
የዘላለም ሕይወት ስጦታ ነው። ክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ስጦታና የዘላለም ሕይወት ነው።
ወደ ሮሜ ሰዎች 6:23 የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው። Rom 6:23 For the wages of sin is death; but the gift of God is eternal life through Jesus Christ our Lord.
የኃጢአት “ደሞዝ” ምንድ ነው? ስለ ኃጢአት ስናስብ “ስጦታ” ብሎ ነገር የለምውም ለኃጢአት ያለው “ደሞዝ” ሲሆን ያም “ሞት” ብቻ ነው። ስለዚህ እንደቃሉ የኃጢአት ደሞዝ ምንድን ነው? «ዘላለማዊ ስቃይ በሲኦል?» ወይስ “ሞት?” እነሆ እንደምናነበው “የኃጢአት ዋጋ ወይም ደሞዝ ሞት ነው” በሲኦል ውስጥ ዘላለማዊ የስቃይ ህይወት አይደለም። አንድ ሰው “ዘለአለማዊ ህይወት” የሚያገኘው ከየት ነው? “ከእግዚአብሔር ስጦታ ከሆነው ከጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ” ነው.። የእግዚአብሔር ስጦታ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። የዮሐንስ ወንጌል 4/10 ኢየሱስ መልሶ፦ የእግዚአብሔርን ስጦታና፦ ውኃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ፥ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ የሕይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር አላት።
የዮሐንስ ወንጌል 17/3 እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት። የእግዚአብሔር ፍቅር ከመንፈሳቹ ጋር ይሁን! ወንድም ቢኒ።