
Binyam TA
ቀደም ካሉ ከጥያቄና መልስ የተወሰደ። #ጥያቄ፤ ሰላም በጸጋው እንጂ በስራ እንዳልዳንን እናውቃለን። በአስሩ ተዛዛት ትክክልና ስህተት የሆነውን ነገር በነሱ እንገነዘባለን። የእኔ ጥያቄ እኔ እና ቤተሰቤ የእግዚአብሔርን ቃል መከተላችን እና ቅዳሜ (ሰባተኛው ቀን) የእኛ (የቤተሰቤ) የዕረፍት እና የአምልኮ ቀን እንዲሆንልን አድርጊያለሁ ይህ ስህተት ነው ትላለህ? ሰንበትን መከተል እንዳለብኝ የተሰማኝ ምክንያት ለፈጣሪያችን ያለንን ፍቅር በመታዘዝ ማሳየት እንዳለብን ተገቢ ምክንያት ነው ብየ ስለማስብ ነው። ዳኒ ነኝ ከሰባተኛው ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን።
#መልስ፤ ሰላም ወንድም ዳኒ። ጥያቄዎችህን በውስጥ መስመር በአጭር ጹሁፍ ለመመለስ በጣም ረጅም ማስረዳትን ስለሚሻ እራሱን የቻለ ጥናትና በቃሉ የተደገፈ ሰፊ ማስረዳት ይጠይቃል። በአጭሩ ትልቅ ማብራርያ የሚሻው ርዕሰ ጉዳይ ነው። ጌታ ቢፈቅድ አንድ ቀን ስለዚህ ጉዳይ በሰፊው እጽፍ ይሆናል እስከዛ ህሊናህን ተከተል ከቤተሰቤህ ጋር በሰንበት እረፉ ወይም አምልኩ ደግሞም አሥሩን ትእዛዛት ለማክበርም ሞክሩ። ሆኖም ፍንጭ ቢጤ ልሰጥህ የምሻው ግን ሕጉ #መንፈሳዊ ነው THE LAW IS #SPIRITUAL “ሕግ መንፈሳዊ እንደ ሆነ እናውቃለንና For we have seen and are aware (know) that the Law [Torah] constantly exists being (is) spiritual (pertaining to spirit) JMT ሮሜ 7፡14” አንተና ቤተሰብህ ይህን እስክትገነዘቡ ድረስ በክርስቶስ ኢየሱስ በጭራሽ አትበስሉም ወይም አትጎለምኑም until you understand that truth you will never mature in the Lord Christ Jesus። በህጉ ያሉት ሊመጡ ላሉ መንፈሳዊ ነገሮች ጥላ ናቸውና፤ አካሉ ግን የክርስቶስ ነው። እናም ይህ የሰንበትን ሕግ እና ሌሎቹን ዘጠኝ የሚያካትት መሆኑን ስትረዳ ፣ “ሰንበትን ለማክበር” ያለህን መሰጠትና አቀራረብ ሕይወትህን ሙሉ በሙሉ ይለውጠዋል። “የሉቃስ ወንጌል 6፡5 #የሰው #ልጅ #ለሰንበት #ጌታዋ #ነው አላቸውም።” “እንግዲህ በምትበሉትም ሆነ በምትጠጡት ወይም በዓልን፣ ወር መባቻንና #ሰንበትን በማክበር ነገር ማንም አይፍረድባችሁ፤ እነዚህ ሊመጡ ላሉ ነገሮች #ጥላ ናቸውና፤ #አካሉ ግን #የክርስቶስ ነው። #ዐጒል #ትሕትናንና የመላእክትን አምልኮ የሚወድ ማንም ሰው እንዳያደናቅፋችሁ ተጠንቀቁ። እንደዚህ ያለ ሰው ስላየው ራእይ ከመጠን በላይ ራሱን እየካበ በሥጋዊ አእምሮው ከንቱ ሐሳብ ተሞልቶ ይታበያል፤ #ይህ #ሰው፣ አካል ሁሉ በጅማትና በማሰሪያ እየተጋጠመ ምግብንም እየተቀበለ እግዚአብሔር በሚሰጠው #ማደግ #ከሚያድግበት #ራስ ከሆነው ጋር ግንኙነት የለውም። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2፡16” “ወደ ዕብራውያን 4:9 እንግዲያስ የሰንበት ዕረፍት ለእግዚአብሔር ሕዝብ ቀርቶላቸዋል። “Consequently, a keeping of Sabbath (state of rest) is being left for (to; in) God’s people.” JMT “ክርስቶስ የሕግ ግብ ወይም ፍጻሜ ነውና። ወደ ሮሜ ሰዎች 10፡4 For Christ [is] an end of Law (or: for Christ [is the] goal of Law; for Christ [is] a termination of [the] Law; for Christ [is] perfection and maturity of law)”JMT እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው። ወንድም ቢኒ።