ይቻላል ወይም አይቻልም የሚል መልስ ብቻ ስጠኝ ከራሴ ዘር ውጭ ከሆነች ሴት ጋር የፍቅር ጓደኝነት መመሥረት ወይም ማግባት ኃጢአት ነው ወይ? ለምሳሌ ጥቁር ሆኜ ነጭ ሴት ወይም ሌላ ብሔር ዘር ማግባት ላይ?


Binyam TA

March 28 at 6:29 PM ·

ቀደም ካሉ ከጥያቄና መልስ የተወሰደ። “ጥያቄ፡ ፈይሳ እባላለሁ። ይቻላል ወይም አይቻልም የሚል መልስ ብቻ ስጠኝ ከራሴ ዘር ውጭ ከሆነች ሴት ጋር የፍቅር ጓደኝነት መመሥረት ወይም ማግባት ኃጢአት ነው ወይ? ለምሳሌ ጥቁር ሆኜ ነጭ ሴት ወይም ሌላ ብሔር ዘር ማግባት ላይ? አመሰግናለሁ።
#መልስ፡ ሰላም ለአንተ ይሁን ውድ ወንድማችን ፈይሳ፤ በማንኛውም ሊያጠምድ በሚተነኩል “ይቻላል ወይም አይቻልም፤ አዎ ወይም አይ” ምላሾች ውስጥ ተቆልፌ መልስ የመስጠት የመገደድ ሁኔታ ውስጥ መግባት አልፈልግም ፡፡ በአእምሮም ቢሆን በመንፈሳዊ ነገሮች ብዙ ምክንያቶች አሉና፡፡ ከነዚህ ውስጥ በጣም ጥቂቶቹ “ይቻላል ወይም አይቻልም። አዎ ወይም አይ” በሚሉ ውስን ቃላት ሊመለሱ አይችሉም ለምሳሌ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ “አሁንስ እህትህንና ሚስትህን መደብደብ አቁመሃል ወይ?” የሚለውን ብጠይቅህ አጣብቂኝ ውጥ ትገባለህ አቁሚያለሁ ብትልም አላቆምኩም ብለህ ብትመልስም ተጠምደሃል፡፡ ወይም ሌላ ምሳሌ ልስጥህ። ጠበቃ ሆና ፍርድ ቤት ውጥት በመስቀለኛ ጥያቄ አጣድፎ ምንም ሊያገኝበት ያልቻለውን ተጠያቂን ሊያጠምደው ፈልጎ በቃ አሁን ለምጠይቅህ ጥያቄ አዎን ወይም አይ ብለህ ብቻ መልስልኝ ቢለው። ሰውየው ጠቢብ ኖሮ እንደእሱማ ተገቢ አይደለም። እኔ አንተ ጠበቃ ሆይ “ሰዎችን መዝረፍ አቁመሃል ወይስ እየዘረፍክ ነው” ብየ ብጠይቅህ አዎ ወይም አይ ብቻ ብለህ መመለስ ትችላለህ? አለው ይባላል። ወዘተ….
ዘርን ወይም ብሔርን ብቻ መሠረት በማድረግ በሁለቱ መካከል የሚደረግ ጋብቻ የሚከለክል ሕግ ወይም ትእዛዝ ከጌታ ዘንድ የለም ፡፡
እርሱ ዘርና ብሄር ግድ አይለውም ነገር ግን ባእድና የጣኦት አምልኮን የሚያመልኩ የማያምኑን ለአንተ ጥቅም የጌታን ስራት የማያውቁን አረማዊያንን ግን በብሉይ ኪዳን ጌታ ወጥመድ እንዳይሆኑብህ ቃል ኪዳን ከነሱ ጋር አታድርግ ብልዋቸው ነበር ሆኖም እርሱ ቢላቸውም ቃሉን ጥሰው ተጋቡ እንዳለው አልቀረም ለባእድ አምልኮ ተሰጡና ሰገዱ እነሱም አስጨነቅዋቸው ለጥፋታቸው ምክንያት ሆኑ።
“ከእነርሱና ከአማልክቶቻቸው ጋር ቃል ኪዳን አታድርግ። አማልክቶቻቸውንም ብታመልክ ወጥመድ ይሆኑብሃልና እኔን እንድትበድል እንዳያደርጉህ በአገርህ አይቀመጡ። ኦሪት ዘጸአት 23፡32-33”
“በዚህ ቀን የማዝዝህን ነገር ጠብቅ፤ እነሆ እኔ አሞራዊውን ከነዓናዊውንም ኬጢያዊውንም ፌርዛዊውንም ኤዊያዊውንም ኢያቡሳዊውንም በፊትህ አወጣለሁ። በመካከልህ ወጥመድ እንዳይሆኑብህ አንተ በምትሄድባት ምድር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን እንዳታደርግ ተጠንቀቅ፤ኦሪት ዘጸአት 34፡11-12”
አንተ ማሰብ ያለብህ የማታምን አለማዊዋን አሁን ወስደህ ብታገባ ምላጭ ነች የሃላ ሃላ ትቆርጥሃለች። ልጁ ናትና አማችህም አጅሬው ይሆናል። አሁን ካለችህ ገና ካልተጋባህ ቃል ኪዳን እስካላፈረስክ ድረስ የግድ ጌታ ወደማመን እስኪያመጣት መተው ይመረጣል። በአዲስ ኪዳን ከማያምኑ ሰዎች ጋር አግባብ ባልሆነ መንገድ አትጠመዱ ይልሃል በሬን ከግመል ጋር በቀንበር አጥምደህ ልረስ ብትል አይመችምና አንገቱ ይሰበራል። “ከማያምኑ ሰዎች ጋር አግባብ ባልሆነ መንገድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዐመፅ ጋር ምን ግንኙነት አለው? ብርሃንስ ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? ክርስቶስ ከቤልሆር ጋር ምን ስምምነት አለው? የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ኅብረት አለው? የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከጣዖታት ጋር ምን ስምምነት አለው? እኛኮ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን፤ እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ተናግሮአል፤ “ከእነርሱ ጋር እኖራለሁ፤ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፤ አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።”2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6፡14-16” ‘ትንቢተ አሞጽ 3
3 በውኑ ሁለት ሰዎች ሳይስማሙ በአንድነት ይሄዳሉን?” ሁለት ሰዎች በጌታ ነገር ሳይስማሙ በአንድነት መሄድ እንዳይችሉ ግልጽ ነው። ጌታ ለአንተ ጥቅም ከማያምኑ ጋር እንዳትጠመድ ነገረህ እንጂ እርሱ ዘረኛ ወይም ብሄርተኛ አልያም እንደ ብዙዎች የፈረንጅ ወይም የጥቁር የቆዳ ቀለም አምላኪ አይደለም። እርሱ ሁሉን በክርስቶስ ወዶ ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅቶ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግዋቸዋልና፥
“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።የዮሐንስ ራእይ 5:9-10” እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው። ወንድም ቢኒ።3Εμμανουήλ χάρις, Nardos Nahusenay and 1 other2 Shares

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal