ጥያቄና መልስ በ[ለምን ገናናዋ ቤተክርስቲያን የዘልአለም እና የዘመን ፍቺ አልበራላትም?]


ጥያቄና መልስ በ[ለምን ገናናዋ ቤተክርስቲያን የዘልአለም እና የዘመን ፍቺ አልበራላትም?]

በሌላ ገጽ ስለዚህ ነጥብ በወገኖች መካከል ጠቃሚ ሀሳቦች ተነስተው ነበር ሌሎች የሚያነቡ ሊያነሱት የሚችላቸው ስለሚሆኑ ብየ ኮፒውን አምጥቸዋለሁ።
ወንድም ጃፊ። በአመት አንዴ ያለው የክህነት አገልግሎት ለምን በክርስቶስ ላይ ማለቂያ ኖሮው ይህ ከተባለ?
” ይህም አንድ ጊዜ በዓመት ለእስራኤል ልጆች ስለ ኃጢአታቸው ሁሉ ያስተስርይ ዘንድ የዘላለም ሥርዓት ይሁንላችሁ። እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ አደረገ።

(ኦሪት ዘሌዋውያን 16:34)

ወንድም ደምስ ኒዳ
በቃ ወንድማችማችን ይህ ነው። ሰፋ ያለ ማብራሪያ የለህም።።
ከላይ ወንድም ቢኒያም የፃፈውን ተመልሰህ አንብበው።።።፣ በወፍ በረር አይሁን!!

ወንድም ጃፊ
በቃ ይህ ነው! ዘላለም በአንድ አካል የተወሰ የጊዜ ሂደት ነው፡፡የዘላለም ባለቤት የሆነው ጅማሬም ማብቂያ ያለው በዘላለም አባት ሲወሰን ብቻ ነው፡፡በተረፈ እናንተ ዘላለም ብላችሁ የምትገልጹት ዘላለማዊ ባደረገው ማንነት ላይ ከሆነ እውነት ነው ይህ ማንነት ጅማሬም ፍጻሜም የለውመም ሆኖም እኛ ሰዎች እየተገለጠልን ባለው ምሳሌ ላይ ተመርኩዛችሁ ትምህርት ብትሰጡ የተሻለ ነው ምክንያቱም ገላጩን ዙፋን ለማጋራት በር የሚከፍት አቅጣጫ ላይ ናችሁና፡፡የሚገለጥበት ማንነት ዘላለማዊ ነው ይህ ማንነት አብሮት እስካለ ድረስ ብቻ ይህ አካል ዘላለማዊ ነው የሚገለጠው ግን ማለቂያ የሌለው የዘላለም ባለቤት ነው፡፡ከዚህ ውጪ ሀቅነት ካለው አስረዳኝ

ወንድም ደምስ
ጃፊ በምድር ተወልዶ፣ አድጎ፣ ሲሞት( የጃፊ ዘላለም ነው)!!! ስለዚህ በማይወሰነው እግ/ር ውስጥ፣፣ የተወሰኑ ዘመናት፣እንደ ዘላለም ተረድተናቸዋል። እግ/ር ግን ዘላለማዊ ነው ሲባል( eternal) ከጊዜ በላይ ነው ማለት ነው፣ ጃፊያችን!!

ወንድም ጃፊ
ጃፊ ተወልዶ እንደሚሞት የጊዜ ገደብ ያለው ጉዳይ ነው፡፡ስለዚህ የሚሞት ሰው ዘላለም ኗሪ ነው አይባልም፡፡በመቀጠል እግ/ር ዘላለሙን የሆነ ሰዓት ላይ የሚቋጨው ሌላ ሀይል ስለሌለ የእርሱ ዘላለማዊነት ማለቂያም መጀመሪያም የለውም፡፡የሌላው ዘላለማዊነት ግን ነገሩ በዚያ መንፈስ እስከጸና ድረስ ብቻ ዘላለማዊ ይሆናል፡፡ከዚያ ውጪ ዘላለማዊነቱ የሚያበቃባቸው ሁኔታዎች ስላሉ ማብቂያ የለውም በሚል የምንሰጠው ዴፍኒሽን ፈጣሪን ዋሾ ያስደርገዋል፡፡ለዘላለም ተብሎ ነገሩ ማብቂያን ሲያገኝ እንዴት ነው ለዘላለም ተብሎ ስርአቱ ያበቃው ? ይዋሻል እንዴ ፈጣሪ ሊያስብልብን ነው፡፡ይህ ነው የእኔ መረዳት

ወንድም ደምስ
ዮናስስ በአሳነባሪ ውስጥ ለዘላለም በሱኦል ልብ ያለው። ከአሳንባሪ ሆድ እስኪወጣ፣ከሆነ ያ ነበር ዘላለም።
ይህ ዘላለም አለቀ በቃ፣፣፣፣
እግ/ር ግን ከጊዜ በላይና ከፍ ያለ ነውና መሸ ነጋ የለውምና ይህ ነው፣፣ ዘላለም። ስለዚህ ሁለት አይነት ነው ያልኩህ።።።

ወንድም ጃፊ
መልካም።

ውንድም ደምስ
ምንም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መነሻና መሠረት ሳይኖራቸው በዘልማድና በአፈ ታሪክ ብቻ የተቀበልናቸው፥ መጻሕፍትን እንደ ቤርያን ወንድሞች ሳንመረምር የእምነታችንን መሠረት የጣልንባቸው አያሌ አስተምህሮዎች ሞልተውናል፡፡ እነርሱ ሳያልፉ ትውልዱን እያሳለፉ እውነት የመሰሉና በሰው የተፈለሰፉ ሐሳቦች የመብዛታቸውን ያህል በተቃራኒው ስለ እነዚህ የእግዚአብሔርን ሐሳብ ተከትለው ትውልዱን ያስጠነቀቁና የተቃወሙ ወገኖች አልታጡም ነበር፡፡ ሥራቸው በትውልዱ ተቀባይነት ቢያገኝም ባያገኝም፡፡ ሐሰት ብዙውን ጊዜ ለመስፋፋቱ ፈጣንና ብዙዎች የሚያሳስት ስለ ሆነ በእውነት ላይ እየተሳለቀ የሚጓዘውን ያህል ይጓዛል፡፡ እርሱም በብዙ ትውልድ መካከል በቆየ መጠን እውነት መስሎ ይታያል፡፡ ብዙዎችም ያንን መርምረው መግለጥ አይታደሉም፡፡ ዛሬ መንፈስ ቅዱስ ባበራው ብርሃን ‹‹መታረም የሚገባቸው የቤተ ክርስቲያን ትምህርቶች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጓሜ ይጎድላቸዋል፤ በመገለጥም ይሁን በትርጉም ችግር ወይም ስሕተት አለባቸው›› የሚል ቢነሣ ለሐሰት ጠበቃ የሚቆሙ አይታጡም፡፡ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የገዘፉና ሰዎች ያስተማሯቸው በትውልድም ያስተላለፏቸው ከመጽሐፍ ያፈነገጡ ትምህርቶችንና ትክል ቀኖናዎችን የሐሳትም ዝማሜ ያላቸውን መረዳቶችን ማረም ጭንቅ ነው፡፡ ብዙዎችም ከሐቁ መንገድ ስሕቱን መንገድ መረጡ። እኛም የኋለኞች ጉምቱ የሃይማኖት መምህራን ተልመው ከሰጡን መንገድ ንቅንቅ ላለማለት የማልን ይመስላል። ያነሣነው ይህ ርዕስ ከብዙዎች የተፋለሱ የመጽሐፍ ትርጉሞች መካከል አንዱ ነው። “ዘላለም የማያቋርጥና የማያልቅ ጊዜ ነው፤ መጀመሪያም መጨረሻም የሌለው ነው” የሚለውን ሀቲት አምነን ስናበቃ አሁን ማን ይመልሰን ዘንድ ይቻል? ሲበዛ ጭንቅ ነው።

ይሁን እንጂ ልዑል እግዚአብሔር በዚህ ዘመን ይህንን ለማድረግ ተነሥቷል፡፡ በመጽሐፍም ሆነ በመንፈስ ላይ ከእንግዲህ ለመዋሸት ዕድሉ የለም፡፡ ከጀመርንባቸው ከደኅንነት፣ ከንስሐ… ጀምሮ የተሰጡ የተጭበረበሩ፣ ከፊል፣ ሙሉ በሙሉ ዓላማቸውን ከሳቱ ትምህርቶች ጀምሮ መታረም አለባቸው፡፡ ስለዚህም እያንዳንዱ የቆመበትን ሊፈትሽ ነው፡፡ ያለ ማወቅ ወራት በሁሉ ላይ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም ሰዎች በገዛ መንገዳቸው እንዲሄዱ ትቷቸዋል፡፡ አሁን ሊያነቃን ሲነሣ – ከገዛ መንገዳችን ሲመልሰን ግን የድሮ መንገዳችንና መረዳታችን አይገባንም፡፡ በእግዚአብሔር እየጨመረ የመጣው ብርሃን ያለፉትን መረዳቶች ሁሉ በአዲስ መልክ እንድያናቸው እየተደረግን አይደለምን?

በአንድ ዘመን ማንበብ (በተለይም መጽሐፍ ቅዱስ) የተፈቀደው ለቀሳውስት ብቻ ነበርና ሌላው ሕዝብ ከዚህ የተለከለከለና የተገዘተ ነበር፡፡ ስለዚህ ያ ዘመን የጨለማ ዘመን – የድንቁርና ዘመን – The dark Age ተብሎ ተጠራ፡፡ ማንም ከሚነገረውና ከሚሰማው በቀር መጻሕፍትን ለመመርመር ዕድሉ አልነበረውም፡፡ ዛሬም መልኩን በለወጠ ሁኔታ ተመሳሳይ ነገር እያስተዋልን አንገኛለን፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን አዕማድ መስለው የሚታዩት ብቻ ያሉትን ተቀብለን እንድንኖርና ያንኑ የሚግቱን ወኪሎቻቸው ከዚያ ካበጁት ክልል እንዳናወጣ እየተገዘትን ነው፡፡ ብዙዎችም በዘመናቸው የበራውን ብርሃን – የእውነትን እውቀት እየሰቀሉ ይገኛሉ፡፡ ያሳዝናል! በየዘመኑ ከነበረው የባሕር አውሬ ድርጅታዊ ሃይማኖት ያመለጡና የእምነትን ለውጥ ያመጡ ተሰደዱ እንጂ ተቀባይነት አልነበራቸውም፡፡ ሕይወታቸው ዘርተው አልፈዋልና ተከታዩ ትውልድ ፍሬአቸውን ማጣጣሙ አልቀረም፡፡ ይሄ እንደዚህ መገኘቱ አስደሳች ቢሆንም በተቃራኒው ዛሬም ክርስትና ተቋም ብቻ ሆኖ መንፈሳዊ አውሬ በመሰለበትና ከሚተዳደርበት ሥነ ሥርዓት ውጭ ያለው ሁሉ እየቀለጣጠመ የሚሄድ ይመስላል፡፡ ስለዚህ በዚህ ዘመን ፈተናው የበዛ ነው፡፡ ሐሰትም ሆነ እውነት እኩል የማስተማር ሕጋዊነትም ሆነ መብት በመንግሥት በኩል ቢኖራቸውም እውነት የሚሮጥባቸው ምክንያቶች ግን ተዳክመዋል፡፡ እግዚአብሔር ከእውነት ጋር ቢራመድም የሰዎችን ስሜት በሚኮረኩር መልኩ ግን አይሠራም፡፡ እውነት ራሱን የሚመራበት ግዙፍ ተቋም የለውም፡፡ ግን እንደ ቅንጣት ዘር ነው፡፡ በአካባቢው ያለውን ማዳበሪያ(የበሰበሰ ሐሰት) እየበላ ይበቅላል፡፡ ሐሰት የተስፋፋባቸው መንገዶችና መሣሪያዎች ለእውነት ሲውሉ ብዙም አልታዩም፡፡ ዓለምና ግኝቷ ለእውነት ተስማሚና አገልጋይ ገና አልሆኑም፡፡ እውነት እርሱ ራሱ ክርስቶስ ጌታ ነውና ሁሉን በማሸነፍ እስኪገዛ መፈተኑ – መሰደዱ – መከራ መቀበሉ የታመነ ይሁን፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በዕብራይስጥ ወይም በግሪክ በመሆኑ ስላነሣነው ሐሳብ ወደ እነዚህ ቋንቋዎች መሳባችን አይቀሬ ነው፡፡ በክርስቶስ መንፈስ ጊዜንና ዘመንን እንደሚመረምሩ ቅዱሳን (1ጴጥ.11÷12) እውነትን በልባችን ለማጽናት መጻሕፍትን መመርመር አለብን፡፡ በእርግጥ መጽሐፍ ቅዱስን የእግዚአብሔር ሰዎች በመንፈስ ተነድተው ቢጽፉትም ተርጓሚዎች በአንዳንድ በኩል የተጻፈበት መንፈስ ሳይኖራቸው እንደ መሰላቸው ስላደረጉ ተከታዩ ትውልድ መሳሳቱ አልቀረም፡፡ ታዲያ ጊዜን በተመለከተ ተመሳሳይ ችግር አለ፡፡

ዘላለም በሚለው ቃል ውስጥ የተቋጠረው ሰፊ ሐሳብ ስላልተረዳነውና መገለጡም ስለ ሌለን እግዚአብሔር ጊዜን የተጠቀመበት ዓይነተኛ ዓላማ አልገባንም፡፡ እግዚአብሔር ከጊዜ ውጭ ሆኖና ኖሮ ጊዜን – ዘመንን – ዘላለምን ስለ ፍጥረት ሲያደርግ በዓላማ ነው፡፡ ይሁንና ዘላለም የሚለው ቃል አንድ ውስን ግን ያልታወቀ ዘመን ወይም ጊዜ እንደ ሆነ ታውቁ ይሆን? የዘመንን – የዘላለምን ትክክለኛ ሥርወ ቃሉንና ትርጓሜውን ስንፈልግ በጽርዕ ‹‹aion›› ይሆናል፡፡ የቃሉም ፍቺ አንድ ውስን ክፍለ ጊዜ (a period of time) ማለት ሲሆን በአንድ ሰው ወይም በአንድ ትውልድ የሕይወት ዘመን የማይታወቅ አጭር ወይም ረዥም ሊሆን የሚችል ጊዜ ነው፡፡ ሆኖም ይሄ ክፍለ ጊዜ መጀመሪያና መጨረሻ ያለው ማለት እንደ ሆነ መታወቅ አለበት፡፡ ስለዚሀ ቃል ከግሪኩ ወድያ ዕብራይስጡንም ብናይ ኦላም ‹‹olam›› ይለዋል፡፡ ቃሉ (to hide, keep secret, obscure) ማለት ይሆናል፡፡ ጨምረውም (obscurity) ብለው ተርጉመውታል፡፡ ስለዚህ ኦላም – ዘላለም የሚለው ቃል በውል ያልታወቀ፣ ምሥጢር ሆኖ የተያዘ ድብቅ… ክፍለ ጊዜ ማለት ያክላል፡፡ የዘላለም መጨረሻ አይታወቅ – ግልጽ አይሁን እንጂ ፍጻሜ የሌለው አይደለም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ፡- ‹‹ኦላም – አይዮን – ዘላለም – ለዘላለም – ከዘላለም እስከ ዘላለም…›› በሚሉት ቃላት ምትክ ዘመን – ክፍለ ጊዜ – ለዘመንና ለዘመናት – ከዘመን እስከ ዘመን – ከትውልድ እስከ ትውልድ… በሚሉት ቃላት ተክተን ብንጠቀም ሊሆን የሚችለው ለውጥ ልብ በሉ፡፡ አያስደንቅም?

ወንድም ቢኒንያም
ድንቅ ነው መልእክተኞን የእሳት ነበልባል ያደረገ እግዚአብሔር የሚወደድ ነው።

ወንድም ሙልጌታ ሽፈራው
ዘላለም ሰባት አመት ሺህ አመት ወይም ኢዩቤልዩ ማለት አይደለም ። ዘላለም የቀናት ብዛትና ክምችት በመለኮቱ ፍቃድ የእግዚአብሔር አሳብ የሚከናወንበት ነው።
በእንዲህ መረዳት በምንመጣበት ግዜ በዘላለም ውስጥ ድንቅ በማድረግ የዘላለምን መታደስንና መለወጥን ያደርጋል ።
ለምሳሌ ያህል ሞት የተገለጠበት ዘመንና ወደ እሳት ባህር እስኪጣል ነገር ሁሉ በአመታት አይቆጠርም ….. ለሞት ፍጻሜን ያደርጋል ። መንፈስህን ትልካለህ ይፈጠራሉም
አንተም የምድርን ፊት ታድሳለህ። ይህ እውነት ይፈጸማል የዘመኑ ርዝመት ምን ያህል መሆኑን የሚያውቅ አንድም የለም ።
ዘላለም ስንልም መነሻ አለው ስለዚህም ከ ዘላለም እስከ ዘላለም ይለናል ። ይህንንም ስንመለከት የዘመኑን ርዝመት ማወቅ ለእኛ አልተፈቀደም ግን በእግዚአብሔር አሰራር ከ—-እስከ ተብሏል ።በዚህም ስናይ በዘላለም ላይ ነገራትን የሚፈጽም ፍቃዱንም የሚያከናውን ዘመናትን የሚያድስና አዲስ ነገር የሚያደርግ እግዚአብሔር ነው ።
ዘላለም ስንል የእግዚአብሔርን ችሎታና የማድረግ አቅሙ ሁሌ አዲስ እንደሆነ ነው።
ምድር ግን ለዘላለም ነው ።መክብብ 1

መልሶ ነገር ሁሉ እስከሚታደስበት ድረስ ያለው ዘመን ዘላለም ይለዋል። መደጋገም ሳይሆን እውነትን ለማስረገጥ ….የምድርንም ፊት (Earth crust ) እንደሚታደስ ነው ።
አሁን የምናያቸው ሰማያት እንደ መጎናጸፊያ ይጠቀልላቸዋል…..ስለ ጌታችን አንተ ግን አንተ ነህ አመታቶችህ ከቶ አያልቁም ። ለጌታ የዘመን ዳርቻ የለም ሕያውና ነዋሪ ነው ። ሰማይ ግን ይለወጣል (ይታደሳል )። ጌታም ሁሉን አዲስ ያደርጋል።
ዘላለም የሚለው ለተፈጠሩት እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ ነገር ሁሉ እስከሚታደስበት ግዜ ድረስ ያለው። በሰውም መመዘኛ የአመታት ርዝመት ገደብ ያልተደረገበት ….ጌታ ነገርን ሁሉ በራሱ አሰራር የሚያከናውንበትን ለመግለጽ ነው።

ወንድም ጃፊ
ሙሉጌታ በትክክል ገልጸከዋል ተባረክ!

ወንድም ቢንያም
ዘልአለም ጅማሪም ፍፃሜም የለውም ብቸኛው ዘልአለምን ሊገልፀው ና እኩሌታ ገላጭ ሊሆን የሚችል ሀይል እራሱ እግዚአብሔር ብቻ ነው። የግዜ ክምችት የግዜ ንጥረ ነገር በዘልአለም ውስጥ የራሳቸው ቦታ አላቸው እንጂ ጊዜ ተከማችቶ ዘልአለምን ወደ ህልውና ያመጣ አይደለም ግዜ ያለውና የሚሰራው ከሰማይ ወይም ከመንፈስ በታች ላለው ሁሉ እንጂ ከሰማይ በላይ በመንፈሳዊው ግዛት ጊዜ አይሰለጥንም።

ወንድም ሙልጌታ
ወንድም
አሁንም በእርጋታ ተመልከት ” ከ—-እስከ የሚለው ምን ማለት ነው ?በሰው የዘመን ቀመር ያልተወሰነ ማለት አይደለምን ?
ግሪኩ እንዱህ እብራይስጡ እንዲያ አለ። ለእኔ ግድ የለኝም ዘለአለም በጥሩ ቋንቋ ጥሩ ትርጉም ባለው ሁኔታ ተጠቅመውበታል።
ስለዚህ ግራና ቀኝ የሚያዘልለኝ ነገር የለም ።
እስከ ዘላለም ። ምን ለማለት ነው። መድረሻን ያመለክታል ።ይህ ግን በሰው ቀመር የተወሰነ አይደለም።
አማርኛችን ሙሉ ነው። በቋንቋ ሚዛን ጎዶሎ የለበትም። ዘለአለም የግዕዝ ቃል ነው።
ጠንቅቀን ካየን ዘላለም የዘመኑ ርዝመት ገደብ ያልተደረገለት ።ልዑል ፍቃዱን ይፈጽማል ።መሻር ያለበት ይሻራል። መደምሰስም ያለበት ይደመሰሳል ።መታደስ ያለበት ይታደሳል።
ምድር ለዘላለም ነው…..አንተ ግን የምድርን ፊት ታድሳለህ።
እስኪታደስ ያለበት የአመታት ክምችት ዘላለም ተብሏል የምድር ፊት ሲታደስ ዘላለምን ሻረው።
ለማንኛውም በእርጋታ ሁሉን ማጥናት መልካም ነው።

ወንድም ቢንያም
ተባረክ ብራዘር: የግሪክ ቃላትን ፍቺ መረዳቱ ፀሓፊው መንፈስ ቅዱስ ያለ ምክንያት እዛ አያስቀምጠው ና በትርጉም ብቻ መመርኮዝ አይቻልም እኔ ለአገሬ ቋንቋ ሁሉ ግድ ይለኛል እኮራበታለሁም የእ/ር ስጦታ ነውና። አሁን ግን ለለእብራይስጡም ለግሪኩም ለአማርኛውም ጠበቃ ከመሆን ኧንፃር ሳይኾን ከእውነት ጋር ያለውን ነው የምናይ ያለነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን ስናይ እራሳቸው አሳታሚዎቹ ብዙዎችን የእንግሊዝኛም ሆኑ የአማርኛችንም ትርጉሞች እደገና ብዙ ታርመው እደገና የሚያትምዋቸው ለምን ይመስልሃል? ኦርጅናል መልክቶች አይደሉም ና ግድፈት ስላለባቸው ነው። ሰው ሲቶረጉም ደግም ቢሳሳት አይደንቅም።

ሳስበው በተለያየ የቋንቌ ዘየ በከፊል አንድ አይነት አሳብ እየተናገርን ያለን ይመስለኛል። ሁለታችንም የእ/ር ሚስጥ ፍፃሜ ጋር በተለያየ እይታ ደርሰንበታል “ከዘልዓለም እስከ ዘልአለም” በአማርኛችን ጥሬውን ወይም ጅንፍሉን ወስደን ካየነው የሰጠከው ፍፃሜ ያስኬዳል። ልክ አንድን ጥሬ የጅንፍሉን ቡና ብትፈለቅቀው የቡና ፍሬውን እደምትይዘው ዋናውን መጠቀሙን ከትርጉም ይልቅ የተሻለ ነው ለማለት ያህል ነው። በትርጉሙ ሳይሆን በዋናው ቃሉ የሚለው ዘላለማዊነትን ወይም ዘላለማዊውን ክብር ተከታተል ሊያመለክት የሚችለውን ፍፃሜ-አልባነትን አያሳይም፤ የሚከተሉትን ሁለት ክፍሎች በማነጻጸር ፍቺውን ያሳየናል በራዕይ 11:15 የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ሆኑ።

በ 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15/24 በኋላም፥ መንግሥቱን ለእግዚአብሔር ለአባቱ አሳልፎ በሰጠ ጊዜ አለቅነትንም ሁሉና ሥልጣንን ሁሉ ኃይልንም በሻረ ጊዜ፥ ፍጻሜ ይሆናል። በዮሐንስ 11:15 ውስጥ ጌታችን, በግሪኩ ጽሑፍ የሚገዛው [Greek “for the ages of the ages”] በአማርኛችን ለዘላለምም እስከ ዘላለም ብሎ ቶርጉሞታል። ግን ስናስተውል በ 1 ቆሮ:15 የእርሱ አገዛዝ እንደ ሚያበቃ ይነገራል። ይሄ የሚነግረን እግዚአብሔር በልጅነት ክብር ወይም እግዚአብሔር እንደ ወልድ አይገዛም ወይም በልጅነት “ከዘመናት እስከ ዘመናት ይነግሣል for the ages of the ages ” የሚለው ሁሉን ከእግሩ ወይም ከስልጣኑ ስር ካስገዛ ቡሃላ ግን ከዚያ ቡሃላ በሰማይም በምድርም የሚታረቅ የለም ሥራው ሲጠናቀቅ እና ሁሉም በክርስቶስ ስልጣን ስር ሲጠቀለል በልጅ ክብር መግዛት ያበቃና ያስረክባል እግዚአብሄር አባትም ሁሉን በሁሉ ይሆናል።

የዘልአለም፡ ፍፃሜ-አልባ ወይም የማይጠፋው ትርጉም በመጽሓፍ የተጠቀሰው አስታራቂ ሃሳብ ሊሆን የሚችለው 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1/3-5 ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም [incorruptible, and undefiled, and that fadeth not away,]ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል።

ሌላው በወደ ሮሜ ሰዎች 1/20-21 የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም [God’s “perpetual” or “imperceptable” power and Godhead, one being unable to see to the end of it! ]ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና፤። ሰላም ይሁን።

ወንድም ሙልጌታ
Binyam TA
ወንድም ተባረክ አሳብህን ተረድቼዋለሁ። ጠቃሚ መልክት ነው።እታነጽበታለሁ
ጌታ ይባርክህ።
ወንድም ደምስ ኒዳ!!
በጣም የሚገርምና ግልጽ በሆነ መንገድ ወንድሜ ቢናያም!! አስቀምጠሃዋልና ይብዛልህ እላለሁ።
ወንድም ቢንያም
አሜን ነው።

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal