የፖለቲካ ጉዳይ ውይይት


ከውይይት የተጠቀሰ፤ የተገለጠ ተግሳጽ፣ ከተደበቀ ፍቅር ይሻላል። በቅድሚያ ወንድም ካሳ ስላንተ እ/ር ይመስገን። የክርስቶስ አካልን ስላገለገልከው ለስሙ ላሳየከው ጽኑ ፍቅር አባታችን ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አንዳልሆነ አውቃለሁ ክብር ለስሙ ይሁን። እኔም ብዙዎችም በዚህ የሚስማሙ ይመስለኛል የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋንና እውነትን መንፈስህን ይሙላው።ወደ ጉዳዩ ስንገባ ሁላችንም እንደምናውቀው የተለያዩ አመለካከቶች ላይ ልዩነት በቀደመው ቤተክርስቲያን ላይ ነው የጀመረው ይህ አዲስ ነገር ስላልሆነ እምብዛም እንደማያሰናክለንና እንደማያስደንቀን አምናለሁ። እንዲያውም በሀዋሪያት መካከል በአንዳንዶቹ ዘንድ ልዩነት የታየበት ጊዜ ነበር። የሐዋርያት ሥራ 15:39። ይህ እውነታ በእንዲህ እንደተጠበቀ ሆኖ በዚህ መልክትህ ግን ለመጀመሪያ ጊዜ በ20 አመቶች ስራህ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ሊባል ባይቻልም በመጠን አልስማማም ያልኩት ምክንያት አለኝ። በጸጋ መሸምገል መልካም ነው እጸጋው የተከማቸ ሞገስ የተነሳ ሽማግሌ ሰው የሚናገረው ሁሉ ይሰማል።በንጉሥ ኢዮርብዓም ዘመን በእግዚአብሔር ቃል ታዞ አንድ ወጣት የእግዚአብሔር ሰው ከይሁዳ ወደ ቤቴል መጣ። መሠዊያውንም በእግዚአብሔር ቃል በመቃወም እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር የሰጠውም ምልክት፣ ‘እነሆ፣ መሠዊያው ይሰነጠቃል፤ በላዩም ላይ ያለው ዐመድ ይፈሳል’ ” የሚል ነው።ንጉሥ ኢዮርብዓምም ያ የእግዚአብሔር ሰው በቤቴል መሠዊያ ላይ ጮኾ የተናገረውን ሲሰማ፣ እጁን መሠዊያው ካለበት በመዘርጋት፣ “ያዙት!” አለ፤ ነገር ግን ያች የዘረጋት እጁ ደርቃ ቀረች፤ ሊመልሳትም አልቻለም እንዲሁም ያ የእግዚአብሔር ሰው በእግዚአብሔር ቃል ተመርቶ በሰጠው ምልክት መሠረት መሠዊያው ተሰነጠቀ፤ ዐመዱም ፈሰሰ።ከዚያም ንጉሡ የእግዚአብሔርን ሰው፣ “እጄ ወደ ቦታዋ እንድትመለስ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ለምንልኝ፤ ጸልይልኝም” አለው፤ ስለዚህም የእግዚአብሔር ሰው እግዚአብሔርን ለመነ፤ የንጉሡ እጅ ወደ ቦታዋ ተመለሰች፤ እንደ ቀድሞዋም ሆነች።ንጉሡም የእግዚአብሔርን ሰው፣“አብረኸኝ ወደ ቤት እንሂድ፤ አንድ ነገር ቅመስ፤ ስጦታም አደርግልሃለሁ” አለው።የእግዚአብሔር ሰው ግን ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ግማሽ ሀብትህን ብትሰጠኝ እንኳ፣ አብሬህ አልሄድም፤ እዚህ፣ እንጀራ አልበላም፤ ውሃም አልጠጣም። በእግዚአብሔር ቃል፤ ‘እንጀራ እንዳትበላ፣ ውሃም እንዳትጠጣ፣ በሄድህበትም መንገድ እንዳትመለስ’ ተብዬ ታዝዣለሁና።” ስለዚህም በመጣበት ሳይሆን በሌላ መንገድ ወደ ቤቴል ተመለሰ።በዚያን ጊዜ በቤቴል የሚኖር አንድ ሽማግሌ ነቢይ ነበር፤ ልጆቹም መጥተው በዚያች ዕለት የእግዚአብሔር ሰው እዚያ ያደረገውን ሁሉና ንጉሡንም ምን እንዳለው ለአባታቸው ነገሩት።ለአባታቸው አሳዩት። ከዚያም በአንድ የወርካ ዛፍ ሥር ተቀምጦ አገኘውና፣ “ከይሁዳ የመጣኸው የእግዚአብሔር ሰው አንተ ነህን?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፣ “አዎን እኔ ነኝ” ብሎ መለሰለት። ስለዚህ ነቢዩ፣ “አብረን ወደ ቤት እንሂድና ምግብ ብላ” አለው።የእግዚአብሔርም ሰው እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ተመልሼ ከአንተ ጋር አልሄድም፤ በዚህ ቦታም አብሬህ እንጀራ አልበላም፤ ውሃም አልጠጣም፤ ‘እዚያ እንጀራ እንዳትበላ፣ ውሃም እንዳትጠጣ፣ በሄድህበትም መንገድ እንዳትመለስ’ ተብዬ በእግዚአብሔር ቃል ታዝዣለሁና” አለው። ሽማግሌው ነቢይ ግን፣ “እኔም እኮ እንዳንተው ነቢይ ነኝ፤ መልአክ በእግዚአብሔር ቃል፣ ‘እንጀራ እንዲበላና ውሃ እንዲጠጣ መልሰህ ወደ ቤትህ አምጣው’ ብሎኝ ነው” አለው፤ነገር ግን ውሸቱን ነበር። ስለዚህ የእግዚአብሔርም ሰው አብሮት ተመልሶ በቤቱ በላ፤ ጠጣም።በማእድ ተቀምጠው ሳሉ፣ የእግዚአብሔር ቃል መልሶ ወደ አመጣው ወደ ሽማግሌው ነቢይ መጣ፤ ከይሁዳ ለመጣውም የእግዚአብሔር ሰው፣ “እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፣ ‘የእግዚአብሔርን ቃል አቃለሃል፤ አምላክህ እግዚአብሔር የሰጠህንም ትእዛዛት አልጠበቅህም፤ ተመልሰህ በመምጣት እንዳትበላና እንዳትጠጣ በነገረህ ቦታ እንጀራ በላህ፤ ውሃም ጠጣህ። ስለዚህ ሬሳህ በአባቶችህ መቃብር አይቀበርም’ ” ሲል ጮኾ ተናገረው።የእግዚአብሔርም ሰው በልቶና ጠጥቶ ካበቃ በኋላ፣ ያ መልሶ ያመጣው ነቢይ አህያውን ጫነለት። ሲሄድ ሳለም አንበሳ መንገድ ላይ አግኝቶ ገደለው፤ ሬሳውም በመንገድ ላይ ተጋደመ፤ አህያውና አንበሳውም አጠገቡ ቆመው ነበር። በዚያ ያለፉ ሰዎች ሬሳው በመንገድ ላይ ተጋድሞ፣ አንበሳውም አጠገቡ ቆሞ ስላዩ፣ ሽማግሌው ነቢይ ወዳለበት ከተማ ሄደው ይህንኑ ተናገሩ።ያም ከመንገድ የመለሰው ነቢይ ይህን ሲሰማ፣ “ይህ የእግዚአብሔርን ቃል ያቃለለው ያ የእግዚአብሔር ሰው ነው፤ እግዚአብሔር ባስጠነቀቀው ቃል መሠረት አሳልፎ ሰጥቶት አንበሳ ሰብሮ ገድሎታል” አለ።ከዚያም ነቢዩ ልጆቹን፣ “በሉ አህያ ጫኑልኝ” አላቸውና ጫኑለት። ከዚያም ሄዶ ሬሳው መንገድ ላይ ተጋድሞ አንበሳውና አህያው በአጠገቡ ቆመው አገኘ፤ አንበሳው ሬሳውን አልበላውም፤ አህያውንም አልሰበረውም። ስለዚህ፣ ነቢዩ የዚያን የእግዚአብሔር ሰው ሬሳ አንሥቶ በአህያው ላይ ጫነ፤ አልቅሶ ለመቅበርም ራሱ ወደሚኖርበት ከተማ አመጣው። 30ከዚያም ሬሳውን በራሱ መቃብር ቀበረው፤ “አወይ ወንድሜን” እያሉም አለቀሱለት። መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 13 ወጣቱ ሽማግሌውን ነብይ ምከር ከነበረው ክብር የተነሳ ከብዶት ሰማ ምክሩ ግን ከታዘዘው የእ/ር ቃል ተቃራኒ ነበር። ምክሩን ተግባራዊ በማድረጉ የእ/ር ቁጣ ነደደ አሳልፎ ሰጥቶት አንበሳ ሰብሮ ገደለው አብሮት ይጋዝ የነበረውን አህያ ግን አልሰበረውም።በቅድሚያ በጽሁፍህ ውስጥ ነገሩ በነፍስህ ውስጥ ከብዶብህ ህዝብን የበደሉ ይሁኑ አንተን የበደሉህን ይቅር ማለት ትግል ሆኖብሃል መሰረታዊው ጸሎት የበደልካቸውን ሳይሆን የበደሉክን ይቅር እንደምትል የምትጸልየው ጸሎት ለጊዜው ውሃ የበላው ይመስላል። “እኛም ደግሞ #የበደሉንን#ይቅር#እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን።” ገዥዎች ሲበዱልህና ሳይበድሉህ ሲቀሩ በውኑ እ/ር ሳያውቀው በአንተ ላይ እጂን የሚጭን አለን? የእንተስ የራስህ ጠጕር ሁሉ እንኳ በፊቱ የተቈጠረ አይደለምን? ወይስ እ/ር ተለውጣል? በአማካይ በአዋቂው የሰው አካል ላይ ወደ 5 ሚሊዮን ያህል የፀጉር አምፖሎች follicles አሉ የወንዶች ከሴቶች በጥቂት መቶ ሺህ ቁጥራቸው ይበልጣሉ ፡፡ ከዚህም ብዙው ቁጥር ከጅማሬው ወደ 100,000 ያህል የራስ ቅል ላይ የፀጉር አቃፊ አምፖሎች ተደግፈው ይገኛሉ። መቶ ሺውም በፊቱ የተቈጠሩ ናቸው።ወንድሜ ሁላችንም በአንድም በሌላም እንደምንፈተነው ነፍስህ በፖለቲካው ትይንት ታውካለች ሸክም ከብዶባታል ወደ አባትህ ቀሊል ቀንበር የዋህነትና የልብም ትህትና ወደተባለው ወደ ልዝብ ሸክም ተመለስ ለነፍስህም እንደገና ዕረፍት ታገኛለህ። እንደነ ዳዊት ነፍሱን የሚሰብክ የተባረከ ነው። ነፍሳቶችን የምትሰበስብ ጠቢብ ሰው ሆይ የገዛ ነፍስህን ወደ ርስትህ ወደ ክርስቶስ ሰብስብ ነፍሴ ሆይ፥ ወደ ዕረፍትሽ ተመለሺ ብለህ ስበካት ወደ እግዚአብሔር መቅደስ ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ በመንፈስ እስክትመለስ ሴቲቱ መጋለብዋን አታቆምም። በነፍስ ያደረ ቁርሾ ገንፍሎ ቅናት ነፍስን ሲያበግን በምህረት እና በፍርድ እ/ር ስለቀጠለ የወለደው የነፍስ የበቀል ጩሆት ነው ይሄ የአራሚ ፍርድ ጥያቄ የመንፈስ ድምጽ አይለም። ቅንዓትም እንደ ሲኦል የጨከነች ናትና። ፍንጣሪዋ እንደ እሳት ፍንጣሪ፥ እንደ እግዚአብሔር ነበልባል ነው። እ/ር አጠፋለሁ ማለቱ ወደ ንስሃ አምጥቶ ንስሃን ሰጥቶ ጽድቅን አስተምሮ እምራለሁ ማለቱ እንደሆነ ባስተዋለ ጊዜ እንደተቆጣው እንደ ነብዩ ዮናስ እስከ ሞት ድረስ እቈጣ ዘንድ ይገባኛል ብትል የአባትህን አካሄድ ትቀይረዋለህን? በቍጣህስ ያለሱ ፈቃድ የእግዚአብሔርን ጽድቅ ምድር ላይ ትፈጽማለህን? አዎን ተቈጣ፤ መልካም ነው ነገር ግን ቁጣህ ኀጢአት እስኪያሰራህ፤ በቍጣህ ላይ ፀሓይ ገብቶ አንተ ዘንድ አይደር አይክረምም።ይህ ቃል እስካሁን ህያው ነውን? “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ጥበበኛ በጥበቡ አይታበይ፤ ኀያልም በኀይሉ አይመካ፤ ሀብታምም በሀብቱ አይኵራራ፤ የሚመካ ግን፣ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ በማወቁና፣ በምድር ላይ ምሕረትን፣ ፍትሕንና ጽድቅን የማደርግ መሆኔን በመረዳቱ፣ በዚህ ይመካ፤ እኔ በእነዚህ ነገሮች፣ እደሰታለሁና፤” ይላል እግዚአብሔር ትንቢተ ኤርምያስ 9፡23”በውኑ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር የዋህ ቃልን ሁሉ ያምናል እንዲል ነፍሳችን በምታገኘው የተቃወሰ የአገራችን ሚዲያ መረጃ የሚዲያ ፍጆታ ሰለባ መሆን ይገባናል። ምድሪቱ በህግ ሳይሆን በመመሪያ በምትታመስበት ዘመን የአመጽ ፈሳሾች በአራቱም ነፋሳት በሚያስጨንቅዋት ሰአት አዳኝ ማነው? ልጆች ዓይናችን እንደምታይ እንፍረድን? ጆሮዎችንም እንደምትሰማ እንበይን ወይስ እግዚአብሔርን በመፍራት ደስታችንን እንደሚያሳየን እንወቅ ታምነንም አንሰማራ። በውኑ ነፍሳችን ባስጨነቀችን ቁጥር ልጆች በምድራዊ ፖለቲካ ዝቅጠት ውስጥ ወርደን ጣልቃ መግባት አለብን? ወይስ በልመናና ጸሎት በምልጃም በምስጋናም ሰላምን በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ የሚሰጠውን የሰላም አለቃውን የሰላም ኑጉሱን እራሱም ሰላም የሆነው አባታችንን ከማንነቱ እንዲያፈስልን እንጠይቃለን? በውኑ ከዚችም ዓለም የምድር ገዦች አንዱ እንኳ መልካም ይሁን ክፉው ከሱ ፈቃድ ውጪ በላይላያችን ላይ ይሰላጥንብናል? በውኑ ሉኡሉ ማነው? አጥንት ቆጠራውን እንተወውና ለመሆኑ አስጨናቂው እ/ር እራሱ ነው ወይስ ጨካኙ ወያኔ/ኢሃዲግ ፓርቲ ወይስ የኢሃዲግ የቦክር ልጅ ክሽን ያለ ከያኒውና phony መሪያለው ብልጽጋና ፓርቲ? በሰውወይም በአንተ ላይ ጨካኙን ወያኔን ቢያዝብህ እጁን ቢጭንብህ እ/ር ሳይፈቅድ ነውን በብልጽግና ዳግማዊ ሳልሳዊ ሽዋሽዋ ብጸራ ያለፈቃዱ ነውን ደግሞስ ክርስቶስን ስብኮ በአዳም ቢገለጥ ያለእርሱ ፈቃድ ነውን? እግዚአብሔር ሁሉን ለእርሱ ለራሱ አልፈጠረምን፥ ኀጥእን ደግሞ ለክፉ ቀን። ኃይልና ጥበብ የእርሱ አይደሉምን የሚስተውና የሚያስተው እእርሱ ናቸውና። ከቀድሞ የነበረው አስፈሪው ግርማ ተቀየረን? ህዝቦችን ላይ የብረትና የእንጨት ቀንበር የሚጭነው ማነው? ራሱ እ/ር አይደለምን? እግዚአብሔር በተለያየ መከራ አገርንና ህዝብን ያስጨንቃቸው አልነበረምን ወደ ምንጩ ወደ እ/ር መመለስ አይሻልም?“እስራኤል ያለ እውነተኛ አምላክ፣ ያለ አስተማሪ ካህንና ያለ ሕግ ብዙ ዘመን አሳልፈዋል። በመከራቸው ጊዜ ግን፣ ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ተመልሰው ፈለጉት፤ እርሱም ተገኘላቸው። በዚያን ዘመን በምድር ነዋሪዎች ሁሉ ዘንድ ታላቅ ሁከት ስለ ነበር፣ በሰላም ወጥቶ መግባት አስተማማኝ አልነበረም። #እግዚአብሔር በተለያየ መከራ #ያስጨንቃቸው ስለ #ነበር፣ አንዱ መንግሥት በሌላው መንግሥት፣ አንዱም ከተማ በሌላው ከተማ ይደመሰስ ነበር። ‘2 ዜና መዋዕል 15:3-6” ያውልህ እንግዲህ እግዚአብሔር በተለያየ መከራ ኢትዮጵያን ያስጨነቃት ይሆንን መፍትሄውስ ምንድን ነው ብሎ ማሰብ አይቀልም?እውነታው እንነጋገር ከተባለ በየዘመናቱ የአገራችን የፖለቲካ ከያንያን ህዝባችንና አገራችን እንዴት እንደሚያስተዳድርዋት የማያሳስበው ኢትዮጵያዊ አለ ብየ አላስብ። ለዚህም ይመስለኛል የመከራው ውጥረቱ ሲበዛብን የነፍስ ፈቃድ ጉልበት አግኝቶ በውስጣችን ሲደልብ ከእ/ር ፈቃድ ውጪ ፖለቲካ ውስጥ በአመጽ የምንሳተፈው ነፍስም ከክርስቶስ ከዕረፍት ውኃ ኮብልላ በባቢሎን ፖለቲካ ገብታ ታቀብላለች። እውነታው እርሱ ምሳሊያችን ከሆነ እንደሚታውቀው እውነተኛ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ተከታይ ማንኛውም የእ/ር ልጅ በዚህ የዓለም ፖለቲካ ውስጥ ሊሳተፍ አይችልም፡፡ ጥሬ ነው ብሎ ለማጽደቅ ብዙ የአሮጌውን አቅማዳ የአመክንዮ መናኛ ወይን ማንቆርቆር ይችል ይሆአል ሆኖም የህይወታችን መሃከል የልጁን መልክ እንድንመስል አስቀድሞ ተወስኖልን ሳለ ከሱ መልክ አካሄድ አፈንገጣችንን መተማመን አለብን። ጌታችን ኢየሱስ በእርግጥም በምድራዊ ነገሮች እንደዚህ ዓይነት ዓለማዊ የፖለቲካ ተግባራት ላይ አልተሳተፈም Our Lord Jesus Christ certainly did not take any part in earthly things any such worldly political activities. እኛ የእ/ር ልጆች ነን የመጽሐፍ ቅዱስ ጽሑፎች ሁሉ ትንታኔዎችን በግልፅ እንደሚናገሩት መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት እና / ወይም በማስተማር ትንተና እና አመክንዮ አስረግጦ መጠቀም ምንም ስህተት የለውም ፡፡ እውነታው ግን እኔም አንተም ወንድሞችም “የክርስቶስ አምባሳደር Ambassador for Christ” ነኝ/ነህ/ናቸው (1 ቆሮ 5 20) ፡፡ አምባሳደር እንደመሆናችን መጠን በውጭ ሀገሮች ፖለቲካዊ ስርአታቸውና ድራማቸው እንዲሁም ቁማራቸው ውስጥ በሕጋዊነት መሳተፍ አንችልም ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ በጨካኙ ጨቋኝ የሮማ መንግሥት brutal oppressors Roman Government በአይሁድ ሕዝብ ላይ በሚሠራው ሥራ ላይ ትንተና ሰጥቶ ይቀጡልን ብሎ ጠይቆ አያውቅም He never got analysis or involved in the operations of the cruel and oppressors ፡፡ እርግጠኛ ነኝ መቼም ቢሆን “በማእከላዊ መንግስት አዲስ አበባ በ4 ኪሎ የገዥው ግቢ ወይም በመቀሌ ክልላዊ መንግስ በር ላይ ሄደን ” እንደ ዋሽንግተን ግብረ ሃይል ሰልፍ እንድንወጣና shame on you አፈርኩብህ ! በራስህ ላይ ነውር! ወዘተ…. እንድንል ከእርሱ አልተማርንም፡፡ እኛ ግን ከዓለም እንድንወጣ በመንፈሱ ተነግሮናል እንድንለይ ተነግሮናል we are told by the spirit to COME OUT OF THE WORLD and are separate ፡፡ “ሙታን ሙታናቸውን ይቀብሩ።” ሆኖም እንዳዘዘን ሁል ጊዜ በሥልጣን ላይ ላሉት ሁሉ እጸልያለሁ (1 ጢሞ. 2: 1-3) “ O well Let the DEAD bury the dead.” However, I do always pray for those all in power, as we are instructed to do (I Tim. 2:1-3). መንፈሳዊውን ነገር በምሳሌ መናገር የኖርክበት የሚገባህም እስከሆነ ድረስ አሁንም በወንድምነት እመክርሃለህ በመንፈሳዊ በሩ በክርስቶስ እርሱ በገባህበት በአብ ቀኝ በሰማያዊ ስፍራ በክብርህ ሲያሻህ መቀመጥ ሲያሻህም ህይወትን ለመግለጥ መውጣትም፤ መግባትም፤ መሰማራትም፤ አይሻልም?። ወይስ አሁን አንደምታደርገው ልክ የሥልጣን ስፍራቸውን ያልጠበቁትን ነገር ግን መኖሪያቸውን የተዉትን መለክተኞች ይመስል ናፍቆት ነው መሰለኝ ወደ አዳም ልጆች ወደ ባቢሎናዊን ከተማ ወርደህ ምክር መስጠት ምን ይባላል? ታየኝ የእ/ር ልጅ ለባቢሎናዊያን ና ጡብን/ጠቡን እንዲህ ስራው በእሳትም ተኵሰው ቅጣውም ጡቡም እንደ ድንጋይ መልህቅ ይሆንልሃል በምድርም ዝፍት ሁሉ ነገር እንደ ጭቃ ይረገጥልሃል ብሎ ሲመክር። እ/ር እራሱ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው አካሄዳችውን ቋንቋቸውን ከደባለቀው አባት ካልፈቀደ ምን ይኮናል። እግዚአብሔርን ደስ ካለው ጠላቶቹ እንኳ አብረውት በሰላም እንዲኖሩ ያደርጋል። አቤቱ፥ ሥራችንን ሁሉ ሠርተህልናልና ሰላምን ትሰጠናለህ። እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፣ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፣ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።መዝሙረ ዳዊት 127፡1 ። ተባረክልኝ። ወንድም ቢኒ።መጽሐፈ ኢዮብ12፡13“ጥበብና ኀይል የእግዚአብሔር ናቸው፤ምክርና ማስተዋልም በእርሱ ዘንድ ይገኛሉ።14እርሱ ያፈረሰውን መልሶ የሚገነባ የለም፣እርሱ ያሰረውን የሚፈታ አይገኝም።15እርሱ ውሃን ቢከለክል፣ ድርቅ ይሆናል፤ቢለቀውም ውሃው ምድሪቱን ያጥለቀልቃል።16ብርታትና ድል ማድረግ በእርሱ ዘንድ ይገኛል፤አታላዩም ተታላዩም በእርሱ እጅ ናቸው።17አማካሪዎችን ከጥበባቸው ያራቍታል፤ፈራጆችንም ማስተዋል ይነሣል።18ነገሥታትን ድግ ያስፈታል፤ገመድም በወገባቸው ያስራል።19ካህናትን ከክህነታቸው ያዋርዳል፤ለዘመናት የተደላደሉትንም ይገለብጣል።20ዕውቅ መካሪዎችን ቋንቋ ያሳጣል፤የሽማግሌዎችንም ማስተዋል ይወስዳል።21የተከበሩትን ውርደት ያከናንባል፤ብርቱዎችንም ትጥቅ ያስፈታል።22የጨለማን ጥልቅ ነገሮች ይገልጣል፤የሞትንም ጥላ ወደ ብርሃን ያወጣል።23ሕዝቦችን ታላቅ ያደርጋል፤ መልሶም ያጠፋቸዋል፤ሕዝቦችን ያበዛል፤ ያፈልሳቸዋልም።24የዓለም መሪዎችን ማስተዋል ይነሣል፤መንገድ በሌለበት በረሓም ያቅበዘብዛቸዋል፤25ብርሃን በሌለበት ጨለማ በዳበሳ ይሄዳሉ፤እንደ ሰካራምም ይንገዳገዳሉ።

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal