ከውይይት የተጠቀሰ፤ ሰላም ይሁን። Alem Wenji የወደቁ መላእክት ወይስ የወደቁ መለክተኞች?


ከውይይት የተጠቀሰ፤ ሰላም ይሁን። Alem Wenji የወደቁ መላእክት ወይስ የወደቁ መለክተኞች? በመላው ክርስትያን ማህበረሰብ ዘንድ አንድ የተለመደው የእይታ አምነት በዚህ ጉዳይ ላይ አለ። አንድ የሚያምር የመላእክት አለቃ ከሌሎቹ መላእክት አንድ ሦስተኛውን ይዞ በእግዚአብሔርና በቀሪው የሰማይ ሠራዊት ላይ እንዲያምፁ እንዳርውጋቸውና እንደከሸፈበት የአብዛኛው የሰፊው ሕዝበ ክርስትና የጋራ እምነት ሆኖ ይነገራል ከተሸነፉ ቡሃላም ወደ መሬት ተጣሉ በኋላም እንደወደቁ መላእክት ተደርገው ይታያሉ። ይህን ተከትሎ ከዚያ በኋላ ሉሲፈር እንደገና ሰይጣን ተብሎ ተሰይሟል ነው አፈ ታሪኩ። ይህ ከፍ ያለ የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ ከተነሣ ከራርመዋል። የእ/ርን ህዝብ ለማጭበርበር እንዲመችም ማስረጃ በቃሉ ፍንትው ብሎ ማሳየት ስለማይችሉ እነዚህ የተሸነፉ የወደቁ መላእክቶች ከሰው ልጅ የመፈጠር ዘመን በፊት ጦርነታቸው እንደተከሰተ ይናገራሉ፡፡

ይህ ሃሳብ ከህዝቄላና ከኢሳያስ ሃሳቦች ጋር አግጭተው በስህተት የትተረዱት ቃል የሚከተለው ነው።

የዮሐንስ ራእይ 127 በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ። ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ፥ አልቻላቸውምም፥ 8 ከዚያም ወዲያ በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም። 9 ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።

በራእይ 1: 1 ይህ ሰው ከመፈጠሩ በፊት በሰማይ የተደረገ የሃላፊ ግዜ ጦርነት አለመሆኑን ግልፅ ያደርግልናል ግን ለወደፊቱ የሚሆነውን የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥን ተከትሎ የሚሆነውን በምልክት የገለጠው መንፈሳዊ የተለያዩ ዝርፈ ብዙ እውነታን የሚያሳይ ነው፡፡ ስለሆነም ከኦርቶዶክስ ሃይማኖት የጀመረው በሁሉም የክርስትና እምነቶነች ዘንድ የሰረጸው የአሸዋ መሠረት እውነት የድምፅ ሞገዶች ታጥቦ ይጠፋል ፡፡ ግን መጀመሪያ ይሁዳ ያለው ጥቅስስ ግዛታቸውን ጥለው ስለሄዱ መላእክት? ይህ ጥቅስ የበለጠ የተረጋጋ እውነት ነው ብለን እናስባለን? እንደዛ ከሆነ አንዳንድ ተጨማሪ እውነቶችን ለመስማት እንዘጋጅ፤ እነዙህ ጠላት የዘራውን መሠረታዊ የሆኑ ትምህርታዊ ስህተቶችን የሚያጠፋ ሌላ ቃል / አባት ይሰጠን ዘንድ ይችላልና።

የቀድሞው ትርጉም፤ 6 መኖሪያቸውንም የተዉትን እንጂ የራሳቸውን አለቅነት ያልጠበቁትን መላእክት በዘላለም እስራት ከጨለማ በታች እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ ጠብቆአቸዋል። ይሁዳ 1 6 ፡፡

መደበኛው ትርጉም፤ 6 የሥልጣን ስፍራቸውን ያልጠበቁትን ነገር ግን መኖሪያቸውን የተዉትን መላእክት በዘላለም እስራት እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ በጨለማ ጠብቆአቸዋል።

ከመጀመሪያው ቋንቋ አንድ ሁለት ቃላት እንድናስተውል ተጨማሪ አጭር ትምህርት ነክ ለማቅረብ ፍቀጅልኝ ፡፡

መጀምርያ

1ኛ፤ መታየት ያለበት ቃል መላክት የሚለው ነው። ቃሉ ከግሪኩ #angelion የተተረጎመ ሲሆን በአጭር ቃንቃ መለክተኛ ማለት ነው። ይህም ከእ/ የተላከ መለክተኛ ወይም እንደራሴ እስኮሆነ ድረስ ሲቶረጎም እንደተረጋሚው እይታ መልአክ ወይም መጋቢ ወይም ነብይ ሊሆን ይችላል። The word from the Greek is ‘angelion’ – a messenger envoy an “angel” or a pastor one who is sent, from God ለምሳሌ መጥምቁ የውሃንስ ሰው እንጂ ክንፍያለው መላክ አይደለም ይህን ቃል ስለ ከመጥምቁ ዮሐንስ ሲያስረዳ ጌታ የተጠቀመበትን እንይ። የማቴዎስ ወንጌል 1110 እነሆ፥ መንገድህን በፊትህ የሚጠርግ #መልክተኛዬን [#angelion መለክተኛ] በፊትህ እልካለሁ ተብሎ የተጻፈለት ይህ ነውና። 11 እውነት እላችኋለሁ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል #ከመጥምቁ #ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፤ በመንግሥተ ሰማያት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል።

2 መታየት ያለበትበዘላለምየሚለውን የአማርኛም ሆነ KJV የትርጉሞች ትርጉም ስህተት አለበት ቃሉ “Aidios” በእርግጠኝነትዘላለማዊማለት አይደለም። ትርጉሙ imperceptible or invisable በአዕምሮ ለመገንዘብ ወይም 6 የስሜት ህዋሳቶች ለመረዳት የማይቻል ወይም የማይታይ ማለት ነው። ቃሉ ሁለት ጥምር ክፍሎች አሉት “A” = not አይደለም እና “idios” = see or perceive ማየት ወይም ማስተዋል። ስለሆነምየማይታይ ወይም የማይስተዋል not see or not perceive” ፡፡ በፍጥረት ውስጥ ሊታይ የሚችል በእግዚአብሔር የስኬቶች ሥራዎች ውስጥ የማይታየውን ነገር የሚያመለክት ነው። What can clearly seen in creation attests or clear evidence to what CANNOT BE SEEN in accurate perception in God’s achievements. የመላእክት እስራት የማይታዩ እና ቃል በቃል የሚወሰድ አካላዊ ሰንሰለቶች አይደሉም ግንለመገንዘብ የማይቻል ወይም በአዕምሮ ወይም በስሜቶች ለመረዳት የማይቻል ወይም የማይታይሰንሰለቶች እንደ ማለት ነው፡፡

ሌላውየሥልጣን ስፍራቸውን ያልጠበቁትን ነገር ግን መኖሪያቸውን የተዉትንበግሪኩ የተቀመጠው ያልጠበቁትን እና የተዉትን የሚሉት ሁለት ቃላቶች በአላፊ ግዜ ሳይሆን በሂደት ላይ ያለ ሃሳብን ነው። aorist[(especially in Greek) an unqualified past tense of a verb without reference to duration or completion of the action.} active participle ሃሳብ በራሱ ድርጊቱ በአይነተኮር መልኩ እንደ አተያይ ንቁ ክፍለ ሁናቴን የሚያመለክት ሃላፊ ግዜን የማያረጋግጥ ነው። ያልተገለጸ እና በተሟላ ወይም ባልተሟላ ድርጊት መካከል ያለውን ልዩነት አመልካች ነው።

በእነዚህ ሁለት ቃላቶች ፍቺ ላይ የሌሉ ፍጹም አላፊ ግዜን የሚያሳዩ ሌሎች የግሪክ ስለ ተጠናቀቀ ድርጊት የሚናገሩ አሉ ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ቃላት በዋናነት ንቁ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉ ናቸው ፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን የዮሐንስ ወንጌል 1711 ቅዱስ አባት ሆይ፥ እነዚህን የሰጠኸኝን እንደ እኛ አንድ እንዲሆኑ በስምህ #ጠብቃቸው.” ይህ ቃል ጠብቃቸው ቃሉ የአላፊ ግዜ ሳይሆን በአሁን ሁኔታ ቀጣይ ድርጊትን የሚያመለክት በመከሰት ላይ ባለ ድርጊት ውስጥ ጥቅም ላይ ሊውል የሚችልበት ገላጭ ቃል ነው።

ከላይ ባስተዋልነው መሰረት፣ በቀደመው ያለፈ ድርጊትና እና ድርጊቱ ወቅታዊ በመካሄ ላይ ያለ perfect past and the imperative መሆኑን በሁለቱ መካከል ያለውን ልዩነት በቀላሉ ማየት እንችላለን ይህም አንዱ ቃል በይሁዳ 16 እና በዮሐንስ 1711 ላይ ያለው የቃል አጣጣል በመከሰት ላይ ያለን ኩናቴን የሚያሳይ ተመሳሳይ መልክት ያዘለ ነው ፡፡ እነዚህ ሁለት ግሶች የአላፊ ግዜ አመልካቾች አይደሉም።

ይህ እንግዲህ በማይታይ የማይበጠስ ሰንሰለት በጨለማ የታሰሩት መለክተኞች ይሁዳ ደብዳቤውን በጻፈበት ጊዜ በዚያን ጊዜ በህይወት የነበሩት ሰዎች ናቸው። መንፈሳዊ ስልጣናቸውንና ስፍራቸውን የተዉትን ያላቸውን የመጀመሪያ ማደሪያ ስፍራ አገልግሎታቸውን በአንድ ወቅት ከኢየሱስ ጋር በዙፋኑ ላይ ተቀምጠዋል የነበሩ ናቸው፡፡ በዛን ወቅት ግን ከጸጋው ወድቀው ወደ አሮጌው የሕጉ አገልግሎት እንደገና ወደ ሚገድለው ፊደል ተመልሰው የተንሸራተቱ በመሆናቸው በመንፈስ ቅዱስ ሃይል የሕይወትን ወንጌል ማገልገላቸውን በወቅቱ አልቀጥሉም ፡፡ እነዚህ አገልጋዮች መላእኮች ወይም መልእክተኞች (aggelos) በቀደመችው ቤተክርስቲያን ዘመን ከነበሩበት ትተው ወደሃላ የሄዱ ነበሩ ፡፡ መልእክተኞቹ ሰው መሆናቸውን በደብ በተጨማሪም የሚገልጥልን የሰዶምና ገሞራ አይነት ለፈተናቸው ተመሳሳይ ፈተናዎች ስር ወድቀዋል ብሎ ቁጥር 7 ይናገራል።

የየሰዶምና ገሞራ የመሰለባቸው በረከሰ አካሄድ በስጋ ፍላጎች የታሰሩ እንደ ሆኑ፤ ሰዎች አንጂ ከሰው በላይ ያሉ ስጋ ያልበሱ መናፍስት የሆኑ የሰማይ መላእክት በሥጋዊ ምኞት እንደማይፈተኑ (አስታውሱ) መላክት ቢሆኑ ኖሮ ጌታ እየሰስ እንደ ነገረንየሰማይ መላእክትም አያገቡም አይጋቡምም ስለሆነም ይሁዳ የሚያመለክተው መንፈስ ከሆኑ ከመላእክት ይልቅ ምድራዊ መልእክተኞች አገልጋዮችን ስለሆኑ እና በተበላሸ ምኞታቸው ምክንያት በጨለማ ተይዘው በቀደመችው ቤተክርስቲያን ዘመን በዚያን ጊዜ ነበሩ ናቸው ፡፡

ውሸትን ለማመን በሚያደርጉት ጠንካራ ምኞት የተነሳ ዛሬ በዘመናችን እንዳሉን አንዳንዶቹ ማለት ነው ፡፡2 ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 2 11-12 ስለዚህም ምክንያት፥ በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዓመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ ፍርድን እንዲቀበሉ፥ ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል።፡፡ ይህም በእሳቱ ሐይቅ መሃል እራሳቸውን በመሃል በማጣሪያው የእሳት ነበልባል እግዚአብሄር አስገብቶ መሰበርን ትህትናን ሀዘንን ተለማምደው ለንስሀ በሚሰራው መንፈሳዊ እሳት እራሳቸውን እስኪያገኙ እስከዚያ የፍርድ ቀን ድረስ ነው።

በየትኛው ዘመን ይሁን / ፍርዱ ቀን ጥሩ ነው የሚገልጠው የሰው ልጆችን ለመጉዳት በበቀልም ለዘላለም ለማጥፋት ወይም ለመረምሰስ ወይም በዘላለም እሳት ለመጥበስ ሳይሆን ሳይሆን የሚጠቀምበት ፍጥረቱን ለማረም፤ ለማቅናት፤ ለማደስ፤ ፅድቅን ለማስተማር፤ ሆኖ በቃሉ ተፅፎ ይስተዋላል። ኢሳ 26/9 ፍርድህን በምድር ባደረክ ጊዜ በአለም የሚኖሩ ፅድቅን ይማራሉ።” whan thy judgments are in the earth the inhabitants of the WORLD will learn righteousness.[uprightness & right standing with GOD.) isaiah 26/9 አስተዋላችሁን ፍርዱ ሲገለጥ በአለም የሚኖሩ ምንን ይማራሉ ይላል? ፅድቅን ይማራሉ። ሀሌሉያ! ሰውን ፅድቅ ለማስተማር የእ/ርን ፍርድ የሚጠይቅ ነው። ወንድም ቢኒ።

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal