ክፍል አራት። የተፈጥራዊ አካል መነጠቅ(rapture) ውሸት ነው!


ክፍል አራት። የተፈጥራዊ አካል መነጠቅ(rapture) ውሸት ነው! ከውይይት የተጠቀሰ፤ በጌታ ፍቅር ሰላም ላንተ ይሁን ወንድም አዩ Ayu Wendimu ። ይህ የምከራከርበት ትልቅ አረስት አይደልም ለኔ ይህ አንደ መንፈሳዊ ኤለመንተሪ ወይም መጀመሪያ ትምህርት ነው። ተቀርፍፎ የሚወደቀውን ገለባ ገለባውን የስጋ ትምክትህን አልቆጥርብህም ስንዴ ስንዴውን የእ/ር ህይወት የያዘውን ቃሉን ብቻ በማየት እዛ ላይ ለመቆየት እጥራለሁ። እውነቱን በፍቅር ልንገርህ በቅድሚያ ለእግዚአብሄር ባለህ ቅናትና ፍቅር ደስ እንደሚለኝ እወቅልኝ በዚህ ጉዳይ ላይ ግን ምንም ገና አልገባህም ተፈጠራዊ እይታ እንጂ ምንም መንፈሣዊ እይታህ ለጊዜውም ሚዛኑን ወደ ተፈጥሮአዊ አጋድሎብሃል። ሁሉ የጌታ ሆኖ ሳለ አንተ በቡድን አድማ ታጥረካልና ገና አሁንም እኔ የጳውሎስ ነኝ፥ እኔስ የአጵሎስ ነኝ፥ እኔ ግን የኬፋ ነኝ፥ እኔስ የክርስቶስ ነኝ በሚለው ተይዘህ መስማት የምትሻውን እንጂ ስለ እውነት ብዙም ግድ አይልህም። ነፍስህ ኰርታለች፥ በውስጥህም ቅን አይደለችም ስልህ ቃሉን ከመነጋገር ይልቅ ምላሽህን እንድታስተውለው ነው እንዳልከው“የምትፅፈው ፅሁፍ እርባና ቢስ የማይጨበጥ የተደጋገመና የተሳከረ ሀሳብ ስላለው ነው” ማለትህ እራስህ የተሳከረ መንፈሳዊ እይታ እንዳለይ አላወከውም። በወንድምህም ዓይን ያለውን ጉድፍ እፍ ልበልልህ ከማለትህ በፊት፥ በመንፈሳዊ ዓይንህ ውስጥ ያለውን ምሰሶ ስለ ምን በቃሉ ሰይፍና ምሳር አስፈልጠህ አንድ በአንድ አታስወግደውም?

concerning spiritual things you have unbalanced spiritual discernment you still think heaven is a piece of real estate “out there” in space somewhere, rather than within your own thinking [within your heart and mind i.e. a state of being], then your road to enlightenment has reached an impasse which requires a total paradigm shift in your thinking. ጌታ እየሱስ የሚያወራው መንፈሳዊ ነገር ነው አንተ የምታወራው በእርሱ ዘመን እንደነበሩት እንደ አይሁድ ቲዮሎጂያን በተፈጥራዊ እይታ ተፈጥራዊ ነገርን ነው።

The Lord Jesus Christ came IN THE #FLESH to lead us #INTO THE #SPIRIT. I know you are our brother in Christ, It’s OK your criticism as you write it it’s according as the Lord hath called you I’m not offended by your ordainend in church realm, There is no one that Father God does not love, and when the time is right he will open your eyes to all things., 1Cor 7:17 What you are advocating right now that was my great Revelation 23 years ago in the Church Realm, but the Lord appeared brother, and give me the seed of Revelation not the whole tree, when he the spirit of truth guide me into all truth immediately I conferred not with flesh and blood follow the Lamb whithersoever he goeth! One Brother ones say “Do not submit God’s revelation to the criticism of some dead church member or preacher, for they like the birds of the air will steal away the seed of the truth before it has a chance to sprout or take root within you.”

2 የጴጥሮስ መልእክት 116 በብልሃት የተፈጠረውን ተረት የማንከተልበት ጊዜ ጌታ አሁን አምጥተዋል። The term “rapture” is not a scriptural or biblical term. “rapture መነጠቅየሚለው ቃል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል አይደለም። ቃሉ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪዎች የግሪኩን ቃል harpazo ሃርፓዞን ለመግለጽ የሚጠቀሙት theological አባባል ነው።

1 ተሰሎንቄ ምዕራፍ 417 ላይ የተጠቀሰውን “catching away” “መያዝ የሚያመለክት ነው። ይህ ደግሞ በሃሳብ ይሁን በመንፈስ ወደ ጌታ ህልውና ከመወሰድ መያዝን የሚያመለክት መንፈሳዊ እንጂ አካላዊ ንጥቀትን አያሳይም፡፡ እንድናስተውለው ለዚህ መነጠቅ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን ይህንኑ የግሪኩን ቃል harpazo ሃርፓዞ “catching away” “መያዝ ተጠቅሞ ጳውሎስ ሲናገር ሁለት ነገርን ነው የተናገረው አስተውል የአካል ንጥቀት አልተናገረም እንደተለመደው ለብዙ ሰው ጣኦት የሆነው የአማርኛው ትርጉም ሃሳቡን ሰውሮታል እንጂ እርሱ ያለው በመንፈሱ ማለት ነውየተነጠቀው በሥጋ ውስጥ ይሁን ወይም ከሥጋ ውጭ ወጥቶ እንደተነጠቀ አላውቅም ነው ያለው “whether #in #the #body, I cannot tell; or whether #out #of the #body KJV” “whether in body (or: in a body; or: within the midst of [the] body), I have not seen and do not know (I am not aware); whether outside of the body, I have not seen and do not know (I am not aware); JMT”

2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:2ከዐሥራ አራት ዓመት በፊት እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ የተነጠቀ በክርስቶስ አንድ ሰው ዐውቃለሁ፤ የተነጠቀው በሥጋ whether #in #the #body ይሁን ወይም ከሥጋ ውጭ whether #out #of the #body አላውቅም፤ እግዚአብሔር ግን ያውቃል። ሌላው ለትምህርታችን ምሳሌ ሊሆነን የሚችለው የዘብዴዎስ ልጅ ዮሐንስየተወደደ ደቀ መዝሙርበራእይ ፍጥሞ ደሴት ታስሮ ሳለ ከእስርቤቱ ሳይወጣ በአካል ሳይነጠቅ በመንፈስ ተወስዶና ተይዞ በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ ሲል በስጋ የአካል ንጥቀት እንዳልተካየደ ግልጽ ነው። በተደጋጋሚበመንፈስም ወደ በረሀ ወሰደኝ” “ በመንፈስም ወደ ታላቅና ወደ ረጅም ተራራ ወሰደኝሲል ግልጽ አድርጎታልና።

ጌታ ኢየሱስ ይልጅነት ህይወት አንዴት እንደሚመላለስ አሳይተዋል። ጌታ እየሱስ በስጋ በምድር እያለ የሰው ልጅ የሚኖረው በሰማይ[በመንፈስ ግዛት] ነው ይላቸው ነበር። የክርስቶስ ንቃተ ህሊና የሚያድረው በሰማይ[በመንፈስ ግዛት] ነው። ሃሌሉያ! ለኛ ከስጋዊ አእምሮ ወደ መንፈሳዊ አእምሮ ሽግግር ነው። ለውጡ ለአንዱ አለም ሞቶ ለሌላኛው ከፍ ላለው መንፈሳዊ ግዛት ህያው መሆን ነው። ለእ/ ከሞተው የአዳም ንቃተ ህሊና ለእ/ ህያው ወደ ሆነው ወደ ክርስቶስ ንቃተ ህሊና መነሳት፤ መያዝ፤ መነጠቅ ነው።! የዮሐንስ ወንጌል 3:13 ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው። ልጅነት እንዲህ ነው ሁለት እግሩ በምድር ቆሞ የሰው ልጅ በመንፈስ አሁን ተነጥቆ የሚኖረው በሰማይ[ the One continuously being (constantly existing) within the heaven] ነው ብሎ እርፍ! “And no one has ascended (stepped up) into the heaven, except the One descending (stepping down) from out of the midst of the heaven: the Son of Mankind (the Son of the human; Humanity’s Son; the Son of man) – the One continuously being (constantly existing) within the heaven . John 3:13

ጌታችን 41 በላይ ምሳሌዎችን መንፈሳዊውን ሚስጥር ለማስረዳት ተናግረዋል Rapturists የተነጣቃዊያን ዜግነት ለራሳቸው የሰጡ የንጥቀት ተስፈኞች የተባሉ ሁሉ ሆኑ የዘልአለም ስቃይ ሰባኪዎች ዶክትሪናቸውን ለማጽደቅ ሁሉም ነጥለው እውነተኛ ታሪክ ነው ብለው የሙጭኝ የሚሉት የአሥሩ ቈንጃጅት የሃብታሙ ሰውና አልአዛር ወዘተምሳሌዎችን በተለየ በመምረጥ ነው። እውነቱ ግን ለማስታወስ ያክል ጌታ ከተናገራቸው ምሳሌዎች መካከል። ከእንቅብ በታች ያለ መብራት፤ የሰናፍጭ ቅንጣት፤ ልባምና ሰነፍ አናፂዎች፤ በአረጀ ልብስ ላይ አዲስ እራፊ፤ በአረጀ አቅማዳ ላይ አዲስ ወይን፤ ዘሪና የመሬት አይነቶች፤ የተሸሸገ እርሾ በባህር ላይ የተጣለ መረብ፤ የጠፋ በግ፤ምህረት የማያደርግ ባርያ፤ አስሩ ቆነጃጅት፤ በጎችና ፍየሎች፤ ደጉ ሳምራዊ፤ የጠፋ ድሪም፤ ወዘተ……

እውነታው ግን ጌታ 41 በላይ ምሳሌዎችን ተናግረዋል አንዳቸውም በእውን የተፈፅሙ የተከሰቱ ታሪኮች ወደ ፊትም በተፈጥራዊ አለም ሊከሰቱ የተነገሩ አልነበሩም ሳይሆኑ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ወክለው የተነገሩ ናቸው። ተምሳሌትን ምሳሌነቱን ትተን ወደ እውነተኛ ታሪክ ስንከረብተው ወይም ስንገለብጠው ተምሳሌነቱ ይጠፋል።

ሁላችንም እንደምናውቀው ምሳሌ ወይም ተምሳሌት የሚነገረው በጥሬው ካለው ትርጉሙ ውጪ ሌላ ነገርን የሚወክል ቃል ወይም ሃረግ ነው። ለምሳሌ አንበሳ የጀግና ምሳሌ ነው፤ በግ ፤እርግብ የየዋህነት የንጽህና ምሳሌ ነው። በተፃራሪው ታሪክ ማለት ደግሞ ባለፉት ዘመናት እውን የነበሩ ክስተቶች ትውፊት፤ የሚዘገብ ክንዋኔ፤ ለምሳሌ ቀድሞ የነበረ ወግ፤ ጀብድ፤ ጀግንነት፤ የሃገር ኩራት፤ ወዘተ….ማንኛውም የሚያኮራ ይሁን አሳፋሪ ክስተት ሁሉ በዘመኑ ባለ ትውልድ እንደነበረየሚታሰብና የሚነገር የሚዘገብ የአላፊ ጊዜክስተትታሪክ ይባላል።

ጌታ እየሱስ በየትኛውም ቦታ ለፈሪሳውያን ይሁን ለህዝቡ ሲያስተምር ያለ ምሳሌ ሲያስተምር አታዩም። ምሳሌዎቹ ግን ብዙ ገፅታ ሊያሳዩ ይችላሉ። የአላፊ ግዜ የወቅቱ ሁኔታ ደግሞም የወደፊቱን የሚያመለክቱ ትንቢታዊ ሊሆኑ ይችላሉ።

ወንድማችን በምላሽህ ላይ እንዳስቀመጥከው አንተ እንደተረዳከው በተቃራኒው በሃጥአን የአካል ንጥቀት እኔ አላምንም በአንተ እይታ እንካን ቢታይ ተቃራኒውን ነው የሚያሳየው ለማለት ነው። ክፉው ቀድሞ እንደሚወገድ እንደቃሉ አምናለሁ። ክፉው ማን እንደሆነ / ያብራል። በአጠቃላይ አኔ እያወራሁ ያለሁት የእየሱስ ቃል መንፈስና ህይወት ነው። ይህ ሁሉ አመልካችነቱ መንፈሳዊ ነውን ነገር የሚያሳይ ነው። መንፈሳዊውን ነገር ለማስረዳትበምሳሌም ብዙ ነገራቸው እንዲህም አላቸውቃሉ ትዝ ይልሃል? የማቴዎስ ወንጌል 1334-35 ኢየሱስም ለሕዝቡ ይህን ሁሉ በምሳሌ ተናገረ፤ በነቢዩም፦ #በምሳሌ አፌን እከፍታለሁ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውንም እናገራለሁ የተባለው ይፈጸም ዘንድ #ያለ #ምሳሌ አልተናገራቸውም። The clouds that you and some of your followers are expecting are very natural clouds and many have tried guessing when this rapture would take place Just how far is ‘up’? 3000 feet, 10 feet, six hundred feet? Keep guessing bro. for we are not told! The word ‘#rapture does not appear in holy scripture!

ጌታ ከክፉ እንድትጠብቃቸው እንጂ ከዓለም እንድታወጣቸው አልለምንም። ቢልም እናንተ ከአለም በአካል እንጥቀት እንደ ሮኬት ልትተኮሱ ታልማላችሁ። እመንፈሳዊ አሰራር በመንፈስ ከእርሱ ጋር አስነሣቶን በመንፈስ በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር በመንፈስ እንዳአስቀመጠን ተሰውሮባቹሃልና። መንፈሳዊ በሩ እኔ ነኝ ያለው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛው ወደ አብ መግቢያው መንፈሳዊ በሩ ወለል ብሎ ተከፍተዋል፤ በዚህ መንፈሳዊ በር አሁን የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ መግባት ብቻ ሳይሆን በመንፈስ ይገባልም በመንፈስ ይወጣልም በመንፈስ ታምኖ ይሰማራል።

ቃሉን አስተውል በምላሽህ ላይመብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን #ሊቀበሉ የወጡ አሥር ቈንጃጅትን ትመስላለች። ….. ሙሽራው መጣ ተዘጋጅተው የነበሩትም ከእርሱ ጋር ወደ ሰርግ ገቡ ደጁም ተዘጋ። እንግዲህ ከዚህ ኢየሱስ ካቀረበው ምሳሌያዊ አነጋገር ቀሩ የተባሉት ሰነፎቹ ቆነጃጅት እንጂ ልባሞቹ ከሙሽራው ጋር እንደ ሄዱ ነው። በዚህ ምዕራፍ እንኳን ማን ወደ ሰርጉ ሄዶ ማን ከሰርጉ እንደ ቀረ በግልፅ እንረዳለን የተወሰዱ የተዘጋጁ ፃድቃን የቀሩት ያልተዘጋጁ ሀጢያን ናቸው።ጠቅሰካል መንፈሳዊ አመልካችነቱ ከመረዳትህ በፊት ወንድም እንደ አንተ ተፈጥራዊ እይታ አሁንም ብናየው ያላስተዋልከው አምስቱ ሰነፎች ደናግል ነበሩ ለኩራዛቸው በቂ ዘይት ስሌላቸው ሊገዙ ሄዱ። ገዝተውም ሁሉም ሙሽራውን ይጠቡቅበት ወደ ነበረው ቤት ተመለሱ ለሰርጉ ስለ ዘገዩ በሩ ተዘግቶ ነበር። ልባም ደናግሎች ደግሞ ሙሽራውን ይጠባበቁት ከነበሩበት ወደ ደጅ ወጥተው እያሉ ተቀብለውት አጅበውትም ማለት ነው ወደ ቤት ይዘውት ተመለሱ ደጁም ተዘጋ እንጂ ወደ ሰማይ አልተወነጨፉም:

በሌላ አነጋገር ሙሽራው ልባም ደናግሎችን ነጥቆ ወደ መንግስተ ሰማይ ይዞ ለመሄድ አልመጣም። ነገር ግን ልባም ደናግሎች ሙሽራውን ይጠባበቁት ወደ ከነበሩበት ወደ ደጅ ወጥተው በአክብሮት ተቀብለውት አጅበውትም ወደ ቤት ተያይዘው ተመለሱ ደጁም ተዘጋ ከጌታ ጋርም አብረው በሰርጉ ተገኙ።

በአየር ለመቀበል” “1ኛወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 4/17 ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል(Greek: apantesis ) ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።ወንድሞች ሁሉደመና” “አየርየሚሉ ቃላትን መልህቅ አርገው ይዝውታል። ደመና እና አየር ምን መንፈሳዊ ፍቺ እንዳላቸው ከማስተዋልህ በፊት አብሮ የተነገረው ቃል #ለመቀበል(Greek: apantesis ) የሚለው እንዲገባህ እስቲ ከቃሉ እናስተውል። እንዲገባህ ወደ ሐዋሪያው መልክት እንመለሰና 1 ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 4 ጌታን በአየር ላይ እንደ #ምንቀበለው ነግሮናል። ይህ ሁሉ መንፈሳዊ ትእይንት ነው ሆኖም እንደአንተ አካላዊ ወይም ተፈጥራዊ እይታ ቢሆን እንኳ ንጥቀቱ አየር ላይ #የምንቀበለውን እንጂ ተቀብለን በዛው እንሄዳለን አይልም መለክቱ። የግሪኩ ቃል መቀበል Greek: apantesis አፓንቴስስ ማለት ወዳጅን ከውጭ #በመቀበል አጅቦ ወደ ቤት #መመለስ ማለት ነው። a (friendly) encounter: meet or (to meet and return with as an escort) ይህ አታንቴስስ የሚለው የግሪኩ ቃል በአዲስ ኪዳን 4 ጊዜ ተጠቅሞበታል: ሙሽራው ስለ መጣ ደናግሎቹ ወጥተው እንዲቀበሉት የተነገራቸው ቦታ

በየማቴዎስ ወንጌል 251 በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ አሥር ቆነጃጅትን ትመስላለች።2 ከእነርሱም አምስቱ ሰነፎች አምስቱም ልባሞች ነበሩ። 3 ሰነፎቹ መብራታቸውን ይዘው ከእነርሱ ጋር ዘይት አልያዙምና፤ 4 ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው ጋር በማሰሮአቸው ዘይት ያዙ። 5 ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ። 6 እኩል ሌሊትም ሲሆን። እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ #ትቀበሉት (Greek: apantesis አታንቴስስ) ዘንድውጡ የሚል ውካታ ሆነ።

በነገራችን ላይ አንተ ክንፍ ያለው መላክ ይታይህ ይሆናል በቁጥር 16 ሙታን እዲነሱ መለከት የሚነፋው የትንሳኤው መልአክ ሚካኤል (HEBREW who (is) like God /ርን የሚመስለው) እደሆነ በዳንኤል 121-3 ግልጽ ያደርግልናል። /ርን የሚመስለው መንፈስ የሆነው በመንፈስ ያለማቋረጥ እየመጣልን ያለው ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ነው። ወደ ቃሉ ስንመለስ ልባም ደናግሎች ሙሽራውን ይጠባበቁት ወደ ከነበሩበት ወደ ደጅ ወጥተው በአክብሮት ተቀብለውት አጅበውትም ወደ ቤት ተያይዘው ተመለሱ ደጁም ተዘጋ : ስለዚህ ተቀበሉት Greek: apantesis አፓንቴስስማለት ወዳጅን ከውጭ በመቀበል አጅቦ ወደ ቤት መመለስ ማለት ነው። ይህ ቃል የተጠቀሰበት ሌላ ቦታ ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ሮም እስረኛ ሆኖ ሲወሰድ በሐዋርያት ሥራ 2815 ከዚያም ወንድሞች ስለ እኛ ሰምተው እስከ አፍዩስ ፋሩስና ሦስት ማደሪያ እስከ ሚባለው ሊቀበሉን(Greek: apantesis አታንቴስስ ) ወጡ፥ ጳውሎስም ባያቸው ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገነ ልቡም ተጽናና።

ታሪኩ ግልጽ ነው አማኞቹ ጳውሎስን ተቀብለው አጅበውት ወደ መጡበት ወደ ሮም ተያይዘው ተመለሱ እንጂ ተቀብለውት እስረኛው ወደ መጣበት ወደ እየሩሳሌም አልሄዱም። በመንፈሳዊነቱም ሆነ በአካላዊነት እንረዳው ጳውሎስ በአየር ላይ እንቀበለዋለን ሲል በአየር ላይ ተቀብለነው በዛው ወደ ሰማያት ይዞን ይወስደናል ማለቱ ሳይሆን አሁንም በመንፈሳዊነቱም ሆነ በአካላዊነት እንረዳው ሊገዛ ሲመለስ በአየር ላይ ተነጥቀን እንቀበለውና አጅበነው እያል ወደ ምድር አብረነው ልንገዛ ሁላችን እንመለሳለን ።ማለቱነው። እንግዲህ ትንቢታዊ መልእክት ያለው 10 ደናግል ስእላዊ መልኩ ይህን ነው የሚመስለው።

ብዙዎች የሚነጠቁት ጌታን ተቀብለው አጅበውት ለመመለስ ሳይሆን ከታላቁ መከራ ለማምለጥ ወደ ሰማያት እንደሮኬት ተፈትልከው ሲወስዳቸው ከመከራ ሲያመልጡ በምናባቸው እየሳሉ ይረዱታል። ለዚህ ማስረጃቸውምየዮሐንስ ራእይ 714 እኔም። ጌታ ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ አልሁት። አለኝም። እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፥ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ።አስተውሉ እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ እንጂ ያመለጡ አይልም። እንዳውም በመከራ ውስጥ ያልፉ ዘንድ የተገባቸው ናቸው እንዳውም ጌታ በማቴ24 ሲናገር ከዚያች ወራትም

ከመከራ በኋላ ነው ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ ያለው።

በአካል ንጥቀት ከሆነና መጭ ብለን ሁልጊዜም በሰማይ ላይ ለመቆየት ከሄድንና ካልተመለስን በምድር ላይ ለመግዛት ከላይ እንደተፃፈው ለእኛ የሚሆን መንገድ አይኖርም በምድር ያሉቱን አሕዛብ ፈጽሞ በጽድቅ በእግዚአብሔር ልጆች ክብር ላይገዙ ተሻረ ማለት ነው። የክርስቶስ ሙሽራም መቼም ቢሆን የእግዚአብሔርን ክብር ለመገለጥ ከሰማይ[ከመንፈስ ግዛት] ስትወርድ አትታይም።

The Holy Spirit will teach us ALL things (John 14:26 with His spiritual word which is very much higher than the natural or literal word of scripture. The Living Word, Jesus Christ, said that His words were spirit and they were life (John 6:63 I pray by God’s help to impress upon your minds, every man needs the spirit of revelation from God. I do not refer to that silly spirit so often found among zealous Christians that is always clamoring to come up with some new idea that they can call a revelation. It is not a flurry of fantastic fancies that we need, but a great spirit of wisdom and understanding given by God that will unfold to us the immutable almighty omniscience of God’s eternal purpose. That spirit of wisdom and understanding from God gives the heart of man the ability to receive and understand the purpose of His divine mind that has been planned from time immemorial. Bro. Bini ወንድም ቢኒ።

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal