May 24, 2012
Posted on May 24, 2012
Brother Binyam T. Alemayehu
agreement with God ከእ/ር ጋር መስማማት
በሰው ደረጃ ስናስተውል ቃሉ ሲያስስተምረን “ትንቢተ አሞጽ 3:3 በውኑ ሁለት ሰዎች ሳይስማሙ በአንድነት ይሄዳሉን?
Amos 3:3 Can two walk together, except they be agreed?” ሲል ሁለት ሰዎች በአንድነት ሊሄዱ የሚችሉት በቅድሚያ ከተስማሙ እንደሆነ ያስተምረናል።
“መጽሐፈ ምሳሌ 1:33 የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል።
Prov 1፡33 But whoso hearkeneth unto me shall dwell safely, and shall be quiet from fear of evil.” ጌታን መስማት በእርጋታ እድንቀመጥ ብቻ ሳይሆን ምንያት የሚሆነን ከመከራ ስጋትም ነጻ የወጣ ህይወት እንድንኖር ያጸናናል።
በራእይ መልእክት የድል ነሺዎች ሃይል መንፈስ የሚናገረውን መስማታቸው እንደሆነ ያስተምረናል። “ዮሐንስ ራእይ 2፡7 መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት ዛፍ እንዲበላ እሰጠዋለሁ።” ድል ነሺ ጌታን ሰምቶ ከእ/ር ጋር የሚስማማ ነው። ወደ ልጁ ህብረት ከጠራን እ/ር ጋር መስማማት አይነተኛ ነገር ነው።
ጌታ እየሱስ ከስጋ ወደ መንፈስ ሊመራን ነው የመጣው። “2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡16 … ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም።” አዎን አሁን 33 ½ አመት በስጋ ውስጥ ተዎስኖ እደነበረው አይደለም ህይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነዋል:: “1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15፡45 …ኋለኛው አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ።” ደግሞም ከሰማያት ሁሉ በላይ አልፎ ሁሉን ሞልቶታል በስጋ ተወስኖ ሁሉ መሙላት አይችልም ወደ መንፈስ ክብሩ ተመልሶ እንጂ። “ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡10 ይህ የወረደው ሁሉን ይሞላ ዘንድ ከሰማያት ሁሉ በላይ የወጣው ደግሞ ያው ነው።
Eph 4፡10 He that descended is the same also that ascended up far above all heavens, that he might fill all things.)”
ጌታ እየሱስ ከስጋ ወደ መንፈስ ሊመራን ነው የመጣው ሲባል በሙሴ ህግ በስጋ መገረዝ፡ ቅዱስ ቀናትን መጠበቅ ሰንበትን መጠበቅ፡ ወዘተ ብዙ ነገሮች አካላዊ ግዴታዎች ነበሩ። ጌታ በጠበቀ ሁኔታ በመንፈስ ህግ መጣ በማቴ 5፡6፡7 ሲናገር እንደዚህ ሲባል ሰምታችሃል(በሙሴ ህግ ማለት ነው) እኔ ግን እዲህ እላችሃለሁ እያለ ምሳሌን ሰጠ
በሙሴ ማል በክርስቶስ ፈጽመህ አትማል
በሙሴ ጠላትህን ጥላ በከርስቶስ ጠላትህን ውደድ
በሙሴ አትዘሙት በክርስቶስ ወደ ምንጩ ሄዶ በአይንህ አይተህ በልብህ አትመኝ
እያለ ከስጋ ድካም ወደ መንፈስ ብርታት ዘወር እድንል አስተምራል።
እምናወራው ያለው ስለ መንፈሳዊ ነገር እደሆነ እንደ ተሰመረበት ይሁንና ስለ ስምምነት ስናነሳ መንፈሳዊውን ስምምነት በምሳሌ የሚያስስረዱ ሁለት አይነት የጋብቻ ግንኝነቶች እንዳሉ ሳይወሳ መታለፍ የሌለበት ነው።
በገላቲያ4: 22/31
22 አንዱ ከባሪያይቱ አንዱም ከጨዋይቱ የሆኑ ሁለት ልጆች ለአብርሃም እንደ ነበሩት ተጽፎአልና።
23 ነገር ግን የባሪያይቱ ልጅ እንደ ሥጋ ተወልዶአል፥ የጨዋይቱ ግን በተስፋው ቃል ተወልዶአል።
24 ይህም ነገር ምሳሌ ነው፤ እነዚህ ሴቶች እንደ ሁለቱ ኪዳኖች ናቸውና። ከደብረ ሲና የሆነችው አንዲቱ ለባርነት ልጆችን ትወልዳለች፥ እርስዋም አጋር ናት።
25 ይህችም አጋር በዓረብ ምድር ያለችው ደብረ ሲና ናት፤ አሁንም ያለችውን ኢየሩሳሌምን ትመስላለች፥ ከልጆችዋ ጋር በባርነት ናትና።
26 ላይኛይቱ ኢየሩሳሌም ግን በነጻነት የምትኖር ናት እርስዋም እናታችን ናት።
27 አንቺ የማትወልጅ መካን፥ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ፥ እልል በዪና ጩኺ፤ ባል ካላቱ ይልቅ የብቸኛይቱ ልጆች በዝተዋልና ተብሎ ተጽፎአል።
28 እኛም፥ ወንድሞች ሆይ፥ እንደ ይስሐቅ የተስፋ ቃል ልጆች ነን።
29 ነገር ግን እንደ ሥጋ የተወለደው እንደ መንፈስ የተወለደውን በዚያን ጊዜ እንዳሳደደው ዛሬም እንዲሁ ነው።
30 ነገር ግን መጽሐፍ ምን ይላል? የባሪያይቱ ልጅ ከጨዋይቱ ልጅ ጋር አይወርስምና ባሪያይቱን ከልጅዋ ጋር አውጣት።
31 ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ የጨዋይቱ ልጆች ነን እንጂ የባሪያይቱ አይደለንም።”
ሐዋሪያው ስለ ሁለት ኪዳኖች በሁለቱ ሚስቶች እንደ ሚመሰሉ ነግሮናል ማለትም አጋርና ሳራ ባሪያይቱና (bondwoman) ነጻ ያልሆነችው ሴትና ጨዋይቱ (freewoman) ነጻይቱ ሴት ማለት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ሁለት የተለያዩ የጋብቻ አይነቶች ነበሩ። ሰውየው ባሪያይቱን ካገባ ያላቸው ግንኝነት የጌታና የባሪያ ነው። እዲህ አይነትዋ ሚስትም ያላት መብት ውስን ሲሆን በቤተሰብ ውሳኔ ውስጥ ምንም ድምጽ የላትም። ባልዋ እድሉን ሊያቀርብ ይችላል ነገር ግን እደዛ እዳያደርግ የተወሰነ ነበረ።
ይህ የአጋር አይነት የጋብቻ ግኑነት ነው። እስራኤል ከእ/ር ጋራ በሲና ተራራ በቃል ኪዳኑ በጋብቻ በተሳሰሩ ጊዜ ያለውንም ያሳያል። ይሄ የአሮጌው ኪዳን ጋብቻ ነው። በዘፅአት 19/5 እስራኤል ለባልዋ ለመታዘዝ መማል ነበረባት። እስራኤልም የእ/ር አገልጋይ ሚስቱ ሆነች። ይሄ መጥፎ አይደለም በዛው አንጻርም እ/ር ከህዝቡጋር ሙሉ ለሙሉ የሚፈልገው ጋብቻ አይደለም። የተሻለ ህብረትን ይሻልና ለዚህም ነበር በአጀንዳው ውስጥ እስራኤልን ሊፈታት እቅዱን ያስቀመጠው።
“ትንቢተ ኤርምያስ 3፡8 ከዳተኛይቱም እስራኤል ስላመነዘረች ስለዚህ ፈትቻታለሁ የፍችዋንም ወረቀት ሰጥቻታለሁ አታላይ እኅትዋ ይሁዳ ግን እንዳልፈራች እርስዋም ደግሞ ሄዳ እንደ ጋለሞተች አየሁ።
Jer 3፡8 And I saw, when for all the causes whereby backsliding Israel committed adultery I had put her away, and given her a bill of divorce; yet her treacherous sister Judah feared not, but went and played the harlot also.” ከዛም በተሻለ ነገር ላይ የተመሰረተውን አዲሱን ኪዳን አደረገ።
አዲሱ ኪዳን የተመሰለው በነጻይቱ ሴት በሳራ ነው። በአዲሱ ኪዳን የተመሰረተው ጋብቻ መታዘዝ በሚለው ሃሳብ ላይ የተመሰረተ አይዳለም። ሁለት የተጋቡ ወንድና ሴት ከተስማሙ እዲታዘዙ መናገር የሚያስፈልግ አይደለም። አንዳቸው አንዳቸው አንድን ነገር እንዲያርጉ በስልጠን የሚያዙበት ምክንያት የለም ስምምነቱ አለና ። የቤተሰብ ስልጣን የሚገለጠው የስምምነት እጥረት በመካከላቸው ካለ ነው።
በዚህ ምንያት እ/ር ድል ነሺ ካልሆኑበቀር ለማግባት ሃሳቡም የለውም። ድል ነሺነው ከእ/ር ጋር ወይም ከጌታ እየሱስ ክርስቶስ ጋር የሚስማማው። ድል ነሺ የጌታን አይምሮ ያውቃል አሊያም እንዲያውቀው ይሻል። የእ/ርን ፈቃድ ሲያገኘውም ከፈቃዱ ጋር ተስማምቶ እራሱን ያገኘዋል። አልያም ከፈቃዱ ጋር ፍጹም አንድ እስኪ ሆን መረዳትን ለመቀበል እስከ መጨረሻው ይሻል። በመንፈሳዊ እድገት የመማር ሂደት ወስጥ በእርግጥም ድል ነሺው የእ/ርን ሃሳብ ቶሎ ላያስተውል ይችላል:: እንደ እ/ር አገልጋይ እ/ርን ይታዘዛል። ሙሉ ግንዛቤን ገና ስላላገኘ ፈቃዱን በማድረግ ብቻ ገና አልረካም የእ/ርን አይምሮ እስኪ ያገኘውና ገብቶት በሙሉ ስምምነት እራሱን እስኪ ያገኘው ወደ ፊት ይዘረጋል።
ከእ/ር ጋር አለመስማማት ምክንያቱ የመረዳት እጥረት ነው። መላው አለምን እ/ር እንደሚያየው ብናየው እ/ር የሚያደርገውን ሁሉለምን እደሚያደረገው ያለመስማማት ባልኖረ ነበር። ችግሩ አለም ሁሉ መለኮት ከሚያየው አካያ አናየውም። ይህ አብ አንድን ሰው ወደ ጌታ እንደ ሳበው በጌታ እንደሆነ የሚገኝ ለውጥ አይደለም። በመንፈስ ሲሞላም በነገር ሁሉ ከእ/ር ፈቃድ ጋር ሙሉ ለሙሉ መስማማቱ ወድያው አይመጣም። ከእ/ር ጋር አብሮ መጔዝን ይጠይቃል አንድ ሰው ከመሬት ተነስቶ የእ/ርን ባህርይ አይበዘብዝም አብሮ ጊዜ ማሳለፍን ይጠይቃል ደቀ መዛሙርቱ ሰዎች ከንግግራቸው የተነሳ ከእየሱስ ጋር እደነበሩ ያወቁት ለሰዎስት አመት ተኩል አብረው በመውጣት በመግባት ባህርዩን በከፊል ስለ ተካፈሉ ነው።
መጽሐፈ ኢዮብ 22
21 አሁንም ከእርሱ ጋር ተስማማ፥ ሰላምም ይኑርህ በዚያም በጎነት ታገኛለህ።
22 ከአፉም ሕጉን ተቀበል፥ በልብህም ቃሉን አኑር፤
23 ሁሉን ወደሚችል አምላክ ብትመለስ፥ ብትዋረድም፥ ኃጢአትንም ከድንኳንህ ብታርቅ፥
24 የወርቅን ዕቃ በአፈር ውስጥ፥ የኦፊርንም ወርቅ በጅረት ድንጋይ መካከል ብትጥል፥
25 ሁሉን የሚችል አምላክ ወርቅና የሚብለጨለጭ ብር ይሆንልሃል።
26 የዚያን ጊዜ ሁሉን በሚችል አምላክ ደስ ይልሃል፥ ፊትህንም ወደ እግዚአብሔር ታነሣለህ።
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1፡19 ….የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ አዎንና አይደለም አልነበረም፥ ነገር ግን በእርሱ አዎን ሆኖአል።
የዮሐንስ ራእይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ። አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው ምስክር፥ በእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው እንዲህ ይላል። ለእ/ር ፈቃድ አሜን እደሆነ እኛንም አሜን ያድርገን።አሜን።
Posted on May 24, 2012
Brother Binyam T. Alemayehu
agreement with God