እየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፤ ራሱም እግዚአብሔር ነው። የሚያስታርቅ ፈልጉልኝ…


ከውይይት የተጠቀሰ፤ ክፍል 1፤ ሰላም ለእናተ ይሁን ወገኖች። መንፈሳዊ ነገር ጥልቅ ነው፥ መንፈስ ብቻ የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር እንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራልና። ከእግዚአብሔር መንፈስ ወደ እውነት ሁሉ ባለ ምሪት በቀር ለእግዚአብሔር ያለውን ማናችንም መንፈሳዊውን ነገር በተፈጥራዊው የአእምሮ ጅምናስቲክ ሁሉን መንፈሳዊ እውነት ቀርቶ ጥቂቱን ቆንጥረን ለማወቅ ብንተጋ ጭንቅ ነው እሊያም ከዚህም ከዚያ በተቃረመች የስነ፟መለኮት ትምህርት ቅርሚያ መታበይ ነው። ቃሉ ሰከን እንድንል በፍቅር ይመክረናል “ዐውቃለሁ የሚል ሰው፣ ማወቅ የሚገባውን ያህል ገና አላወቀም። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 8፡2” እውነቱ ሁላችንንም የእ/ር መንፈስ ወደ እውነት ሁሉ ያለማቃረጥ ካልመራን ከውቂያኖስ ይልቅ ከሚጠልቀው መንፈሳዊ እውቀቱና ማስተዋሉ በመንፈሱ ወደ መንፈሳችን የሚያስረዳ እንካን ውቂያኖስን በጭልፋ እንደ መጨለፍ ያክል በመጠን ነው። ለዚህም ነው ጌታ ኢየሱስ ”የዮሐንስ ወንጌል 16፡12 የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ፥ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም።”ወደ መነሻ ሃሳቡ ስንመለስ “ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4:11” ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ ቤተ ክርስቲያን ወግ ና ትውፊት ይናገር አይለንምና ወይም ወንድማችን እንዳልከው መንፈሳዊውን ነገር በተለያዩ ተፈጥራዊ ዘየዎችና በቄንጠኛ ስያሜዎች ልንፈታው አንችልም አይለንም። ቃሉን የሚፈታልን ቃሉ ባቻ ነው እንጂ እንደተጨበጨበለት “በስነ አመክንዮ ይሁን፣ በስነ አፈታት ወይም በስነጥበብ፣ ካስፈለገም በስነ መገለጥ ወዘተ…” ያስታርቅ አይልምና ነገሩን እንደ እ/ር ቃል እውነት እንየው። እነዚህ የሰው ቃል ብቻ ናቸውና ስሜትን ከመኮርኮር በቀር በራሳቸው እውነትን ተክተው መልስ አይሆኑንም። እንደምናውቀው እንድ የቃሉ እውነት አንድ ሺ ውሸትን ያፈርሳልና “በእውነትህ ቀድሳቸው ቃልህ እውነት ነውና”። እንደሚለን “ጤናማ በሆነ ትምህርትን በመስበክ [2] የሚቃረኑትን ውድቅ አድርግ ቲቶ 1፡9 – አዲሱ የተሻሻለው መደበኛ ስሪት] preach with #sound#doctrine and [2] #refute those who #contradict” [Titus 1:9 – The New Revised Standard Version] ስለዚህ መንፈሳዊውን ነገር ከመንፈሳዊው ነገር ጋር አስተያይተን መንፈስ በሚያስተምረን ቃል እውነትን አስተውለን እንናገራለን እንጂ የሰው ጥበብ በሚያስተምረን ቃል እንዳልሆነ ለሁላችንም ግልጽ ነው። ስለዚህ ከብዙ በጥቂቱ ከረጅም ባጭሩ ከዚህም መልካም ነገር እንዲቀርላችሁ እ/ር ከፈቀደ ጥቂት ፍሬ ሃሳቦችን ነካክቼ በውይይታችሁ ላይ ላክልበት።እንደምናውቀው ። ቃል በራሱ መንፈስ ነው ሕይወትም ነው። የዮሐንስ ወንጌል 6፡63 ቃል ሥጋ #ሆነ! ዮሃ 1፡14 ሲለን የሆነ ትርጉሙ #ሆነ ነው። እንዴ ሆነ ማለት ተፈጥራዊ እንጂ የመንፈሳዊ ሰው ጥያቄ አይደለም በሰው ዘንድ የማይቻል በእግዚአብሔር ዘንድ ሁሉ እንደሚቻል መንፈሳዊ ሰው ያውቀዋልና። በሌላ አገላለጽ መንፈስ ወይም መለኮት ስጋ #ሆነ deity or spirit become (come into being) flesh or in human expression he become embodied in the form of flesh in human form “God incarnate” ቃሉ ሆነ ይላል እንጂ ሌላ አይልም ወይም አሁንም እንዲገባን በሰው እይታ አነጋገር የለበሰው ወይም ቃል ስጋ ወደ መሆን የተለወጠው ተራ ስጋ ሳይሆን ጸጋንና እውነትንም የተሞላ ስጋ ነው በዚህ ሙላት በእኛ አደረ እኛም ክብሩን አየን። ስጋ ከመሆኑ በፊት ምን ነበረ? ዮሐንስ ምዕራፍ 1: 1. በመጀመሪያው ቃል (The Word ፡ ግሪክ፤ logos ሎጎስ ማለት የእ/ር ሀሳብ/የአስተሳሰቦቹ ስብስብ፤ ምክንያት፤ ተግባብ ወይም ንግግር የኮሙኒኬሽን፤ የቃላት መግለጫ ሐሳብ ሎጎስ) ነበረ። ቃልም (ሎጎስ: የእ/ር ሐሳቡ) በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። ቃልም (ሎጎስ: የእ/ር ሐሳቡም) እግዚአብሔር እራሱ ነበረ።John 1:1. Within a beginning there was The Word (logos: The Thought; The Collection of Thoughts; The Idea; The Reason; The Discourse; The Communication; The Verbal Expression). And the Word (logos: the thought; the expression) was (and continued being) facing, directed and moving toward (or: with) God. And the Word (logos: the thought; the idea; the reason; the expression) continued being God. [or: Originally the Word was existing and continued to be, and the Word was being {projected} toward God. And the Word, It was existing being God (idiomatically: And the Word was just what God was; And the Expression was {an extension of} Deity). JMT….ክፍል 2 ወንድም ቢኒ።ክፍል 2…. ” ቃል ሥጋ ሆነ “ይላል። ዮሐንስ 1 ፡14 የእ/ር ልዕለ፟ተፈጥሮ ሐሳቡ ስጋ ሆነ። ኢየሱስ ሲወለድ ማለትም “እግዚአብሔር የነበረው ቃል” እና “ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ” ለስው ልጆች ወይም ለተፈጥራዊው አእምሮ እንዲገባው በዚህ መልኩ እናስቀምጠውና መንፈስ የሆነውን የማይታየውን የአባትነትን ክብር በሚታይ ማንነት በልጅነት ክብር ተገልጦ ተረጎመው የማይታየውን መንፈስን እርሱ የሚታይ ክብር ሆኖ ገልጦታል ፤ መንፈስን በሚታየው ቦታም አወጣው ፡፡ መንፈስን ወደ ስጋ ቋንቋ ተርጉሞታል አሳወቀውም ። (John 1:18 [AMP]) No man has ever seen God at any time; the only unique Son, or the only begotten God, Who is in the bosom [in the intimate presence] of the Father, He has declared Him [He has revealed Him and brought Him out where He can be seen; He has #interpreted Him and He has made Him known].በቀላሉ በሁሉን ቻይነቱ ቃል የሥጋ ቅርጽ ወይም መልክ ያዘ ወይም ሆነ የሰውነት ቁመናም የያዘ ሆነ። took the form of human flesh። መንፈስ በዚያን ቀን ሥጋ ሆነ። በእ/ር አጀንዳ ውስጥ የዚህ ክስተት አንድምታ እጅግ በጣም ሰፊ ግብ ነበረው።አስተውልው ወንድማችን ቃልም እግዚአብሔር ነበረ! the Word was God! ቃልም (ሎጎስም: የእ/ር ሐሳቡም) በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። ይህ መንፈሳዊ ነገር ነው ሆኖም ለማስተዋል ያክል አንተን እንደምሳሌ እንጠቀምና የወንድማችን Sam Tir ሃሳቡም ከከወንድማችን Sam Tir ጋር ነበረ ከተባለ ሃሳቡ ሌላ ግለሰብ ወንድማችን Sam Tir ሌላ ግለሰብ ነው ማለት ነው? ወይስ ሃሳብህ የወንድማችን ሌላ ክሎኔቲክ በጄኔቲክ ተመሳሳይህ ወዘተ…ነው? Hybrid human clone genetically identical copy ኮፒየ ነው ኮፕየ ነው ዘራፍ ሃሳቤ ከኔ ተቀብቶ የተላከ ነው። ሃሳቤን ፈትጥሬዋለሁ በስልጣን በመለኮት አንድ ነን? ወዘተ…. ማለት ከቻልን ትንሽ መንፈሳዊውን እንደ ተፈጥራዊው ሰው ሞኝነት ሆኖ ታይቶናልና ያስቅ ይሆናል። እናስተውል ቃልም (ሎጎስም: የእ/ር ሐሳቡም) በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። የሚለውን ሌላ አምላክ እንዳለ አድርገን መረዳታችን ድንቅ ነው። ቃሉ ላይ እንቆይ። ክፍል…3ክፍል 3…. ልጨምርልህ እንደቡዙሃኑ በተፈጥራዊ ስሌት ከጋለብን ከንቱ ነው ውጢጤቱ ሲባዛ በዜሮ ይሆናል። የሚቀጥለውን ሃሳብ በቃሉ እንየው። በቅድሚያ የሰው ልጅ አባት ማን ይመስላችሀል? እንየው። ጌታ እየሱስ ክርስቶስ በብፅዕት[በደስተኛዋ] ድንግል ማርያም ማህፀን #የተረገዘው( CONCEIVED by the Holy Spirit.) በሉኡሉ ሃይል በመንፈስ ቅዱስ መፅለል ነበር። እንደ እምናስተውለው መንፈስ ቅዱስ ለእርግዝናዋ ምክንያት ነው። እየሱስም ተወለደ ያስረገዛት መንፈስ ቅዱስ ቢሆንም የመንፈስ ቅዱስ ልጅ ግን አልተባለም አልነበረምም ነገር ግን የአባት(አብ) ልጅ ነው።”the Son of the FATHER” (II John 2:3) ያስረገዛት መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር መንፈስ ነው እንጂ ከ3ቱ ስላሴዋች አንዱ አይደለም። ቢሆን ኖሮ እርሱ ባስረገዘ ሌላ አባት ባልተባለ። እንደ የስላሴ አፈ ታሪክ ቲፎዞዋች አባባል መንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ ስብእና ለብቻው ያለው ቢሆን ኖሮ ወይም ከ3ቱ ስላሴዋች አንዱ ቢሆን ኖሮ መንፈስ ቅዱስ አባቱ በተባለ ነበር እንጂ ሌላ ጣልቃ የገባ መለኮት አብ የተባለ በጉልበት አባቱ ባልሆነ። ይህ ወደጠለቅ እይታና ጥያቄ ያስገባናል። ነገሩ በዚ አያበቃምና። Even any simple minded person can understand that, whoever conceives a child in a mother’s womb is the biological F-A-T-H-E-R OF THAT CHILD when it is born, NOT SOME OTHER PERSON or member of Trinity….።አሁን ሌላ እናስተውል እየሱስ ክርስቶስ ቃል የነበረው እ/ር ብቻ ሳይሆን እየሱስ ክርስቶስ እራሱ ጳራቂላጦስ አጽናኙ የተባለው መንፈስ ነው። በእ/ር ቃል እንየው። ጌታ ምን እንዳለ በግማሽ ሳይሆን በሙሉ አጽናኦት እናስተውል። “ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም ወደ እናንተ እመጣለሁ።” ኢየሱስ ተናጋሪው እራሱ መጣ እሺ ከዛስ በኋላስ መንፈስ ስለሆነ ምን አለ? “ዓለም አያየኝም እናንተ ግን ታዩኛላችሁ” በዚያን ግዜ ምን ይከሰታል? ማወቅ ይከሰታል። ‘እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ .’ ሃይሉ ያለው ማወቁ ላይ ነው ዓለም አያየኝም እናንተ ግን ታዩኛላችሁ ታውቃላችሁ። ‘ቅኔውን ሲፈታው ስለራሱ እንጂ ስሌላ አካል እያወራ እንዳልሆነ አስተዋላችሁ? . የዮሐንስ ወንጌል 14/18 ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ. 19 ገና ጥቂት ዘመን አለ ከዚህም በኋላ ዓለም አያየኝም እናንተ ግን ታዩኛላችሁ። እኔ ሕያው ነኝና እናንተ ደግሞ ሕያዋን ትሆናላችሁ. 20 እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ . John 14፡18 I will not leave you #comfortless: I will come to you. ወንድም ዮሐ 14:18 ጌታችን ምን እንዳለ በግማሽ ሳይሆ በሙሉ ትኩረትህ አሁን አስተውል። መንፈስ ማን እንደሆነ መንፈስ ቅዱስ ምን እንደሆነ ግልጽ ያደርግልናል . የስላሴ 3 ኛ አካል ነው? ጌታ እራሱ ይናገር። የዮሐንስ ወንጌል 14/28 #እኔ#እሄዳለሁ#ወደ#እናንተም#እመጣለሁ እንዳልኋችሁ ሰማችሁ[ሄዶ በመንፈስ ክብሩ ተመልሶ የሚመጣው ማነው? እየሱስ እራሱ አጽናኝ ሆኖ]. “#ወደ#እናንተ#እመጣለሁ[እኔ] አስተዋላችሁ ጌታ ምን አለ? እኔ እሄዳለሁ: እኔም ወደ አንተ እመጣለሁ! ወደ እናንተ እመጣለሁ[ማ ይመጣል እየሱስ] 20 እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን [አጽናኙ በሚመጣበት ቀን] ታውቃላችሁ. ( “በዚያም ቀን እናንተ እኔ በአባቴ እንዳለሁ ታውቃላችሁ እናንተም በእኔ ውስጥ [መቼ ቀን? አጽናኝ ሲመጣ]” የዮሐንስ ወንጌል 14/28 #እኔ#እሄዳለሁ#ወደ#እናንተም#እመጣለሁ እንዳልኋችሁ ሰማችሁ[ሄዶ በመንፈስ ክብሩ ተመልሶ የሚመጣው ማነው? እየሱስ እራሱ አጽናኝ ሆኖ]. “#ወደ#እናንተ#እመጣለሁ[እኔ] አስተዋላችሁ ጌታ ምን አለ? እኔ እሄዳለሁ: እኔም ወደ አንተ እመጣለሁ! እኔ እሄዳለሁ ወደ እናንተም እመጣለሁ! አሁን እየሱስ ክርስቶስ እራሱ ጳራቂላጦስ ተብሎ መጠራቱን በእ / ር ቃል እናረጋግጥ. አፅናኝ [ጳራቂላጦስ] ሌላ አጽናኝ [ጳራቂላጦስ] ይሰጣችኋል ያለው ጳራቂላጦሱ ማን እንደሆነ እናያለን። የዮሐንስ ወንጌል 14 / 15-16 ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ. እኔም ወደ አብን እጸልያለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ [ጳራቂላጦስ; parakletos አጽናኝ፤ አማላጅ, consoler:. Advocate, አጽናኝ] ይሰጣችኋል። ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ዘንድ።1 ኛ የዮሐንስ መልእክት 2 ፡1 ልጆቼ ሆይ: ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ. ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ #ጠበቃ [ግሪክ፤ ጳራቂላጦስ; parakletos አጽናኝ፤ አማላጅ, consoler: -advocate, ጠበቃ አጽናኝ] አለን #እርሱም#ጻድቅ#የሆነ #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ነው። አመለጠህ? ልድገምልህ #ጠበቃ [ጳራቂላጦስ; parakletos አጽናኝ፤ አማላጅ, consoler: -advocate, ጠበቃ አጽናኝ] አለን #እርሱም #ጻድቅ #የሆነ #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ነው። ፡)…ክፍል 4 ቢኒ።ክፍል 4፤ ተጨማሪ ሌላ ሃሳብ እ/ር ቢፈቅድ እናስተውል። ህግን በሲና ተራራ ለሙሴ የሰጠውና ስጋ የለበሰው ያህዌ እየሱስ ክርስቶስ ነው! ከላይ ያህዌ ኢየሱስ መሆኑን ተናግረናል። በአዲስ ኪዳን ስናስተውል በዘጸአት 20 ያህዌ የሰጠውን ህግ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ በምን ስልጣን ነበር የተራራው ስብከት ተብሎ በሚታወቀው በማቲዮስ 5-7 ትምህርቱ ላይ የህጉን ፍቺ ትክክለኛ ትርጉም ሲያርም የነበረው? እየሱስ ህግን የሰጠውና ስጋ የለበሰው ያህዌ ነው! ጌታ እየሱስ ክርስቶስ በስጋ የመጣው ወደ መንፈስ ሊመራን ነው። በመጀመሪያው ቃል የነበረው እግዚአብሔር እንደ ነበረ። የዮሐንስ ወንጌል 1፡1 በመጀመርያ ቃልም ሥጋ ሆኖ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ እንደመጣ የማያምን ሁሉ ሃሰተኛ መንፈስ ነው የክርስቶስ ተቃዋሚውም መንፈስ ነው፤ ። ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ግን ከእግዚአብሔር ነው። “1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4/2 የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፥3 ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ እንደ መጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ይህም የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው፤ ይህም እንዲመጣ ሰምታችኋል፥ አሁንም እንኳ በዓለም አለ”*እየሱስ ፈጣሪም ነው ህግን የሰጠውና ስጋ የለበሰውም ያህዌ እሱ ነው! “የዮሐንስ ወንጌል 1/3 ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።” ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም #አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ #እግዚአብሔር #ከእኛ #ጋር የሚል ነው። በሌላ አነጋገር የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ መገኘቱና ዝቅ ብሎ ልጅ መሆን ማለት #እግዚአብሔር #ከእኛ #ጋር ሆነ ማለት ነው። ያህዌ እየሱስ መሆኑን በመንፈስ ልዩ መረዳት ይመራን ዘንድ ጸሎቴ ነው። ይህንን እውነት ለማስተዋል በቀደሙት ክፍሎች በብዙ አይተነዋል እንዲሁም እያንዳንዱን መጽሐፍት ብትመረምሩ ጌታን በዛ ውስጥ ታገኙታላችሁ። የእብራይስጥ ቋንቋ እራሱ ይህንን እውነት ያረጋግጠዋል። አንድ የእብራይስጥና የግሪክ ቋንቋ ማንም መረዳቱ የተሰጠውና ቃሉን የሚያጠና ሊቅ ሁሉ ሊያውቀው የተገባው የእየሱስን መለኮታዊ ምንጭ ነው። “የእብራይስጥ ቋንቋ በአብዛኛው የአንድ ቃል ፍቺ ሃብታም ከመሆኑ የተነሳ ከአንድ በላይ ደራርቦ ሃሳብን ሊያሳይ ይችላል። የእብራይስጥ ቋንቋ ቃላት ስእላዊ ገላጭ ያለውና የድምጽ ገላጭም አጣምሮ የያዘ ሊሆንም ይችላል፡፡ለምሳሌ ሁሉም ፈደሎች ቁጥርም ናቸው ቃላትም ናቸው። ለምሳሌ አልፍ “alef” የመጀመርያው ፊደል ነው ያው ፊደል የመጀመርያው ቁጥር አንድ ማለትም ነው። “alef” የሚለው ያው ቃል በሬ ማለት ሲሆን ስእላዊ ገላጩም ጥንካሬን፤ ብርታትን [ymbolizes, strength] የሚያመለክት ነው። ሁለተኛው ቤዝ ወይም ቤት “beth” ቁጥር ሁለት ነው። “beth” የሚለው ቃል እራሱ ቤት ፤ቤተ ሰዎችና ፤ቤተሰቦችን [house or household] ያካተተ ፍቺ አለው።በእብራይስጥ ቋንቋ ህግ ማለት ቶራ Torah ነው። በእብራይስጥና ቋንቋ ቶራ[ Torah] ሲፃፍ tav-vav-resh-hey ሆኖ ይፃፋል። ይህ ከተያያዛበት ለየብቻው ቃሉ ሲተረጎም Tav ማለት ምልክት ወይም መስቀል ማለት “a mark or sign” [of the cross] ሲሆን። በዋናው በመጀመርያው ጥናታዊ ያልተበረዘ በእብራይስጥ ቋንቋ “መስቀል” ተብሎ ነበር የተፃፈው። በዘመናይ በእብራይስጥና ቋንቋ ተለይቶ ይገኛን። ይህም የሆነው በባቢሎን 70 አመት ምርኮ ጊዜ የባህል ወረራ ስለደረሰ ከአረሚክ ቋንቋ ጋር ተዳቅሎ ተበረዘ።ሁለተኛው “vav” የሚለው በግልጽ ትርጉሙ እንደ አገባቡ የተሰቀለው፤በሚስማር፤የተጠረቀመው፤የተቸከለው “a nail or peg.” ሲሆን ሶስተኛው “resh” የሚለው በግልጽ መሪ ወይም ራስ “a head, or leader.” ማለት ነው። በመጨረሻም “hey” በቃሉ መጨረሻ ሲቀመት ትርጉሙ ከሱ ወይ ከዛ የወጣ የተገኘ ማለት ነው። “what comes from.” በእብራይስጥና ቋንቋ ህግ ማለትም Torah ከሚለው ቃል ፍቺ እንደ ምናስተውለው “በመስቀል ላይ ከተሰቀለው መሪ ወይም ራስ የተገኘ” ማለት ነው። “what – comes – from – the – Leader- nailed- to- the – Cross” ማለት ነው ። በሌላ አነጋገር እየሱስ ህግን የሰጠውና በመስቀል ላይ የተሰቀለው መሪ ወይም ራስ እሱ መሆኑን በዚህ ታላቅ ሚስጥር ውስጥ የእ/ር ድንቅ ስራ ይስተዋላል። ሃሌሉያ! አባት ይብዛላችሁ። ወንድም ቢኒ።የውይይቱ ጠቋሚ። https://www.facebook.com/sam.tir.96/posts/3607922312576049

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal