ጥያቄ ና መልስ የሃብታሙ ሰውና አልአዛር ምሳሌ ፍቺ ላይ


የሃብታሙ ሰውና አልአዛር ምሳሌ ፍቺ

የሉቃስ ወንጌል 16/19 ቀይ ልብስና ቀጭን የተልባ እግር የለበሰ አንድ ባለ ጠጋ ሰው ነበረ፥ ዕለት ዕለትም እየተመቸው በደስታ ይኖር ነበር።

20 አልዓዛርም የሚባል አንድ ድሀ በቍስል ተወርሶ በደጁ ተኝቶ ነበር፥

21 ከባለ ጠጋውም ማዕድ ከሚወድቀው ፍርፋሪ ሊጠግብ ይመኝ ነበር፤ ውሾች እንኳ መጥተው ቍስሎቹን ይልሱ ነበር።

22 ድሀውም ሞተ፥ መላእክትም ወደ አብርሃም እቅፍ ወሰዱት፤ ባለ ጠጋው ደግሞ ሞተና ተቀበረ።

23 በሲኦልም በሥቃይ ሳለ አሻቅቦ አብርሃምን በሩቅ አየ አልዓዛርንም በእቅፉ።

24 እርሱም እየጮኸ፦ አብርሃም አባት ሆይ፥ ማረኝ፥ በዚህ ነበልባል እሣቀያለሁና የጣቱን ጫፍ በውኃ ነክሮ መላሴን እንዲያበርድልኝ አልዓዛርን ስደድልኝ አለ።

25 አብርሃም ግን፦ ልጄ ሆይ፥ አንተ በሕይወትህ ሳለህ መልካም እንደ ተቀበልህ አስብ አልዓዛርም እንዲሁ ክፉ፤ አሁን ግን እርሱ በዚህ ይጽናናል አንተም ትሣቀያለህ።

26 ከዚህም ሁሉ ጋር ከዚህ ወደ እናንተ ሊያልፉ የሚፈልጉ እንዳይችሉ፥ ወዲያ ያሉ ደግሞ ወደ እኛ እንዳይሻገሩ በእኛና በእናንተ መካከል ታላቅ ገደል ተደርጎአል አለ።

27 እርሱም፦ እንኪያስ፥ አባት ሆይ፥ ወደ አባቴ ቤት እንድትሰደው እለምንሃለሁ፤ አምስት ወንድሞች አሉኝና፤

28 እነርሱ ደግሞ ወደዚህ ሥቃይ ስፍራ እንዳይመጡ ይመስክርላቸው አለ።

29 አብርሃም ግን፦ ሙሴና ነቢያት አሉአቸው፤ እነርሱን ይስሙ አለው።

30 እርሱም፦ አይደለም፥ አብርሃም አባት ሆይ፥ ነገር ግን ከሙታን አንዱ ቢሄድላቸው ንስሐ ይገባሉ አለ።

31 ሙሴንና ነቢያትንም የማይሰሙ ከሆነ፥ ከሙታንም እንኳ አንድ ቢነሣ አያምኑም አለው።

 

ክፍል አንድ: ብራዘር በጌታ ፍቅር ሙሉ ሰላም ይሁን። እ/ር የሰላም እንጂ የሁከት አምላክ አይደለም። “መጽሐፈ መሣፍንት 6/24 ..እግዚአብሔር ሰላም ነው።”  እኔም እንዳተ የኔን እየሱሴን ማ አላስነካም ብየ እንደ ጴጥሮስ የሰውን ጆሮ በሰይፍ የምቆርጥበትን ዘመን አስታወስከኝ እኔም አልፌበታለሁ። ጌታም ለልቤ በቃሉ ብርሃን ተው ሰይፍህን ወደ ሰገባው መልስ አልያ ሰይፍ የሚያነሳ በሰይፍ ይጠፋል የሚለኝን ትዝታየን ቀሰቀስክብኝ።

የሆነ ሆነና በበሰሉት መካከል ጥበብን እንናገራለን ባልበሰሉ መካከል ግን የሀይል አገልግሎት የግድ ነው። እንደበሰሉ የእ/ር ልጆች ሁላችንም ለመተናነጽ የሚማር ልብ አለን ሰው ይናገረው እ/ር ይናገር እንጂ ። አሜን ነው። ስለዚህ በበጎ ህሊና ነገሮችን መመርመር እ/ር ወደ እውነት ሁሉ ከመራን መልካም ካልሆነም መልካም ያለንን ጠብቀን መቀጠል ነው።

ብዙ ጠቃሚ ነጥቦችን ነካክተሃል  በጌታ ግዜ የሚብራሩ ሊኖሩ ይችላሉ። ጌታ ቢፈቅድና ቢረዳኝ ግን አንዱን ለመመለስ እሞክራለሁ የቀሩት ሃሳቦች የብዙ ወንድሞችና እህቶች ዘንድ በየጊዜው ተነስተዋል እኔም ከዚህ በፊት ተጠይቄ ወይም በትምህርት መልክ ስለፃፍካቸው የተሰማው ሰው ካለ ማንበብም ያለማንበብ መብቱ ነው። በማንበው ውጥ ሃይል አለ እውቀት መልካም ነው እውቀት ሁሉ ግን እውነት ወይም ብርሃን አይደለም በመንፈስ ምስክርነት ላይ ከቆምን ግን ተጠቃሚዎች እንሆናለን።

ዛሬ ለማየት የፈለኩት ግን ደጋግመህ ካነሳካቸው ዋናው ”የሃብታሙ ሰውና አልአዛር”ን ፍቺ ነው።

የተነበበው የሃብታሙ ሰውና አልአዛር ጹሁፍ የዘልአለም ስቃይ ትምርት ለማስተማር ተቀዳሚ ሆኖ የሚቀርብ ቲዮሎጂካል ፓስፖርት ሆኖ የሚያሳዩ መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው።

የጠቢብ መንገዱ አካሄዱን ያስተውል ዘንድ ነውና በውኑ” የሃብታሙ ሰውና አልአዛር” ምሳሌ ነው ወይስ እውን ታሪክ?ጌታ ከረዳን እንዳልበሰሉ ሰዎች እኔ የጳውሎስ ነኝ፥ እኔስ የአጵሎስ ነኝ፥ እኔ ግን የኬፋ ነኝ፥ እኔስ የክርስቶስ ሳንል ማንንም ሳንወግን በሰከነ መንፈስ ድጋሚ እውነቱን ለማየት እንሞክር ዘንድ በጌታ ፍቅር እጠይቃለሁ በእውቀት ልዩነት ወንድሜን እህቴን ከማጣ በክርስቶስ ፍቅር የመንፈስን አንድነት በመጠበቅ ሁላችንም እ/ር ወዳየልን ብስለት ያመጣናል ብየ አስባለሁ።

በቅድሚያ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ በአገልግሎቱ ሁሉ በምሳሌ ማስተማሩ ማወቅ በራሱ በረከት ነው። “የማቴዎስ ወንጌል13/34-35 ኢየሱስም ለሕዝቡ ይህን ሁሉ በምሳሌ ተናገረ፤በነቢዩም፦ በምሳሌ አፌን እከፍታለሁ፥ ዓለም ከተፈጠረ

ጀምሮ የተሰወረውንም እናገራለሁ የተባለው ይፈጸም ዘንድ ያለ ምሳሌ አልተናገራቸውም።” ይህንንም በነብዩ ዳዊት ላይ ሆኖ መንፈስ በመዝሙር 77/2 ላይ አስቀድሞ ተናግሮት ነበረ። እንደ ምናስተውለው ትንቢቱ ፍፃሜ ያገኘው ጌታ ያለ ምሳሌ ስላስተማረ ነው።

በዚህም መሰረት ጌታ ከ 41 በላይ ምሳሌዎችን ተናግረዋል የዘልአለም ስቃይ ሰባኪዎች ግን ነጥለው እውነተኛ ታሪክ ነው የሚሉት የሃብታሙ ሰውና አልአዛር ምሳሌን ነው።

ክፍል ሁለት

ጌታ ከተናገራቸው ምሳሌዎች ለማስታወስ ያህል። ከእንቅብ በታች ያለ መብራት፤ የሰናፍጭ ቅንጣት፤ ልባምና ሰነፍ አናፂዎች፤ በአረጀ ልብስ ላይ አዲስ እራፊ፤  በአረጀ አቅማዳ ላይ አዲስ ወይን፤ ዘሪና የመሬት አይነቶች፤ የተሸሸገ እርሾ ፤ በባህር ላይ የተጣለ መረብ፤ የጠፋ በግ፤ምህረት የማያደርግ ባርያ፤ አስሩ ቆነጃጅት፤ በጎችና ፍየሎች፤ ደጉ ሳምራዊ፤ የጠፋ ድሪም፤ ወዘተ……

ዶክትሪናቸውን ለማጽደቅ ሁሉም የዘልአለም ስቃይ ሰባኪዎች  ነጥለው እውነተኛ ታሪክ ነው ብለው የሙጭኝ የሚሉት የሃብታሙ ሰውና አልአዛርን ምሳሌን ነው።

እውነታው ግን ጌታ ከ 41 በላይ ምሳሌዎችን ተናግረዋል አንዳቸውም በእውን የተፈፅሙ የተከሰቱ ታሪኮች አልነበሩም። ተምሳሌትን ምሳሌነቱን ትተን ወደ እውነተኛ ታሪክ ስንከረብተው ወይም ስንገለብጠው ተምሳሌነቱ ይጠፋል።

ሁላችንም እንደምናውቀው ምሳሌ ወይም ተምሳሌት የሚነገረው በጥሬው ካለው ትርጉሙ ውጪ ሌላ ነገርን የሚወክል ቃል ወይም ሃረግ ነው። ለምሳሌ አንበሳ የጀግና ምሳሌ ነው፤ በግ/እርግብ የየዋህነት የንጽህና ምሳሌ ነው።

በተፃራሪው ታሪክ ማለት ደግሞ ባለፉት ዘመናት እውን የነበሩ ክስተቶች ትውፊት፤ የሚዘገብ ክንዋኔ፤ ለምሳሌ ቀድሞ የነበረ ወግ፤ ጀብድ፤ ጀግንነት፤ የሃገር ኩራት፤ ወዘተ….ማንኛውም የሚያኮራ ይሁን አሳፋሪ ክስተት ሁሉ በዘመኑ ባለ ትውልድ እንደ “ነበረ” የሚታሰብና የሚነገር የሚዘገብ የአላፊ ጊዜ “ክስተት” ታሪክ ይባላል።

ጌታ እየሱስ በየትኛውም ቦታ ለፈሪሳውያን ይሁን ለህዝቡ ሲያስተምር ያለ ምሳሌ ሲያስተምር አታዩም። ምሳሌዎቹ ግን ብዙ ገፅታ ሊያሳዩ ይችላሉ። የአላፊ ግዜ ፤ የወቅቱ ሁኔታ ፤ ደግሞም የወደፊቱን የሚያመለክቱ ትንቢታዊ ሊሆኑ ይችላሉ።

እንደበሰሉ ልጆች ማስታወስ ያለብን በቀድሞ ዘመን መጽሐፍ ቅዱስ በዘመናችን እንዳለው በጥራዝ መልክ በቁጥር ከመካፋፈሉ በፊት በብራና መልክ የተፃፈ ወጥ ጹሁፍ እንደ ነበር እናውቃለን። ዋናው ፁሁፍ [ኦርጂናሉ] ትርጉም ያልሆነው ማለቴ ነው አሮጌው ኪዳን በብራና መልክ ወጥ ጹሁፍ ሆኖ በምእራፍ ሳይከፋፈል ከ1400-400 አመተ ክርስቶስ ልደት በፊት በልዩ ልዩ ቦታዎች አርባ በሚህሉ ፀሓፊዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተፃፈ።

አዲስ ኪዳን ደግሞ ከጌታ ውልደት ቡሃላ ከ40-96 አመተ ምህረት በስምንት ሰዎች ፀሓፊዎች እንዲሁ  በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው በብራና መልክ ወጥ ፁሁፍ ሆኖ በቁጥር በምእራፍ ሳይከፋፈል ተፃፈ። በ1560 ጄኔቫ መጽሓፍ ቅዱስ በመባል የሚታወቀውን አንድ ትርጉም የሊቃውንት ቡድን በጄነቭ ሆነው ሰሩ። ሁለተኛ እትሙም በ1652 ታተመ።

ይህ ነበረ የመጀመርያው ከእንግሊዝኛ ትርጉሞች በብራና መልክ ወጥ ጹሁፍ የነበረውን መጽሃፍ ቅዱስ ለአንባብያን እንዲመች በምእራፍና በቁጥር ተከፋፍሎ የተሰራው። በቁጥር በምእራፍ ከተከፋፈለ ቡሃላ እስከ 2000ሺ እ.ኤ.አ. በነበረው ጥናት መሰረት፡  መጽሃፍ ቅዱስ በሙሉ ወይም በከፊል ከ2100 ቋንቋዎች በላይ ተተርጉመዋል።

ክፍል ሶስት

መልካም : ታሪካዊ ሂደቱን ካስተዋልን ዘንዳ ጌታ እየሱስ ከምእራፍ 15 ጀምሮ እስከ ምእራፍ 16 ድረስ ተከታታይ አምስት ምሳሌዎችን ተናግረዋል። እነዚህ አምስት ተከታታይ ምሳሌዎች በብራና ፁሁፍ ሳሉ በምእራፍ ያልተከፋፈሉ በአንድ ስብከቱ ጊዜ የተናገራቸው በአንድ ወጥ ፁሁፍም የሚገኙ ምሳሌዎች ናቸው።  የሃብታሙና የአልአዛር ምሳሌም አምስተኛው ምሳሌ ነው። እናስተውል

የሉቃስ መጽሓፍ እንደ ሌሎች መጽሓፍት ሁሉ እስከ ተካፋፈለበት ቅጽበት ድረስ የተያያዘ ነበረ። የሚገርመው የዘልአለም ስቃይና ፍርድ ሰባኪዎች አራቱን ምሳሌዎች አድርገው ይወስዱና አምስተኛው ላይ ሲደርሱ እውነተኛ ታሪክ ነው ዘራፍ! ይላሉ።  ይህንም የሚያደርጉት ምንም እንካን እ/ር በእቅዱ ፍፁም የሆነ ቢሆንም, አሁን እንካ ከ6 ቢልዮን ህዝብ በላይ አለ ዓስቡት እንግዲህ ፍቅር ብለው የሚሰብከት እግዚያብሄራቸው አለም ከተፈጠረ ጀምሮ ያለውን አብዛኛውን ህዝብ ለዘልአለም በእሳት ይቀቅለዋል ድንቄም ፍቅር።

ይህን ስብከታቸውን ለማጽደቅ በእ/ር አጀናዳ ላይ ማለትም እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ

እንደ እርሱ አሳብ፥ በክርስቶስ ለማድረግ ያቀደውን እንደ ወደደ እንደአሳቡ፥ የፈቃዱን ምሥጢር እንዳስታወቀን በዘመን ፍጻሜ ሊያደረግ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ቢሆንም ይህን ለማረግድ አቅሙ የለውም ብለው የማይወሰነውን የእስራኤል ቅዱስን እንደ እስራኤላውያን ስለ ሚወስኑት የአምልኮ መልካ ያሳዩ ና ሃይሉን ግን ይክዱታል።

ኅይል ሁሉ ግን የእ/ር መሆኑን ማን በነገራቸው። ወደ ሰማይ ቢወጡ፥ ወደ ሲኦልም ቢወርዱ፥

እ/ር በዚያ እንዳለ ባስተዋሉ “መዝሙረ ዳዊት 139/8 ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ ነህ፤ ወደ ሲኦልም ብወርድ፥በዚያ አለህ።”

የመጨረሻው ጠላይ የሚደመሰሰው የሞትና የሲኦልም መክፈቻ ፊልሙ ተፈፀመ የሚልበት መዝጊያ መደምሰሻ በእጁ እንዳለ ማን በነገራቸው  “የዮሐንስ ራእይ1/18 ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።” “1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15/26 የኋለኛው ጠላት የሚሻረው ሞት ነው፤” የእ/ር ፍርዱ ጽድቅን ለማስተማር እንደ ሆነስ ባስተዋሉ። “ትንቢተ ኢሳይያስ 26/9 ፍርድህን በምድር ባደረግህ ጊዜ በዓለም የሚኖሩ ጽድቅን ይማራሉና”

 

ክፍል አራት :*የሃብታሙ ሰውና አልአዛር ፍቺ

ወደ አንካሩ ሀሳብ ወደ ሃብታሙ ሰውና አልአዛር እንመለስና እንዳንረሳ የምናይ ያለነው ትርጉሞች በብራና መልክ ወጥ ጹሁፍ የነበረውን መጽሃፍ ቅዱስ ለአንባብያን እንዲመች በምእራፍና በቁጥር ተከፋፍሎ ከመሰራቱ በፊት መሆኑን አንርሳ። አስተውሉ ተያያዥ ምሳሌዎችን ሁሉ “ይህንም ምሳሌ ነገራቸው እንዲህ ሲል፦”

“የሉቃስ ወንጌል 15/1 ቀራጮችና ኃጢአተኞችም ሁሉ ሊሰሙት ወደ እርሱ ይቀርቡ ነበር።2 ፈሪሳውያንና ጻፎችም፦ ይህስ ኃጢአተኞችን ይቀበላል

ከእነርሱም ጋር ይበላል ብለው እርስ በርሳቸው አንጐራጐሩ።3 ይህንምምሳሌ ነገራቸው እንዲህ ሲል፦”

 

ምሳሌዎቹም እነዚህ ናቸው በተከታታይ ስናስቀምጣቸው መቶ በግ የነበረው ሰው፤ ከዚያም “ወይም” የሚለውን አያያዥ ቃል ተጠቅሞ አስር ድሪም ያላት ሴት፤ 3ኛው ምሳሌ ደግሞ  “እንዲህም አለ” የሚለውን አያያዥ ቃል ተጠቅሞ ለጠፋው ልጅ የአባትን ልብ የሚያሳየው  ሁለት ልጆች ስለ ነበሩት አባት። 4ኛው ምሳሌ ደግሞ “ደግሞም” የሚለውን አያያዥ ቃል ተጠቅሞ መጋቢ የነበረው አንድ ባለጠጋ ሰው ፤

ይህንንም ሁሉ ሰምተው ፈሪሳውያን ያፌዙበት ነበር። “የሉቃስ ወንጌል 16/14 ገንዘብንም የሚወዱ ፈሪሳውያንይህን ሁሉ ሰምተው ያፌዙበት ነበር።”

ጌታም ከገሰፃቸው ቡሃላ እንዲህም አላቸው፦ ተያያዥ ቃል ተጠቅሞ “የሉቃስ ወንጌል 16/15 እንዲህም አላቸው፦ራሳችሁን በሰው ፊት የምታጸድቁ እናንተ ናችሁ፥ ነገር ግን እግዚአብሔር ልባችሁን ያውቃል፤ በሰው

ዘንድ የከበረ በእግዚአብሔር ፊት ርኵሰት ነውና።” ወድያው በዛው የቁጣ መንፈስ እንዳለ  የሃብታሙ ሰውና አልአዛር ምሳሌ ነገራቸው።

ማስተዋል ያለብን ከላይ እንደ ገለጽነው። ምሳሌን ወይም ተምሳሌትን በጥሬው ካለው ትርጉም ዉጪ ሌላ ነገርን የሚወክል ቃል ወይም ሃረግ ነው። በጥሬው ያለውን ትርጉም እንዳለ ከወሰድነው ምሳሌው ተወክሎ የተነገረበት እውነት አናገኘውም።

ጌታ እየሱስ የመንግስትን ወንጌል ለማስረዳት አያሌ ምሳሌዎችን ተናግረዋል የሃብታሙ ሰውና አልአዛር ምሳሌም አንዱ ነው ካልን ና ካስተዋልን ዘንዳ ታድያ ጌታ ምሳሌውን ምንን እንዲ ወክልለት ተናገረው። የሚለውን ማስተዋል አለብን።

ሃብታሙ ሰው ማንን ይወክላል? በደጅ የወደቀው የተገፋና  የሚለምን በቁስል የተወረሰው ድሃ ሰውስ ማንን ይወክላል? ይህ ምሳሌ ከሞት ቡሃላ ሚሽነሪ ሳይጀመር በፊት የጌታን አዳኝነት ሳይሰሙ የሞቱ እና ሰምተውም ጌታን ያለተቀበሉ ሁሉ ከሞት ቡሃላ የሰዎች እጣ ፈንታ በሲኦልና በመንግስተ ሰማያት ምን እንደ ሚመስል የተነገረ አይደለም። ነገር ግን ይቃወሙ ለነበሩት የህግ መምህራን ለፈሪሳውያንና ለሰቁቃውያን የተነገረ ነበረ።

ሃብታሙ ሰው ለምን ጠፋ? ድሃውስ ለምን ዳነ?  በውኑ ሰው ሃብታም ወይም ቲጃር በመሆኑ ወደ ሲኦል የሚያስወርድ ከሆነስ በመጀመርያ መጨነቅ ያለባቸው ህይወትን ሳይሆን የብልፅግና ሰባኪዋችና በብልጽግና ለመኖር የሚራራጡት የብልጽና ወንጌል ሰባኪዎች ዋንኛዎቹ ናቸው።

በመጽሓፍ ስታስተውሉ ግን ሃብታም መሆን በራሱ ሃጥያት አይደለም ። ገንዘብ በራሱ ሳይሆን ገንዘብን መውደድ [የገንዘብ ፍቅር] ነው የክፋት ሁሉ ስር። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 6/10 ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉሥር ነውና፥

 

በመጽሐፍ ስታስተውሉ ሃብታም ሆነው እ/ርን ያከበሩ በገዛ ዘመናቸው የእ/ርን ፈቃድ አገልግለው የለፉ አሉ። እዮብ፤ አብርሃም፤ ይሳቅ፤ ያቆብ፤ ዮሴፍ፤ ዳዊት ወዘተ…. የባረካቸውም እራሱ እ/ር ነበረ። እነዚህ ሁሉ የጥበባቸው መጀመርያ እ/ርን መፍራት ስለነበር ከክፋት የራቁ ነበሩ።

የልባቸው የመጀመርያ ክፍል ወይም መሃከለኛ እራሱ እ/ር ነበረ በተቃራኒው ሃብት አግኝተውም አይናቸው ወደ ከንቱነት ያዘነበለ ልባቸው ወደ ስስት ያዘነበለ እ/ር  ሳይሆን ገንዘብን መውደድ ተጠናውታቸው እ/ርን ሳያከብሩ ያለፉ አሉ።

ክፍል አምስት

ሃብታሙ ሰው በምሳሌው ስታስተውሉ የአብርሃም ዘር ነበር። በሲኦል ሆኖ እንካን የዘሩን ምንጭ አልረሳም። “አብርሃም አባት ሆይ “ እያለ ሲማጠን ታያላችሁ፤ ሃብታሙ ሰው “ሀብታሙ ሰው ሃምራዊና ቀጭን በፍታና የለበሰ ነበረ” ሃምራዊ በመጽሐፍ ቅዱስ የንጉሳዊ መአረግ ልብሰ መንግስት ነው። ሃምራዊ የሚለብሱት መሪዎች ነበሩ።、ቀጭን በፍታ የሚለብሱትም የክህነት ስልጣን ከእ/ር የተሰጣቸው ነበሩ። ሃብታሙ ሰው የመንግስቱ ቅሪት መሆኑ ያመለክታል። ሃብታሙ ሰው ማንን ያመለክታል?

ሃብታሙ ሰው የሚያመለክተው የአይሁድ ወይም ከእስራኤል ቤት ህዝብን ነው። የአይሁድ ህዝብ ቀጭን በፍታ የሚለብስ ህዝቡ ሁሉ ከምድር ህዝብ ተለይቶ  “የካህናት መንግሥት” ሊሾም የተጠራ ህዝብ ነው። “ኦሪትዘጸአት 19/6 እናንተም የካህናት መንግሥት የተቀደሰምሕዝብ ትሆኑልኛላችሁ።”

ሃብታሙ ሰው ህዝቡን ብቻ ሳይሆን በተለይም የበላዮቻቸው የመሪዎቻቸውን የፈርሳውያንና የአይሁድን መንፈስና ባህርይ የሚወክል ነው።

ሃብታሙ ሰው ክፉና ንፉግ ሰውን ያመለክታል። እንደ ተለመደው ክርስቶስን የተቃቃሙትና የሰቀሉትን አይሁድና የበላየቻቻውን የፈርሳውያንና ሰዱቃውያንን ይወክላል።

ይህ ሃብታም ሰው አብርሃምን “አባት ሆይ” ብሎ ሲጠራው አብርሃም ያላቸውን ግኑኝነት “ልጄ ሆይ” በግሪክ Grk. Teknon- offspriing ዘሬ ፤ ሃረጌ ብሎ ሲያናግረው ይስተዋላል። ሃብታሙ ሰው የአብርሃም ዘር ነበር ። ታላቅ የእ/ር መወደድ ያለው ወይም ሞገስ የተሰጠው በሞገስ የጠገበ ብቸኛ ህዝብ ነበር። ህዝቡ ሁሉ ደግሞም የፈርሳውያንና ሰዱቃውያንን ሁሉ  የአብርሃም ዘር በመሆናቸው ይመካሉ።

የአብርሃም ዘር ወይም ልጅነት ብቻ መንግስተ ሰማያት እንደሚገቡ በኩራት ይናገራሉ። በቁጥር  19″ በደስታና በተድላ የሚኖሮ ማእዱም የተትረፈረፈ ነበር።” ብቸኛው የእ/ር ቃል የተሰጠው በየቀኑ በቃሉ መአድ የሚደሰት ህዝብ ነበር። በመንፈሳዊ ማእድ በረከትና ተድላ ጠረጴዛው የሞላና የተትረፈረፈለት ህዝብ ነበር።

 

በበረከት ባለፀጋ ነበረ፤ በምህረት ሃብታም፤ እንደ አይሁድ ህዝብ በእ/ር የተወደደ አልነበረም። የእ/ር ሞገስ ያጠገበው በድል የተከበበ ህዝብ ነበር፤ የሉኡሉ ክብር ያጠገበው፤ ሃብታም ህዝብ ነበረ። ለብቻው ከምድር ህዝብ ተለይቶ ቃል ኪዳን የተሰጠው ሃብታም ህዝብ ነበር።

እ/ር በመካከላቸው ሊያድር የፈቀደ ህዝብ፤ ነብያት የተሰጠው ህዝብ፤ ከበረከቱ ምንም ያልጎደለ ሃብታም ህዝብ። በምድረ በዳ ሳይቀር በመካከላቸው ዳዌ ያልነበረበት በጤና ሃብታም የሆነ ህዝብ ነበር። የእ/ር ህልውና ያልተለየው ሃብታም ህዝብ ነበር። በመውጣቱ በመግባቱ የተባረከ ከመልካም ነገር ያልጎደለ ሃብታም ህዝብ ነበር። በእርግጥም ሃብታሙ ሰው የሚወክለው የአይሁድ ህዝብን ነበር።

እህልና ውሃው የተባረከለት ህዝብ በምድሩም መካንነትና ጭንገፋ የማይሆንበት ህዝብ ፤የዘመኑ ቁጥር የሞላለት ህዝብ፤ በእርግጥም ሃብታሙ ሰው የአይሁድ ህዝብ ነው። የእ/ር ብርቱ እጅ የደገፈው በዘይት የበለፀገ በወይን የበለፀገ የተትረፈረፈ በሃብት ከላይ የተባረከ፤ በትምህርት ሃብታም፤ በእ/ር ቃል ሃብታም በታሪክ ሃብታም። በወግና በባህል ሃብታም መንግስትነት ከእ/ር የተሰጠው ሃብታም እንድ ብቻውን አይሁድ ህዝብ ነበረ።

የእ/ር መንግስት ከእነሱ እስከ ተወሰደበት ጊዜ ድረስ የእ/ር መንግስት ከሌሎች ህዝብ በተለየ መንግስንነት የተሰጠው ሃብታም ህዝብ ነበረ።

“የማቴዎስ ወንጌል 21/43 ስለዚህ እላችኋለሁ፥የእግዚአብሔር መንግሥት ከእናንተ ትወሰዳለች ፍሬዋንም ለሚያደርግ ሕዝብ ትሰጣለች።”45 የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ምሳሌዎቹን ሰምተው ስለ እነርሱ እንደ ተናገረ አስተዋሉ፤46 ሊይዙትም ሲፈልጉት ሳሉ ሕዝቡ እንደ ነቢይ ስላዩት ፈሩአቸው።”

በዛው በሃብታሙ ሰውና አልአዛር ምሳሌ መጨረሻ ላይ ጌታ እንደተናገረው ከልባቸው ድንዳኔ የተነሳ እየሱስ ከሙታን አንዱና ቀዳሚው ሆኖ ቢነሳም አላመኑም።የሉቃስ ወንጌል 16/31 … ከሙታንም እንኳ አንድ ቢነሣ አያምኑም አለው።

ክፍል ስድስት [የመጨረሻው]

የሃብታሙ ሰው ተቃራኒ በውጪ የተጣለው አልአዛር ነው። አልአዛር የሚያመለከተው “አህዛብን” ነው። ከእ/ር ቃል ኪዳን ውጪ ያለ ቃልኪዳን የሚኖር መንፈሳዊ በረከት ፈጽሞ የሌለው። መንፈሳዊ ርሃብ የጠበሰው መንፈሳዊ ምግብ [የእ/ር ቃል] ከሃብታሙ ሰው ከጠረቤዛው የወደቀውን ትርፍራፊ ለመቃረም በተስፋ የሚመኝና የሚለምን ሆኖም ማንንም የማያቀምሰው። ብቸኛው መጽናናቱ ከሌሎች ውሾች[አህዛብ] ብቻ የሆነ። ይህ ቃል ከጌታ እየሱስ ቃል ተረጋግጠዋል።

የማቴዎስ ወንጌል 15/22 እነሆም፥ ከነናዊት [ከአህዛብ መካከል የሆነ ህዝብ] ሴት ከዚያ አገር ወጥታ፦ ጌታ ሆይ፥የዳዊት  ልጅ፥ ማረኝ፤ ልጄን ጋኔን ክፉኛ ይዞአታል ብላጮኸች።23 እርሱ ግን አንዳች አልመለሰላትም። ደቀ መዛሙርቱምቀርበው፦ በኋላችን ትጮኻለችና አሰናብታት እያሉ ለመኑት።24 እርሱም መልሶ፦ ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም አለ።25 እርስዋ ግን መጥታ፦ ጌታ ሆይ፥ እርዳኝ  እያለች ሰገደችለት።26 እርሱ ግን መልሶ፦ የልጆችን[የአይሁድ ወይም ከእስራኤል ቤት ]  እንጀራ ይዞ ለቡችሎች(dogs ውሾች)[ለአህዛብ] መጣል አይገባም አለ።27 እርስዋም፦ አዎን ጌታ ሆይ፤ ቡችሎችም (dogs ውሾችም)[አህዛብም]   እኮ ከጌቶቻቸው ማዕድ የወደቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ አለች።28 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ፦ አንቺ ሴት፥  እምነትሽ ታላቅነው፤ እንደወደድሽ ይሁንልሽ  አላት። ልጅዋም ከዚያች ሰዓትጀምሮ ዳነች።

የሃብታሙ ሰውና የአልአዛር ምሳሌ ታላቅ ለውጥ ስፍራውን ሊይዝ እንደሆነ ለማሳየት ነበረ የተናገረው። “ሃብታሙ ሰው” [የአይሁድ ወይም ከእስራኤል ቤት ]  ከሃያሉ እ/ር ፍርድ ስር መውደቁን በአንፃሩም ደግሞ “አልአዛር” [ከቃል ኪዳኑ ውጪ ያሉት አህዛብ] በእ/ር ቃል ሊባረኩ እንደተቃረበ የሚናገር ነበር።

ስለዚህ “ሃብታሙ ሰው” [የአይሁድ ወይም ከእስራኤል ቤት ]  በወቅቱ የመንግስት ልጆች የነበሩት ፍርዳቸውን ተቀበሉ። ይከውም የአይሁድ ህዝብ ጌታን በሰቀሉ ጊዜ “ደሙ በእኛና በልጆቻችን ይሁን” እንዳሉ የሰቀሉት ትውልድ ሳያልፍ በህይወት እያሉ ታይተስ በተባለ የሮማ ጀነራል በ70 A.D.  ኩፍኛ ተመቱ። እዮርሳሌምን አቃጠላት።  ቤተ መቅደሱን አፈረሰ፤ አምልጠው ወደ የአገሩ ከተበተኑት በቀር ታላላቅና ታናሾችዋን ሰቀለ።

 

የመአቱ መራራነትና ታላቅነት የታሪክ አዋቂዎች ሲያስቀምጡት በእዮርሳሌምና በአከባቢዋ የነበረውን ዛፎች ለመስቀል የተጠቀሙበት አልበቃ ስላላቸው በአንድ ግንድ ላይ ብዙ አይሁዶችን ይሰቅሉበት ነበር። ሃብታሙ ሰው [የአይሁድ ቤት] ህዝብ በዚህ ሁኔታ ከመንግስቱ ወደ ውጪ ተጣለ ።

 

ከዛ “አልአዛር” “አህዛብ” በክርስቶስ በመስቀሉ ስራ ወንጌልን ተቀበሉ። ሃብታሙ ሰውና ወንድሞቹ በአይሁድ እምነት ቀሩ። ከዚያን ግዜ ጀምሮ እየተሰቃዩ ነው። ላለፉት 2000ሺ አመታትም “በዚህ እሳት እየተሰቃየን ነው” እያሉነው።

 

“በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው” እስኪሉም ጌታን አያዩትም። ጌታ በሌላ ስፍራ እንደተነበየው   “የማቴዎስ ወንጌል 21/43  ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የእግዚአብሔር  መንግሥት ከእናንተ ትወሰዳለች ፍሬዋንም ለሚያደርግ ሕዝብ ትሰጣለች።”45 የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ምሳሌዎቹን ሰምተው ስለ እነርሱ እንደ ተናገረ አስተዋሉ፤46 ሊይዙትም ሲፈልጉት ሳሉ ሕዝቡ እንደ ነቢይ ስላዩት ፈሩአቸው።” የእግዚአብሔር መንግስት ከነሱ ተወስደ። ላለፉት 2000ሺ አመታትም ለአህዛብ ተሰጥቶ የመንግስቱን ወንጌል አህዛብ እየሰበኩት ነው።

 

አልአዛር[አህዛብ] እራሱን ወደ አብርሃም እቅፍ ተወስዶ አግኝቶታል። ያም ማለት ከአብርሃም ጋር ወደ ተቀራረበ ህብረትና ግኑኝነት ተሰጠው። አይሁድ ጌታን በመቃወማቸው ከተስፋ ሲጎድሉ በአንፃሩ አህዛብ  ለአብርሃም የተገባው የመንፈስ ተስፋ ወራሽ ሆኑ። “ወደገላትያ ሰዎች 3/14 የመንፈስን ተስፋ በእምነትእንድንቀበል፥ የአብርሃም በረከት ወደ አሕዛብ በኢየሱስክርስቶስ ይደርስላቸው ዘንድ።” ወገኖቼ አስተዋላችሁን ተስፋው ምን ነበር? የመንፈስ ተስፋ! ለማን ተሰጠ በክርስቶስ በኩል? ለአህዛብ! ሃሌሉያ!ሰላም ይሁን።

ወንድም ቢኒ

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal