውል። ጌታ እየሱስ ከሞቱና ከትንሳኤው ቡሃላ በኖህ ዘመን አልታዘዝ ያሉት አመጸኞች በእስራት ለነበሩትን ነፍሳትን (spirits መናፍስትን) ሰበከላቸው። ለነሱም የማስታረቁን ቃል ይዞላቸው ወረደ። ይህ እውነት የሚያሳየንም ክርስቶስ ለሃጢያታቸው መሞቱን ብቻ ሳይሆን መነሳቱም ለመጽደቃቸው መሆኑን ነው።
ይህንን ቃል Weymouth’s translation. ከተባለውን ትርጉም እናስተውል 1Pe3:18 Christ also once for all died for sins, the innocent One for the guilty many, in order to bring us to God. He was put to death in the flesh, but made alive in the spirit, in which He also went and proclaimed His Message to the #spirits that were in prison, 1Pe 3:20 who in ancient times had been disobedient, while God’s longsuffering was patiently waiting in the days of Noah during the building of the Ark, in which a few persons–eight in number–were brought safely through the water.”
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3 ፡18 ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፥ 19 በእርሱም ደግሞ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው፤ 20 ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ በውኃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ፥ የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኅ ዘመን በቈየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም። አንድአንዶች ይህንን ቃል ጠምዝዘው ሄዶ የሰበከው ከሱ በፊት ለሞቱ ጻድቃን ሰዎች ለማውጣት ነው ይላሉ ከየት እንዳመጡት አይታወቅም።
ከቃሉ እዳየነው ግን የሰበከው በእስራት የነበሩትን መናፍስትን ነው:: ለአቤል ለሴም ፤ለሄኖክ፤ ለኖህ፤ ለአብርሃም፤ ለያቆብ ፤ለኢሳቅ ወይም ለሙሴ፤ ለእያሱ ወይ ለኤልያስ ወይም ለየትኛውም በቀድሞ ኪዳን አካየዳቸውን ከእ/ር ጋር ያደረጉ ጻድቃን ለማናቸውም አይመለከትም::
እነዚህ ሁሉ ለእ/ር ህያዋን ናቸውና በመንፈሳዊው አለም : አለም ሳይፈጠር በፊት የታረደው በግ ታርዶላቸዋልና ስርየት በእ/ር አይን ሆኖላቸዋል። ከአፈር የተሰራው ስጋቸው ወደ እፈር ሲመለስ ከእ/ር ያመጣው መንፈሳቸው ወደ እ/ር ተመልሰዋልና ። የሉቃስ ወንጌል 20፡38 ሁሉ ለእርሱ ሕያዋን ስለ ሆኑ፥ የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም ይለናል።
ትንሳኤው በዚህ ምድር ከክርስቶስ ጋር አብረው ይገዙ ዘንድ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰው የሚለብሰው እንጂ እነሱ በመንፈሳዊው አለም ጊዜ ሰለሌ የጊዜ ሃይል ሳይዛቸው ተመልሰው ከብረዋል።
ለምሳሌ ያህል የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም። ብሎ ጌታ እንደ ተናገረ ሙሴና ኤልያስ ህግንና ነብያትን የሚወክሉት እንዳለ ሆኖ ሙሴ ሞትን አይተው የከበሩትን ኤልያስ ሞትን ሳያዩ የከበሩትን ይወክላሉና ።
ከስርየቱ በፊትም ህያዋን ሆነው እናስተውላለን በጉ የታረደውአለም ሳይፈጠር በፊት ነውና። “የዮሐንስ ራእይ 13፡8 ከዓለምም ፍጥረት ጀምሮ በታረደው በግ…” በዚህም የሕያዋን አምላክ እንጂ የሙታን እንዳይደለ እንገነዘባለን።
በጌታ ኢየሱስም የመስቀሉን መከራ ከተቀበለልን ቡሃላ ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ መንፈሱን እንደሰጠ። ሞተው ከነበሩት ከቅዱሳን ብዙ ስጋዎች ተነሱ የሚለው በስብሶ የነበረው ስጋቸው ከትንሳኤው ሃይል አቋድስዋቸው
ለምስክርነት ይሆኑ ዘንድ ስጋቸውን ለብሰው መነሳታቸውን የሚያሳይ ነው እንጂ መንፈሳቸው እማ እስቀድሞ ወደ መጠባት ወደ እ/ር ተመልሶ እንደነበር ግልጽ ነው።
“KJV፣ Eccl 12፡7 Then shall the dust return to the earth as it was: and the spirit shall return unto God who gave it. መጽሐፈ መክብብ 12፡7 አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥ ነፍስም (spirit መንፈስህ) ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ።”
ሰለዚህ የነዚህ ሰዎች ትንሳኤ በስብሶ የነበረው ስጋቸው የማይበሰብሰው ከእ/ር ወጥቶ ወደ እ/ር የተመለሰው መንፈሳቸውን በትንሳኤው ሃይል እ/ር በማዋሃድ ያስነሳቸው ናቸው። የማይበሰብሰውን ለብሰው ወደ ቅዲስትቱ ከተማ ወደ ሰማያዊትዋ እየሩሳሌም መግባት ቻሉ ከዛም በምድርም ለብዝዎች ተገልጠው መታየት ቻሉ። በራእይ ሂዱና አስተውሉ በፍልስጤም ምድር ያለችው ምድራዊትዋን እየሩሳሎም ምንም ቅዲስትቱ
ከተማ የሚያስብላት እንደሌለ ታያላችሁ ሰማያቱን እየሩሳሌምን ቅድስቲቱም ከተማ ብሎ ሲጠራት እናያለን “የዮሐንስ ራእይ 21፡2 ቅድስቲቱም ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም፥” እንደዚሁ በ(የዮሐንስ ራእይ 21፡10)
ጌታ የተሰቀለባት እና ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደሉት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቃን ደም ሁሉ ያለባትና የሚደርስባት ምድራዊትዋ እየሩሳሌም እንካንስ ቅድስቲቱም ከተማ ብሎ ሊጠራት ቀርቶ በታሪክ ገናና እንደ መሆንዋ መጠን ታላቂቱ ከማለት በቀር በስማ ብቻ እንኻ አይጠራትም “የዮሐንስ ራእይ 11፡8 በድናቸውም በታላቂቱ ከተማ አደባባይ ይተኛል እርስዋም በመንፈሳዊ ምሳሌ ሰዶምና ግብጽ የተባለች ደግሞ ጌታቸው የተሰቀለባት ናት።”
የሙሴና የኤልያስን ህያውነት እናስተውል የማቴዎስ ወንጌል 17፡1 ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። 2 በፊታቸውም
ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። 3 እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። 4 ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን። ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ አለ። 5 እርሱም ገና ሲናገር፥
እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።
“መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 2፡11 ሲሄዱም። እያዘገሙም ሲጫወቱ፥ እነሆ፥ የእሳት ሰረገላና የእሳት ፈረሶች በመካከላቸው ገብተው ከፈሉአቸው ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ወጣ።” እንግዲህ አፈርየሆነው ስጋቸው ወደ ነበረበት ምድር ሲመለስ፥ (spirit መንፈሳቸው) ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ተመልስዋልና በመንፈስ ህያዋን ናቸው በዚህም ለጌታ ሁሉ ለእርሱ
ሕያዋን ስለ ሆኑ፥ የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን እንዳይደለ እወቁያለውን እንገነዘባለን። ነገር ግን በ “19 በእርሱም ደግሞ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት(spirit መንፈሳቸው) ሰበከላቸው፤ 20 ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ በውኃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ፥
የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኅ ዘመን በቈየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም።” እነዚህ ለየት የሚያደርጋቸው ( spirit መንፈሳቸው) ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር እንደ መመለስ ፈንታ እ/ር አሰራቸው።
ጌታም ሄዶ በኖህ ዘመን የእግዚአብሔር ትዕግሥት 120 ያስጨረሱትን በኖኅ ዘመን አልታዘዙም ለሚላቸው ወንጌልን ሰበከላቸው። ለምን ወንጌሉን መስበክ አስፈለገው?
እዛው ወረድ ብሎ በ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4፡6 መልሱን ይነግረናል። በነገራችን ላይ መጽሐፍ ቅዱስ በብራና መልክ የተዘጋጀ ወጥ ፅሑፍ ነበረ። ለአንባቢያን እንዲመች በምእራፍና በቁጥር ተከፋፍሎ የተሰራው በ1560 ጄኔቫ መጽሃፍ ቅዱስ በመባል የሚታወቀው አንድ የሊቃውንት ቡድን በጄነቭ ሆነው ሰሩ። ሁለተኛው እትሙም በ1652 ታተመ። ይህ ነበር የመጀመርያው
የእንግሊዝኛ ትርጉም በምእራፍና በቁጥር ተከፋፍሎ የተሰራው ። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4፡6 ስናስብ የተያያዘ ጽሁፍ መሆኑን መዘንጋት የለብንም። ቃሉም “እንደ ሰዎች በሥጋ እንዲፈረድባቸው በመንፈስ ግን እንደ እግዚአብሔር እንዲኖሩ ስለዚህ ምክንያት ወንጌል ለሙታን ደግሞ ተሰብኮላቸው ነበርና።” “1Pet 4፡6 for this cause was the gospel preached also to them that are dead, that they might be judged according to men in the flesh, but live according to God in the spirit.”
የሃዋሪያው መልእክት ግልጽ ነው። ስጋቸው በተመለከተ ሙታን ናቸው። ህያዋን ሆነው ያሉት በመንፈስ እንደ ሆነና ታስረውም እንዳሉ ወንጌሉ ተሰበከላቸው። መገንዘብ ያለብን በሲኦል የዘላለም ስቃይ ይጠብቅሃል ተብለው አይደለም የተሰበከላቸው። ነገር ግን የመዳናቸው ወንጌል ነው። ወንጌል የምስራች መልካም ዜና የእ/ር ኁይል ለማዳን ነው የተሰበከላቸው።
በስጋቸው ሳሉ ሃጢያታቸው የከፋ ስለ ነበር እ/ር ጎርፍ ልኮ በውሃ በማስጠም በጎርፉ ጠራርጎ ወደ ሲኦል ወሰዳቸው በዚያም ለዘላለም ሳይሆን ያሰራቸው ለ 2350, (ሁለት ሺ ሶስት መቶ ሃምሳ) ዘመናት ታሰሩ። “እንደ ሰዎች በሥጋ እንዲፈረድባቸው የሚለን ያንን ነው ።
በመንፈስ ግን እንደ እግዚአብሔር እንዲኖሩ በሲኦልም ላይ ስልጣን ያለው ጌታ ሄዶ ወንጌልን ሊሰብክ ሄደ እንጂ ለቫኬሽን አልሄደም ወንጌሉም የእ/ር ታላቅ ስራ ፍርዱ የዘላለም ሳይሆ በዘመናት ወስጥ የተወሰነ እንደሆነ እናስተውላለን ። በዚህም በመንፈስ ግን እንደ እግዚአብሔር እንዲኖሩ ሆኑ። “አቤቱ ትፈራ ዘንድ ከአንተ ዘንድ ምህረት አለ” አሜን። ማንም ሲናገር እንደ እ/ር ቃል ይናገር። አሜን! ወንድም ቢኒ።