The fruit of the Spirit የመንፈስ ፍሬ
Posted on March 20, 2012
Brother Binyam T. Alemayehu
the fruit of the Spirit የመንፈስ ፍሬ
የመንፈስ ፍሬ ዘጠኝ ናቸው። በገላቲያ እንደ ተዘረዘሩት ”ወደ ገላትያ ሰዎች 5፡22 የመንፈስ ፍሬ ግን 1ፍቅር፥ 2ደስታ፥ 3ሰላም፥ 4ትዕግሥት፥ 5ቸርነት፥ 6በጎነት፥ 7እምነት፥ 8የውሃት፥ 9ራስን መግዛት ነው። Gal 5፡22 But the fruit of the Spirit is love, joy, peace, longsuffering, gentleness, goodness, faith,” ናቸው፡፡ የመንፈስ ፍሬ የሚያሳዩን መረጃነታቸው በመንንፈሳዊ እድገታቸው ህያዋን ለሆኑት የባህሪያቸው ለውጥ እውን ምልክት ነው።
ሌሎች ዘጠኝ የመንፈስ ስጦታዎችም አሉ። የነዚህም ዝርዝር 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12 1Cor 12 8 ለአንዱ ጥበብን መናገር በመንፈስ ይሰጠዋልና፥ ለአንዱም በዚያው መንፈስ እውቀትን መናገር ይሰጠዋል፥ 8 For to one is given by the Spirit the word of wisdom; to another the word of knowledge by the same Spirit; 9 ለአንዱም በዚያው መንፈስ እምነት፥ ለአንዱም በአንዱ መንፈስ የመፈወስ ስጦታ፥ ለአንዱም ተአምራትን ማድረግ፥ 9 To another faith by the same Spirit; to another the gifts of healing by the same Spirit; 10 ለአንዱም ትንቢትን መናገር፥ ለአንዱም መናፍስትን መለየት፥ ለአንዱም በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፥ ለአንዱም በልሳኖች የተነገረውን መተርጎም ይሰጠዋል፤ 10 To another the working of miracles; to another prophecy; to another discerning of spirits; to another divers kinds of tongues; to another the interpretation of tongues:
የመንፈስ ስጦታዎች ዛፉ አብዝቶ እንዲያፈራ የሚጠቅሙ ልእለ ተፈጥሮ መሳሪያዎች ናቸው። በራሳቸው ፍጻሜ ወይም ግብ አይደሉም የመሳሪያዎቹ አላማ የመንፈስን ፍሬ ለማምጣት ነው። እነዚህ መንፈሳዊ ስጦታዎች ልእለ ተፈጥሮ ጥራት ስላላቸው ብዙ ስጋዊ አይምሮ ያላቸው ሰዎች ከመንፈስ ፍሬዎች ይልቅ አጥብቀው ይመኝዋቸዋል። ከሁሉ የሚበልጠውን የመንፈስ ፍሬ ሁሉ ዋንኛ የሆነውን ፍቅርን በቅድሚያ ከተከተሉ መመኘቱ መልካም ነው የመንፈስ ስጦታዎች የሚሰሩት በፍቅር ነውና። “1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14 ፡1 ፍቅርን ተከታተሉ፥ መንፈሳዊ ስጦታንም ይልቁንም ትንቢት መናገርን በብርቱ ፈልጉ። 1Cor 14፡1 Follow after charity, and desire spiritual gifts, but rather that ye may prophesy.” ስለሚል ቅደም ተከተሉ እስካልተዛባ ድረስ መልካም ነው።
እነዚህ የመንፈስ ስጦታዎች የታደሉት በአማኞች መካከል በጴንጤቆስጤ ሃይል ነው። ልእለ ተፈጥሮ መሳሪያ ሆነው የሚሰሩትም የሰውን የልቡ ሃሳብ በመግለጥ መንፈስ ቅዱስ ወደ አባት አይምሮና ፈቃድ እንዳመጣቸው መጠን ነው። የእነዚህ የመንፈስ ስጦታዎች ተጽኖ እና ውጤት በአማኖች ላይና በማያምኑት ላይ የተላያየየ ነው። ለአማኞች ስጦታው የሚወክለው የእ/ር ልእለ ተፈጥሮ ሃይል በህይወታቸው መስራቱን የሚያሳይ ከምልክቶች አንዱ ነው። ለማያምኑት ደግሞ የተሰወረውን የልባቸውን ሚስጥር በመግለጥ ወደ ንስሃ ያመጣቸዋል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14 1Cor 14 24 ሁሉ ትንቢት ቢናገሩ ግን የማያምን ወይም ያልተማረ ሰው ቢገባ በሁሉ ይወቀሳል፥ በሁሉም ይመረመራል፤ 24 But if all prophesy, and there come in one that believeth not, or one unlearned, he is convinced of all, he is judged of all: 25 በልቡም የተሰወረ ይገለጣል እንዲሁም። እግዚአብሔር በእውነት በመካከላቸው ነው ብሎ እየተናገረ በፊቱ ወድቆ ለእግዚአብሔር ይሰግዳል። 25 And thus are the secrets of his heart made manifest; and so falling down on his face he will worship God, and report that God is in you of a truth. ከዚህ እንደ ምናስተውለው የመንፈስ ቅዱስ ፍርድ በአማኖች ላይና በማያምኑት ላይ የተላያየየ ተጽኖ ሲያመጣ እናያለን። ወይ ይወቅሳል ወይ ነጻ ያወጣል።
ጻድቅ ከቀድሞ ኪዳን ጀምሮ ህይወቱ መልካም ፍሬ እዲያሳይ የእ/ር ቃል ያስተምራል:: ለምሳሌ ያህል መጽሐፈ ምሳሌ 11፥30 የጻድቅ ፍሬ የሕይወት ዛፍ ናት፥ ነፍሶችንም የሚሰበስብ እርሱ ጠቢብ ነው። 12፥12 የኅጥኣን ፈቃድ የክፉዎች ወጥመድ ናት የጻድቃን ሥር ግን ፍሬን ያፈራል። 12፥14 የሰው ነፍስ ከአፉ ፍሬ መልካም ነገርን ትጠግባለች፥ ሰውም እንደ እጁ ሥራ ዋጋውን ይቀበላል። 13፥2 ሰው ከአፉ ፍሬ መልካምን ይበላል የዓመፀኞች ነፍስ ግን ግፍን ትሻለች። 14፥14 ልቡን ከጽድቅ የሚመልስ ሰው ከመንገዱ ፍሬ ይጠግባል፥ ጻድቅም ሰው ደግሞ በራሱ። 18፥20 የሰው ሆድ ከአፉ ፍሬ ይሞላል ከንፈሩም ከሚያፈራው ይጠግባል። 18፥21 ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው የሚወድዱአትም ፍሬዋን ይበላሉ።
በአዲስ ኪዳንም ጌታ ብዙ ፍሬ ስላማፍራት አስተምረዋል። ለምሳሌ ያህል በሉቃስ ወንጌል 8 Luke 8 5 ዘሪ ዘሩን ሊዘራ ወጣ። ሲዘራም አንዳንዱ በመንገድ ዳር ወደቀ ተረገጠም፥ የሰማይ ወፎችም በሉት። 5 A sower went out to sow his seed: and as he sowed, some fell by the way side; and it was trodden down, and the fowls of the air devoured it. 6 ሌላውም በዓለት ላይ ወደቀ፥ በበቀለም ጊዜ እርጥበት ስላልነበረው ደረቀ። 6 And some fell upon a rock; and as soon as it was sprung up, it withered away, because it lacked moisture. 7 ሌላውም በእሾህ መካከል ወደቀ፥ እሾሁም አብሮ በቀለና አነቀው። 7 And some fell among thorns; and the thorns sprang up with it, and choked it.
8 ሌላውም በመልካም መሬት ላይ ወደቀ፤ በበቀለም ጊዜ መቶ እጥፍ አፈራ። ይህን በተናገረ ጊዜ። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ ብሎ ጮኸ። 8 And other fell on good ground, and sprang up, and bare fruit an hundredfold. 9 ደቀ መዛሙርቱም። ይህ ምሳሌ ምንድር ነው? ብለው ጠየቁት። 9 And his disciples asked him, saying, What might this parable be? 10 እርሱም እንዲህ አለ፦ ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ ለሌሎች ግን እያዩ እንዳያዩ እየሰሙም እንዳያስተውሉ በምሳሌ ነው። 10 And he said, Unto you it is given to know the mysteries of the kingdom of God: but to others in parables; that seeing they might not see, and hearing they might not understand. 11 ምሳሌው ይህ ነው። ዘሩ የእግዚአብሔር ቃል ነው። 11 Now the parable is this: The seed is the word of God.
12 በመንገድ ዳርም ያሉት የሚሰሙ ናቸው፤ ከዚህ በኋላም ዲያብሎስ ይመጣል አምነውም እንዳይድኑ ቃሉን ከልባቸው ይወስዳል። 12 Those by the way side are they that hear; then cometh the devil, and taketh away the word out of their hearts, lest they should believe and be saved. 13 በዓለት ላይም ያሉት ሲሰሙ ቃሉን በደስታ የሚቀበሉ ናቸው፤ እነርሱም ለጊዜው ብቻ ያምናሉ እንጂ በፈተና ጊዜ የሚክዱ ሥር የሌላቸው ናቸው። 13 They on the rock are they, which, when they hear, receive the word with joy; and these have no root, which for a while believe, and in time of temptation fall away. 14 በእሾህ መካከልም የወደቀ እነዚህ የሚሰሙት ናቸው፤ መንገዳቸውንም ሄደው በሕይወት ዘመን በአሳብና በባለ ጠግነት ምቾት ይታነቃሉ፥ ሙሉ ፍሬም አያፈሩም። 14 And that which fell among thorns are they, which, when they have heard, go forth, and are choked with cares and riches and pleasures of this life, and bring no fruit to perfection. 15 በመልካም መሬት ላይም የወደቀ እነርሱ በመልካምና በበጎ ልብ ቃሉን ሰምተው የሚጠብቁት በመጽናትም ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው። 15 But that on the good ground are they, which in an honest and good heart, having heard the word, keep it, and bring forth fruit with patience. አሜን!
Posted on March 20, 2012 Brother Binyam T. Alemayehu