ስለ ዲያብሎስ ሰይጣን ውይይት ክፍል 2


ከውይይት የተጠቀሰ። በእግዚያብሔር ተፈጥሮ ከእርሱ ስልጣን ስር ያልሆነ ወይም ያፈነገጠ ኅይል የለም። ለመንፈሳዊው ሰው ሁሉ መንፈሳዊ ነው ለተፈጥራዊው ሰው ሁሉ ነገር ተፈጥራዊ ነው። እንደ መንፈሳዊያን እንየው። መቼም የነዳቪንቼንና የነ አፈወርቅ ተክሌን ወዘተ እያሰብን ተፈጥራዊ ክንፍ ያለው ሰይጣን እንደማናስብ አምናለሁ። ወደ መፅሀፍ ቃል መመርመር መመለስ አለብን እምነታችንን በቃሉ ልንቃኝ ይገባል እላለሁ። ሰይጣን በመጀመርያው የመላእክት አለቃ ሳይሆን ሰይጣን ሆኖ በእ/ር የተፈጠረ ነው።ስጋዊው አእምሮ የሰውን እንጂ የእ/ርን የማያስብ ሰይጣን ነው። የክርስቶስ ጠላት ነው the carnal mind is enmity against God ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ መጀመሪያ የገደለው ነፍስ በመፅሃፍ ቅዱስ ወንድሙን አቤልን ነበር። ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ማትዮስ16:23 እርሱ ግን ዘወር ብሎ ጴጥሮስን። ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አ-ን-ተ ሰ-ይ-ጣ-ን፤ የ-ሰ-ው-ን እንጂ የ-እ-ግ-ዚ-አ-ብ-ሔ-ር-ን አ-ታ-ስ-ብ-ም-ና ዕንቅፋት ሆነህብኛል አለው።የዮሐንስ ወንጌል 8/44 እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ #ከ፟-መ-ጀ-መ-ሪ-ያ ነ-ፍ-ሰ ገ-ዳ-ይ #ነ-በ-ረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውናወደ ሮሜ ሰዎች 8/7 ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም ተስኖታል፤Rom 8/7 Because the carnal mind is enmity against God: for it is not subject to the law of God, neither indeed can be.።የዮሐንስ ወንጌል 6:70 ኢየሱስም፦ እኔ እናንተን አሥራ ሁለታችሁን የመረጥኋችሁ አይደለምን? #ከእናንተም#አንዱ#ዲያብሎስ#ነው ብሎ መለሰላቸው። የዮሐንስ ወንጌል 13/27 ቍራሽም ከተቀበለ በኋላ ያን ጊዜ ሰይጣን #ገባበት[መተርጎም የነበረበት #ተነሳበት#arise ነው : ማንነት ነውና። ሊቃውንቱ እይታቸው ተፈጥራዊ ነውና ሰይትጣን እንደሚመስላቸው ገባበት እያሉ ተርጉመውታል] እንግዲህ ኢየሱስ፦ የምታደርገውን ቶሎ ብለህ አድርግ አለው። GREEK 1525 eiserchomai ice-er’-khom-ahee- arise።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።ይህ ሰዮጣን በየአንዳንድሽ ሲነሳ ያስተዋለ እውነተኛ ማነው? ” #የሰውንም_አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ #የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን፥” (2ቆሮ.10:5)የዮሐንስ ወንጌል 8/44 እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ #ከ፟-መ-ጀ-መ-ሪ-ያ ነ-ፍ-ሰ ገ-ዳ-ይ #ነ-በ-ረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውናወደ ሮሜ ሰዎች 8/7 ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም ተስኖታል፤አጥፊው የወደቀ መላክ አይደለም ከ-፟መ፟-ጀ-መ-ሪ-ያ-ም በእ/ር አጥፊ ሆኖ የተፈጠረ ነው። ከ-፟መ፟-ጀ-መ-ሪ-ያ-ም ነፍሰ ገዳይ ነበረ። እባቡ ከ-፟መ፟-ጀ-መ-ሪ-ያ-ም እግዚአብሔር አምላክ ሲፈጥረው ከምድር አውሬ ሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ ሆኖ ነበር።‘“……..የፈጠርሁ እኔ ነኝ፤ ጥፋት እንዲያደርስም የፈጠርሁ እኔ ነኝ አጥፊውንም የፈጠርሁ እኔ ነኝ፤ ‘ኢሳይያስ 54:16 Isa 5416 Behold, …….I have created the waster to destroy. አለሙን ሁሉ ያሳተው የቀድሞው እባብ በተንኮሉ ተክኖ አድጎ በዘመናችን ዘንዶ ሆኖ ይህ ማነት እሳት እየተፋ ነው።የዮሐንስ ራእይ 20/2 የቀደመውንም እባብ ዘንዶውን እርሱም ዲያብሎስና ሰይጣን የተባለውን ያዘው። ሌላው እ/ር ፍርዱን የሚገልጠው የሰው ልጆችን ለመጉዳት በበቀልም ለዘላለም ለማጥፋት ወይም ለመረምሰስ ወይም በዘላለም እሳት ለመጥበስ ሳይሆን ሳይሆን የሚጠቀምበት ፍጥረቱን ለማረም፤ ለማቅናት፤ ለማደስ፤ ፅድቅን ለማስተማር፤ ሆኖ በቃሉ ተፅፎ ይስተዋላል። ኢሳ 26/9 ፍርድህን በምድር ባደረክ ጊዜ በአለም የሚኖሩ ፅድቅን ይማራሉ።” whan thy judgments are in the earth the inhabitants of the WORLD will learnrighteousness.[uprightness & right standing with GOD.) isaiah 26/9 አስተዋላችሁን ፍርዱ ሲገለጥ በአለም የሚኖሩ ምንን ይማራሉ ይላል? ፅድቅን ይማራሉ። ሀሌሉያ! ሰውን ፅድቅ ለማስተማር የእ/ርን ፍርድ የሚጠይቅ ከሆነ ዘንዳ ለዘመናት በቲዮሎጂያን ስለ እር ፍርድ የተሰጡትን ትምህርቶች እንደ ገና በእ/ር ቃል መፈተን አለባቸው። በዚህም የእ/ርን ፍርድ ከፍቅሩ ጋር እኩል እናከብረዋለን።ስማ! የዘላለም ፍርድ ስትል የዘመናት ፍርድ ማለትህ ነውን?የዘላለም ፍርድ, eternal judgment ወይም ፍፃሜ-አልባ ቅጣት, endess punishment ብሎ ነገር መፅሀፍ ቅዱስ አያስተምርም። የፍርድን ተፈጥሮ ከማስተዋላችን በፊት ዘመን እና ዘላለም የሚሉ ሁለት ቁልፍ ቃላቶች ልዩ ነታቸውንና ተናጋሪው መንፈስ የሆነው እ/ር ከተናገራቸው አካያ ማስተዋሉ እጅግ ጠቃሚ ሆኖ ስላገኘነው በትኩረት በቅድሚያ እነሱን ማየቱ ጠቃሚ ሆኖ አግኝተነዋል። “የዘላለም ፍርድ ቅጣት እውነት እንደሆነ ለማረጋገጥ ከመፅሀፍ ቅዱስ የሚጠቀሱት ቃላቶች ፡፡ ‘ዘላለም” የሚለው ቃል ከዋናው ቅጂ ሲተረጎም የእንግሊዝኛውም የአማርኛውም ላይ ከተፈጠረው የትርጉም ስህተት የተገኘ ፅንሰ ሀሳብ ነው። “መፅሀፍትንና የእ/ር ሀይል ካወቅን አንስትም” በሚለው ፁሁፋችን እንደገለፅነው የትርጉም ስራዎች እንደ ፍፁም ስራ እንዳንደገፍባቸው ታሪካዊ አመጣጣቸውንበማስተዋል መቃኘታችን ለዚህና ለሌሎች ሀሳቦች እንደ መንደርደርያ እንዲጠቅመን ነው። በአዲስ ኪዳን “ዘላለምeternal,everlasting“ የሚለው ቃል ከዋናው የግሪኩ ቅጂ ላይ “aionions“ ከሚለው ቃል የተተሮጎመ ሲሆን የቃሉ ስር ወይም ንብረትነቱ “AON“ ነው። ትርጉሙም “ዘመን age’ ማለት ነው። ሁለቱ የተለያየ ትርጉም ያላቸው ቃላት ናቸው ማለት አይደለም። aion[the noun formሰዋሰው ወይም ነባር ስም ] ሲሆን aionions [the adjective form, ቅፅል] ነው። ሁለቱ ቃላት ሰዋሰው እና ቅፅል ናቸው። ለምሳሌ ሳምንትሰዋሶው ሲሆን ሳምንታዊ ደግሞ ተቀፅላው ነው። ልክ እለት እለታዊ፤ አመት, አመታዊ እንደ ሚባለው ማለት ነው። “በመረዳት ብርሀን ማስተዋል ያለብን ዘመን ማለት ዘላለም ማለት አይደለም። ብዙ ጊዜዎችና ብዙ ወቅቶች አሉ። ነገር ግን አንድ ዘላለም ብቻ አለ። ዘልአለም ጅማሬ የለውም። ዘላለም ፍፃሜም ቢሆን የለውም።ነገር ግን ጊዜ፤ ዘመን፤ ወቅቶች ሁሉም ጅማሬ አላቸው ደግሞም ፍፃሜም አላቸው። ጊዜ ሲያበቃ ዘላለም ይጀምራል የሚለው አባባል ፈፅሞ ስህተት ነው። ምክንያቱም ዘላለም ጅማሬ የለውም የሚያበቃም አይደለም።ዘላለም ጌዜ ሲጀምርም የመጣ አይደለም። ዘመናት በዘላለም ውስጥ የራሳቸው የሆነ ቦታ አላቸው ልክ ሴኮንድ በደቂቃ ውስጥ ቦታ እንዳለው ደቂቃም በአመት ውስጥ የራሱየሆነ ቦታ እንዳለው። አመታት ያልቃሉ ዘላለም ግን አያበቃም። ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ ግልፅ እይታ ይኖረን ዘንድ እጅግ ጠቃሚ ነው። ዘመን የሚመደበው በጊዜ ውስጥ ሲሆን ዘላለም ግን ጊዜ አልባነው።“በመፅሀፍ ቅዱስ ጥናታችን ውስጥ ስለ ዘመን የተነገሩትና ስለ ዘላለም የተነገሩትን ለይተን ማስተዋሉ የእ/ርን ጠቅላላ ምክሩ እናስተውል ዘንድ እጅግ ይጠቅመናል። የተጠቀሰ። በጣም የሚያሳዝነው አብዛኛዎቹ የእንግሊዝኛም ሆነ የአማርኛ ትርጎሞች በብዙ የሚመሰገኑበት ቢኖርም “ዘመንን በተመለከተ ሲተሮጉሙ ግን ግድየለሽ ሆነው ”ዘላለም እያሉ በመተርጎማቸው በእ/ርህዝብ ላይ ትልቅ ግራ መጋባትን አስከትለዋል።ይህም ብዙ ትውልዶችን ለአያሌ ዘመናት የተዛባ መረዳት ውስጥ ቆልፎ አስቀምጥዋቸዋል። ለመጥቀስ ያህል የአማርኛ ትርጉሞችም ላይም ሆነ የእንግሊዝኛ ትርጉሙ “King James Version“ ላይ እንዲሁም በዚህ መፅሀፍ ተፅኖ ስር የተተሮጎሙ ሁሉ ላይ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ቅዱስን ስለ ሚሳደብ ሰው የተናገረውን ቃል እንዲህ ያስቀምጡታል። “ማር3/29 መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ ሁሉ ግን የዘላለም ሀጢያት እዳ ይሆንበታል እንጂ ለዘላለም አይሰረይለትም።” ከዚህም የተሳሳተ ትርጓሜ ምክንያት የተፀነሰ የተሳሳተ አስተሳሰብም ተወልደዋል። ‘ለዘላለም ይቅር የማይባል ሀጥያት አለ ብለን ድምዳሜ ላይ እንድንደርስ አድርጎን ነበር።ነገር ግን የቃሉን ትክክለኛ ፍቺ እንዲያቀብል አርገው ከተሮጎሙት ከጥቂት የእንግሊዝኛ ትርጉሞች መካከል “Emphatic Diaglott“ የተባለው ትርጉም ትክክለኛውን ትርጎም እንዲህ ያስቀምጠዋል። “Whoever may blasphemy the Holy Spirit has no forgiveness to the age, but is exposed to aionian[age lasting] judgment. Mark 3/29” መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ ሁሉ ለዘመኑ ይቅር አይባልም። ነገር ግን ለዘመኑ ፍርድ ይጋለጣል።” እንደምናስተውለው ይቅር የማይባለው ለፍርዱ የሚጋለጠው ለዘመኑ ነው እንጂ ለዘላለም አይደለም።በማቲዮስ12/32 እንዲህ ተብሎ ተተርጉሞዋል “በመንፈስ ቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ በዚህ አለም ቢሆን በሚመጣው አይሰረይለትም” አለም የሚለው ቃል ከግሪኩaion ማለትም ‘ዘመን ago ተብሎ መተርጎም ከነበረበት ቃል የመጣ ነው። ቃሉ መተርጎም የነበረበት “በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚናገር ሁሉ በዚህ ዘመንም ቢሆን በሚመጣው አይሰረይለትም።” ነው ። ጌታ እየሱስ የተወለደው በህግ ዘመን ስለ ነበር በዚህ ዘመንም ቢሆን ማለቱ የህግን ዘመን ለማሳየት ሲሆን በሚመጣውም ዘመን ቢሆን ሲል ደግሞ አሁን እኛ ያለንበት የፀጋው ዘመን ማለቱ ነው። በእብራይስጥ ትክክለኛው ገሃነም Gehenna [የሄኖም ሸለቆ Ge-Hinnom “valley of Hinnom”]የአሮጌው ኪዳኑ “hell” ወይም ገሃነመ እሳት ስያሜ ምንጭ የመጣበት በእዮርሳሌም፡ በስተደቡብ ይገኝ ከነበረ “የሄኖም ሸለቆ” ከተባለው ነው። በእንግሊዝኛው “Hell” በአማርኛ “ገሃነም” “ሲኦል” ተብሎ የተተረጎመው ነው። ክፉ አፀያፊ ባእድ አምልኮ ይለማመዱ የነበሩ ነገስታት በነበሩት በአክአዝና በምናሴ ዘመነ መንግስት ሞሎክ ለተባለ ለአሞናውያን ጣኦት ሰዎች በጭካኔ ወንድ ልጁን እና ሴት ልጁን መስዋእት አድርገው በዚህ ሸለቆ ያቀርቡበት ነበር። ይደረግ የነበረው ክፉ አፀያፊ ባእድ አምልኮም የተነሳ ኢዮስያስ ይህን ሸለቆ ርኩስ ሆኖ እንዲቆጠር አደረገ። ይህም ስፍራ ለዘመናት የከተማው ቆሻሻ መጣያ ና ማቃጠያ ቦታ ሆነ ቡሃላም የፍርድ ቅጣት ተምሳሌት ሆኖ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ተጠቅሞበታል። ከዚህ ሸለቆ አጠገብም ከፍ ባለው አቀበት ወይም ከፍታ ላይ ነበር እዮርሳሌም የተገነባችው።መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 23/10 ማንም ሰው ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን ለሞሎክ በእሳት እንዳያሳልፍ በሄኖም ልጆች ሸለቆ የነበረውን ቶፌትን ርኩስ አደረገው።[የቀድሞው ትርጉም]‘በሄኖም ሸለቆ የነበረውን ቶፌት የተባለውን ማምለኪያ አረከሰ፤ ይኸውም ማንም ሰው ወንድ ወይም ሴት ልጁን ለሞሎክ በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ እንዳያቀርብበት ነው። ‘2 ነገሥት 23:10[መደበኛው ትርጉም]2Kgs 23/10 And he defiled Topheth, which is in the valley of the children of Hinnom, that no man might make his son or his daughter to pass through the fire to Molech.[KJV]ኤርምያስ 7:30-32/ የይሁዳ ልጆች በፊቴ ክፉን ነገር ሠርተዋል፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ያረክሱትም ዘንድ ስሜ በተጠራበት ቤት ርኵሰታቸውን አኑረዋል። 31 እኔም ያላዘዝሁትንና በልቤ ያላሰብሁትን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት ያቃጥሉ ዘንድ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ያለችውን የቶፌትን መስገጃዎች ሠርተዋል።32 ስለዚህ፥ እነሆ፥ ስፍራ ከማጣት የተነሣ በቶፌት ይቀበራሉና የእርድ ሸለቆ ይባላል እንጂ ቶፌት ወይም የሄኖም ልጅ ሸለቆ ዳግመኛ የማይባልበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር።[የቀድሞው ትርጉም]‘እኔ ያላዘዝኋቸውን፣ ከቶም ያላሰብሁትን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት አቃጥለው ለመሠዋት በሄኖም ልጅ ሸለቆ የቶፌትን መስገጃ ኰረብቶች ሠሩ። ስለዚህ አስተውሉ፤ ይላል እግዚአብሔር ፤ ስፍራ እስከማይገኝ ድረስ ሙታንን በቶፌት ስለሚቀ ብሩ፣ የዕርድ ሸለቆ እንጂ ከእንግዲህ ቶፌት ወይም የሄኖም ልጅ ሸለቆ ተብሎ የማይጠራበት ጊዜ ይመጣል። ‘ ኤርምያስ 7:31-32። እግዚአብሔር በነብይ ኤርምያስ የእ/ርን ቁጣ በትንቢት ተናገረ ፍርድ በእዮርሳሌም ሲመጣ “የዕርድ ሸለቆ” ተብሎ እንደ ሚጠራ ተነበየ። ትንቢተ ኤርምያስ 19/6 ስለዚህ፥ እነሆ፥ ይህ ስፍራ የእርድ ሸለቆ ይባላል እንጂ ቶፌት ወይም የሄኖም ልጅ ሸለቆ ዳግመኛ የማይባልበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡[የቀድሞው ትርጉም]Jer 19/6 Therefore, behold, the days come, saith the Lord, that this place shall no more be called Tophet, nor The valley of the son of Hinnom, but The valley of slaughter.እ/ር በትንቢት ሲናገር ፍርድ በእዮርሳሌም ሲመጣ “የሸክላ ገምቦውንም ከአንተ ጋር በሄዱ ሰዎች ፊት ትሰብራለህ፤ ይህን ሕዝብና ይህቺን ከተማ እንዲሁ እሰብራለሁ፤” ብለዋል ብለህ ንገራቸው አለው።‘“ገምቦውንም ከአንተ ጋር በሄዱ ሰዎች ፊት ትሰብራለህ፤ እንዲህም ትላቸዋለህ፤ ‘የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የሸክላ ሠሪው ገንቦ እንደ ተሰበረና ሊጠገን እንደማይቻል፣ ይህን ሕዝብና ይህቺን ከተማ እንዲሁ እሰብራለሁ፤ የቀብር ቦታ ከመታጣቱ የተነሣ ሙታናቸውን በቶፌት ይቀብራሉ። ‘ኤርምያስ 19:10-11ከዛም እዮርሳሌም ትንሽ ቆይታ በባቢሎናውያን ሰራዊት ጠፋች። ከአንድ ክፍለ ዘመን ቡሃላ በነህምያ ዘመን ድጋሚ ተሰራች። ላለፉት 2000 ሺ አመታት በተደጋጋሚ ጠፍታ ነበር። የደገመች ተሰራች። ከተማዋም አሁን ቆማለች። የኤርምያስ ትንቢት የመጀመርያው የፍርድ ገጽታ ነው የተፈፀመው። የዚህ ትንቢት ሙሉ ጥፋት የሚያካትተው ቅሪት አለው።ጌታ እየሱስም ከገሃነም ጋር ተያይዞ የተነገረውን ትንቢት በእዮርሳሌም ላይ የተነገረውን ጭምርና በተምሳሌነትም ደጋግሞ ተናገረው። በገሃነም ምሳሌም 11 ግዜ ተጠቅሞበታል። ( በማቴ 5:22 , 29 , 30 ; 10:28 ; 18: 9 , 23:15 , 33 ; ማርቆስ 9 43 , 45 , 47 ; ሉቃስ 12 5 ያንብቡ ።)‘ “እናንተ እባቦች፤ የእፉኝት ልጆች! ከገሃነም ፍርድ እንዴት ልታመልጡ ትችላላችሁ? ስለዚህ ነቢያትን፣ ጠቢባንንና መምህራንን እልክላችኋለሁ፤ ከነዚህም አንዳንዶቹን ትገድላላችሁ፤ አንዳንዶቹን ትሰቅላላችሁ፤ ሌሎቹንም በምኵራቦቻችሁ ትገርፏቸዋላችሁ፤ ከከተማ ወደ ከተማ ታሳድዷቸዋላችሁ። ስለዚህ፣ ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በመቅደሱና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ ለፈሰሰው ንጹሕ ደም ሁሉ እናንተ ተጠያቂዎች ናችሁ። እውነት እላችኋለሁ፤ ላለፈው ነገር ሁሉ ይህ ትውልድ ይጠየቅበታል። ‘ማቴዎስ 23:33-36ቡሃላ ወረድ ብሎ በእዮርሳሌም ላይ የፍርድ ቃሉን ሲናገር እናያለን።‘ “አንቺ ነቢያትን የምትገድዪ፣ ወደ አንቺ የተላኩትንም በድንጋይ የምትወግሪ ኢየሩሳሌም ሆይ፤ አንቺ ኢየሩሳሌም! ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ ሥር እንደምትሰበስብ፣ ልጆችሽን ለመሰብሰብ ስንት ጊዜ ፈለግሁ! እናንተ ግን ፈቃደኛ አልሆናችሁም፤ እነሆ፤ ቤታችሁ ወና ሆኖ ይቀርላችኋል! እላችኋለሁና፤ ‘በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው’ እስከምትሉ ድረስ ዳግመኛ አታዩኝም።”’ማቴዎስ 23:37-39ኤርሚያስ የእዮርሳሌምን ጥፋት ከገሃነም ሸለቆ ላይ እንደተሰበረው የሸክላ ገንቦ እንደምትሰባበር ከፍርድ ጋር ካያያዘው ቡሃል ገሃነም የእ/ር ቃል የሚቃወሙት ላይ የመለኮት ፍርድ ተምሳሌት ሆነ ። ጌታም እዮርሳሌም እንደምትጠፋ ደግሞ ተነበየ።ስለዚህ፣ ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በመቅደሱና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ ለፈሰሰው ንጹሕ ደም ሁሉ እናንተ ተጠያቂዎች ናችሁ። እውነት እላችኋለሁ፤ ላለፈው ነገር ሁሉ ይህ ትውልድ[genea, “ዘር race, ዝርያ offspring”] ይጠየቅበታል። ‘ማቴዎስ 23:34-36ጌታ እየሱስ አማኞች እየሩሳሌም በውጭ ጦር ስትከበብ ከከተማዋ ፈትለክ ብለው እንዲያመልጡ አስጠነቀቃቸው። እነሱም ከ 66-67A.D. ገደማ ተበተኑ። በ70AD ላይ ታይተስ የተባለ የሮማ ጀነራል እዮርሳሌምን አጠፋት። አሁንም የትንቢቱ ሙልአት ገና በመሆኑ አማኞች የእየሱስን ቃል ሊያስቡበት ይገባል። አማኞች እየሩሳሌም በውጭ ጦር ስትከበብ ከከተማዋ ፈትለክ ብለው ሊያመልጡ ይገባል እ/ር ያድነናል ብለው መቀመጥ የለባቸውም ይህ ትንቢት ከላይዋ ነው እና። የነብዩ ኤርሚያስ ትንቢት ግልጽ ነው ዳግም ልትስራ እስከማትችል በገሃነም ሸለቆ ላይ እንደሰበረው የሸክላ ገንቦ እንደምትሰባበር ተናግረዋልና አማኞች የወረራ ምልክት ካዩ ሊዘናጉ አይገባም። ምናልባትም ከተማይቱ መርገሙየሚሰበርላት “በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው” ብላ ክርስቶስን ከተቀበለች ብቻ ነው።ስለዚህ ጌታ ጋሃነም የሚለውን የእብራይስጥ ቃል ተጠቅሞ ለግሪኮችና ለሮማዊያን ዝምድና የሌለው ቃል ቢሆንም ለ11 ግዜ በእርሱ ቃል የማይታመኑትን እነሱም እያስጠነቀቀ ካላመኑ የኤርሚያስ ትንቢት እንደ ሚፈፀምባቸው እየነገራቸው ነበረ። እነሱም በግላቸው በጅምላ ፍርዱ ላይ ተካተው ሊገኙ እንደሚችሉ ኤርሚያስ እንደ ተነበየው “የእርድ ሸለቆ” እንደ ሚሆን አስጠነቀቃቸው። ሌላው ጌታ ከተናገራቸው የገሃናም ተምሳሌት ፍርድ መካከል ሊታዩ የሚገባቸው አንዱ “በገሃነም ትሉ አይሞትም፤ እሳቱ አይጠፋምና፤” የሚለው ቃል ነው።‘ዐይንህ ብታሰናክልህ ጐልጒለህ አውጣት፤ ሁለት ዐይን ኖሮህ ወደ ገሃነም ከመጣል፣ አንድ ዐይን ኖሮህ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት ይሻልሃል፤ “በገሃነም ትሉ አይሞትም፤ እሳቱ አይጠፋምና፤ ‘ማርቆስ 9:47-48 ጌታ የጠቀሰውና የተነተነው የነብዩ ኢሳያስን ትንቢት ነበር። ‘“ወጥተውም በእኔ ላይ ያመፁትን ሰዎች ሬሳ ያያሉ፤ ትላቸው አይሞትም፤ እሳታቸው አይጠፋም፤ ለሰውም ዘር ሁሉ አስጸያፊ ይሆናሉ።”’ኢሳይያስ 66:24ኢሳያስ እየተናገረ የነበረው ስለ አሮጌዋ እዮርሳሌምና ስለ አዲስትዋ እዮርሳሌም ነበር።‘“ወዳጆቿ የሆናችሁ ሁሉ፣ ከኢየሩሳሌም ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ስለ እርሷም ሐሤት አድርጉ፤ ለእርሷ ያለቀሳችሁ ሁሉ፣ ከእርሷ ጋር እጅግ ደስ ይበላችሁ። ‘ኢሳይያስ 66:10 “እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር በፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፣ የእናንተና የዘራችሁ ስም እንደዚሁ ጸንቶ ይኖራል” ይላል እግዚአብሔር ፤ ‘ኢሳይያስ 66:22ስለዚህም ነበር ጌታ ገሃናምን የተጠቀመው ይደረግ የነበረው ክፉ አፀያፊ ባእድ አምልኮም ርኩሰት በዛ ዘመን ቆሞ ነበርና በዚያ ዘመንም ይህም ስፍራ ለዘመናት የከተማው ቆሻሻ መጣያ ና ማቃጠያ ቦታ ሆነ ቡሃላም ብዙ የሞቱ እንስሶች እና የሰዎች አካል ሳይቀር ይጣልበት ነበርና የበሰበሰም የበዛበት ያለማቋረጥ በትላትሎችም የተሞላ ነበረ። ጠረኑን ለመቋቋም ሲባል ቆሻሻውንም ለማቃጠል ሁልጌዜ የማይጠፋ ፍምና እሳት ይታይበት ነበረ። በዚህም የፍርድ ቅጣት ስፍራ ምሳሌ ሆኖ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ “በገሃነም ትሉ አይሞትም፤ እሳቱ አይጠፋምና” የሚለውን ተጠቅሞበታል።‘ዐይንህ ብታሰናክልህ ጐልጒለህ አውጣት፤ ሁለት ዐይን ኖሮህ ወደ ገሃነም ከመጣል፣ አንድ ዐይን ኖሮህ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት ይሻልሃል፤ “በገሃነም ትሉ አይሞትም፤ እሳቱ አይጠፋምና፤ ‘ማርቆስ 9:47-48 ሌላው ሲኦል የሚለው ቃል በመጀመርያ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ የሚገኘው ፔንታቱክ [ባለ አምስት ቅጽ መጽሓፍት(ማለት ነው)] ተብለው በሚታወቁት አምስቱ የሙሴ ጹሁፎች መካከል በኦሪት ዘኍልቍ 16/30 ሲሆን ከዛ ቡሃላ በብዙ ቦታ ላይ ተጽፈዋል። ይህም አንድ የእብራይስጥ ቃል እናም ሰዎስት የግሪክ ቃል በእንግሊዝኛው “Hell” በአማርኛ “ሲኦል” በማለት የተተረጎመው ነው። በአብዛኛው በብሉይ ወይም በአሮጌው ኪዳን በሁሉም የእንግሊዝኛ ትርጉሞች ሁሉ “SHEOL” የሚለው ቃል ተጠቅመውበታል ትርጉሙም ድርብ ሳይሆን ነጠላ የሆነ “የሙታን ቦታ” “the place of the dead.” ማለት ነው። ሌላው ትርጉሙ የሙታን መቃብር grave, ጉድጋድ pit የሙታን ግዛት the realm of the dead።ኦሪት ዘኍልቍ 16/30 እግዚአብሔር ግን አዲስ ነገር ቢፈጥር፥ ምድርም አፍዋን ከፍታ እነርሱን ለእነርሱም ያለውን ሁሉ ብትውጣቸው፥ በሕይወታቸውም ወደ ሲኦል ቢወርዱ፥ ያን ጊዜ እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔርን እንደ ናቁ ታውቃላችሁ። Num 16/30 But if the Lord make a new thing, and the earth open her mouth, and swallow them up, with all that appertain unto them, and they go down quick into the pit[ sh’owl sheh-ole’] then ye shall understand that these men have provoked the Lord.ሌሎች ተዛማች ሊጠኑ ሊታዩ የሚገባቸው ሃሳቦች ቢኖሩም እነዚህ ምንም ይሁኑ ምንም የሲኦል እና የገሃነም ፍፃሜው በጥቂቱ ካለፈው ፁሁፍ “እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ቃል የሁለተኛው ሞትና የእሳት ባህር ፍቺ” ከሚለው ላይ ፍፃሚያቸውን እናያለን። ……ክፍል 4 በወንድም ቢኒ፤ክፍል 4 በወንድም ቢኒ፤ “ስለዚህ ሃሳብ በብዙ ሰዎች ብዙ ተጽፎ አንብቢያለሁ ሚዛን የሚደፋና፡ብሎም የማይደፋም ቀልሎ የተገኘም አጋጥሞኛል። በእ/ር ቃል ሲመዘን ማለቴ ነው። በዚህ ሃሳብ ላይ በብዙ ሰዎች ዘንድ ሰፊ የሆነ ግራ የተጋባ አመለካከት እንዳለ ግልጽ ነው። ለብዙወገኖች ይጠቅማል በማለት ይህን የመረዳት ብርሃን አብረን እንድናየው እወዳለሁ መልካም ነገር አለውና። ከቀድሞው አባቶች ሲኦል ዘልአለማዊ ነውን? (is hell eternal or will GOD’S plan fail?) በRev-Charles pridgeon ከነቮበር ወ 1920 እትም መጽሐፋቸው። የእሳት ባህርን በተመለከተ ከገለጡት እጅግ ከሚያስደንቀው የመረዳት ብርሃን የተሞላበት የሊቅ ወይምየእስኮላር ስራቸው ለተሻለ ግንዛቤ ለብዙ አስተዋዮች እንደ ታገዙበት ሁሉ እኔም ከታገዝኩበትና ከተረዳሁበት መካከል ለወገኖች ጥቅም ልጠቅስ እወዳለሁ። “የእሳት ባህርና ዲኑ (BRIMSTONE) የሚያመለክቱት እሳቱ ከዲኑ ጋር ሲነድ ነው። ዲን፡brimstone ወይም ድኝ፡ sulphur የሚለው የእሳቱ ባህርይ ነው።የግሪኩ ቃል THEION ሲተረጎም ዲን፡brimstone ተብሎ የተተረጎመ ሲሆን ያው የግሪኩ ቃል እራሱ THEION መለኮት ማለት ነው። በጥንታውያን ግሪኮች መካከል ድኝ ፡sulphur የተቀደሰ ነበረ። እናም ለማጠን፤ ለማንፃት፤ ለማጥራት ለአምላካቸው ያውሉት ነበር። ለዚህም አላማ ያጥኑ ነበር። homer’s lliad[16:228] አንድ ሰው በእሳትና በዲን ዋንጫውን እያፀዳ እንደሆነ ሊናገር ይችላል። THEION ከሚለው ቃል የተሳበው ግስ {ግስ፡ ማለት የቌንቋ አረባብ የዘርና ነባር መሰረት ቃል ነው። } THEIOO ሲሆን ማለትም ማወደስ፤ መለኮትን መስራት፤ ለአምላክነት መለየት ማለት ነው። [liddel and scott Greek English Lexicon, 1897 Edition] ተመልከት/ቺ።ለማንኛውም ግሪካዊ ወይም በግሪክ ቋንቋ ለሰለጠነ ሰው “የእሳት ባህርና ዲን” ሆኖ መረዳት የነበረበት “የመሎከት የማጣርያ ብህር፣a lake of divine purifcation” ነበር። ፍርድ የሚለው ሃሳብ መከልከል የለበትም። እ/ር መንገዱ ሁሉ እውነትና ፍርድ ነውና። በጥንታዊ ግሪክ ቋንቋ መለኮታዊ ማጣርያና ለመለኮት ማዋል የሚል ነው ፍቺው። በተራው አገላለጽ ይህ የቃሉ ትርጉም ገንጥለው አውጥተውታል። አመፀኛ ሃፍረት የለውም ተብሎ እንደ ተፃፈ ምንም ነገር ሳያስቀሩ ግን የዘልአለም ስቃይ ጋር አዛምደውታል።” የተጠቀሰው ተፈፀመ።በነገራችን ላይ THEION የሚለው ቃል የተሳበው theo ከሚለው የግሪክ ቃል ሲሆን እግዚአብሔር (መለኮት) GOD እየተባለ በአብዛኛው የተተረጎመው ቃል ነው። ቲዮሎጂ {Theologi or Theology is the study of GOD} የስነ መለኮት ጥናት ወይም ስለ ስነ መለኮት ማጥናት ከዚህ ሃሳብ የተገኘ ነው።የእ/ርን አሰራርና አደራረጉን ለማወቅ አንድ ሰው ቃሉን እያጠና መንፈስም መረዳትን እያበዛለት ሲመጣ የቃሉን መንፈሳዊ አመልካች በትክክል ማስተዋል ሲጀምር በመጽሐፉ ፀሐፊ በእ/ር የዘልአለም አጀንዳ በቅዱሱ ልእለ ተፈጥሮ ውበትና እንዲሁም በታላቅ ጥበቡ፤ በፍቅሩ ብልጽግና ይነደፋሉ። እ/ርንም ውድድድ ያደርገዋል። በእ/ር ዘንድ ያለው ፍርድ ለማቅናት እንደሆነ ማስተዋል ይጀምራልና።ሰዎች ለመከራ ይቀጣሉ። እ/ር ግን በፍርዱ ያቀናል ያፀዳል።በግሪኩ ቃል የጠራ ወይም የነፃ pur በዚህ ዘመን እንግሊዝኛ ማጽዳት ወይም ማጥራት ፡ ንፁህ ማድረግ PURGE and PURIFY ለሚሉት ቃላት ስር ወይም ምንጭ ነው። የእ/ር እሳትም የሚያደርገው ይህንኑ ነው። የእ/ር ባህርይና ተፈጥሮ ያሳያል። በዛሬው ጥናታችን በጥቂቱ የእሳቱን ባህሪ በመፅሐፍ ቅዱስ የእውነት ቃል እናጠናለን። ይህን እሳት እየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ለኩሶታል። በእሳት የሚያጠምቅ ሆኖም መጥተዋል። ለሚከተሉት ሁሉ እንደ እሳት መምጣቱን ቀጥለዋል። ገናም ለፉጡራኑ ሁሉ ይመጣል። አሜን ጌታ ሆይ ማራናታ አብዝተህ ቶሎ ቶሎ ምጣ። አሜን። ወንድም ቢኒ።

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal