Discussion Quotes፡ Amanueal Zawdie ብራዘር ከላይ የጠቀስከው ማቲዮስ ወንጌል5፤18፤23 ቋንቋው symbolic ምሳሌያዊ ወይም ምልክታዊ ነው። የማቴዎስ ወንጌል 13፡34-35 ኢየሱስም ለሕዝቡ ይህን ሁሉ በምሳሌ ተናገረ፤ በነቢዩም፦ በምሳሌ አፌን እከፍታለሁ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውንም እናገራለሁ የተባለው ይፈጸም ዘንድ ያለ ምሳሌ አልተናገራቸውም። ይህንንም በነብዩ ዳዊት ላይ ሆኖ መንፈስ በመዝሙር 77/2 ላይ አስቀድሞ ተናግሮት ነበረ። እንደ ምናስተውለው ትንቢቱ ፍፃሜ ያገኘው ጌታ ያለ ምሳሌ ስላስተማረ ነው።በዚህም መሰረት ጌታ ከ 41 በላይ ምሳሌዎችን ተናግረዋል የዘልአለም ስቃይ ሰባኪዎች ግን ነጥለው እውነተኛ ታሪክ ነው የሚሉት የሃብታሙ ሰውና አልአዛር የበጎችና ፍየሎች ወዘተ…. ያስፈራራሉ የሚልዋቸውን ምሳሌዎችን ነው።
ጌታ ከተናገራቸው ምሳሌዎች ለማስታወስ ያህል። ከእንቅብ በታች ያለ መብራት፤ የሰናፍጭ ቅንጣት፤ ልባምና ሰነፍ አናፂዎች፤ በአረጀ ልብስ ላይ አዲስ እራፊ፤ በአረጀ አቅማዳ ላይ አዲስ ወይን፤ ዘሪና የመሬት አይነቶች፤ የተሸሸገ እርሾ ፤ በባህር ላይ የተጣለ መረብ፤ የጠፋ በግ፤ምህረት የማያደርግ ባርያ፤ አስሩ ቆነጃጅት፤ በጎችና ፍየሎች፤ ደጉ ሳምራዊ፤ የጠፋ ድሪም፤ ወዘተ…… ዶክትሪናቸውን ለማጽደቅ ሁሉም የዘልአለም ስቃይ ሰባኪዎች ነጥለው እውነተኛ ታሪክ ነው ብለው የሙጭኝ ይላሉ።
እውነታው ግን ጌታ ከ 41 በላይ ምሳሌዎችን ተናግረዋል አንዳቸውም በእውን የተፈፅሙ የተከሰቱ ታሪኮች አልነበሩም። ተምሳሌትን ምሳሌነቱን ትተን ወደ እውነተኛ ታሪክ ስንከረብተው ወይም ስንገለብጠው ተምሳሌነቱ ይጠፋል።
ሁላችንም እንደምናውቀው ምሳሌ ወይም ተምሳሌት የሚነገረው በጥሬው ካለው ትርጉሙ ውጪ ሌላ ነገርን የሚወክል ቃል ወይም ሃረግ ነው። ለምሳሌ አንበሳ የጀግና ምሳሌ ነው፤ በግ/እርግብ የየዋህነት የንጽህና ምሳሌ ነው።
በተፃራሪው ታሪክ ማለት ደግሞ ባለፉት ዘመናት እውን የነበሩ ክስተቶች ትውፊት፤ የሚዘገብ ክንዋኔ፤ ለምሳሌ ቀድሞ የነበረ ወግ፤ ጀብድ፤ ጀግንነት፤ የሃገር ኩራት፤ ወዘተ….ማንኛውም የሚያኮራ ይሁን አሳፋሪ ክስተት ሁሉ በዘመኑ ባለ ትውልድ እንደ “ነበረ” የሚታሰብና የሚነገር የሚዘገብ የአላፊ ጊዜ “ክስተት” ታሪክ ይባላል።
ጌታ እየሱስ በየትኛውም ቦታ ለፈሪሳውያን ይሁን ለህዝቡ ሲያስተምር ያለ ምሳሌ ሲያስተምር አታዩም። ምሳሌዎቹ ግን ብዙ ገፅታ ሊያሳዩ ይችላሉ። የአላፊ ግዜ ፤ የወቅቱ ሁኔታ ፤ ደግሞም የወደፊቱን የሚያመለክቱ ትንቢታዊ ሊሆኑ ይችላሉ። ወንድም ቢኒ።