
Hailegiorgis Tefera to Binyam TA
February 18, 2019 · ቢኒዬ እባክህ ወንድሜ ይሔን እስቲ መልስልኝ በጌታ ፍቅር ፦ እግዚአብሔር ሁሉን ሲፈጥር ፈጠረ ይላል ሰውን ግን እንፍጠር አለ ይሔ ምን ይመስልሀል ወንድሜ ?ቢኒዬ እባክህ ወንድሜ ይሔን እስቲ መልስልኝ በጌታ ፍቅር ፦ እግዚአብሔር ሁሉን ሲፈጥር ፈጠረ ይላል ሰውን ግን እንፍጠር አለ ይሔ ምን ይመስልሀል ወንድሜ ?2You and Birtukan Gebru2 Comments1 ShareLikeCommentShare
Comments
- Binyam TA ሰላም ብራዘር ሃይለ ጊዮርጊስ፡ ከዚህ ሃሳብ ጋር ተመሳሳይ ከአንድ ወንድም ጋር ስነወያይ የሰጠሁት መልስ በሊንኩ ላይ ያልው ነው። ሆኖም በዚህ ጉዳይ ላይ ሁለት መረዳት ነው ያለኝ አንድ ከኤሎሂም ቡድን ጋር እያወራ ነው የሚል ሲሆን ሌላው በዚህ ሊንክ ላይ የገለጽኩት ነው። ኦሪት ዘፍጥረት 1፡26 እግዚአብሔርም[‘elohiym el-o-heem’ ኤሎሂም] አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ ከራሱ ጋድ አንድ የሆኑት ኤሎሂም የሚላቸው ደግሞ ልጆችን ነው። መዝሙረ ዳዊት 82:6 እኔ ግን፦ አማልክት[‘elohiym el-o-heem’ ኤሎሂም] ናችሁ፥ ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ፤ የዮሐንስ ወንጌል 10፡34 ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፦ እኔ፦ አማልክት[theos theh’-os a deity, the supreme Divinity፣ God መለኮት] ናችሁ አልሁ ተብሎ በሕጋችሁ የተጻፈ አይደለምን? https://www.facebook.com/photo.php?fbid=17256970975162412Edit or delete this
- Hailegiorgis Tefera Binyam TA ተመልሶልኛል እግዚአብሔር ይስጥልኝ ። ወንድሜ2Delete or
(11) Binyam TA – ከጥያቄና/መልስ የተወሰደ Binyam TA Israel Samuel Heaven ወንድም…
Binyam TAMay 21, 2018 · ከጥያቄና/መልስ የተወሰደ Binyam TA Israel Samuel Heaven ወንድም ቢንያም ኣንድ ጥያቔ ኣለኝ፡ከዚህ የምትለው ትምህርት ጋር ትገናኛለች፡፡በዘፍጥረት ያህዌ ከማን ጋራ ነበር የሚናገረው”ብምስላችን ሰው እንፍጠር”ብሃላም” ኣዳም ኣንድ እንደኛ ሁነዋልና”ይላል ክተሳሳተ በሃላ፡ይህ ቃል ከድሮ የስላሴ መገለጫ ስንጠቀምበት የነበረ ቀዳሚ ቃል ነው፡፡በእርግጥ የሰሶት መገለጫ ኣይደለም፡ብዙነት ስለሚናገር ግን ካለው ሶስትነት ልምምዶች ጋር ኣገናኝተን ይዘንዋል፡፡ለዚህ ሃሳብህ ምን ይሆናል?ተባርከሃል
ዘፍጥረት 1:26 እኛ ሲል ስላሴን አያሳይም ባይ ነኝ። የቃሉ ፍቺ ለተፈጥራዊው አእምሮ ስሜት ስለማይሰጠው አይቀበለውም ስሜቱን ያለ…መኮርኮሩ ትክክል ነው ይህ መንፈሳዊ እንጂ 5ቱ የስሜት ህዋሳት ሰፈር ዘንድ ስፍራ የለውምና። መንፈሳዊውን ነገር በመንፈስ ይምንረዳው ነውና። ብዙ ሰዎች በመቆጣትም በድንጋጤም እኛ ሲል ስላሴን አይደል እንዴ የሚያሳየው ብለውኛል እንደደረሱበት ነው እንግዲህ? ጥሩ ጥያቄ ነው እኛ የሚለው ቃል 3ቱ ሥላሴን እግዚያብሄሮች ለማሳየቱ በምን እርግጠኛ ይኮናል ትሆናለህ/ሽ? እኛ 2ለትም 3ትም 4ትም 5ትም ከዛም በላይ የሚያሳይ ሊሆን ይችላልና።
በቤተክርስቲያን ውስጥ ስለ ሥላሴ በአብያተ-ክርስቲያናት ክርክር ውስጥ ዋናው ነጥቡ ተደርጎ ይነሳል። አንድ ጊዜ አምላክ ሥላሴ እንደሆነ አድርገው ከተረዱና ካወቁ በኋላ እንደገና በእግ/ር ቃል ለመታረም ለብዙዎች ጭንቅ ነው። በውኑ እነሱ በትክክል 3 እግዚአብሔር ሲሉ እንደ ቃሉ ተረድተዋልን? ለራስህ/ሽ ቃሉን መመርመር መልካም ነው።
ይልቁኑ ይህ ቃል የእግዚአብሔርን ሙሉነት የሚያስረዳ በድርብ ክብሩ እራሱን የገለጠበት ነው እላለሁ።
የእግዚአብሔር አምሳያ ጣእም ድርብ ስለሆነ ወንዶችና ሴቶች መፍጠሩ የሱ መልክ ነው። የጥንት የስነ-መለኮት ምሁራን በስላሴ ላይ በጣም ትኩረት ስላደረጉበት በዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ለይ የእግዚአብሔርን ቃልን ዋናን ሃሳብ ሳያስተውሉት ቀርተዋል። “ከዚያም እግዚአብሔር አለ ሰውን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር አለ. እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፡ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፡ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ።
ሀይማኖት ያጔሯ : የእግዚአብሔር መንፈሳዊ መልክ ወንድና ሴት ነው ማለትም ማንም ሳያግዘው በራሱ ሊያዘጋጅ ይችላል። ይህን ለማለት ለሰው የሚቸግረው የሰው አእምሮ ከሥጋ ፍትወት ጋር የተቆራኘ ስለሆነ ግልፅ ነው። እግዚአብሔርን መንፈስ እንጂ ስጋ ስላልሆነ ፍትወተ ሥጋ አይመለከተውም። እርሱ ልእለ ተፈጥሮና ልእለ ፍጡራን ነውና ። የእግዚአብሔር ክብር ሌላ ነው የሰው ክብር ሌላ ነው የመንፈስ ክብር ሌላ ነው የሥጋ ክብር ሌላ ነው።
የቃሉ ፍቺ ያበራል።
“እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፡ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፡ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ።”
እንደምናስተውለው የእግዚአብሔር መልክ አምሳል እና አምሳያ በዚህ ቃል መሰረት የወንድን እና የሴትን ገጽታ ያካትታል። ይህ ባይሆን ኖሮ ምድራዊው የእግዚአብሔር አምሳያ ተብሎ የፈጠረው ሰው አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት የያዘ ባለ አንድ ፆታ ብቻ ሆኖ ይፈጥረው ነበረ። ሲፈጥራቸው ግን በአንድ አዳም ውስጥ ሁለት ፆታ ነበር እግዚአብሔር ግን ቡሃላ ለሁለት ከፈላቸው።
እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፡ በመልኩ? በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፡ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ;;
በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፡ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ? ግልጽ ነው። ።Gen 1 verse 27, “And God created man in His own image, in the image of God He created him; male and female He created them.” The #image and #likeness of #God, then, #includes#male and #female#aspects of #God. If this were not so, then the #earthly #image of God would #express just #one#sex, either male or female. ወንድም ቢኒ።
በእርግጥ የጥንት የነገረ-መለኮት ምሁራኑ አምላክን በአዎንታዊነት ለመግለጽ እውነትን ለማሳየት አልቻሉም። እግዚአብሔር በራሱ ሙሉ ስለሆነ ማንም ሳያግዘው መለኮታዊ ሙልአቱን ተጠቅሞ ማዘጋጀት እንደሚችል ከገለፁት እየተገዘቱ መገለል እንዳይደርስባቸው እውነትን መቅበር ይመረጣሉ።ሌላው ችግር ብዙዎቹ የጣዖት አምልኮ አምላኪዎችና አማልክቶች የሴት አገላለጾች ስለሚጨምሩ ሁሉ እርስ በራሱ እየተፈራራ ችግር ነበረ። ወንድም ቢኒ።See MoretagTag PhotocheckmarkDone TaggingpinAdd LocationpencilEdit5Mulugeta Shiferaw, Alemayeyhu Abebe and 3 others7 Comments3 SharesLikeCommentShare
Comments
- Neba Christ Tube ሶስትነቱን አዲስ ኪዳን ብቻ ሳይሆን ብሉይ ኪዳንም ይናገራል በተለይ ኢሳያስ 48፥1-16 ላይ እግዚአብሔር አንድ አምላክ በሶስትነት ፍፁም አንድነትና ሕብረት የሚኖር ዘለዓለማዊ አምላክ መሆኑን ይገልፃል፤
ተባረክ ወንድሜ!…Delete or hide this - Binyam TA Neba Christ Tubeሰላም ይሁን እህታችን። የቱጋ ነው እንደአንቺ አባባል “እግዚአብሔር አንድ አምላክ በሶስትነት ፍፁም አንድነትና ሕብረት የሚኖር ሶስት በአንድ አምላክ” መሆኑን የሚናገረው ክፍል? ሰው የልቡ ጣኦት ይዞ ያልተፃፈውን ወደሚመቸው ይተረጉመዋል። እኔ በዚህ ቃል የማየው አንድ እ/ር ነው። “በእኢሳያስ 48/12 እኔ ነኝ፤ እኔ ፊተኛው ነኝ እኔም ኋለኛው ነኝ።” አለ በራእይ ላይ የፊተኛው እኔ ነኝ ብሎ አንዱ እ/ር ደገመው እንጂ ሌሎች ከ3ቱ ስላሴዎች አንዱ እኛ አላለም። “የዮሐንስ ራእይ 1/17 …አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥” “የዮሐንስ ራእይ 1/8 ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፦ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል” ይከውልሽ እየሱስ ክርስቶስ እኔ ነኝ ብሎሽ እርፍ ።
ቁጥር 16 ላይ KJV እና በሱ ተጽኖ ስር የተተረጎሙ መጽሐፍሶች ሁሉ ትርጉሞች ሁሉ ብዙ የተሳሳተ የቃላት ትርጉም ስተት ይዘዋል ያንን ለማስተዋል በትጋት ካላጠናሽው በቀር ከአስተማሩሽ የበለጠ አስተዋይ መሆን አትችይም። የፃድቅ ሃብቱ ትጋቱ ነውና። [መዝሙረ ዳዊት 119/99 ምስክርህ ትዝታዬ ነውና ካስተማሩኝ ሁሉ ይልቅ አስተዋልሁ።} የስላሴን ትምህርት በቁጥር 16 ላይ መመስረት የአገዳ ቤት በመሰረቱ ክርስቶስ ላይ መመስረት ነው እሳቱ ሲመጣ ተረረር እያለ ይነድልሻልና። በመጀመርያ “ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ” ይሁን እንካ ብንል ችግር ላይ መውደቅሽ ነው 3ቱ ሳይሆን 2ቱ አምላኮች ሊሆኑብሽ ነው ። በዚያ ላይ መተርጎም የነበረበት ጌታ እ/ር መንፈሱን በእኔ ውስጥ ከኔጋር ላከ ነበር [AMP, And now the Lord God has sent His Spirit in and with me. NET, the Sovereign LORD has sent me, accompanied by his Spirit.]
ትንቢተ ኢሳይያስ 48/16 …..አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል።
ተመልከቺ ትክክለኛው ትርጉም እንዲህ መሆን ነበረበት። ተባረኪ።
(Isa 48:16 [AMP]) Come near to me and listen to this: I have not spoken in secret from the beginning; from the time that it happened, I was there. And now the Lord God has sent His Spirit in and with me.
(Isa 48:16 [NET2])
Approach me! Listen to this! From the very first I have not spoken in secret; when it happens, I am there.” So now, the Sovereign LORD has sent me, accompanied by his Spirit.Edit or delete this - Emabet Safawo አሜን እግዚአብሔርን የየዉ አንድም የለም ነገር ግን አንድያ ልጁ ተርኮታል የእግዚአብሔርን ሙሉ መንነት የሰዉ ልጅ እንድረደዉ መንፈስ በስጋ የተገለጠዉ የዘለለም መንፈስ ክርስቶስ ነው ።Delete or hide this
- Rahel Wolde NIV:Therefore go and make disciples of all nations, baptizing them in the name of #the Father and of #the Son and of #the Holy Spirit,
(Matthew 28:19)
የእግዚአብሔር መልክ ወንድ እና ሴት ነው የሚለው እውነት ነው.. ይህንንስ እንዴት እንተርጉመው?Delete or hide this- Binyam TA Binyam TA Rahel Wolde፡ ሰላም እህት ራሄል፡ ይህ በቤተክርስቲያን ጥንታዊ ታሪክ ብዙ ማረጋገጫ ያለ ነው ሊንኩን አስቀምጬላችሃለሁ። ማቴዎስ ወንጌል 28/19-20፡ የሚገርመው ጌታ ሲያዛቸው በማቴዎስ ወንጌል 28/19-20 ትክክለኛው በእ/ር ቃል ውስጥ በማስረጃ እንየው። “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በስሜ እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አ…See MoreEdit or delete this
- Rahel Wolde አመሰግናለሁ።1Delete or hide this
- Binyam TA Rahel Wolde፡ ሰላም እህት ራሄል፡ ይህ በቤተክርስቲያን ጥንታዊ ታሪክ ብዙ ማረጋገጫ ያለ ነው ሊንኩን አስቀምጬላችሃለሁ። ማቴዎስ ወንጌል 28/19-20፡ የሚገርመው ጌታ ሲያዛቸው በማቴዎስ ወንጌል 28/19-20 ትክክለኛው በእ/ር ቃል ውስጥ በማስረጃ እንየው። “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በስሜ እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።” ነበር ያላቸው ቡሃላ ሲተረጉሙን የስላሴን ትምህርት እጅ ጠምዝዘው ለማሰራጨት በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም ተብሎ እንዲጨመርበት ተገደደ። ሆናም ይህን እውነት የሚፈታላችሁ የእ/ር ቃል እራሱ ነው። ሃዋርያት የታዘዙትን ብቻ እንዳደረጉ ግልጽ ነው። “ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው” በስሜ አንጂ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም ብሎ አዝዋቸው ቢሆን ከቃሉ ፈቀቅ አይሉም ነበር። አስተውሉ እነሱ ለአንዴም እንካን በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም አላጠመቁም አልታዘዙምና ባዘዛቸው በእየሱስ ስም ብቻ ግን አጠመቁ።
የሐዋርያት ሥራ 2/38 ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።
የሐዋርያት ሥራ 8/16 በጌታ በኢየሱስ ስም ብቻ ተጠምቀው ነበር እንጂ ከእነርሱ በአንዱ ላይ ስንኳ ገና አልወረደም ነበርና።
የሐዋርያት ሥራ 10/48 በኢየሱስ ክርስቶስ ስምም ይጠመቁ ዘንድ አዘዛቸው። ከዚህ በኋላ ጥቂት ቀን እንዲቀመጥ ለመኑት።
የሐዋርያት ሥራ 19/5 ይህንም በሰሙ ጊዜ በጌታ በኢየሱስ ስም ተጠመቁ፤
የሐዋርያት ሥራ 19/4 ጳውሎስም፦ ዮሐንስስ ከእርሱ በኋላ በሚመጣው በኢየሱስ ክርስቶስ ያምኑ ዘንድ ለሕዝብ እየተናገረ በንስሐ ጥምቀት አጠመቀ አላቸው። ወንድም ቢኒ። https://www.facebook.com/photo.php?fbid=17236742477185261Edit or delete this