counsel ምክር
Posted on February 01, 2012 Brother Binyam T. Alemayehu
counsel ምክር
መጽሐፈ ኢዮብ 12
13 በእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ኃይል አለ ለእርሱ ምክርና ማስተዋል አለው።
KJV
Job 12
13 With him is wisdom and strength, he hath counsel and understanding.
መጽሐፈ ኢዮብ 21
16 እነሆ፥ ሀብታቸው በእጃቸው ውስጥ አይደለምን? የኃጥአን ምክር ከእኔ ዘንድ የራቀች ናት።
KJV
Job 21
16 Lo, their good is not in their hand: the counsel of the wicked is far from me.
| መዝሙረ ዳዊት | ||
| 1፥1 | ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ። | |
s 1
1 Blessed is the man that walketh not in the counsel of the ungodly, nor standeth in the way of sinners, nor sitteth in the seat of the scornful.
መዝሙረ ዳዊት 33
10 እግዚአብሔር የአሕዛብን ምክር ያጠፋል፥ የአሕዛብንም አሳብ ይመልሳል።
KJV
Ps 33
10 The Lord bringeth the counsel of the heathen to nought: he maketh the devices of the people of none effect.
መዝሙረ ዳዊት 33
11 የእግዚአብሔር ምክር ግን ለዘላለም ይኖራል። የልቡም አሳብ ለልጅ ልጅ ነው።
KJV
Ps 33
11 The counsel of the Lord standeth for ever, the thoughts of his heart to all generations.
መዝሙረ ዳዊት 66
5 ኑ የእግዚአብሔርንም ሥራ እዩ ከሰው ልጆች ይልቅ በምክር ግሩም ነው።
KJV
Ps 66
5 Come and see the works of God: he is terrible in his doing toward the children of me
መዝሙረ ዳዊት 73
24 በአንተ ምክር መራኸኝ ከክብር ጋር ተቀበልኸኝ።
KJV
Ps 73
24 Thou shalt guide me with thy counsel, and afterward receive me to glory.
መዝሙረ ዳዊት 89
7 በቅዱሳን ምክር እግዚአብሔር ክቡር ነው በዙሪያው ባሉት ሁሉ ላይ ታላቅና ግሩም ነው።
KJV
Ps 89
7 God is greatly to be feared in the assembly of the saints, and to be had in reverence of all them that are about him.
| መዝሙረ ዳዊት 107 | Ps 107 |
| 11 የእግዚአብሔርን ቃል ስለ ዐመፁ፥ የልዑልንም ምክር ስለ ናቁ፥ | 11 Because they rebelled against the words of God, and contemned the counsel of the most High: |
| 12 ልባቸው በድካም ተዋረደ ታመሙ የሚረዳቸውም አጡ። | 12 Therefore he brought down their heart with labour; they fell down, and there was none to help. |
| 13 በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፥ በመከራቸውም አዳናቸው። | 13 Then they cried unto the Lord in their trouble, and he saved them out of their distresses. |
| 14 ከጨለማና ከሞት ጥላ አወጣቸው፥ እስራታቸውንም ሰበረ። | 14 He brought them out of darkness and the shadow of death, and brake their bands in sunder. |
| 15 ለሰው ልጆች ስላደረገው ተኣምራት ስለ ምሕረቱም እግዚአብሔርን ያመስግኑ | 15 Oh that men would praise the Lord for his goodness, and for his wonderful works to the children of men! |
መጽሐፈ ምሳሌ 1
5 ጠቢብ እነዚህን ከመስማት ጥበብን ይጨምራል፥ አስተዋይም መልካም ምክርን ገንዘቡ ያደርጋል።
KJV
Prov 1
5 A wise man will hear, and will increase learning; and a man of understanding shall attain unto wise counsels:
መጽሐፈ ምሳሌ 1
8 ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ምክር ስማ፥ የእናንትህንም ሕግ አትተው
KJV
Prov 1
8 My son, hear the instruction of thy father, and forsake not the law of thy mother:
| መጽሐፈ ምሳሌ 1 | Prov 1 |
| 29 እውቀትን ጠልተዋልና፥ እግዚአብሔርንም መፍራት አልመረጡምና | 29 For that they hated knowledge, and did not choose the fear of the Lord: |
| 30 ምክሬን አልፈቀዱምና፥ ዘለፋዬንም ሁሉ ንቀዋልና | 30 They would none of my counsel: they despised all my reproof. |
| 31 ስለዚህ የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ፥ ከራሳቸው ምክር ይጠግባሉ። | 31 Therefore shall they eat of the fruit of their own way, and be filled with their own devices. |
| 32 አላዋቂዎችን ከጥበብ መራቅ ይገድላቸዋልና፥ ሰነፎችንም ቸልተኛ መሆን ያጠፋቸዋልና። | 32 For the turning away of the simple shall slay them, and the prosperity of fools shall destroy them. |
| 33 የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። | 33 But whoso hearkeneth unto me shall dwell safely, and shall be quiet from fear of evil. |
መጽሐፈ ምሳሌ 8
14 ምክርና መልካም ጥበብ የእኔ ነው ማስተዋል እኔ ነኝ፥ ብርታትም አለኝ።
KJV
Prov 8
14 Counsel is mine, and sound wisdom: I am understanding; I have strength.
መጽሐፈ ምሳሌ 11
14 መልካም ምክር ከሌለ ዘንድ ሕዝብ ይወድቃል በመካሮች ብዛት ግን ደኅንነት ይሆናል።
KJV
Prov 11
14 Where no counsel is, the people fall: but in the multitude of counsellors there is safety.
መጽሐፈ ምሳሌ 12
5 የጻድቃን አሳብ ቅን ነው የኃጥኣን ምክር ግን ተንኰል ነው።
KJV
Prov 12
5 The thoughts of the righteous are right: but the counsels of the wicked are deceit.
መጽሐፈ ምሳሌ 12
15 የሰነፍ መንገድ በዓይኑ የቀናች ናት ጠቢብ ግን ምክርን ይሰማል።
KJV
Prov 12
15 The way of a fool is right in his own eyes: but he that hearkeneth unto counsel is wise.
መጽሐፈ ምሳሌ 13
10 በትዕቢት ጠብ ብቻ ይሆናል ጥበብ ግን ምክርን በሚቀበሉ ዘንድ ናት።
KJV
Prov 13
10 Only by pride cometh contention: but with the well advised is wisdom.
መጽሐፈ ምሳሌ 15
22 ምክር ከሌለች ዘንድ የታሰበው ሳይሳካ ይቀራል መካሮች በበዙበት ዘንድ ግን ይጸናል።
KJV
Prov 15
22 Without counsel purposes are disappointed: but in the multitude of counsellors they are established.
መጽሐፈ ምሳሌ 19
20 ምክርን ስማ፥ ተግሣጽንም ተቀበል በፍጻሜህ ጠቢብ ትሆን ዘንድ።
KJV
Prov 19
20 Hear counsel, and receive instruction, that thou mayest be wise in thy latter end.
መጽሐፈ ምሳሌ 19
21 በሰው ልብ ብዙ አሳብ አለ የእግዚአብሔር ምክር ግን እርሱ ይጸናል።
KJV
Prov 19
21 There are many devices in a man’s heart; nevertheless the counsel of the Lord, that shall stand.
መጽሐፈ ምሳሌ 20
5 ምክር በሰው ልብ እንደ ጠሊቅ ውኃ ነው አእምሮ ያለው ሰው ግን ይቀዳዋል።
KJV
Prov 20
5 Counsel in the heart of man is like deep water; but a man of understanding will draw it out
መጽሐፈ ምሳሌ 20
18 አሳብ በምክር ትጸናለች፥ በመልካምም ምክር ሰልፍ አድርግ።
KJV
Prov 20
18 Every purpose is established by counsel: and with good advice make war.
መጽሐፈ ምሳሌ 21
30 ጥበብ ወይም ማስተዋል ወይም ምክር በእግዚአብሔር ላይ የለም።
KJV
Prov 21
30 There is no wisdom nor understanding nor counsel against the Lord.
መጽሐፈ ምሳሌ 22
20-21 የእውነትን ቃል እርግጥነት አስታውቅህ ዘንድ፥ ለሚጠይቅህም እውነትን ቃል መመለስ ይቻልህ ዘንድ፥ በምክርና በእውቀት የከበረን ነገር አልጻፍሁልህምን?
KJV
Prov 22
20 Have not I written to thee excellent things in counsels and knowledge,
21 That I might make thee know the certainty of the words of truth; that thou mightest answer the words of truth to them that send unto thee?
መጽሐፈ ምሳሌ 24
6 በመልካም ሥርዓት ሰልፍ ታደርጋለህ ድልም ብዙ ምክር ባለበት ዘንድ ነው።
KJV
Prov 24
6 For by wise counsel thou shalt make thy war: and in multitude of counsellors there is safety.
መጽሐፈ ምሳሌ 27
9 ሽቱና ዕጣን ልብን ደስ ያሰኛሉ እንዲሁ ነፍስ በወዳጁ ምክር ደስ ይላታል።
KJV
Prov 27
9 Ointment and perfume rejoice the heart: so doth the sweetness of a man’s friend by hearty counsel
ትንቢተ ኢሳይያስ 5
19 ሥራውንም ያፋጥን እናውቃትም ዘንድ የእስራኤል ቅዱስ ምክር ትቅረብ፥ ትምጣ ለሚሉ ወዮላቸው!
KJV
Isa 5
19 That say, Let him make speed, and hasten his work, that we may see it: and let the counsel of the Holy One of Israel draw nigh and come, that we may know it!
ትንቢተ ኢሳይያስ 11
2 የእግዚአብሔር መንፈስ፥ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፥ የምክርና የኃይል መንፈስ፥ የእውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።
KJV
Isa 11
2 And the spirit of the Lord shall rest upon him, the spirit of wisdom and understanding, the spirit of counsel and might, the spirit of knowledge and of the fear of the Lord;
ትንቢተ ኢሳይያስ 16
3 ምክርን ምከሪ፥ ፍርድን አድርጊ፥ በቀትር ጊዜ ጥላሽን እንደ ሌሊት አድርጊ የተሰደዱትን ሸሽጊ፥ የሸሹትን አትግለጪ።
KJV
Isa 16
3 Take counsel, execute judgment; make thy shadow as the night in the midst of the noonday; hide the outcasts; bewray not him that wandereth.
ትንቢተ ኢሳይያስ 28
29 ይህም ደግሞ ድንቅ ምክር ከሚመክር በግብሩም ማለፊያ ከሆነው ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ወጥቶአል።
KJV
Isa 28
29 This also cometh forth from the Lord of hosts, which is wonderful in counsel, and excellent in working.
ትንቢተ ኢሳይያስ 30
1 ለዓመፀኞች ልጆች ወዮላቸው! ይላል እግዚአብሔር ከእኔ ዘንድ ያልሆነን ምክር ይመክራሉ፥ ኃጢአትንም በኃጢአት ላይ ይጨምሩ ዘንድ ከመንፈሴ ዘንድ ያልሆነውን ቃል ኪዳን ያደርጋሉ።
KJV
Isa 30
1 Woe to the rebellious children, saith the Lord, that take counsel, but not of me; and that cover with a covering, but not of my spirit, that they may add sin to sin:
ትንቢተ ኢሳይያስ 25
1 አቤቱ፥ አንተ አምላኬ ነህ ድንቅን ነገር የዱሮ ምክርን በታማኝነትና በእውነት አድርገሃልና ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ ስምህንም አመሰግናለሁ።
KJV
Isa 25
1 O Lord, thou art my God; I will exalt thee, I will praise thy name; for thou hast done wonderful things; thy counsels of old are faithfulness and truth.
ትንቢተ ኢሳይያስ 36
5 እኔ። ለሰልፍ የሆነው ምክርህና ኃያልህ ከንቱ ነገር ነው አልሁ አሁንም በእኔ ላይ ያመፅኸው በማን ተማምነህ ነው?
KJV
Isa 36
5 I say, sayest thou, (but they are but vain words) I have counsel and strength for war: now on whom dost thou trust, that thou rebellest against me?
ትንቢተ ኢሳይያስ 47
13 በምክርሽ ብዛት ደክመሻል አሁንም የሰማይን ከዋክብት የሚቈጥሩ፥ ከዋክብትንም የሚመለከቱ፥ በየመባቻውም የሚመጣውን ነገር የሚናገሩ ተነሥተው ከሚመጣብሽ ነገር ያድኑሽ።
KJV
Isa 47
13 Thou art wearied in the multitude of thy counsels. Let now the astrologers, the stargazers, the monthly prognosticators, stand up, and save thee from these things that shall come upon thee.
ትንቢተ ኤርምያስ 18
18 እነርሱም፦ ሕግ ከካህን፥ ምክርም ከጠቢብ፥ ቃልም ከነቢይ አይጠፋምና ኑ፥ በኤርምያስ ላይ አሳብን እናስብ። ኑ፥ በምላስ እንምታው፥ ቃሉንም ሁሉ አናድምጥ አሉ።
KJV
Jer 18
18 Then said they, Come, and let us devise devices against Jeremiah; for the law shall not perish from the priest, nor counsel from the wise, nor the word from the prophet. Come, and let us smite him with the tongue, and let us not give heed to any of his words.
ትንቢተ ኤርምያስ 23
18 ቃሉን ያይና ይሰማ ዘንድ በእግዚአብሔር ምክር የቆመ ማን ነውና? ቃሉንስ ያደመጠ የሰማስ ማን ነው?
KJV
Jer 23
18 For who hath stood in the counsel of the Lord, and hath perceived and heard his word? who hath marked his word, and heard it?
ትንቢተ ኤርምያስ 32
19 በምክር ታላቅ በሥራም ብርቱ ነህ ለሁሉም እንደ መንገዱና እንደ ሥራው ፍሬ ትሰጥ ዘንድ ዓይኖችህ በአዳም ልጆች መንገድ ሁሉ ተገልጠዋል።
KJV
Jer 32
19 Great in counsel, and mighty in work: for thine eyes are open upon all the ways of the sons of men: to give every one according to his ways, and according to the fruit of his doings:
የሉቃስ ወንጌል 3
18 ስለዚህ ሕዝቡን በብዙ ሌላ ምክር እየመከራቸው ወንጌልን ይሰብክላቸው ነበር፤
KJV
Luke 3
18 And many other things in his exhortation preached he unto the people.
የሐዋርያት ሥራ 20
27 የእግዚአብሔርን ምክር ሁሉ ነግሬአችኋለሁና፥ ምንም አላስቀረሁባችሁም።
KJV
Acts 20
27 For I have not shunned to declare unto you all the counsel of God.
የሉቃስ ወንጌል 7
30 ፈሪሳውያንና ሕግ አዋቂዎች ግን በእርሱ ስለ አልተጠመቁ የእግዚአብሔርን ምክር ከራሳቸው ጣሉ።
KJV
Luke 7
30 But the Pharisees and lawyers rejected the counsel of God against themselves, being not baptized of him.
የሐዋርያት ሥራ 21
14 ምክርንም ሊቀበል እምቢ ባለ ጊዜ። የጌታ ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም አልን።
KJV
Acts 21
14 And when he would not be persuaded, we ceased, saying, The will of the Lord be done.
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4
5 ስለዚህም በጨለማ የተሰወረውን ደግሞ ወደ ብርሃን የሚያወጣ የልብንም ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ፤ በዚያን ጊዜም ለእያንዳንዱ ምስጋናው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሆናል።
KJV
1Cor 4
5 Therefore judge nothing before the time, until the Lord come, who both will bring to light the hidden things of darkness, and will make manifest the counsels of the hearts: and then shall every man have praise of God.
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1
11 እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንደ እርሱ አሳብ፥ አስቀድመን የተወሰንን በክርስቶስ ደግሞ ርስትን ተቀበልን።
KJV
Eph 1
11 In whom also we have obtained an inheritance, being predestinated according to the purpose of him who worketh all things after the counsel of his own will:
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6
4 እናንተም አባቶች ሆይ፥ ልጆቻችሁን በጌታ ምክርና በተግሣጽ አሳድጉአቸው እንጂ አታስቆጡአቸው።
KJV
Eph 6
4 And, ye fathers, provoke not your children to wrath: but bring them up in the nurture and admonition of the Lord.
| ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች | ||
| 2፥1 | በክርስቶስም አንዳች ምክር ቢሆን፥ የፍቅር መጽናናት ቢሆን፥ የመንፈስ ኅብረት ቢሆን፥ ምሕረትና ርኅራኄ ቢሆኑ፥ ደስታዬን ፈጽሙልኝ፤ | |
| 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ | ||
| 3፥16-17 | የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል። | |
| ወደ ዕብራውያን | ||
| 12፥5-6 | እንደ ልጆችም ከእናንተ ጋር። ልጄ ሆይ፥ የጌታን ቅጣት አታቅልል፥ በሚገሥጽህም ጊዜ አትድከም፤ ጌታ የሚወደውን ይቀጣዋልና፥ የሚቀበለውንም ልጅ ሁሉ ይገርፈዋል ብሎ የሚነጋገረውን ምክር ረስታችኋል። | |
| 13፥22 | ወንድሞች ሆይ፥ የምክርን ቃል እንድትታገሡ እመክራችኋለሁ፥ በጥቂት ቃል ጽፌላችኋለሁና። | |
የሐዋርያት ሥራ 20
27 የእግዚአብሔርን ምክር ሁሉ ነግሬአችኋለሁና፥ ምንም አላስቀረሁባችሁም።
KJV
Acts 20
27 For I have not shunned to declare unto you all the counsel of God.
አሜን!
Posted on February 01, 2012 Brother Binyam T. Alemayehu