
እኔ ነኝ ! (እግዚአብሔር አንድ አምላክ ነው ወይስ ስላሴ[ሶስት] ? )
በወንድም ቢንያም አለማየሁ 2/25/2018 Brother Binyam T. Alemayehu
ከመጀመርያ የተናገርኩት ነኝ!
ከመጀመርያው የተናገረውና የሙሴን ህግ የሰጠው ማነው?
ስማ አምላካቸን እግዚአብሔር አንድ አምላክ ነው።
እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን?
የዘልአለም አባት
ክፍል አንድ፦
እኔ ነኝ ! የእ/ር[እግዚአብሔር] አንድየነት አሮጌ ኪዳኑም ሆነ አባቶች እንዲሁም ጌታ እየሱስም ሆነ አዲስ ኪዳን አረጋግጦታል። “የያዕቆብ መልእክት 2:19 እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል።” እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ የማያምን መንፈሳዊ ኪሳራ ከስረዋል ለማይታወቅ አምላኮች ይሰግዳልና አጋንንት እንኳ በእምነት በልጦታል እግዚአብሔር ሦስት ሳይሆን አንድ እንደ ሆነ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማልና።
“እኔ ነኝ” ይህን ቃል ከብዙ ምእተ አመታት በፊት ሙሴ አንገቱን ወደ መሬት ደፍቶ ከእ/ር መገኘት የተነሳ በተቀደሰው መሬት በባዶ እግሩ ሆኖ ልቡ በፍርሃት እየመታ ከሚነደው ቁጥቋጦ ስር የሰማው የእ/ር ቃል ነበር። በህይወት ጉዞ ብዙ ካሳለፈ ቡሃላ በመጨረሻ በጎችን በመጠበቅ ባለበት ዘመኑ ነበር ለአዛውንቱ ለሙሴ በቅርቡ የሚጀምር ነፃ የማውጣት አገልግሎት እንዳለው የተነገረው።
በግብጽ በባርነት ወዳሉ ወንድሞቹ እንዲመለሰና ተሰምቶ ወደ የማይታወቅ ታላቅ በረከት መርቶ እንዲያ መጣቸው የተነገረው፡ ሙሴም በመጀመርያ በነገሩ አልተስማማም ነበር። የእ/ር ክብር ባየ ጊዜ ግን ወደ ግብጽ ለመውረድ ቁርጥ መሆኑን ከተረዳ ቡሃላ እ/ርን “ማን ላከኝ ልበላቸው?” ብሎ ጠየቀ የዚህን ጊዜ ነበር እ/ር እንዲህ ብሎ በጊዜ ተፈትነው በማይበሰብሱ ቃላቶቹ የመለሰለት “ያለውና የሚኖረው እኔ ነኝ… እኔ እኔ ነኝ ላከኝ በላቸው” [I AM that I AM, tell the pepople that I AM hath sent you] ለመጀመርያ ግዜ ለሰሙት እንግዳ ስም እንደ ሚሆንባቸውና ግራ ሊያጋባቸው ይችላል። ነገር ግን በዚህ አስደናቂ ስም ውስጥ ታምቆ የያዘው ፍቺ ብዛትና የተጠቀሰው እውነት በብዙ ትውልዶች ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም።
ከብዙ ምእተ አመታት ቡሃላ ፈሪሳውያን ከአዳኙ ጋር ስለ ስልጣኑና ስለ መለኮታዊ ምንጩ (about his authority & divine origin) ሲከራከሩት በመለሰው መልስ በቁጣ ተሞልተው የልባቸው ምሳሌ የሆነውን ዲንጋይ አንስተው ቢቻላቸው ሊወግሩትና ሊገድሉት ተመኝተው ነበር እርሱ ግን ተሰወረባቸው ማለትም ከስጋ ወደ መንፈስ ተቀየረባቸው። ያበገናቸው መልሱ ነበር “…ከአብርሃም በፊት “እኔ ነኝ” (before Abraham was “I AM” )የቀድሞ ትርጉም ተርጋሚዎች እዚህ ላይ ስላልገባቸው ከJOV (Jusus opinonative versions ኪኪኪ…)ብናየው የተሻለ ነት ልጆቹ የእ/ር መልኮታዊ እይታ[Divine Perspectiv of GOD) ልንይዝ የግዴታ ነውና ዋናውን ተናጋሪ ልናስተውል የግድ ነው። ያቃጠላቸው በዋናው ቌንቋ “…ከአብርሃም በፊት ነበርኩ ሳይሆን ያላቸው “ከአብርሃም በፊት እኔ ነኝ! I was ሳይሆን I AM ነው ያላቸው። “እኔ ነኝ“ ማን እደሆነ ስለሚያውቁ አጓሩ።
(John 8:58. ] Jesus says to them, “It is certainly so (Amen, amen)! I am telling you, before Abraham comes into being, I AM.”[JMT]
(John 8:58 [NET]) Jesus said to them, “I tell you the solemn truth, before Abraham came into existence, I am!”
KJV: የዮሐንስ ወንጌል 8:56 አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ፥ አየም ደስም አለው።
56 Your father Abraham rejoiced to see my day: and he saw it, and was glad.
57 አይሁድም፦ ገና አምሳ ዓመት ያልሆነህ አብርሃምን አይተሃልን? አሉት።
57 Then said the Jews unto him, Thou art not yet fifty years old, and hast thou seen Abraham?
58 ኢየሱስም፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ[“እኔ ነኝ” ] አላቸው።
58 Jesus said unto them, Verily, verily, I say unto you, Before Abraham was, I am.
“እኔ ነኝ” ማን እደሆነ ስለሚያውቁ የማጓረታቸው ምክንያት ሆነ። “እኔ ነኝ” የሚለው ስም የማን መጠርያ እንደሆነ እውቀቱ አላቸው ቀድሞ አባትን የሚያውቁት በፈራጅነቱ; እሳት ሲያወርድ፤ ባህር ሲከፍል፤ ፈርኦንን ሲመታ፤ በአንድ ቃል አቀባይ ነብይ ነገስታትን ሲያስነሳ ነገስታትን ሲያፈልስ፤ ጥበብን ለጠቢባን እውቀትን ለአስተዋዮች ሲሰጥ፤ሲና ተራራ ላይ በእሳት ህግ ሲገለጥ፤ ወዘተ… በአጠቃላይ አስፈሪ ግርማው በኅይል ሲገለጥ በብርቱ እጁ ሲገለጥ እ/ርን ያውቁታል።
አሁን ምንም እንካን “አማኑኤል ትርጋሜውም እ/ር ከኛ ጋር ማለት ነው” እያሉ ቢጠቡቅትም እ/ር በሰው ደረጃ ወርዶ ውሃ ከብርጭቆ እንደ ሚፈስ የማይታየውን የዘልአለም ሃይሉን መለኮትነቱን አአፍስሶ ቱሁት ሆኖ የነገስታት ንጉሱ የፍጥረት ሁሉ ፈጣሪና ገዢ [እኛ ነገስታት ነን እሱ የነገስታት ንጉስ ነው(በህይወት ነግሰናል)የነገስታት ንጉስ ግን አይደለንም እሱ የጌቶች ጌታ ነው እኛ ጌቶች ብቻ ነን የጌቶች ጌታ አይደለንም። የሚገርመው ግን ከክብር ወደ ክብር እየተለወጥን በቀድሞ ከእ/ርን ክብር (ከክርስቶስ) እንደ ጎደልና የዚያንም የመሬታዊውን መልክ እንደ ለበስን የሰማያዊውን መልክ ደግሞ እንለብሳለን። ጌታ መንፈስ ነው የእርሱን መልክ እንድንመስል ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን፤ ፀጉሩን እንዳይነጭ አዳም አይስማ እንጂ እኛ የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ እስከበረታን ድረስ ይህ ፍቅር “እስከ እግዚአብሔርም ፍጹም ሙላት” ደርሰን እንድንሞላ በዚህ ፍቅር ጉዞው ቀጥለዋል ።
አባት በክብሩ በመንፈስ ከእኛ ውስጥ ወደመታየት እየወጣው ነው እኛም ወደክብሩ በመንፈስ ወደ አባት እየገባን ነው።ሃሌሉያ። ‘ጌታ መንፈስ ነው፤ …. እኛም ሁላችን ባልተሸፈነ ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያንጸባረቅን፣ የእርሱን መልክ እንድንመስል ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን፤ ይህም የሚሆነው መንፈስ ከሆነ ጌታ ነው።’ 2 ቆሮንቶስ 3:17-18 መደበኛ ትርጉም ወደ ኤፌሶን ሰዎች 3/18-19 ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል፥ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ፥ እስከ እግዚአብሔርም ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ።]የባርያ መልክ ያውም በሰው ደረጃ ወርዶ ቃል የነበረው እ/ር ስጋ ሆኖ የቃሉ እውነት ከነሱ ሃሳብ ጋር ሰማይ ከምድር እንደሚርቅ ባስተዋሉ ጊዜ አልተዋጠላቸውም። “እኔ ነኝ” “I am” ።
“የዮሐንስ ወንጌል 1:1 ….. ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።
የዮሐንስ ወንጌል 1:14 ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥”
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2:6 እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ …..7 ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥
‘እርሱ በባሕርዩ አምላክ ሆኖ ሳለ፣ …. ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ፣ በሰውም አምሳል ተገኝቶ፣ ራሱን ባዶ አደረገ፤ ሰው ሆኖ ተገልጦም፣ ራሱን ዝቅ አደረገ፤ እስከ ሞት፣ ያውም በመስቀል ላይ እስከ መሞት ድረስ ታዛዥ ሆነ። ‘ፊልጵስዩስ 2:6-8 አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ከደቀ መዛምርቱ አንዱ ጠርጣራው ቶማስ እያማረረ ጌታን ጠየቀ “ወዴት እንደምትሄድ አናውቅም መንገዱንስ እንዴት እናውቃለን” እኔ ነኝ መንገዱ፤ እየሱስም ደገመ፤ እኔ ነኝ እውነቱ፤ እየሱስ ሰለሰ እኔ ነኝ ህይወቱ፤ ማርታ በሃዘን በተሞላ አነጋገር”በመጨረሻው ቀን በትንሳኤ እንዲነሳ አውቃለሁ አለችው” እየሱስም መለሰ “ትንሳኤ እኔ ነኝ፤ ህይወት እኔ ነኝ” ;;
መጽሃፍት ትመረምራላችሁ መጽሓፍት ሁሉ ግን ስለኔ ይናገራሉ ህይወት እንዲሆንላችሁ ግን ወደኔ ልትመጡ አትወዱም። ምን ምን? መጽሓፍት ሁሉ ግን ስለኔ ይናገራሉ ? ሁሉ ስለኔ የሁሉ ትርጉም ሁሉ ነው። “እኔ ነኝ” “I am” መጨረሻ የለውም የወይኑ ግንዱ እኔ ነኝ፤ በሩእኔ ነኝ፤ መልካም እረኛ እኔ ነኝ፤ የአለም ብርሃን እኔ ነኝ ፤ አልፋ እኔ ነኝ ፤ ኦሜጋ እኔ ነኝ ፤ የመጀመርያው እኔ ነኝ፤ የመጨረሻው እኔ ነኝ፤ የምዋጀው እኔ ነኝ ፤ ብርታትህ እኔ ነኝ ፤ የሚኖረው እኔ ነኝ ፤ ሞቶ የነበረው እኔ ነኝ ፤ ትንሳኤው እኔ ነኝ ፤ የዘጋሁትን ማንም የማይከፍተው የከፈትኩትን ማንም የማይዘጋው እኔ ነኝ ፤ የዳዊት ስርና እኔ ነኝ ፤ የንጋት ኮከብ እኔ ነኝ፤ ስሙም ድንቅ መካር እኔ ነኝ ፥ ኃያል አምላክ እኔ ነኝ ፥ የዘላለም አባት እኔ ነኝ ፥ የሰላም አለቃ እኔ ነኝ “ያለውና የሚኖረው እኔ ነኝ:
እኔ ነኝ፤ እኔ ነኝ፤ እኔ ነኝ፤ እኔ ነኝ… እኔ እኔ ነኝ በላቸው” [I AM that I AM, tell the pepople that I AM hath sent you] እነሆ ለስነቱ መጨረሻ የለውም ። “ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2:9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤የዮሐንስ ራእይ 1:8 ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፦ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።” አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ ያለኝ እኔ እኔ፤ የታመነውና እውነተኛው ምስክር እኔ ነኝ፥።የዮሐንስ ራእይ 4:10-11 ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ፦ ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም[ለደስታህ ተፈጥረውማልና for thy pleasure they are and were created.] ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ።
ከመጀመርያው የተናገርኩት ነኝ
ስለ አብ እንደ ነገራቸው አላስተዋሉም። “ የዮሐንስ ወንጌል 8/25 እንግዲህ፦ አንተ ማን ነህ? አሉት። ኢየሱስም፦ ከመጀመሪያ ለእናንተ የተናገርሁት ነኝ። ….27 ስለ አብ እንደ ነገራቸው አላስተዋሉም። 28 ስለዚህም ኢየሱስ፦ የሰውን ልጅ ከፍ ከፍ ባደረጋችሁት ጊዜ እኔ እሆን ዘንድ …. ታውቃላችሁ። “( Jo 8:27 They understood not that he spake to them of the F-A-T-H-E-R. 28 then said Jesus unto thme,When you have lifted up the son of man ,then shall ye Know that I A-M H-E.)
የሚገርመው ከሰቀሉት ቡሃል እርሱ እንደሆነ እንደሚያቁ ነገራቸው ከተመረጡ ውጭ ግን ሁሉ ገና አላወቁትም የአሕዛብ ሙላት እስኪገባ ድረስ መንፈሳቂ ድንዛዜ[ በከፊል እውርነት blindness in part] በእስራኤል በአንዳንድ በኩል ሆነባቸዋልና፤that blindness in part is happened to Israel, until the fulness of the Gentiles be come in.] ‘ ነገሩ በመገለጥ ነው እንጂ አብ ማን እንደሆነ ወልድ ማን እደሆነ በአእምሮ ጂምናስቲክ የሚታወቅ አይደለም። ከወልድና ወልድ ራሱ ፈቅዶ ከሚገልጥላቸው ሌላ አብን የሚያውቅ የለም። ብሎዋልና “ሁሉ ነገር ከአባቴ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ ሌላ ወልድን የሚያውቅ የለም፤ ከወልድና ወልድ ራሱ ፈቅዶ ከሚገልጥላቸው ሌላ አብን የሚያውቅ የለም። ‘ማቴዎስ 11:27 ይህን የመለኮት ሚስጥር በመገለጥ እንጂ በትምህርት አታውቀውም።
ከመጀመርያው የተናገረውና የሙሴን ህግ የሰጠው ማነው? ህግን ለሙሴ የሰጠው እራሱን “ያህዌ (Yahweh)” ብሎ በሚነደው ቁጥቋጦ ጠርተዋል። “ያህዌ” የሚለው የፈጣሪ ስም እ/ር መጀመርያና መጨረሻ የሌለው ዘልአለማዊና እራሱን በራሱ ህላዌ(ህልውና) [self-existent] ያለው መሆኑን የሚያመለክት ነው። ይህ አዲስ ስም ነበር። ለአብርሃም ለይሳቅ ለያቆብ አልተገለጣላቸውም ነበር። “’እግዚአብሔርም (Hebrew፣ ኤሎሂም elohiym el-o-heem) ሙሴን አለው፤ “እኔ እግዚአብሔር (Hebrew፣ያህዌ Yhovah yeh-ho-vaw’) ነኝ። ሁሉን የሚችል አምላክ (ኤልሻዳይ ‘el ale Shadday shad-dah’-ee) ሆኜ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ ተገለጥሁላቸው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር (Hebrew፣ያህዌ Yhovah yeh-ho-vaw’) በተባለው ስሜ ራሴን አልገለጥሁላቸውም። ‘ ዘፀአት 6:2-3 አዲሱ መደበኛ ትርጉም
እንደትረሱ አንዱ እ/ር ኤልሻዳይ፤ያህዌ ብሎ እራሱን ገለጠ ሁለት እግዚአብሔሮች አይደሉም ቡሃላ ነገሩን ስለምናያይዘው ማስተዋሉመልካም ነው።
የህግ ሰጪው ማንነት በዘፀ፤20:2 አስርሩን ትእዛዛት ሲሰጥ በህግ መቅድሙ ላይ ሲናገር ‘“ከግብፅ ከባርነት ምድር ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ (ያህዌ self-Existent በራሱ የሚኖር ። በራሱ ህልውና ያለው) እኔ ነኝ።” “ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይኑሩህ። ‘ ዘፀአት 20:2-3”
ለአብርሃም ሲገለጥ እንደ ኤልሻዳይ አወቀው ‘አብራም ዕድሜው 99 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ተገልጦለት እንዲህ አለው፤ “እኔ ኤልሻዳይ” ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ፤ ነቀፋም አይኑርብህ፤ ‘ ዘፍጥረት 17:1 ከዘፍጥረት እስከ ዘዳግም የፃፈው ሙሴ ነው። ይህም ማለት እነ አብርሃም ያልበራለቻው ያህዌ የሚለው የእ/ር ስም ከገባው ቡሃላ የፃፈው ስለሆነ ያህዌ እያለ በእብራይስጥ ተጠቅሞበታል ኤልሻዳይ እና ያህዌ አንድ አምላክ እንደሆነ እናያለን ። “እኔ እግዚአብሔር (Hebrew፣ያህዌ Yhovah yeh-ho-vaw’) ነኝ። ሁሉን የሚችል አምላክ (ኤልሻዳይ ‘el ale Shadday shad-dah’-ee) ሆኜ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ ተገለጥሁላቸው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር (Hebrew፣ያህዌ Yhovah yeh-ho-vaw’) በተባለው ስሜ ራሴን አልገለጥሁላቸውም። ‘ ዘፀአት 6:2-3 አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ከዚህ የምንረዳው እ/ር እራሱን በተለያየ ስምና መልክ[ስም በመጽሓፍ ቅዱስ የሚያሳየው የአንድን ነገር ባህርዩ ን ወይም ተፈጥሮዉን ነው] እራሱን እንዴት እንደሚገልጥ እናስተውላለን። በአዲስ ኪዳን ቃል የነበረው እ/ር ስጋ ሆኖ በክርስቶስ እየሱስ ተገለጠ የእብራይስጥ ስሙ “እያሱ [yashua or Joshua]” ነው። ትርጉሙም “ደህንነት፤አዳኝ [እ/ር ያድናል ]” ማለት ነው። ይከውም በግሪክ ቋንቋ “እየሱስ” ይባላል ትርጉሙም “አዳኝ” ማለት ነው።
ጌታ በሉቃስ ወንጌል 24:27 ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጐመላቸው። እንደ ምናስተውለው ጌታ ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ላይ የተፃፈው ስለሱ መሆኑንና ለመረዳት ግን ጌታ በመንፈሱ ካልተረጎመልና መጻሕፍትን እናስተውል ዘንድ አእምራችን ካልከፈተልን በትዮሎጂ እውቀት ከማበጥ ውጪ እውነትን ለመረዳት ይከብደናል። የሉቃስ ወንጌል 24/45 በዚያን ጊዜም መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው፤
የዮሐንስ ወንጌል 5:39 እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፤ የዮሐንስ ወንጌል 7:15 አይሁድም፦ ይህ ሰው ሳይማር መጻሕፍትን እንዴት ያውቃል? ብለው ይደነቁ ነበር።
ጌታ እንዳለው ከሙሴ ዘንድ ስለሱ ተጽፈዋል እስቲ ይህን የሚደንቅ ምጢር እንመልከት። ‘ እግዚአብሔር (ያህዌ) ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም[ደህንነቴም yashua: እያሱ በእብራይስጥ እየሱስ በግሪክ] ሆነልኝ፤ እርሱ አምላኬ ነው፤ አመሰግነዋለሁ፤ የአባቴ አምላክ (ኤሎሂም) ነው፤ እኔም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ። እግዚአብሔር (ያህዌ) ተዋጊ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር (ያህዌ) ነው። ‘ ዘፀአት 15:2-3 አስተዋላችሁትን ቢቱን እግዚአብሔር (በያህዌ) ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም[ደህንነቴም yashua: እያሱ በእብራይስጥ እየሱሴም በግሪክ] ሆነልኝ። እንዲገባን በግልጽ አማርኛ እንየው “ያህዌ ደህንነቴ ወይም እየሱሴ ሆነልኝ[“ያህዌ እየሱሴ ሆነልኝ”]”
ይህ የእየሱስ ስጋ የመልበሱ ትንቢት ነው። የአሮጌው ኪዳን እ/ር በአዲስ ኪዳን ሰው ሆኖ ስለመገለጡ ነው። ይህም በኢሳያስ 12:2-3 ‘እነሆ፣ እግዚአብሔር ድነቴ[እየሱሴ] ነው፤ እታመናለሁ፣ ደግሞም አልፈራም፤ ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም [እየሱሴም]ሆኖአል።” ከድነቴ[እየሱሴ] ምንጮች ውሃ በደስታ ትቀዳላችሁ። ‘ ኢሳይያስ 12:2-3 እንደምናስተውለው ኢሳያስ በሙሴ መጽሐፍ በዘፅአት የተፃፈውን ደግሞ ሲጠቅስ እናስተውላለን። በዚህ አያበቃም እየሱስ ይህን በመጥቀስ አጽንቶታል።
ጌታ እየሱስ ይህን ትንቢት ግልጽ አድርጎ ፈቶታል። ‘የበዓሉ መጨረሻ በሆነው በታላቁ ቀን፣ ኢየሱስ ቆሞ ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ አለ፤ “ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ፤ በእኔ የሚያምን፣ መጽሐፍ እንዳለ የሕይወት ውሃ ምንጭ ከውስጡ ይፈልቃል።” ‘ ዮሐንስ 7:37-38 በሌላ የእንግሊዝኛ ትርጉም ማንም ከተጠማ ከደህንነት ምንጭ ዉሃ ይጣጣ ይላል።
ይህ ግልጽ ቃል የሚያስረዳን በአሮጌው ኪዳን እየሱስ [በእብራይስጥ እያሱ] ስለ ድነት ወይም ደህንነት ተደብቆ የነበረው ሚስጥር እንደሆነ ነው። ጌታ እየሱስ ስጋ የለበሰው ያህዌ ነው። “ያህዌ እየሱሴ ሆነልኝ” በቀድሞው ኤልሻዳይ ብሎ እራሱን የጠራው በራእይ[በእየሱስ ክርስቶስ መገለጥ መጽሐፍ] እራሱን በድጋሚ ሲያረጋግጥ ሁሉን ቻይ ብለዋል። ጌታ እየሱስ ክርስቶስ በአዲስ ኪዳን አስር ቦታ ላይ (ኤልሻዳይ ‘el ale Shadday shad-dah’-ee) ተብሎ ተጠርተዋል። ልናየው ያልቻልነው ተርጋሚዎቹ ኤልሻዳይ እንደማለት ፈንታ በአማርኛችን ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ በእንግሊዝኛ Almighty ብለው ስለተረጎሙት ነው ። የፃድቅ ሃብቱ ትጋቱ ነውና ማጥናት ትችላላችሁ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:18 , የዮሐንስ ራእይ 1:8, 4:8, 11:17, 15:3, 16:7, 16:14, 19:6, 19:15, 21:22
በአሮጌው ኪዳን ለአብ የተነገሩት በአዲስ ኪዳን ለጌታ እየሱስ ክርስቶስ ስለመነገራቸው የሚያሳዩ ጥቂቶችን ለመጥቀስ ያህል
የዮሐንስ ራእይ 1/8 ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ(በእብራይስጥ ኤልሻዳይ ‘el ale Shadday shad-dah’-ee በግሪክ pantokrator pan-tok-rat’-ore፤ the all-ruling, i.e. God (as absolute and universal sovereign):–Almighty, Omnipotent.)፦ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።
Rev 1/8 I am Alpha and Omega, the beginning and the ending, saith the Lord, which is, and which was, and which is to come, the Almighty. (በእብራይስጥ ኤልሻዳይ ‘el ale Shadday shad-dah’-ee በግሪክ pantokrator pan-tok-rat’-ore፤ the all-ruling, i.e. God (as absolute and universal sovereign):–Almighty, Omnipotent.)
የዮሐንስ ራእይ 4:8 አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሉአቸው፥ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዓይኖች ሞልተውባቸዋል፤ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም።
Rev 4:8 And the four beasts had each of them six wings about him; and they were full of eyes within: and they rest not day and night, saying, Holy, holy, holy, Lord God Almighty, which was, and is, and is to come.
ጌታ ሙሴ የፃፈው ስለኔ ነው ሙሴን የማያምን መጻሕፍትን አያምንም ጌታንም አያምንም ሙሴ የፃፈው ሁሉስለ ጌታ እየሱስ ትንቢታዊና ገላጭ ቃል ነበረ። “የዮሐንስ ወንጌል 5/46 ሙሴንስ ብታምኑት እኔን ባመናችሁ ነበር፤ እርሱ ስለ እኔ ጽፎአልና።47 መጻሕፍትን ካላመናችሁ ግን ቃሌን እንዴት ታምናላችሁ?” ህግ እራሱየሚገልጸወ የህግ ሰጪው አቃምን ነው። አይሁድ ስለ ጌጽእየሱስ ሲያስቡ 33 ½ ዓመት በምድር ላይ ስጋ ለብሶ የተመላለስበትን ብቻ ስለሚያስተውሉ የምሎ ኮታዊምንጭ ማንነት አልተዋጠላቸውም። ለዚህ ነበር ከአብርሃም በፊት ነኝ ሲል ጉድ ጉድ ከአብርሃም በፊት እኔ ነኝ 50 ዓመት እንካ ሳይሞ ላው ምን እያለ ነው እያሉይ መፃደቁ ነበር። የኅይል ሁሉ ራስ እራሱን አርግቶ በፈጠረው በሰው ቅርጽ ወይም መልክ በመሃላቸው ሲከሰት እንዴት ተፈጥራዊው አእምሮ ሊገባው ይችላል?
የዮሐንስ ራእይ 11:17 እንዲህ አሉ፦ ያለህና የነበርህ ሁሉን የምትገዛ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ትልቁን ኃይልህን ስለ ያዝህ ስለ ነገሥህም እናመሰግንሃለን፤
Rev 11:17 Saying, We give thee thanks, O Lord God Almighty, which art, and wast, and art to come; because thou hast taken to thee thy great power, and hast reigned.
የሚገርመው አብርሃም የእምነት ሰው ስለነበር ቀኑን በእምነት አሻግሮ አይቶ ሐሤት አደረገ፥ አየም ደስም አለው። የዮሐንስ ወንጌል 8/56 አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ፥ አየም ደስም አለው። እነሱ ደግሞ በምድረበዳ ለነበረችው ቤተ ክርስቲያን አለት ሆኖ ዉሃ ያጠጣቸውን ክርስቶስን ሊያስታውሱት አልቻሉም። ይከተላቸው ከነበረው መንፈሳዊ ዐለት አንተ ማነህ ይሉታል? ‘ሁሉም ከአንድ መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፤ ይከተላቸው ከነበረው መንፈሳዊ ዐለት ጠጥተዋልና፤ ያ ዐለት ክርስቶስ ነበረ። ‘ 1 ቆሮንቶስ 10:4
ከላይ ያነሳሁት ሃሳብ አማርኛችን በስተት ማህበሩ ብሎ ተርጉሞታል መተርጎም የነበረበት [የምድረ በዳ ቤተ ክርስቲያን the church in the wilderness] ነበር። ሐዋርያት ሥራ 7:38 ይህ ሰው በሲና ተራራ ከተናገረው መልአክና ከአባቶቻችን ጋር በምድረ በዳ በማኅበሩ ውስጥ የነበረው ነው፤ ይሰጠንም ዘንድ ሕይወት ያላቸውን ቃላት ተቀበለ፤
Acts 7:38 This is he, that was in the church in the wilderness with the angel which spake to him in the mount Sina, and with our fathers: who received the lively oracles to give unto us:
ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን ለራስህ አዘጋጀህ
የካህናት አለቆችና ጻፎች ዳዊት ለብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር በበገና ሲያቀነቅን የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችን ባየሁ ጊዜ፥ ጨረቃንና ከዋክብትን አንተ የሠራሃቸውን፥ ወዘተ… እያለ መንፈሳዊ ቅኔ ሲደረድር ቃሉ ለማን እንደሆነ የተነገረው ያውቁታል ጌታ እየሱስ ክርስቶስ በአይናቸው ፊት ሌላ ቅኔ ደገመላቸው የአሮጌው ኪዳን እግዚአብሔር እኔ ነኝ ዳዊት የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችን ባየሁ ጊዜ፥ ጨረቃንና ከዋክብትን አንተ የሠራሃቸውን፥ ብሎ በመንፈስ ቅዱስ ያዜመው ለኔ ነው ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን ለራሴ ያዘጋጀሁት እኔው ለራሴ ነው ብልዋቸው ቁጭ። የካህናት አለቆችና ጻፎች ያደረገውን ድንቃ ድንቅ በመቅደስም፦ ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ እያሉ የሚጮኹትን ልጆች ባዩ ጊዜ፥ ተቈጥተው፦16 እነዚህ የሚሉትን አትሰማምን? አሉት። ኢየሱስም፦ እሰማለሁ፤ ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን ለራሴ ያዘጋጀሁት እኔው ለራሴ ነው ብልዋቸው እርፍ። ሃይማኖት ዞረበት። ኪኪኪ….
“መዝሙረ ዳዊት 8:1 አቤቱ ጌታችን፥ ስምህ በምድር ሁሉ እጅግ ተመሰገነ፥ ምስጋናህ በሰማዮች ላይ ከፍ ከፍ ብሎአልና።2 ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ ስለ ጠላትህ፥ ጠላትንና ቂመኛን ለማጥፋት።3 የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችን ባየሁ ጊዜ፥ ጨረቃንና ከዋክብትን አንተ የሠራሃቸውን፥4 ታስበው ዘንድ ሰው ምንድር ነው? ትጐበኘውም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድር ነው?”
“የማቴዎስ ወንጌል 21:15 ነገር ግን የካህናት አለቆችና ጻፎች ያደረገውን ድንቃ ድንቅ በመቅደስም፦ ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ እያሉ የሚጮኹትን ልጆች ባዩ ጊዜ፥ ተቈጥተው፦16 እነዚህ የሚሉትን አትሰማምን? አሉት። ኢየሱስም፦ እሰማለሁ፤ ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን ለራስህ አዘጋጀህ የሚለውን ቃል ከቶ አላነበባችሁምን? አላቸው።”
ስማ/ሚ ! አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው።
ሐዋርያው ጳውሎስ ሲናገር ”አሁን እኔ ጐሽ ለመባል የምሻው በሰዎች ዘንድ ነው ወይስ በእግዚአብሔር ዘንድ? ወይስ ሰዎችን ደስ ለማሰኘት እየተጣጣርሁ ነው? ሰዎችን ደስ ለማሰኘት የምጥር ብሆን ኖሮ፣ የክርስቶስ አገልጋይ ባልሆንሁ ነበር። ገላትያ 1:10” አያችሁ እንደ እ/ር ልጅነታችሁ አንድ ልታስደሱትት የሚገባ አንዱን እ/ር ብቻ ነው። ምናልባት ሰውን ሊያስደስት የሚጥር ሊኖር ይችል ይሆናል ሚዛኑን ከጠበቀ መጥፎ አይደለም ሆኖም እ/ር ካልቀደመ በመጨረሻው ሳይሳካላችሁ ታያላችሁ ፤ ሰው ለምርኩዝ አይሆንም ሸንበቆ ነውና ይሰበራል ተሰብሮም ስንጥቁ ሊያደማ ይችላል። እውነተኛ የዘልአለም አምባ መደገፊያችን የትውልዶች ሁሉ መመኪያና መጠግያ እ/ር እራሱ ነው።
‘እስራኤል ሆይ ስማ፤ አምላካችን(ኤሎሂም) እግዚአብሔር (ያህዌ) አንድ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነው ። ‘ዘዳግም 6:4 በ1406 አ.ቅ.መ. [አመተ ቅድመ ክርስቶ] ገደማ ነበር ይህ አስደናቂ ቃል ከሙሴ አፍ የተነገረው። ይህ በቀደሙት አባቶች ሁሉ ለሺ አመታት ተቀብለውት የኖረ እውነት ነው። የስላሴ ትምህርት እስከ ተጀመረበት 325 ዓ/ም[From the first church council in 325 A.D. that established the doctrine of the Trinity]
እስቲ የቃሉ ስልጣን በራሱይናገረን። ‘እግዚአብሔርም (ኤሎሂም) ሙሴን፣ “እኔ፣ ያለሁና የምኖር ነኝ (ያህዌ) ፤ ስለዚህም፣ ‘ያለና የሚኖር’ ልኮኛል ብለህ ንገራቸው” አለው። ‘ ዘፀአት 3:14
‘“ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይኑሩህ። ‘ዘፀአት 20:3
አብ በመባል የሚታወቀው በአሮጌው ኪዳን የፊተኛውም እኔ ነኝ፤ የኋለኛውም እኔ ነኝ፤ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም።’“የእስራኤል ንጉሥና ቤዛ እግዚአብሔር ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ የፊተኛውም እኔ ነኝ፤ የኋለኛውም እኔ ነኝ፤ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም። ‘ኢሳይያስ 44:6 “ምን? ምን? ምን? የፊተኛውም እኔ ነኝ፤ የኋለኛውም እኔ ነኝ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም።? በአዲስ ኪዳን እየሱስ ክርስቶስ[ወልድ] በራእይ ሲናገር፦ ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፦ አልፋና[የመጀመርያው] ዖሜጋ[የመጨረሻው] እኔ ነኝ ይላል።
፤ሞቶ የነበረው ሕያውም የሆነው ፊተኛውና መጨረሻው እንዲህ ይላል፦ ለእየሱስ ክርስቶስ ሲሰግዱ አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሉአቸው፥ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዓይኖች ሞልተውባቸዋል ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም። የዮሐንስ ራእይ 4/8 ምን ምን? ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ ታድያ በአሮጌው ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የተባለለት አብ አይደል ? ትንቢተ ኢሳይያስ 6/3 አንዱም ለአንዱ፦ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽ ነበር።
ሌላ እንጨምር ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች ? የእ/ር ክብር ማነው? ”ትንቢተ ዕንባቆም 2/14 ውኃ ባሕርን እንደሚከድን ምድር የእግዚአብሔርን ክብር በማወቅ ትሞላለችና። ሲመለከት የእግዚአብሔርን ክብር ኢየሱስንም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየና “የሐዋርያት ሥራ 7/55 መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ ወደ ሰማይ ትኵር ብሎ ሲመለከት የእግዚአብሔርን ክብር ኢየሱስንም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየና፦“
‘“ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ፣ እርሱ እኔ እንደሆንሁ ትረዱ ዘንድ፣ እናንተ ምስክሮቼ፣ የመረጥሁትም ባሪያዬ ናችሁ” ይላል እግዚአብሔር ። “ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም፤ ከእኔም በኋላ አይኖርም። እኔ፣ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔም ሌላ የሚያድን የለም። ገልጫለሁ፤ አድኛለሁ፤ ተናግሬአለሁ፤ በመካከላችሁ እኔ እንጂ ባዕድ አምላክ አልነበረም። እኔ አምላክ እንደሆንሁ፣ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ” ይላል እግዚአብሔር ፤ “ከጥንት ጀምሮ እኔው ነኝ፤ ከእጄም ማውጣት የሚችል የለም፤ እኔ የምሠራውን ማን ማገድ ይችላል?” ‘ኢሳይያስ 43:10-13
ትንቢተ ኢሳይያስ 44/8 አትፍሩ አትደንግጡም፤ ከጥንቱ ጀምሬ አልነገርኋችሁምን? ወይስ አላሳየኋችሁምን? እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ። ከእኔ ሌላ አምላክ አለን? አምባ የለም ማንንም አላውቅም።
‘“ከማሕፀን የሠራህ፣ የተቤዠህም፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ሁሉን ነገር የፈጠርሁ፣ ብቻዬን ሰማያትን የዘረጋሁ፣ ምድርን ያንጣለልሁ፣ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። ‘ኢሳይያስ 44:24
ትንቢተ ኢሳይያስ 45/22 እናንተ የምድር ዳርቻ ሁሉ፥ እኔ አምላክ ነኝና፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና ወደ እኔ ዘወር በሉ ትድኑማላችሁ።
የእ/ር አንድየነት ጌታ እየሱስም ሆነ አዲስ ኪዳን አረጋግጦታል። “የያዕቆብ መልእክት 2/19 እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል።” “1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2/5 አንድ እግዚአብሔር አለና፥”
‘ከሁሉም በላይ የሆነ፣ በሁሉም የሚሠራ፣ በሁሉ የሚኖር የሁሉም አባት የሆነ አንድ አምላክ አለ። ‘ ኤፌሶን 4:6
ወደ ሮሜ ሰዎች 3/29-30 …የሚያጸድቅ አምላክ አንድ እ/ር ብቻ ነው።
‘ለእኛ ግን ሁሉም ነገር ከእርሱ የሆነ፣ እኛም ለእርሱ የሆን አንድ አምላክ አብ አለን፤ ‘1 ቆሮንቶስ 8:6
እስቲ ነገሩን መንፈሳችሁን ገዝታችሁ በሰከነ መንፈስ እንደገና አጢኑት የዮሐንስ ወንጌል 4/24 እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ ብሎ ያውጃል እውነትም እ/ር የማይታይ መንፈስ ነው የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና፤ መንፈስ በመሆኑም የሚኖረው ለስነቱ በሚሆነው በመንፈስ ግዛት ነው።
እናስተውል ፦ ያም የዘልአለም ግዛት ሲሆን የጊዜ ንጥረ ነገር የለበትም ከሰማይ በላይ ለሆነ ሁሉ ዘመን የለውም፥ ከሰማይ በላይ ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አይሰለጥንበትም። ነገር ግን ለሁሉ ዘመን ያለው፥ ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ነው። ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ ሰልጥኖበታል። ዘመን የተመደበለት ለሰው ልጆች እንጂ ለእ/ር አይደለምና “የሐዋርያት ሥራ 17/26-27 ምናልባትም እየመረመሩ ያገኙት እንደ ሆነ፥ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ፥ የተወሰኑትንም ዘመኖችና ለሚኖሩበት ስፍራ ዳርቻ መደበላቸው። ቢሆንም ከእያንዳንዳችን የራቀ አይደለም።”
ባለፈው እንዳነሳሁት የዘመን ትርጉም ደግሜ ልጥቀሰውና በመረዳት ብርሃን ማስተዋል ያለብን ዘመን ማለት ዘልአለም ማለት አይደለም። ብዙ ጊዜና ብዙ ወቅቶች አሉ። ነገር ግን አንድ ዘልአለም ብቻ አለ። ዘልአለም ጅማሬ የለው ፍፃሜም ቢሆን የለውም።
ነገር ግን ጊዜ ዘመን ወቅቶች ሁሉም ጅማሬ አላቸው ፍፃሜም አላቸው። ጊዜ ሲያበቃ ዘልአለም ይጀምራል የሚለው አባባል ፈጽሞ ስህተት ነው። ምክንያቱም ዘልአለም ጅማሬ የለውም የሚያበቃም አይደለም። ዘልአለም ጊዜ ሲመጣ የሚጀምር አይደለም።ዘመናት በዘልአለም ውስጥ የራሳቸው የሆነ ቦታ አላቸው።
ልክ ሴኮንድ በደቂቃ ውስጥ ቦታ እንዳለው ደቂቃም በሰአት ውስጥ የራሱ ቦታ እንዳለው ሰአትም በአመታት ውስጥየራሱ ቦታ እንዳለው። አመታት እና ዘመናት ያልቃሉ በዘልአለም ውስጥም የራሳቸው የሆነ ቦታ አላቸው። ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን ጊዜ እናስተውል ዘንድ በነዚህ ቃላቶች መካከል ያለው ልዩ ነት ግልጽ እይታ ሊኖረን ወሳኝነው። ዘመን የሚመደበው በጊዜ ውስጥ ሲሆን ዘልአለምግን ጊዜ አልባ ነው። በመጽሐፍ ስለ ዘመን የተናገሩትንና ሰለ ዘልአለም የተናገሩትን ለይተን ማስተዋሉ የእ/ርን ጠቅላላ ምክር እናስተውል ዘንድ እጅግ ይጠቅመናል።
እ/ር በራሱ ህይወት ያለው ህያው ነው። ከዘፍጥረት አንድ በፊት እ/ር የት ነበረ የሚለውን አሁን ያለበት ሊቀረብ በማይቻል ብርሃን መንፈሳዊ ግዛት ውስጥ ይኖራል፤ ከማለት በቀር ሌላ መልስ ሊያመጣ የሚችል የለም። ‘እርሱ ብቻ ኢመዋቲ ነው፤ ሊቀረብ በማይቻል ብርሃን ውስጥ ይኖራል፤ እርሱን ያየ ማንም የለም፤ ሊያየውም የሚችል የለም። ለእርሱ ክብርና ኀይል ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁን፤ አሜን። ‘1 ጢሞቴዎስ 6:16
‘ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የማይታየው የእግዚአብሔር ባሕርይ ይኸውም ዘላለማዊ ኀይሉና መለኮትነቱ፣ ከፍጥረቱ በግልጽ ይታያል፤ ስለዚህ ሰዎች ማመካኛ የላቸውም። ‘ ሮሜ 1:20 አስተውሉ የእግዚአብሔር ባሕርይ ይኸውም ዘላለማዊ ኀይሉና መለኮትነቱ፣ የማይታይ ነው ለፍጥረቱ መታየት ፈለገና በመጀመሪያው ቃል የነበረ እግዚአብሔር ወደ ሚታየው እራሱን መግለጥ ፈለገ ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ። እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ እንደሌለ ግልጽ ነው። ፤ የዮሐንስ ወንጌል 1/18 መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ ለሙሴ እንደነገረው ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልህም ብሎታል እ/ር በክብሩ ቢገለጥ ሰው አይድንም ኦሪት ዘጸአት 33/20 ደግሞም፦ ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልህም አለ።
ቃል ወይም መንፈስ የሆነው ጌታ ስጋ ሆኖ በልጅነት ክብር ተገለጠ ። ምክንያቱም መንፈስ የሆነውን ጌታ ማንም ሊያየው በማይችል ብርሃን የሚኖሮ ከሆነ እ/ርን ማየት ለስጋ ለባሽ የማይቻል ነው። የስጋዊው አእምሮ መንፈሳዊን አለም ያስተውል ዘንድ ብቃት የለውምና። እ/ር መንፈስ እንደሆነ እንደኛም ተፈጥራዊ አካል እንደሌለው ካስተዋልን ዘንዳ በብሉይ ኪዳን ዘመን እ/ር አንድን ሰው ማናገር ከፈለገ ወይም ሊገለጥለት ከፈለገ እራሱን በሚታይ ነገር በሚዳሰስ ነገር ለምድር ነዋሪዎች ሊረዱት በሚችሉት በቋንቋቸው ማለትም በዚህ በሚገባው ቋንቋ ወይም ነገር እራሱን ይገልጥ ነበር።
መንፈሳዊውን ነገር በተፈጥራዊው ቋንቋ ካልገለጠው በቀር ለማስተዋል አይቻልምና ለዚህም ነው የራእይን መጽሓፍ ጨምሮ መንፈሳዊውን ነገር በሚወክሉ በምልክቶች ለባርያው አሳወቀው ይለናል። ስለዚህ በብሉይ ወይም በአሮጌው ኪዳን ተፈጥራዊውን ነገር እራሱን ለመግለጥ ይጠቀም፡ነበር ። ይህም ሆኖ መንፈስ የሆነው ጌታ አጠገባቸው በመካከላቸው ሆኖ ሳለ የሚያየው አልነበረም ውጤቱን ግን ያዩ ነበር።
እስራኤልን በምድረ በዳ ብታስተውሉ መንፈስ የሆነው ጌታ በመካከላቸው መኖሩን አያስተውሉም ነበር እሩቅ ሰማይ ላይ ቁጭ ያለ ስለሚመስላቸው ማንም የለም ብለው እ/ርን ያሙታል እሱ መንፈስ ነውና ህያውም ነውና ከነሱጋር እንዳለ ግን ማንም አላስተዋለም።የሚያስተውሉት በሆነ መልክ ሲገለጥ ነበረና። እሱ ግን እዛው ከነሱጋር ስለሆነ እንዲህ አላቸው በጆረዮ አማችሁኝ፡ እኔ ሕያው ነኝና በጆሮዬ እንደ ተናገራችሁት እንዲሁ በእውነት አደርግባችኋለሁ።
“ኦሪት ዘኍልቍ 14/27 የሚያጕረመርምብኝን ይህን ክፉ ሕዝብ እስከ መቼ እታገሠዋለሁ? በእኔ ላይ የሚያጕረመርሙትን የእስራኤልን ልጆች ማጕረምረም ሰማሁ። 28 እንዲህ በላቸው፦ እኔ ሕያው ነኝና በጆሮዬ እንደ ተናገራችሁት እንዲሁ በእውነት አደርግባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤”
መንፈሳዊው ነገር ረቂቅ ነው ነፋስ ወደሚወደው ይነፍሳል፤ ድምፁንም ትሰማለህ፤ ነገር ግን ከየት እንደ መጣ፣ ወዴት እንደሚሄድም አታውቅም፤ የመንፈስም ነገር እንደዚሁ ነው። የእ/ር ቃል ሲነግረን የነፋስ መንገድ እንዴት እንደ ሆነች አጥንትም በእርጉዝ ሆድ እንዴት እንድትዋደድ እንደማታውቅ፥ እንዲሁም ሁሉን የሚሠራውን የእግዚአብሔርን ሥራ አታውቅም። ይላል።
መንፈሳዊው ነገር ልናስተውለው ከምንችለው በላይ ታላቅ ነውና እርሱ ወዶ የገለጠልን ብቻ እናስተውላለን። የሕያዋን ሁሉ ነፍስ እና የሰውም ሁሉ መንፈስ በእጁ ናትና በሰው ውስጥ መንፈስ አለና ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ማስተዋልን ይሰጣል።
ክፍል ሁለት ይቀጥላል ወንድም ቢኒ
እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን?