Posted on March 07, 2012 Brother Binyam T. Alemayehu

diligent ትጋት 

መጽሐፈ ምሳሌ 13፡11 በችኰላ የምትከማች ሀብት ትጐድላለች ጥቂት በጥቂት የተከማቸች ግን ትበዛለች።

Prov 13፡11 Wealth gotten by vanity shall be diminished: but he that gathereth by labour shall increase.

የጻድቅ ሃብት የምትከማቸው ቀስ በቀስ ነው። ያልሰራህበት በችኰላ የምትከማች ሀብት ይሁን ምንም ነገር ግን በእጅህ ብዙ አይቆይም።

መጽሐፈ ምሳሌ 21፡5 የትጉህ አሳብ ወደ ጥጋብ ያደርሳል ችኵል ሰው ሁሉ ግን ለመጕደል ይቸኩላል።

Prov 21፡5 The thoughts of the diligent tend only to plenteousness; but of every one that is hasty only to want.

ከተግባር ሁሉ በፊት ሃሳብ ይቀድማል ትርፍ የምታመጣ ሃሳብ በአንተ ውስጥ አለች ወደ ተግባር ትለውጣት ዘንድም ትጠብቅሃለች። ስለዚህም የተግባር ሰው ሁን።

መጽሐፈ ምሳሌ 14፡23 በድካም ሁሉ ልምላሜ ይገኛል ብዙ ነገር በሚናገር ከንፈር ግን ድህነት ብቻ አለ።

Prov 14፡23 In all labour there is profit: but the talk of the lips tendeth only to penury.

በመመኘት ውጤት አታገኝም በመስራት ግን ውጤትን ታገኛለህ።

መጽሐፈ ምሳሌ 19፡15 ተግባር መፍታት እንቅልፍን ታመጣለች፥ የታካችም ነፍስ ትራባለች።

Prov 19፡15 Slothfulness casteth into a deep sleep; and an idle soul shall suffer hunger.

ያለስራ መኖር መጨናነቅ ነው።

መዝሙረ ዳዊት 1፡3 እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።

Ps 1፡3 And he shall be like a tree planted by the rivers of water, that bringeth forth his fruit in his season; his leaf also shall not wither; and whatsoever he doeth shall prosper.

ብልጽግና ከሰማይ አይወድቅም የሚሰሩ እጆችን ግን ይከተላል።

2ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 3;10 ደግሞ ከእናንተ ጋር ሳለን። ሊሠራ የማይወድ አይብላ ብለን አዘናችሁ ነበርና።

2Thess 3;10 For even when we were with you, this we commanded you, that if any would not work, neither should he eat.

ያልሰራህበት በአፍህ ውስጥ አይጣፍጥህም።

መጽሐፈ መክብብ 3፡13 ደግሞም ሰው ሁሉ ይበላና ይጠጣ ዘንድ በድካሙም ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው።

Eccl 3፡13 And also that every man should eat and drink, and enjoy the good of all his labour, it is the gift of God.

ሰው ከስራው ሁሉ ይበላና ይጠጣ ዘንድ በድካሙም ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ የእግዚአብሔር ስጦታ ነውና ስጦታውን አክብረው።

Posted on March 07, 2012  Brother Binyam T. Alemayehu