
ድነት ወይም ደህንነት (Salvation) እርቅ Reconciliation እስከ ምን ድረስ ርቆ ይሄዳል?
BROTHER BINYAM T. ALEMAYEHU
ከብዙ ወገኖች ከኛ በፊት ከነበሩትም ሆነ በፊታችን ካሳለፋቸው ሃያላን እንዲሁም መንፈሳዊ የዱላ ቅብብሉን ከተቀበለው ከዚህ ትውልድ ጭምር የበዛ የህይወት ውሃ ወንዞች እንደ ሃያል ጅረት ሲወርዱ በማየቴ ሃሴት አደርጋለሁ። ወንዞቹም በደረሱበት ሁሉ ስለ ሚፈውሱ እና የአመፅ ፈሳሾችን ደፍቀው በመጠራረግ በማጽዳት ላይ ስለሆኑ በክብሩ ባለጠጋ ለሆነው መንፈሳዊ አባታችን እ/ር ምስጋና ይሁን። አሜን ፈቃድህ ይሁንብን! እግዚያብሄር ሆይ ብዛልን!
ስለ ሰማነው የመዳናችን ወንጌል፥ ጥቂት መጣጥፍ ልጣፍ። ወንጌል ከመሰረቱ መልካም ዜና ነው። ምንም ኩፉ ዜና የለበትም!ወንጌል ‘gospel’ የሚለው ቃል ኢቫንጀል ከግሪክ (‘evangel’ from the Greek) ቃል የተተሮገመ ሲሆን፡ ይህም ከሁለት የቃላት ውህድ የተገኘ ነው። መልካም እና መልእክት(‘eu’ – good, and ‘angelion’ – message). ስለዚህ ወንጌሉ በቀላል ቋንቋ መልካም መልእክት ማለት ነው። ወንጌል መልካም መልክት ሆኖ ሳለ ክፉውን መልእክት የዘልአለም ስቃይን ከየት አምጥተው እንደበረዙት ይገርማል።
ለመሆኑ የምስራቹ ምንድ ነው? ወንጌሉስ ምንድ ነው? በኤፌሶን ላሉት ቅዱሳን የምስራቹን ከሰሙ ቡሃላ ሳይሆን በክርስቶስ ኢየሱስም ቁዱሳን ሳይባሉ ገና ሃጥአን፡ ሳሉ የተነገራቸው የሰሙት የምስራቹ ወንጌል ወይም መልካም ዜናው የተባለው ይሄ ነው “የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የ-መ-ዳ-ና-ች-ሁ-ን ወ-ን-ጌ-ል” ነው። አስተውሉ በአላፊ ጊዜ (past tense) የተቀመጠ ነው። ገና ትድናላችሁ እያላቸው ሳይሆን የተፈፀመውን መዳናቸውን ነው የነገራቸው።
የተነገረው በአይሁዳዊ ሆነ እንጂ ይህ የምስራች የተነገረው በኛ አገር እናቶች ቢሆን ኖሮ ይህንን የምስራች የሚነግሩት በዚህ መልኩ ነበር ብየ አስባለሁ። የባህል ልብሳቸውን እንደለበሱ ሁለት እጆቻቸውን ወደ ሰማይ ዘርግተው ወደ ሃጥአኑ እየሮጡ እልልልልልልልል…. እ/ር በክርስቶስ አዳናቹሁ እኮ! እሰይ! እሰይ! እሰይ! እያሉ በደስታ ተቃቅፈፍ ይሳሳሙ ነበር ። “ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1-13 እናንተም ደግሞ “የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፤” “(Eph 1:13 [KJV]) In whom ye also trusted, after that ye heard the word of truth, the gospel of your salvation: in whom also after that ye believed, ye were sealed with that holy Spirit of promise,”
መዳን በእምነት ነው በእርግጥም እውነት ነው! ጥያቄው የሚዳንበት፡ እምነት መንፈሳዊ ንጥረ ነገሩ ምንጩ ማነው? ነው ጥያቄው። ሰው ሁሉ በአዳም ወገብ ውስጥ ሳለ ከአዳም ጋር ተባብረህ ሃጥያት ሰርተሃል የእ/ር ክብርም ጎድሎሃል።
ደግሞም በሃጥያታችሁና በበደላችሁ ሙታን ናችሁ ከተባለ ዘንዳ። ሙታን ፈቃድ አላቸውን? በእነሱ ዘንድ ዕውቀት አለን? “መጽሐፈ መክብብ 9/5 …ሙታን ግን አንዳች አያውቁም!” ወይስ የእምነት ፋብሪካው ሰው ነውን? ከየትስ መጣ ከሰው ውስጥ እንደ ድማሚት የፈነዳ ከእ/ር ያልሆነ በሰው ውስጥ ያለ ከሰው የተዘጋጀ ነውን? ወይስ ምንጩ ከእ/ር ነው? እንደ ሚጥሚጣ የሚያቃጥለው ጥያቄው ያነው።
በቅድሚያ መንፈሳዊ ሙታን እንካንስ እምነት ሊኖራቸው በቅድሚያ ከሙታን በትንሳኤው ሃይል መነሳት አለባቸው። ከሙታን የሚነሱት በእ/ር ሃይል ብቻ ነው! ከዛም ቅደም ተከተሉ ይቀጥላል። እሱ ብቻውን …ለሙታን ሕይወት በሚሰጥ ነውና። “ወደ ሮሜ ሰዎች 4/16 …ለሙታን ሕይወት በሚሰጥ የሌለውንም እንዳለ አድርጎ የሚጠራ ።”
ታዲያ በኤፌሶን ያላሉት የምስራቹን ከሰሙ ቡሃላ አምነዋል አሁን በክርስቶስ ኢየሱስም ቁዱሳን ሳይባሉ ገና ሃጥአን ሳሉ መንፈሳዊ ሙታን፡ ሳሉ እምነቱን ኬት አመጡትና አመኑ? በቅድምያ ከክርስቶስ ጋር ህይወትን ሰጥቶ ከሙታን አስነሳቸው። “ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2-5 ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥ ”
“ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3/1 … ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ ” “ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2-12 … ከእርሱ ጋር ተነሣችሁ” እምነት በተፈጥሮው መንፈሳዊ ነው መንፈስም ነው። “2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4/13 ነገር ግን፦ አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ ተብሎ እንደ ተጻፈ ያው አንዱ የእምነት መንፈስ ስላለን፥ እኛ ደግሞ እናምናለን ስለዚህም እንናገራለን፤” የእምነት መንፈስ የሚሰጥ ማነው?በእርግጥም እ/ር ነው።
“ወደ ገላትያ ሰዎች 3/2 ይህን ብቻ ከእናንተ እንድማር እወዳለሁ፤ በሕግ ሥራ ወይም ከእምነት ጋር በሆነ መስማት መንፈስን ተቀበላችሁን? 3 እንዲህን የማታስተውሉ ናችሁ? በመንፈስ ጀምራችሁ አሁን በሥጋ ትፈጽማላችሁን?
5 እንግዲህ መንፈስን የሚሰጣችሁ ….
ለኤፌሶን ሰዎች ሲናገር “ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥” እምነት ከእ/ር ዘንድ የተሰጠ ወይም የታደለ ነው። እምነት አንዴ የሰጠው ወይም እንደ ከረሜላ ያደለው አሁንም እራሱ እግዚአብሔር። ነው።
1ኛ “….ለቅዱሳን አንዴና ለመጨረሻ ስ-ለ ተ-ሰ-ጠ-ው እ-ም-ነ-ት እንድትጋደሉ ለመምከር እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።”ይሁዳ 1:3 አዲሱ መደበኛ ትርጒም እምነት ከራሱ ከእ/ር የተሰጠ ነው!
(KJV)Jude 1:3 for the faith which was once delivered (የታደለ፣ ) unto the saints.
(Jude 1:3 [Weymouth])Dear friends, since I am eager to begin a letter to you on the subject of our common salvation, I find myself constrained to write and cheer you on to the vigorous defense of the faith delivered once for all to God’s people.
(Jude 1:3 [YLT]) Beloved, all diligence using to write to you concerning the common salvation, I had necessity to write to you, exhorting to agonize for the faith once delivered to the saints,
(Jude 1:3 [Webster]) Beloved, when I gave all diligence to write to you concerning the common salvation, it was needful for me to write to you, and exhort you that ye should earnestly contend for the faith, which was once delivered to the saints.
2ኛ በሌላ ቃል ደግሞ እንየው ብዙም ማብራራት ቃሉ አያስፈልገውው የቃሉ ስልጣን በራሱ ይናገራልና። “ወደ ሮሜ ሰዎች 12:3 እግዚአብሔር ለ-እ-ያ-ን-ዳ-ን-ዱ የ-እ-ም-ነ-ት-ን መ-ጠ-ን እ-ን-ዳ-ካ-ፈ-ለ-ው፥ እንደ ባለ አእምሮ እንዲያስብ እንጂ ማሰብ ከሚገባው አልፎ በትዕቢት እንዳያስብ በመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ በተሰጠኝ ጸጋ እናገራለሁ።” እምነት ከእ/ር የተካፈልነው ነው!
(Rom 12:3 [YLT])For I say, through the grace that was given to me, to every one who is among you, not to think above what it behoveth to think; but to think so as to think wisely, as to each God did deal a measure of faith,
(Rom 12:3 [Weymouth])For through the authority graciously given to me I warn every individual among you not to value himself unduly, but to cultivate sobriety of judgement in accordance with the amount of faith which God has allotted to each one.
(Rom 12:3 [KJV])For I say, through the grace given unto me, to every man that is among you, not to think of himself more highly than he ought to think; but to think soberly, according as God hath dealt to every man the measure of faith.
3ኛ ጸጋውም እምነቱም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:9 ለአንዱም በዚያው መንፈስ እምነት፥ …ያካፍለዋል።
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:8 ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።”
(JMNT) Eph 2: 8. For by (to; in) the Grace you are (you continuously exist being) ones having been delivered (saved; made whole) through [some MSS +: the] Faith, and this not forth from out of you folks, [it is] God’s gift (present associated with sacrifice or offering),9. not out of works (deeds done), to the end that no one may boast
(Eph 2:8 [YLT])for by grace ye are having been saved, through faith, and this not of you–of God the gift, not of works, that no one may boast;
(Eph 2:8 [Weymouth])For it is by grace that you have been saved through faith; and that not of yourselves. It is God’s gift, and is not on the ground of merit—
በዚህ ወንጌል ማስተዋል ካለብን አንዱ የእ/ር ቃል እርቅ Reconciliation፦ የሚለው ፅንሰ ሃሳብ ነው። እ/ር ለአማኞች የሰጠው “ቃል የእርቅን አገልግሎት ነው” 2ኛቆሮ5-13-21
እ/ር ወደ አለም እንድንነግራቸው የላከን “የምስራቹን ነው” ያም በክርስቶስ እ/ር አለሙን ወደ ራሱ ሲያስታርቅ የሰዎችን በደል አይቆጥርባቸውም ነበር። በእርሱ ዘንድ እርቅ ወርደዋልና ደስ ይበላችሁ እልላለን። እኛስ በደልን ልንቆጥር የጠራን ነን? ከፍ ወደ አለው የእ/ር የልጅነት ብስለት ልንመጣ የግድ ነው። ሁሉ በድንጋይ ትወገር ቢልም ልጅነት ግን የምህረትን ቀመር ይቀምር ነበር።
አይናችን በሚያየው ከፈረደ ጆራችንም በሚሰማው ብቻ የምንበይን ከሆነ ሰው ብቻ መሆናችን አይደለምን? ምኑን ልጁን መሰልነው? ቅንድ ፍርድ እንጂ በመልክ ወይም በሚታየው መፍረድ ቅዱሱን አያስደስተውምና ። “ምህረትን እወዳለሁ ያለውን ሂዱና ተማሩ” “የማቴዎስ ወንጌል 9-13 ነገር ግን ሄዳችሁ፦ ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም ያለው ምን እንደ ሆነ ተማሩ፤ ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና አላቸው።”
ገና የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን የልጅነት ክብራችን በሙልአት በለበስን ግዜ ፍጥረትን ሁሉ ደግሞ ከጥፋት ባርነት ወደ በእ/ር ልጅነት ወዳለ ነፃነት አውጥተን ለእግዚአብሔር ልጆች ወደ ሚሆን ክብርና ነፃነት በእ/ር ኋይል እንቀላቅላቸዋለን። ሃሌሉያ!
ገና ቅዱሳን በዓለም ላይ እንደ አባታቸው በምህረትን እንዲፈርዱ አታውቁምን? “1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6-2 ቅዱሳን በዓለም ላይ እንዲፈርዱ አታውቁምን? በዓለምስ ላይ ብትፈርዱ ከሁሉ ይልቅ ትንሽ ስለሚሆን ነገር ልትፈርዱ አትበቁምን?” አሊያ እንደዛ ኩፉ ሰራተኛ መሆን ነው ንጉሱ ብዙ እዳ ያለበትን ሰው ምህረትን አደረገለት ከእዳው ትልቅነም የተነሳ እሱንም፡ቤተሰቡንም ወደ ባርነት ግዞት የሚያስልክ እዳ ነበረበት። ጌታው ምሮት ካበቃ ቡሃላ ግን እዳ ያለበትን ሌላ ሰው አገኘ። “በተማራችሁበት ምሕረት ማሩ” የሚለው ጥበብ እሱ ዘንድ አትታወቅም። ያለብህ እዳ ክፈል ብሎ ያን ሰው አንቆ ወደ ግዞት ጣለው።
ንጉሱም ነገሩን ሰማ አዘነም ምህረትን ይማርም ዘንድ ብርቱ ክንድ ወደ ሂወቱ ላከበት። በተማሩበት ምሕረት የማይንቀሳቀሱ ዛሬም የኑጉሱን መንፈስ የሚያሳዝኑ ብዙዎች አሉ። ለብርቱ ክንዱም የተጠበቁናቸው። “ወደ ሮሜ ሰዎች 11:31 እንዲሁ በተማራችሁበት ምሕረት እነርሱ ደግሞ ምሕረትን ያገኙ ዘንድ እነዚህ ደግሞ አሁን አልታዘዙም።” ወደ ሮሜ ሰዎች 11/32 እግዚአብሔር ሁሉን ይምር ዘንድ ሁሉን በአለመታዘዝ ዘግቶታልና።
ያነበብነውን አስተዋልነውን?
አሁን ስለ ፍጡራኑ ስናስብ እ/ር ህጉን በመፃረር የሚፈጽሙትን ሃይለኝነትና አመጽ አልቆጠረባቸውም። ከባዱ የፍርድ እጁም እነሱን በመቃወም፡ አልተዘረጋችም። በዚህም ሰዎች ሁሉ ከእርሱ ጋር እንዳ ይስማሙና ህብረትም እንዳይኖራቸው ደግሞም ከጽድቅ መንገድ እራሳቸውን ከሚያሸሹበት ምክንያቶቻቸው እንዲያልቅ አደረገ። ስለዚህ ምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ይሁኑ በሰውና በእ/ር መካከል የተደረገው እርቅ ተመልሶ በሰው ድካም የማይሰበር አድርጎ በፊቱ አፀናው አተመው።
ይህ የእርቅ ስራ የተሰራው ለቤተ ክርስቲያን ሰዎች ብቻ አይደለም። ጌታ የፈፀመው ለመላው የሰው ዘር ሁሉ ነው። በሌላ ቋንቋ የእ/ር ፍቅር የተገለጠው ለመላው የሰው ልጆች ነው። የከፋ ሃጢያተኛ በአለም ያለ ቢሆንም እንደ አማኙ ወደ እ/ር የታረቀ ነው።
“ሮሜ 5:6 ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለ ኃጢአተኞች ሞቶአልና።….8 ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።” አስተውሉ “ወደ ሮሜ ሰዎች 5-10 ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ …” ታረቅን የሚለው ቃል የተቀመጠው በአላፊ ጊዜ Past tense አመልካቹነቱ ነው። ያም የሚያመለክተው እ/ር አባትና አምላካችን በሱና በመላው አለም ዘንድ ያለውን መንፈሳዊ ህብረት ማደሱን ነው።
“1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1-9 ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው።” ይህን ያደረገው መላው አለም “በመተላለፋቸውና በበደላቸው ሙታን ሳሉ ነው።” እራሳቸውንም መርዳት በማይችሉበት ደካሞች ሳሉ በሞትም ሃይል ተይዘው ሳሉ ነው። ሮሜ3/23፣11/32፡ ገላ 3/22 ኤፌ1/1-2 በጌታ እየሱስ በሞቱ በመቀበሩ በመነሳቱ እ/ር ሁሉን የምድረ ገጽ ፍጥረት ከዛም በላይ በሰማይ በምድር ያሉቱን ሁሉ ወደ ራሱ አንጽቶ በክርስቶስ እስኪ ጠቀልል ድረስ ያም ማለት ሚስጢሩን እደነገረን ሚስጥሩ በዘመን መጨረሻ ሊደረግ ያለው በሰማይ በምድር ያሉትን ሁሉ የእግሩ መረገጫ እስኪ ያደርግ ድረስ ወይም ከስለጣኑ ስር እስኪ ጠቀልል ድረስ ፍጥረትን ይቅር ብሎ ህብረቱን አድሶታል።
ዕብ9/23-28, 10/71-4
“ዕብ 10/10 በዚህም ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ አንድ ጊዜ ፈጽሞ በማቅረብ ተቀድሰናል።11 ሊቀ ካህናትም ሁሉ ዕለት ዕለት እያገለገለ ኃጢአትን ሊያስወግዱ ከቶ የማይችሉትን እነዚያን መሥዋዕቶች ብዙ ጊዜ እያቀረበ ቆሞአል፤12 እርሱ ግን ስለ ኃጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፥13 ጠላቶቹም የእግሩ መረገጫ እስኪደረጉ ድረስ ወደ ፊት ይጠብቃል። 14 አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋልና።15-16 መንፈስ ቅዱስም ደግሞ ስለዚህ ይመሰክርልናል፤……”
“1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4/9 ይህ ቃል የታመነ ሁሉም እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤10 ይህን ለማግኘት እንደክማለንና፥ ስለዚህም እንሰደባለን፤ ይህም ሰውን ሁሉ ይልቁንም የሚያምኑትን በሚያድን በሕያው አምላክ ተስፋ ስለምናደርግ ነው።” እ/ር ሰውን ሁሉ የሚያድን ነው ለሚያምኑት ግን የተለየ ጥቅም አለው።
“JMT:1st TIMOTHY1/9. The Word [is] full of faith (or: Faithful {Trustworthy} [is] the word) and worthy of all welcomed reception,10. for into this [end] are we constantly working hard unto weariness, and are continuously struggling in the contest (contending for the prize; other MSS: being reproached), because we have placed our expectation (hope) and thus rely upon a living God (or: upon [the] living God), Who is (exists being) [the] Savior (Deliverer; Rescuer; Restorer to health and wholeness) of all mankind especially of believers (of ones full of faith and trust; of faithful ones)!”
ለመሆኑ የሁሉ ነገር መታረቅ እስከ ምን ድረስ ርቆ ይሄዳል ለሰው ልጆች ብቻ ነው ወይስ ለፍጥረት ሁሉ? “እውነት የሆነውን አስቡ” ቦሎናል ደግሞም “ቃልህ እውነት ነው” ይላልና እውነቱን በቃሉ እንድናይ እ/ር ይርዳን። “ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1/19-20 እግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ በእርሱ እንዲኖር፥ በእርሱም በኩል በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና።
Col 1/19 For it pleased the Father that in him should all fulness dwell;20 And, having made peace through the blood of his cross, by him to reconcile all things unto himself; by him, I say, whether they be things in earth, or things in heaven.”
መቸም እንደ ነዚህ ያሉ እውነቶች መንፈስ ከቃሉ ሲገልጥ የሚሆነው የታወቀ ነው። ጌታ አገልግሎቱን በጀመረበት ቀን የሆነው ቢደገም አይገርመኝም። የነብዮን ኢሳያስ መጽሐፍ በሰጡት ጊዜና መጽሐፍን በተረተረ ጊዜ ሲኦል ሁሉ ቡሃላ መዝጋትዋ ላይቀር አፍዋን እንደ ከፈተችበት ሁሉ ያ የሃይማኖት መንፈስ አሁንም እንደ ሚንጫጫ ይጠበቃል።
ለመሆኑ ቆላስይስ ምዕራፍ አንድ በሰማይና በምድር ያሉት ወደ ራሱ ያስታረቃቸው እነማን ናቸው? መቸም በምድር ያሉት ሲል በአብዛኛው ከሰው ጋር የተያያዘ እንደሆነ እናውቃለን በሰማይ የሚታረቁት እነማን ናቸው? “ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1/15-16 እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው፤ የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድርያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፤
Col 1/15 Who is the image of the invisible God, the firstborn of every creature:16 For by him were all things created, that are in heaven, and that are in earth, visible and invisible, whether they be thrones, or dominions, or principalities, or powers: all things were created by him, and for him:”
ከቃሉ እንደ ምናስተውለው እርቁ ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን ከዛም በላይ መሆኑን በቃሉ ከማስተዋላችን በፊት ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፤የሚላቸውን ከቃሉ ውስጥ ሁሉ የሚላቸውን በዝርዝር እንየው።
በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል። ካለን ቡሃላ በሰማይ ከመንፈሳዊው አለም ይጀምርና የማይታዩትን ካሳየን ቡሃላ በሚጨበጠው አካላዊ አለም በምድር ያሉትን የሚታዩትን እንዲሁ ያሳየናል። ከዛም ይቀጥልና ሲዘረዝራቸው ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ብሎ አለቅነት ደግሞም ሥልጣናት፥ ጠቅሎ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ደግሞም ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፤ ይለናል።
በዚህ ቃል ውስጥ የሚገርመው በሰማይ ከጠቀሳቸው ውስጥ አለቅነትና ሥልጣናትን፥ ወዘተ… መቸም የእ/ርን ቃል የሚፈታው የእ/ርን ቃል በማመሳከር ነውና በኤፌሶን 6 መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ነው ብሎ በዝርዝር ይገባበታል። “ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6/12 መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።”
በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና። ጥያቄው በምድር የሚታረቁትን እናውቃለን በሰማይ የሚታረቁት እነማን ናቸው እንደ ሰው አልጠፉምና ይድናሉ አይልም ታርቀዋል ግን ይላል። በሰማይ ያሉት አለቆችና ከሥልጣናት የዚህም የጨለማ ዓለም ገዦች ፡ በሰማያዊም ስፍራ ያሉ የክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ሳይቀር እርቁ አጀንዳ ውስጥ አስገብታቸዋል። እንዴት? “ሚስጥሩ ለእ/ር ነው የተገለጠው ለእኛ ነው” የዘመን ፍፃሜ የአጀንዳው ጠቅላላ ምክሩ ይህን ይመስላል።
የእውነት መንፈስ ወደ እውነት ሁሉ እንደመራን መጠን በጉ ወደ ሄደበት እንከተለዋለን እንማራለን። “እቋሪ ዉሃ አይፈወስም” “ወራጅ ውሃ ግን ይፈወሳል” ስለ ሚንቀሳቀስ ማለት ነው። “ልጆችሽ ከእ/ር የተማሩ ይሆናሉ ሰላማቸው የበዛ ይሆናል” እንግዲህ ቃሉ ነው የሚለው እ/ርን እዩ “ሰውን የሚያይ ይሰበራል እ/ርን የሚያይ ግን ይጠገናልና።”
“ወደ ሮሜ ሰዎች 5/8 ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።”
“JMT: Rom5/8. Yet God constantly stands with His own Love into us [or: But God continuously places (sets; puts) together the Love from Himself into us], because our still continuing to exist being failures (ones missing the target; sinners), Christ dies over us (on our behalf; for our sake).” (this is my favorite Bible translation (jmt)
ለሃጥያተኞች ከሞተ እንደ ቃሉ ለሁሉም ሃጥያተኞች ሞተዋል ። ምክንያቱም “ሁሉ ሃጥያትን ሰርተዋል የእ/ር ክብርም ጎድላቸዋል። ሮሜ 3/23” እንደ ገናም “ሃጢያቶችን ወደ ንስሃ እንጂ ፃድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና። ማቴ 9/13” ሁላችንም በሃጥያት የመርገም ሸለቆ እንደ ተዘፈቅን ያውቃልና። ግን በመስቀሉ ደም ሰላም አደረገ። ስለ ዚህም ለኛ ያለው ሃሳብ የሰላም ነው እንጂ ለከፋ ፍፃሜ የሚዳርግ ሃሳብም አይደለም።
ድነት ወይም ደህንነት (Salvation)
“1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4/9 ይህ ቃል የታመነ ሁሉም እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤10 ይህን ለማግኘት እንደክማለንና፥ ስለዚህም እንሰደባለን፤ ይህም ሰውን ሁሉ ይልቁንም የሚያምኑትን በሚያድን በሕያው አምላክ ተስፋ ስለምናደርግ ነው።”
“JMT:1st TIMOTHY1/9. The Word [is] full of faith (or: Faithful {Trustworthy} [is] the word) and worthy of all welcomed reception,10. for into this [end] are we constantly working hard unto weariness, and are continuously struggling in the contest (contending for the prize; other MSS: being reproached), because we have placed our expectation (hope) and thus rely upon a living God (or: upon [the] living God), Who is (exists being) [the] Savior (Deliverer; Rescuer; Restorer to health and wholeness) of all mankind especially of believers (of ones full of faith and trust; of faithful ones)!”
ጳውሎስ በግልጽ እ/ር “የሰዎች ሁሉ” አዳኝ እንደሆነ በግልጽ አስቀምጦታል። አንድ የምንረዳው ነገር አለ ደህንነት ለሚያምኑቱ የተለየ ነው። የተለየ የሚያደርገውም ለሚያምኑት የደህንነት ጥቅሙን በዚህ ህይወት ይለማመዱታልና። ድነት ወይም ደህንነት ምንድ ነው? ድነት የሚዛመደው ከሃጥያተኛው ጋር ነው።
ድነት ወይም ደህንነት ማለት ከሃጥያትና ከሞት ሃይል ነፃ መውጣት ማለት ነው። ይህም ማለት ለሚያምንቱ የሆነ የእ/ር የነፃ ስጦታ ነው። “የማቴዎስ ወንጌል 1-21 ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።” ሕዝቡ መዳን ያስፈለጋቸው ከኃጢአታቸው ነው።
“ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2/8 ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤9 ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።” ይሄ ደህንነት ቀድሞ ጊዜ ወደ ሰው ዘሮች ሁሉ የተላለፈው በአዳም ላይ የተነገረው የመርገም ቃልን በእዮሱስ የመስቀሉ ስራ ወደ በረከት ገልብጦታል። ሁሉ ማንፈሳዊ፤ ሃሳባዊ፤ አካላዊ፤ ለሰው ዘሮች ሁሉ ተቃዋሚ ኅይላት የሆኑት ኅይል ኧልባ ተደርገዋል።
ይህም ለሃጥያት ተገዥነትን አላቀዋል። ሮሜ 6/6,14 ከዲያብሎስ ስራ ነፃነትን 1ኛ ዮሃ3/5-11 ከሞት ፍርሃትና ባርነት ነፃነትን። ዕብ 2/14-15 አውጥቶ በምትካቸው ፅድቅን፤ ሰላም፤ደስታ የሂወታቸው መሃከለኛ ሆኖ እንዲ ለማመዱት የሚያደርግ ሆነዋል። አሜን!
መደምደሚያ
“አዲሱመደበኛ ትርጉም: 2 ቆሮንቶስ 5/19እግዚአብሔር በክርስቶስ ዓለምን ከራሱ ጋር ሲያስታርቅ የሰዎችን በደል አይቈጥርባቸውም ነበር፤ ለእኛም ደግሞ የማስታረቅ ቃል ሰጠን። 20ስለዚህ እኛ የክርስቶስ እንደራሴዎች ነን፤ እግዚአብሔርም በእኛ አማካይነት ጥሪውን ያቀርባል፤ እኛም ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን በክርስቶስ እንለምናችኋለን።”
“2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5/19 እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ”
“JMT: 2nd Corinthians 19. as that God was existing within Christ (God was and continued being within [the] Anointed One) continuously transforming [the] world ([the] system of culture, religion and government) down to be other [than it is] (progressively bring [the] ordered system down into another [position]; repeatedly changing [the] universe to correspond with other [conditions; perceptions]; progressively altering [the] ordered arrangement down to be another one; habitually and progressively changing [the] world from enmity to friendship; reconciling [the] world [of mankind]) in Himself (to Himself; for Himself; by Himself), not accounting to them (not putting to their account; not logically considering for them; not reasoning in them) their falls to the side (their trespasses; their offences), even placing within us the Word (the Idea; the Reason; the message) of the corresponding transformation (the full alteration; the change from enmity to friendship; the conciliation).