ከውይይት የተጠቀሰ። ሰላም BizunehBekele እኩል ሌሊትም ሲሆን፦ እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚል ውካታ ሆነ።(ማቴ.25:6)
እንደምመጣ ቢያውቁም ያነቃቸው ግን ሙሽራውን ያመጣው የውካታ ድምፅ ነው፡፡
መልስ፤ በሁካታው ድምፅ ሁሉም ለድምፁ ነቁ ዘይቱ ወይም መንፈሱ ግን ልዩነትን አምጥተዋል። “መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን #ሊቀበሉ የወጡ አሥር ቈንጃጅትን ትመስላለች። ….. ሙሽራው መጣ ተዘጋጅተው የነበሩትም ከእርሱ ጋር ወደ ሰርግ ገቡ ደጁም ተዘጋ። አምስቱ ሰነፎች ደናግል ነበሩ ለኩራዛቸው በቂ ዘይት ስሌላቸው ሊገዙ የሄዱት። ገዝተውም ሁሉም ሙሽራውን ይጠቡቅበት ወደ ነበረው ቤት ተመለሱ ። ለሰርጉ ስለ ዘገዩ በሩ ተዘግቶ ነበር። ልባም ደናግሎች ደግሞ ሙሽራውን ይጠባበቁት ከነበሩበት ወደ ደጅ ወጥተው ሆ እያሉ ተቀብለውት አጅበውትም ማለት ነው ወደ ቤት ይዘውት ተመለሱ ደጁም ተዘጋ እንጂ ወደ ሰማይ አልተወነጨፉም:፡በሌላ አነጋገር ሙሽራው ልባም ደናግሎችን ነጥቆ ወደ መንግስተ ሰማይ ይዞ ለመሄድ አልመጣም። ነገር ግን ልባም ደናግሎች ሙሽራውን ይጠባበቁት ወደ ከነበሩበት ወደ ደጅ ወጥተው በአክብሮት ተቀብለውት አጅበውትም ወደ ቤት ተያይዘው ተመለሱ ደጁም ተዘጋ ከጌታ ጋርም አብረው በሰርጉ ተገኙ።“በአየር ለመቀበል” “1ኛወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 4፡/17 ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል(Greek: apantesis ) ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።” ወንድሞች ሁሉ “ደመና” “አየር” የሚሉ ቃላትን መልህቅ አርገው ይዝውታል። ደመና እና አየር ምን መንፈሳዊ ፍቺ እንዳላቸው ከማስተዋል በፊት አብሮ የተነገረው ቃል #ለመቀበል(Greek: apantesis ) የሚለው እንዲገባን እስቲ ከቃሉ እናስተውል። እንዲገባን ወደ ሐዋሪያው መልክት እንመለሰና 1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 4፡ ጌታን በአየር ላይ እንደ #ምንቀበለው ነግሮናል። ይህ ሁሉ መንፈሳዊ ትእይንት ነው ሆኖም እንደሚባለው አካላዊ ወይም ተፈጥራዊ እይታ ቢሆን እንኳ ንጥቀቱ አየር ላይ #የምንቀበለውን እንጂ ተቀብለን በዛው እንሄዳለን አይልም መለክቱ። የግሪኩ ቃል መቀበል Greek: apantesis አፓንቴስስ ማለት ወዳጅን ከውጭ #በመቀበል አጅቦ ወደ ቤት #መመለስ ማለት ነው። a (friendly) encounter: meet or (to meet and return with as an escort) ይህ አታንቴስስ የሚለው የግሪኩ ቃል በአዲስ ኪዳን 4 ጊዜ ተጠቅሞበታል:፡ ሙሽራው ስለ መጣ ደናግሎቹ ወጥተው ወደራሳቸው እንዲቀበሉት የተነገራቸው ቦታ ነው ።በየማቴዎስ ወንጌል 25፡1 በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ አሥር ቆነጃጅትን ትመስላለች።2 ከእነርሱም አምስቱ ሰነፎች አምስቱም ልባሞች ነበሩ። 3 ሰነፎቹ መብራታቸውን ይዘው ከእነርሱ ጋር ዘይት አልያዙምና፤ 4 ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው ጋር በማሰሮአቸው ዘይት ያዙ። 5 ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ። 6 እኩል ሌሊትም ሲሆን። እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ #ትቀበሉት (Greek: apantesis አታንቴስስ) ዘንድውጡ የሚል ውካታ ሆነ።፨ በነገራችን ላይ ብዙዋች ክንፍ ያለው መላክ ይታያቸው ይሆናል በቁጥር 16 ሙታን እዲነሱ መለከት የሚነፋው የትንሳኤው መልአክ ሚካኤል (HEBREW፣ who (is) like God እ/ርን የሚመስለው) እደሆነ በዳንኤል 12፡1-3 ግልጽ ያደርግልናል። እ/ርን የሚመስለው መንፈስ የሆነው በመንፈስ ያለማቋረጥ እየመጣልን ያለው ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ነው። አንተም የክርስቶስ አካል እግዚያብሔርን የምትመስለው ነህ። ወደ ቃሉ ስንመለስ ልባም ደናግሎች ሙሽራውን ይጠባበቁት ወደ ከነበሩበት ወደ ደጅ ወጥተው በአክብሮት ተቀብለውት አጅበውትም ወደ ቤት ተያይዘው ተመለሱ ደጁም ተዘጋ :፡ ስለዚህ ተቀበሉት በGreek: apantesis አፓንቴስስማለት ወዳጅን ከውጭ በመቀበል አጅቦ ወደ ቤት መመለስ ማለት ነው። ይህ ቃል የተጠቀሰበት ሌላ ቦታ ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ሮም እስረኛ ሆኖ ሲወሰድ በሐዋርያት ሥራ 28፡15 ከዚያም ወንድሞች ስለ እኛ ሰምተው እስከ አፍዩስ ፋሩስና ሦስት ማደሪያ እስከ ሚባለው ሊቀበሉን(Greek: apantesis አታንቴስስ ) ወጡ፥ ጳውሎስም ባያቸው ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገነ ልቡም ተጽናና።ታሪኩ ግልጽ ነው ። አማኞቹ ጳውሎስን ተቀብለው አጅበውት ወደ መጡበት ወደ ሮም ተያይዘው ተመለሱ እንጂ ተቀብለውት እስረኛው ወደ መጣበት ወደ እየሩሳሌም አልሄዱም። በመንፈሳዊነቱም ሆነ በአካላዊነት እንረዳው ጳውሎስ በአየር ላይ እንቀበለዋለን ሲል በአየር ላይ ተቀብለነው በዛው ወደ ሰማያት ይዞን ይወስደናል ማለቱ ሳይሆን አሁንም በመንፈሳዊነቱም ሆነ በአካላዊነት እንረዳው ሊገዛ ሲመለስ በአየር ላይ ተነጥቀን እንቀበለውና አጅበነው ሆ እያል ወደ ምድር አብረነው ልንገዛ ሁላችን እንመለሳለን ።ማለቱነው። እንግዲህ ትንቢታዊ መልእክት ያለው መንፈሳዊው ቁንጽል እይታው የ10 ደናግል ስእላዊ መልኩ ይህን ነው የሚመስለው። ወንድም ቢኒ። https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1241253999572214&id=100010628760470