ለአወዛጋቢ ጥያቄ በቃሉ የተሰጠ መልስ። ጥያቄ ከወንድም ማክ፤ “ፍቺ እና እንደገና ማግባት ዝሙት ነው ወይስ አይደለም?”


ለአወዛጋቢ ጥያቄ በቃሉ የተሰጠ መልስ። ጥያቄ ከወንድም ማክ፤ “ፍቺ እና እንደገና ማግባት ዝሙት ነው ወይስ አይደለም?” መልስ ከወንድም ቢኒ።፤ ሰላም ወንድም Mak Menge በዚህ ጉዳይ ላይ መልስ መስጠት ባልሻም ብዙ ወገኖች ዘንድ ሊጠራ የሚገባው እይታ ስላለ እውነቱን በእ/ር ቃል ልናየው ተገቢ እንደሆነ ስለተሰማኝ እ/ር እንደረዳኝ መጠን በቃሉ ውስጥ ላስተውለው እንደምችለው መጠን ልጻፈው። መጽሐፍ ቅዱስ በእ/ር ቃልም ይህን ሃሳብ በተመለከተ ግልጽ አድርጎታል። ከፍጥረት መጀመሪያ ግን እግዚአብሔር ወንድና ሴት አደረጋቸው፤ ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል፥ ወንድና ሴት ሲጋቡ  አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም።ዘፍ 2፡24 ፤  እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው ሲል ቅልብጭ ያለ ሃሳብ ሰጥተዋል። የማቴ 19፡5፤ የማር 107 በአጠቃላይ እ/ር መፋታትን ይጠላል እ/ር የጠላውን ልጆች ሊጠሉ የወደደውን ሊወዱ ተገቢ ነው ሆኖም ስለፍቺ በእ/ር ቃል በጥልቀት በጥቂቱ ማወቁ አይከፋም። ወደ ዝርዝሩ ከመግባታችን በፊት የሚቀጥሉት ከብዙ በጥቂቱ የእ/ር ቃል አቁዋም እንድናስታውስ ስለትዳር የተነገሩ ጥቂት የእ/ር ቃላት ለማስታወስ ያክል እነሆ እውነት የሚመሰረተው ቢያንስ በሁለትና በሰዎስት ምስክርነት ነውና። ኦሪት ዘዳግም 17፡6፣ 19፡15፤ ዘኍልቍ 35፡30። “የማቴዎስ ወንጌል 18፡16 በሁለት ወይም በሦስት ምስክር አፍ #ነገር #ሁሉ ይጸናል”

“ትንቢተ ሚልክያስ 2፡16 መፋታትን እጠላለሁ፥ ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፥ ልብሱንም በግፍ ሥራ የሚከድነውን ሰው እጠላለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ስለዚህ እንዳታታልሉ መንፈሳችሁን ጠብቁ።”

“1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7፡27 አግብተህ ከሆነ መፋታትን አትሻ” “መጽሐፈ ምሳሌ 24:3 ቤት(ቤተሰብ)[ HEBREW: bayith bah’-yith a house in the greatest variation of applications, especially family, etc.] በጥበብ ይሠራል፥ በማስተዋልም ይጸናል” በነገራችን ላይ ሰው በኃይሉ አይበረታምና ለሰው ልብ ጥበብንና ማስተዋልን የሚሰጥ እ/ር ነው። (መጽሐፈ ኢዮብ 38፡36 በውስጡስ ጥበብን ያኖረ፥ ለሰውስ ልብ ማስተዋልን የሰጠ ማን ነው? መጽሐፈ ኢዮብ 39፡17 እግዚአብሔር ጥበብን ከእርስዋ ከልክሎአልና፥ ማስተዋልንም አልሰጣትምና።)

ወደ ዕብራውያን 13፡4ጋብቻ በሁሉም ዘንድ ይከበር፤ መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር በአመንዝሮችና በሴሰኞች ሁሉ ላይ ይፈርዳል። 5ራሳችሁን ከፍቅረ ንዋይ ጠብቁ፤ ባላችሁ ነገር ረክታችሁ ኑሩ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር፣ “ከቶ አልተውህም፤ በፍጹም አልጥልህም” ብሎአል።

Heb 13፡4. The marriage is precious (of great price and honor) within all, and the conjugal bed unstained; yet God is continuously judging (separating and making a decision about) fornicators and adulterers.

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፡31 ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።32 ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፥ እኔ ግን ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እላለሁ። 33 ሆኖም ከእናንተ ደግሞ እያንዳንዱ የገዛ ሚስቱን እንዲህ እንደ ራሱ አድርጎ ይውደዳት፥ ሚስቱም ባልዋን ትፍራ።

ይህን መልስ በተሳሳተ መልክ ተረድቶ ፍቺን ማንም ሊጠቀምበት ቢያስብ እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል። ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች፤ ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች የሚለውን ቃለን ዳይረሳ።

 ይህ እውነት በእንዲህ ሳለ ከሰዎች ድካም ማለትም በሰው ልብ ጥንካሬ ደግሞም ከአለምም ማሰናከያ ሳይመጣ አይቀርምና በእንቅፋት የተጎዳ ሰው ካለ መጽሐፍ ቅዱስ ፍቺ እና እንደገና ማግባት ዝሙት አይደለም እንደሚል ወይም እንደማይል በቃሉ እውነት እናስተውል፡፡

ያስተውሉ ይህ መልስ ፍቺን ለማበረታታት የተጻፈ አይደለም ፣ ነገር ግን አንድ ግለሰብ ወይም ሰው ህጋዊ ከሆነው ፍቺ በኋላ እንደገና ካገባ እንደ እ/ር ቃል መሰረት ከሆነ ፣ ምንዝር እንዳልፈፀመ እውነቱን በቃሉ እውነት አጥርተን ለማሳየት እና ካልተገባ የኩኔኔ ህሊና ወይም የጥፋኝነት ጸጸት ከክፉ ሕሊና ለመንጻት ልቦናን በቃሉ የእውነት ጥሩ ውኃ ረጭተንና አጥበን ነጻ ለመልቀቅ ብሎም እንደ እ/ር ፈቃድ እንደገና የተጎዳው አገግሞ በጎ ህሊናን ለመመለስ ይረዳል በሚል ነው። በቅድሚያ ፍቺ በራሱ ሳይሆን ኃጢያት የኃጢያት ፍርድ ነው ፡፡ ብዙ የእንግሊዝኛም ሆነ የአማርኛ ትርጉሞች ማቴ፤ 5፡32 የኢየሱስን ቃል እንደገና ማግባት እንዳወገዘ ወይም እንደሚከለክል አስመስለውታል ፣ እንድናስተውል የፈለኩት ግን ጽሑፉ በተሳሳተ መንገድ እንደተተረጎመና  ከዚያም በተሳሳተ መንገድ ቤተክርስቲያን እንደተረዳችው በቃሉ እውነት እናየዋለን ፡፡ ጌታ ኢየሱስ ሕጉን አልሻረም ወይም በመጣስ ህጉን አልደፈረም ሙሴ ስለ ሰው ልብ ጥንካሬ ይህችን ትእዛዝ ጻፈዋልና። በዘዳግም፤ 24 1-4 በተለይም ፍቺን እና እንደገና ማግባትን ይፈቅዳል ፡፡

ዘዳግም፤ 24፡1 ሰው ሴትን ወስዶ ቢያገባ፥ የእፍረት ነገር ስላገኘባት በእርሱ ዘንድ ሞገስ ባታገኝ፥ የፍችዋን ጽሕፈት ጽፎ በእጅዋ ይስጣት፥ ከቤቱም ይስደዳት። 2 ከቤቱም ከወጣች በኋላ ሌላ ወንድ ብታገባ፥ 3 ሁለተኛውም ባል ቢጠላት፥ የፍችዋንም ጽሕፈት ጽፎ በእጅዋ ቢሰጣት፥ ከቤቱም ቢሰድዳት፥ ወይም ሚስት አድርጎ ያገባት ሁለተኛው ባልዋ ቢሞት፥4 የሰደዳት የቀድሞ ባልዋ ከረከሰች በኋላ ደግሞ ያገባት ዘንድ አይገባውም፤ ያ በእግዚአብሔር የተጠላ ነው፤ አምላክህም እግዚአብሔር ርስት አድርጎ የሰጠህን ምድር አታርክስ።

የማቴዎስ ወንጌል 5፡32 እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ አመንዝራ ያደርጋታል፥ የተፈታችውንም የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል። የቀድመው ትርጉም።

መደበኛው ትርጉም። ማቴ. 5፡32 እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በላዩ ላይ ስታመነዝር ካላገኛት በስተቀር፣ ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ እንድታመነዝር ያደርጋታል፤ በዚህ ሁኔታ የተፈታችውን ሴት ያገባም እንዳመነዘረ ይቈጠራል።

Matt 5:32. “Yet I, Myself, am now saying to you folks that every man proceeding in dismissing (loosing-away) his wife – outside of a case of infidelity (fornication; prostitution; sexual misconduct) – proceeds in making her a subject of adultery. JMT

በቅድሚያ ማወቅ ያለብን ሰው ፍቺ ውስጥ ሊገባ የተፈቀደለት እጅግ ጠባብ በሆነ ምክኛት ብቻ መሆኑን ነው: – በአማርኛም ትርጉምም ይሁን በኪንግ ጄምስ ውስጥ ቃል በቃ የጌታን ቃል ስናስተውል ኢየሱስ ፍቺ ውስጥ ሊገባ የሚችለው ብቸኛው መንገድ እና ሌላ ማግባት እንደሚችል ጌታ ኢየሱስ የተናገረው ብቸኛው መንገድ እንደሚከተለው ነው ፡፡ “pornia” ማለት በዝሙት፤ በዘማዊነት “ዝሙት አዳሪ” forniction “pornia ማለትም prostitution ዝሙት አዳሪ ወይም ዝሙት አዳሪነት ፡” ሲጠናወት እንደ ማለት ነው። ግን ደግሞ sexual immorality የወሲባዊ ግንኙነት ብልግና  ማለትም ሊሆን ይችላል። ነገሩ ብዙ ገጽታን አመልካች ሊሆንም ይችላል። ብልግና በራሱ ብዙ የጋጠወጥ ባህርይንም በውስጡ ሊያካትት ይችላል፡፡  ጳውሎስ አንድ ሰው ለቤተሰቡ የሚያስፈልገውን መሰረታዊ ነገር የማያቀርብ ከሆነ ፣ “ከማያምነው ይልቅ የከፋ ነው #WORSE than an infidel [WORSE GREEK፡ cheiron khi’-rone ፡ more evil or aggravated assault (physically, mentally or morally):–worse sorer. የበለጠ ክፋት ወይም የባሰ የከፋ ጥቃት አድራሽ። (በአካል ፣ በአእምሮ ወይም በስነምግባር): ፣ የከፋ ዘራፊ ፡፡” ነው ሲል ጳውሎስ የሞራል ውድወት ኢ-ስነምግባራዊነትን ነግሮናል ፡፡ “1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 5፡8 ነገር ግን ለእርሱ ስለ ሆኑት ይልቁንም ስለ ቤተ ሰዎቹ የማያስብ ማንም ቢሆን፥ እምነቱን የካደ ከማያምንም ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው።”  አንድ ሰው በተመሳሳይ ሁኔታ ቤተሰቡን በማያቃርጥ ፈሰስ የሚበድል  ወይም ሚስቱን ወይም ልጆቹን የሚያሰቃይ ከሆነ immorality ከብልግና ጋር ተመሳሳይ ነው ፡፡ በእንደዚህ ዓይነት “ሥነ ምግባር የጎደለው” ሁኔታ የትዳር አጋር ዘንድ መታሰር እንዳለበት ተደርጎ መታሰብ የለበትም ፡፡

በማቴዎስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 32 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን በተሳሳተ መረዳት እና የተሳሳተ ግምቶች ላይ በመመስረት የቤተክርስቲያን አስተያየት ለዘመናት ከፍቺ በኋላ እንደገና ማግባት ምንዝር እንደሆነ ሊቃውንትዋ አስተምራዋል እያስተማሩም ነው ፡፡ በዚህ የከረመ የተሳሳተ እይታ ለኩነኔ ሆኖ ለተወሰኑት ውጤቱ ማለትም ትዳራቸው በፍቺ የፈረሰ ከሆነና እና እንደገና ከተጋቡ ብዙ ሰዎች ያለማቅማማት ተገልለው ከአብያተ ክርስቲያናቶቻቸው ህብረትም የተባረሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ ሌሎች ደግሞ የመሪነት ቦታ ተነፍግዋቸው ይኖራሉ አልያም “በቋሚነት በምንዝር በመኖራቸው” ታርጋ ተለጥፎባቸው የጥፋተኝነት ስሜት የተያዙ ሆነው ተስብረው ያዘግማሉ ፡፡ ይህ አሳዛኝ ሁኔታ እንደቃሉ አስፈላጊ ፍርድ አይደለም ብዙ ጊዜ በዚህ ሸለቆ ያለፉ ሰዎች በሚሰማቸው መገለል ምክኛት መራራ ስር ያበቅሉና ከምእመናን የምላስ ጅራፍ ለመሰውር በማመፅ ከእግዚአብሔር ቤትና ህዝብ ሁሉንም ትተው ብን ብለው ይጠፋሉ እራሳቸውን አግልለው ይኖራሉ፡፡ ሌሎችም በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በፍቺ ለተጎዱ የተፈፀመ ግፍ ነው ብለው በቃሉ ያዝናሉ አሊያም እንደገና ማባት ባለመፈቀዱ በቀሪው የሕይወት ዘመናቸው ነጠላ ወይም ላጤ ሆነው ለመቆየት ባለመቻላቸው ምክንያት በተስፋ መቁረጥ ይዋልላሉ ፡፡

አሁን እናስተውል በአሮጌው ኪዳን ቃል የነበረው እ/ር ስጋ ከመልበሱ በፊት ጌታ በነብዩ በኩል ከእስራኤልና ከይሁዳ ጋር ያለው ቃል ኪዳን የጋብቻ ቃል ኪዳን እንደሆነ አስጠንቅቆ ተናግረዋል። ፍቺ እና ጋብቻን በተመለከተ የእግዚአብሔር ሕግን ስናስተውል ሁለቱም ወገኖች ማሟላት ያለባቸውን ሁኔታዎችን የሚገልጽ ቅድመ ሁኔታ (ውል) ያዘለ ነው ፣ እናም አንደኛው ወገን የጋብቻ ውሉን ወይም ኮንትራቱን ከጣሰ ተጎጂው ወገን በውሉ ላይ ስለደረሰበት ጥፋት በሕግ ሊጠየቅ ይችላል ፡፡ በቀላሉ ማብራራት የጋብቻ ኮንትራቶች conditional contracts ሁኔታዊ ውሎች ናቸው ፡፡ በጥንት ጊዜያት ሁሌም የጋብቻ ውል  እንደዚህ ነበር ፣ እናም በዚህ ረገድ የእግዚአብሄር ህግ ጋር ሙሉ በሙሉ መንፈሳዊ ተይንቱም ከዚህ ጋር ይስማማል።

ፍቺ ማለት በቃሉ መሰረት ከጋብቻ ውሉ ውስጥ ሙሉ  ለሙሉ ሕጋዊ በሆነ መልኩ መለያየት ማለት ነው።  ምክንያቱም ሁሉም የጋብቻ ውሎች በሁለት ወገኖች መካከል የገቡትን ቃለ መሐላ ማክበር ይኖርባቸዋልና ፡፡ እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር በሲና ተራር በፈጸመው በጋብቻ ፣ እስራኤል (ሙሽራዋ) ለሥልጣኑ ለመገዛትና ህጎቹን ለመታዘዝ ተስማምታለች ( ዘጸ. 19 3-8 ) ፡፡ እግዚአብሔር በሌላ በኩል መንግሥቱንና በኩርነት ወይም የልደት መብቱን በረከቶችን ሁሉ ሊሰጣቸው ተስማምተዋል ፡፡ እነዚህም ክብርን ፣ ጥበቃን ፣ ምግብን እና ልጆችን ያካትታሉ ( ዘፍ. 12 1-3 ) የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እስከጠበቁ ድረስ፥ በመንገዱም ሰከሄዱ ድረስ፥ እግዚአብሔር እንደ ማከላቸው ለእርሱ የተቀደሰ ሕዝብ አድርጎ እንደሚያቆማቸው ቃል ኪዳን ገባላቸው። ሆኖም እስራኤል ሙሉ በሙሉ ታዛዥ ለመሆን ስለማትችል ይህንን ውል ጣሰች ፣ ንስሐም አልገባችም ፡፡ እናም ባሏ ፈትቶ ከቤቱ አስወጣት ይህ እንዲገባን ጠለቅ ብለን እንየው።

በማርቆስ 10: 2-9 ፈሪሳውያንም ቀርበው፦ ሰው ሚስቱን ሊፈታ ተፈቅዶለታልን? ብለው ሊፈትኑት ጠየቁት። ፡፡ ጌታም  መልሶ፦ ሙሴ ምን አዘዛችሁ? ብሎ መልሶ ጠየቃቸው ፡፡ እነርሱም፣ “ሙሴማ የፍች ወረቀት ጽፎ እንዲፈታት ፈቅዶአል” አሉ። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ ሙሴ ይህን ሕግ የጻፈላችሁ ልባችሁ ደንዳና በመሆኑ ነው። ነገር ግን በፍጥረት መጀመሪያ እግዚአብሔር ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፤ ከሚስቱም ጋር ይጣመራል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ፤ ከእንግዲህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ሁለት አይደሉም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ያጣመረውን ማንም አይለየው። ሲል ፍቺ መጀመሪያ ላይ የተቋቋመውን ፍጹም የሆነውን የፍጥረት ቅደም ተከተል እንደማያብራራ አብራራላቸው ፡፡ በሌላ አገላለጽ ፍቺ ጥሩ ነገር አይደለም ነገር ግን የሰዎች ልቦች ደንዳኖች ስለሆኑ የተበላሹ የተሰበሩ የጋብቻ ውሎችን ለመቆጣጠር ህጋዊ ዝግጅት መደረግ  ነበረበት ፡፡ ለጋብቻ ኩነቶች ብቻ ሳይሆን በተመሳሳይ ምክንያት እግዚአብሔር በመጀመሪያ ደረጃ የሚመደቡ ግድያዎችን የሰውን ነስፍስ የነጠቀን ነፍሱን እንዲከፍል የሞት ፍርድን አቋቁሟል ፡፡ ሆኖም ነገሩ ከጥንት ጀምሮ እንዲህ አልነበረም እግዚአብሔር አብረን መስምምነት እንድንኖር አድርጎ ፈጥሮናልና ፡፡ ግን የሰዎች ልቦናዎች ጥንካሬ የተነሳ  እንዲህ ዓይነቱን የሃይለኝነት የጥፋት ወንጀል ለማስቆም በጣም አስፈላጊ ውሳኔ ነበር ፡፡ BROTHER BINYAM T. ALEMAYEHU WRITINGS

እውነታው  ሁሉም ህጎች በመጽሐፉ የሚገኙት በሰዎች ልብ ጥንካሬ ምክንያት ብቻ ነው። ሰዎች ሁሉ ፍጹም ቢሆኑ ኖሮ ሕጎች በልባችን ውስጥ ስለተጻፉ የውጨኛው ሕጎች አያስፈልጉም  ነበር። ጳውሎስ 1 ጢሞቴዎስ 19  ፡፡ሕጉ የተሰጠው ለጻድቁ አይደለም ነገር ግን ለዐመፀኛው እና ለማይታዘዘውነው ሲል ግልጽ አድርጎታል። ስለሆነም በሰዎች ክፉ ምኞቶች እና ድርጊቶች ላይ በህግ የተወሰነ ቁጥጥር እንዲኖር ብሎም በምድር ላይ ዓመፀኛ ሰዎች እስካሉ ድረስ ህጉ በስራ ላይ ውሎ ሊጸና ይገባ ነበር።

ስለሆነም  በቀድመው ኪዳን ህጉ ወሳኝ እና አስፈላጊ ነበር። አሁን ባለው አዲሱ ኪዳን የሰዎች ሁኔታ በጸጋው የማስቻል ብቃት በትክክል ለእ/ር ፈቃድ እንዲገዙ ለማስቻል አቅም ስላለው እግዚአብሔር በአዲሱ ቃል ኪዳን ሙሉ በሙሉ ወደ መጡ ክርስቶስ ወይም ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነውና ከጸጋ በታች እንጂ ከህግ በታች አይደሉም። ወደ ሮሜ ሰዎች104 የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና። 1310 ፍቅር ለባልንጀራው ክፉ አያደርግም፤ ስለዚህ ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው። እናም ሰዎች በክርስቶስ ከመሆናቸው በፊት በፍቺ ላይ የተሰጡት የእግዚአብሔር ሕጎች እጅግ አስፈላጊ ናቸው ፡፡ ክርስቶስ ወይም ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ስለሆነ እርስ በርሳችሁ በመዋደድ ወይም ሌላውን የሚወድ ሕግን ሁሉ ፈጽሞታልና ሮሜ 13፡8። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል በፍቅር የማይኖር ግን ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም። ስለዚህ መፋታት በክርስቲያኖች መካከል አስፈላጊ መሆን የለበትም። ሆኖም ክርስቲያኖችም ቢሆኑ ብዙውን ጊዜ ሕግን የሚጥሱ እና ለእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ የማይታዘዙ ናቸው ፡፡ በዚህ ምክንያት ለፍቺ  ያለው ኩናቴ እንኳን ለክርስቲያኖች አንዳንዴ አስፈላጊ ናቸው ፡፡

የጋብቻ ውል በክርስቲያኖች መካከል ሲቋረጥ እና በተለይም አንዱ ወይም ሁለቱም ወገኖች ንስሃ ለመግባት እና ህጋዊውን ስርዓት ለማስመለስ እምቢ ካሉ ፍቺ ብቸኛው መፍትሄ ሊሆን ይችላል። ጥፋተኛው ወገን ይህንን ለማድረግ ፈቃደኛ በማይሆንበት ጊዜ ንፁሁ  አካል ውሉ ውሉን እንዲያከብር እ/ር አይጠብቅበትም ፡፡የማቴዎስ ወንጌል 24
12 ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ባትጠፋም ትቀዘቅዛለችና እስከ መጨረሻ በፍቅር የሚጸና ግን እርሱ በሞቀ ፍቅር ከእ/ር ጋር ሊኖር ይችላል። የትዳር ኮንትራቱ ሁል ጊዜ ሁኔታዊ ነው። ስለሆነም ኢየሱስለልብህ/ሽ ጥንካሬየሚለው አባባል መፋታት ራሱ ኃጢአት ነው ለማለት አይደለም ፡፡ አስታውሱ እግዚአብሔር ራሱ ፍቺ ከስራኤል ጋር ፈጽመዋል በኤር፤ 3: 8 ጌታ አምላክ እ/ር  እስራኤልን በመፋቱ ኃጢአት አልሠራም ፡፡ ይህን በተመለከተ ወደ መጨረሻው እናያዋለን።

ለመሆኑ ከፍቺ በኋላ ኢየሱስ እንደገና ማግባትን በሕገወጥነት ነው እንዴ ያስቀመጠው?

ፍቺው ከተፈጸመ በኋላ እንደገና ማግባት ምንዝርና መሆኑን ለማሳመን ማቴዎስ 5:31 , 32 ብዙ ሰዎች የሚጠቀሙበት ዳግም በጥሞና መፈተሽ ያለበት በጣም አስፈላጊው ምንባብ ነው ፡፡ ያነባል

31 “ ‘ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ የፍቺ ወረቀት መስጠት አለበትእንደ ተባለ ሰምታችኋል። 32እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በላዩ ላይ ስታመነዝር ካላገኛት በስተቀር፣ ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ እንድታመነዝር ያደርጋታል፤ በዚህ ሁኔታ የተፈታችውን ሴት ያገባም እንዳመነዘረ ይቈጠራል።

Matt 5:31. “Now it was declared, ‘Whoever should dismiss (loose-away; = divorce) his wife, let him give a certificate of divorce (or: a divorce; a standing-off and away) to her.’32. “Yet I, Myself, am now saying to you folks that every man proceeding in dismissing (loosing-away) his wife – outside of a case of infidelity (fornication; prostitution; sexual misconduct) – proceeds in making her a subject of adultery JMT

(Matt 5:31 [AMP])It has also been said, Whoever divorces his wife must give her a certificate of divorce.32 But I tell you, Whoever dismisses and repudiates and divorces his wife, except on the grounds of unfaithfulness (sexual immorality), causes her to commit adultery, and whoever marries a woman who has been divorced commits adultery. [Deut. 24:1-4]

በዚህ ክፍል ላይ ብዙ ትርጉሞች እንደተተረጎመው ኢየሱስ ፍቺን እና እንደገና ማግባትን በጥብቅ ያወገዘ ይመስላል በዚህም የእግዚአብሔር ህግ ከመለኮታዊ ሥነምግባራዊ እሴቶች በታች መሆኑን ያሳያል ፡፡ በእውነቱ ፍቺ አንድ ሰው ዝሙት እንዲፈጽም የሚያደርገው ከሆነ በእግዚአብሔርም በዝሙት ዕዳ ተጠያቂነት ሕግ መሠረት መፋታት ራሱ ኃጢአት በሆነ ነበርና። እንደገና ማግባትም ምንዝርናን በህጉ የሚስከትል በሆነ ነበር፡፡ ሆኖም ቀጥለን እንደምናሳየው ኃጢያት እንዳልሆነ ነው፡፡

በህጉ አታመንዝር/ሪ  ተብሎ ሰው ታዘዋል። ጌታ ሲናገር በእያንዳንዱ ሁኔታ በተጠየቀው ጥያቄ ውስጥ ወይም የተራራው ስብከትበሚያስትምርበት ግዜ ያለው ሕግ የፈርስያዊያንና የሱዱቃዊያንን እይታ እየቀየረ በሚከተለው አዲስ የእይታ ቅርጸት ለህዝቡ ሲሰጥ ይስተዋላል  በአጭሩ ጌታ እየሱስ ከስጋ ወደ መንፈስ ሊመራን ነው የመጣው ሲባል በሙሴ ህግ በስጋ መገረዝ፡ ቅዱስ ቀናትን መጠበቅ ሰንበትን መጠበቅ፡ ወዘተ ብዙ ነገሮች አካላዊ ግዴታዎች ነበሩ። ጌታ በጠበቀ ሁኔታ በመንፈስ ህግ መጣ በማቴ 567 ሲናገር እንደዚህ ሲባል ሰምታችሃል(በሙሴ ህግ ማለት ነው) እኔ ግን እዲህ እላችሃለሁ እያለ ምሳሌን ሰጠ

በሙሴ ማል በክርስቶስ ፈጽመህ አትማልበሙሴ ጠላትህን ጥላ በከርስቶስ ጠላትህን ውደድበሙሴ አትዘሙት በክርስቶስ ወደ ምንጩ ሄዶ በአይንህ አይተህ በልብህ አትመኝእያለ ከስጋ ድካም ወደ መንፈስ ብርታት ዘወር እድንል አስተምራልግን እኔ እላለሁ ይህ ማለት ኢየሱስ እነዚህን ሁሉ መለኮታዊ ሕጎች ሁሉ ያስወግዳል ማለት አይደለም ወይም እያንዳንዱን በተለየ ወይም በተሻለ ነገር ይተካል ማለት አይደለም ፡፡ የእግዚአብሔር ሕግን አልሻረም እሱ ማይስማማው የሕጉ  የፈሪሳዊያንን ምኩራብ ትርጓሜ  መንፈስ ነው። በሌላ አገላለፅ ኢየሱስ  ነገር ግን እኔ እላችኋለሁ እያለ መግዳልን ህጋዊ አላደረገውም ማመንዘርንም እንዲሁ በሙሴ አትዘሙት በክርስቶስ ወደ ምንጩ ሄዶ በአይንህ አይተህ በልብህ አትመኝየማቴዎስ ወንጌል 5፡28 እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል።

ለማጠቃለል ያህል የተራራው ስብከትዓላማው በሕጉ ትርጓሜ እና አተገባበሩ ላይ መለኮታዊ እይታን የማሻሻል ነበር ፡፡ የሕጉ እውነተኛ መንፈስ በሽማግሌዎች ወግ ለዘመናት ጠፍቷል ፡፡

ከላይ ያየነውን አውድ በማሰብ  ጌታ ኢየሱስ ሕጉን እንዳላጠፋ ካወቅን ማቴዎስ 5 : 31 – 32 በበለጠ ዝርዝር እንመልከት ፡፡ እነዚህ ሁለት ጥቅሶች ከላይ ሲጀምር አታመንዝርየማቴዎስ ወንጌል 527-28  በሚለው የአስተያየቱ ክፍል  ናቸው ስለሆነም የአስተያየቱ የመጨረሻ እምብርት ከፍቺ እና ከጋብቻ ጋር በተያያዙ ህጎች መዘርዘር ነው ፡፡ ቁጥር 31 በቀላሉ ዘዳምን ያመለክታል ፡፡  ኦሪት ዘዳግም 241 ሰው ሴትን ወስዶ ቢያገባ፥ የእፍረት ነገር ስላገኘባት በእርሱ ዘንድ ሞገስ ባታገኝ፥ የፍችዋን ጽሕፈት ጽፎ በእጅዋ ይስጣት፥ ከቤቱም ይስደዳት። 2 ከቤቱም ከወጣች በኋላ ሌላ ወንድ ብታገባ አላመነዘረችም

 ወንዶች ሚስቶቻቸውን በሕግ ከመፍታታቸው ወይም ከመተዎቸው አልያም ከማስወጣታቸው በፊት  ለሚስቶቻቸው እንዲሰጣቸው #WRITTEN bill of divorcement ለፍትሃዊነት የፍቺ ጽሕፈት ጽፎ በእጅዋ  እንዲሰጡ እግዚአብሔር በህጉ ጠየቀ ፡፡ ቁጥር 2 በእርግጥ የተፈቱ ፈት የቀድሞ ሚስቶች ሕጋዊ ፍቺ ካደረጉ በኋላ እንደገና እንዲያገቡ ህጉ ፈቅ ደዋል ፡፡ በመቀጠል ትክክለኛ ትርጉም ማግኘት እንድንችል የመጀመሪያው ግሪክ ቁልፍ የሆኑ ጥቂትቃላትን በማስተዋል በማቴዎስ 5:31/ 32 ላይ አብረን እንይ ፡፡

31 ሚስቱን የሚፈታት(apoluo ሙሉ በሙሉ ነፃ የሚያደርጋት፤ የሚለቃት ፣የሚያሰናብታት ፤የሚተዋት ፣ ወይም (በተለይም) ለፍቺ።)  ሁሉ የፍችዋን ጽሕፈት ይስጣት ተባለ። 32 እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ አመንዝራ ያደርጋታል፥ የተፈታችውንም የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል።

አስተውሉ የዙህን paraphrase የዓረፍተ-ነገሮችን ግልጸት። በህግ በጋብቻ ከታሰረችበት መፈታትዋን  በጽሑፍ የሰፈረ የፍቺ ሂሳብ በእጅዋ ሳትይዝ  እንደገና ካገባች ምንዝር እንደፈጸመች ህጉ ይቆጥራታል  ነው ሃሳቡ፡፡ BUT I SAY UNTO YOU እኔ እላለሁ እላለሁ (ፍቺ ወረቀትዋን ሳይሰጣት በኢፍትሃዊ መንገድ ባዶ እጅዋን ካስወጣት እንደዚህ ባለ ሁኔታዎች ውስጥ ተገዳገባች ሲጨንቃት ሌላ ሰው  ብታገባ በሕገወጥ በሆነ መንገድ  እንዳገባች ስለሚቆጠር ባልዋ በተዘዋዋሪ አመንዝራ ያደርጋታል ስለሆነም ባልዋ በትክክል እሷን በህጉ መሰረት ሳይፈታ ከቤቷ ያስወጣን ሴት ወይም (የፍቺ ወረቀቶች ሳይኖራት) የተለቀቀችውን ሁሉ ያገባ  እስዋ ብቻ ሳትሆን ያገባትም ያመነዝራል ምክንያቱም የሌላውን ሰው ሚስት እንዳገባ ህጉ ይቆጥራታልና።  

ጌታችናና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እዚህ ላይ እያወቀሰ ያለው ሚስቶቻቸውን የፍቺ ወረቀትዋን ሳይሰጣት በኢፍትሃዊ መንገድ ባዶ እጅዋን ካስወጣት የባቢሎናዊያን ዘይቤ በግፍ ሚስቱን እንድታመነዝር እያስገደዳትነው። ይህ እንዳይሆን ሲፈታት በእግዚአብሔር ሕግ ስለፍቺ በተደነገገው መሰረት ከመለያየት ይልቅ እዚህ ላይ ህጉን አምጾ ሴቲቱን እያወረደ ነው ስለዚህ የቃሉ ፍርድ ተጠያቂ ያደርገዋል፡፡ በእ/ርተጠያቂነት ህጎች ስር ባልዋ የፍቺ ወረቀቶች ሳይኖራት ስላባረራት ይህች ሴት እንደገና ማግባት ከፈለገች በዝሙት ጥፋተኛ እንድትሆን ያደርጋታልና ባልዋ በአምንዝራዊ ህግ ተጠያቂነት በእ/ር የፍርድ ስር ይጠየቃል፡፡ ስለዚህ የዚህ ሐተታ አጠቃላይ ሃሳብ  በወቅቱ ቲዮሌጅያን ፈሪሳውያን በትርጓሜዎቻቸው ያልተሸፈነ የሕግ ነጥብ ወደ ትኩረታቸው ማምጣት መሆኑን ፍንትው አድርጎ ያሳየናል ፡፡

የሚፈራ ሌላ ሃሳብ  “KJV “saving for the cause of fornication በአማርኛ ትርጉማችን “ያለ ዝሙት ምክንያት የሚለው ሐረግስ? ይህ ምን ማለት ነው? ብዙ ሰዎች ይህ ማለት አንድ ሚስት ምንዝር ከፈጸመች መፍታት የተፈቀደለት እንደሆነ ይሰማቸዋል ፡፡ ሆኖም ቃሉካልሆነ በስተቀርአይልም። በተጨማሪም በሙሴ ህግ ምንዝር የሚያስከትለው ቅጣት ሞት እንጂ ፍቺ አይደለም። እንደዛ ከሆነ ስለዚህዝሙት fornicationምን ማለት ነው? የትዳር ጓደኛን በዝሙት fornication ጉዳይ የፍቺ ወረቀቶችን መጣል ለምን ችግር የለውም?

የዝሙት fornication ትርጉም  በግብረ፟ስጋ የወሲብ ሃጥያት ከመውደቅ ያለፈ ትርጉም ሰጥቶ መጽሃፍ ተጠቅሞበታል።

በጣም የተለመደው የዝሙት ዓይነት ሽርሙጥና ነው። ኦሪት ዘጸአት 22፡16 ሰው ያልታጨችውን ድንግል ቢያስታት፥ ከእርስዋም ጋር ቢተኛ፥ ማጫዋን ሰጥቶ ሚስት ያድርጋት።  በህጉ አንድ ሰው ካላገባች ሴት ጋር ያለጋብቻ ወሲባዊ ግንኙነት ከፈጸመ አመነዘረ ይባላል። በህጉ መሰረት መፍትሄው ካሳዋን ሰጥቶ ማግባት ነው ( ዘጸ. 22:16 ፣ 17 ) ወይም የአባትዋ ቤት እምቢ ካሉ የድንግልናዋ ካሳዋን ሰጥቶ ንስሐ ገብተው መለያየት ነው። ሆኖም የዝሙት fornication  የሚለው የቃሉ ፍቺ ሌሎች ሕገወጥ የወሲባዊ ግንኙነቶችን ዓይነቶችንም ይሸፍናል ፡፡ ዕብራውያን 12:16 ላይ ኤሳውን fornicator ሴሰኛው ይለዋል። “16ለአንድ ጊዜ መብል ሲል ብኵርናውን እንደ ሸጠው እንደ ዔሳው ማንም ሴሰኛ fornicator ወይም እግዚአብሔርን የማያከብር ሆኖ እንዳይገኝ ተጠንቀቁ።” ነገር ግን ዝሙት  ስለመገዛቱ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ አንድም የለም ፡፡ ግን ዘፍጥረት 26፡34 ዔሳውም አርባ ዓመት ሲሆነው የኬጢያዊ የብኤሪን ልጅ ዮዲትን፥ የኬጢያዊ የኤሎንን ልጅ ቤሴሞትንም ሚስቶች አድርጎ አገባ ይላል ፡፡ በመጻሕፍት ውስጥ ካለው ተዛዝ አንጻር ከከነዓናውያን ሚስት እንዳያገባ እግዚአብሔር የሰጠውን ትእዛዝ እንደጣሰ ግልጽ ነው ፡፡ ስለዚህ ፣ ሕገ-ወጥ ጋብቻ ተብሎ ሊመደብ ይችላል ፡፡

“ዝሙትfornication” የሚለውን ቃል እንደገና “በ 1 ቆሮ 5፤ 1፡ 1 በአጭር ቃል በመካከላችሁ የዝሙት ርኵሰት እንዳለ በርግጥ ይወራል፤ እንዲህ ያለው ርኵሰት በአረማውያን ዘንድ እንኳ ታይቶ የማይታወቅ ነው፤ የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው አለና” ስለዚህ ጳውሎስ “ዝሙት” የሚለውን ቃል የተጠቀመበት በዘሌዋውያን 18 ፡7 ፡ 8 የተከለከለውን ሌላ ህገ-ወጥ ጋብቻን ወይም የግብረ ሥጋ ግንኙነትን ለመግለጽ ነው ፡፡ “7 የአባትህን ኃፍረተ ሥጋና የእናትህን ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ እናትህ ናት፤ ኃፍረተ ሥጋዋን አትግለጥ።8 የአባትህን ሚስት ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የአባትህን ኃፍረተ ሥጋ ነው።”

ሊአላው ምሳሌ ይሁዳ ቁ፤7 እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል። “እንግዳ ሥጋ.” ይህ ደግሞ በግልፅ የወሲባዊ ኃጢአት ነው ፣ ስለ ወሲባዊ ዝንባሌዎቻቸው በመጽሓፍ የተመዘገበ ብቸኛው ነገር የግብረ-ሰዶማዊነት ወይም “ሰዶማዊነት” ነው ( ዘፍ፤ 19 4-8 ) ፡፡ እንዳስተዋልነው እነዚህ ምሳሌዎች ሁሉ አንድ የጋራ ተመሳሳይ ነገር አላቸው ሁሉም ሕገወጥ ወሲባዊ ግንኙነቶች ናቸው ። ስለሆነም ሁለቱንም ወገኖች አንድ ላይ ለማጣመር የሚያስችል የጋብቻ ውል በመጽሐፍ የለም ፡፡ በሌላ አገላለጽ እግዚአብሔር በመጀመሪያም ይህ አይነት “ጋብቻን” አያውቀውም  ከመጀመሪያውም ጀምሮ ከውል ባዶ ነው።

ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ በዝሙት fornication ጉዳይ የትዳር ጓደኛን “መተው” (ያለ ፍቺ ወረቀቶች መለየት) ችግር የለውም ብሎ የተናገረበት ምክንያቱ ግልፅ ነው ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ በሕግ የሚያስገድድ የጋብቻ ውል በመካከላቸው አልተገኘም። ስለሆነም አንድ ሰው የፍቺ ወረቀት እንዲጣስ ወይም ወደ እግዚአብሔር ሕግስ እንዴት ይግባኝ ማለት ይችላል? እግዚአብሔር እንደዚህ ዓይነት ህገወጥ ኙኝነት ላይ የፍቺ ወረቀቶችን አይፈልግም ፡፡ ሆኖም ባልና ሚስቱ እንደዘመናይ እንደዚች የዚህ ዓለም ትዕዛዝ ካሉ ከአለማዊያን ስልጣን ስር ከሰብአዊነት መንግሥት የጋብቻ ፈቃድን ካገኙ እናም ለፍቺም መጠየቅ አለባቸው ግልጽ ነው። ምክንያቱም የሰብአዊ  መንግስታት የእግዚአብሔር ህግ የማያውቃቸውን በርካታ የጋብቻ ግንኙነቶች ያውቃሉ ፡፡ ምንም እንኳን ሁለቱ ወገኖች የጋብቻ ውል ቢፈርሙም እንኳን እግዚአብሔር የሚጸየፈው ግብረ ሰዶማዊ ጋብቻ፣ የቅርብ ዘመድ ጋብቻ ወይም በሌላ መንገድ የተከለከሉትን ግንኙነቶች እግዚአብሔር አያውቃቸውም፡፡ የፍቺ ወረቀቶች አስፈላጊ የማይሆንበት ሌላ ጉዳይ በዝሙት አዳሪነት ውስጥ ያለ ርክክብ ነው ፡፡ እያወራ ያለው አያድርስ እንጂ ጌታ እያለ ያለው የፍቺ ወረቀቶች አስፈላጊ የሚሆነው በህጋዊ ጋብቻ ለተጣመሩት መለያየታቸው ቁርትጥ ከሆነ ነው።

ከላይ ያየነውን አውድ በማሰብ  ጌታ ኢየሱስ ሕጉን እንዳላጠፋ ካወቅን ማቴዎስ 5 : 31 – 32 በበለጠ ዝርዝር እንመልከት ፡፡ እነዚህ ሁለት ጥቅሶች ከላይ ሲጀምር አታመንዝርየማቴዎስ ወንጌል 527-28  በሚለው የአስተያየቱ ክፍል  ናቸው ስለሆነም የአስተያየቱ የመጨረሻ እምብርት ከፍቺ እና ከጋብቻ ጋር በተያያዙ ህጎች መዘርዘር ነው ፡፡ ቁጥር 31 በቀላሉ ዘዳምን ያመለክታል ፡፡  ኦሪት ዘዳግም 241 ሰው ሴትን ወስዶ ቢያገባ፥ የእፍረት ነገር ስላገኘባት በእርሱ ዘንድ ሞገስ ባታገኝ፥ የፍችዋን ጽሕፈት ጽፎ በእጅዋ ይስጣት፥ ከቤቱም ይስደዳት። 2 ከቤቱም ከወጣች በኋላ ሌላ ወንድ ብታገባ አላመነዘረችም

በማጠቃለያ እንዲገባን በአሮጌው ኪዳን የነበረው ጋብቻ ከባሪያይቱ እንጂ ከጨዋይቱ ጋር እንዳላሆነ ቃሉ ይነግረናል። በገላትያ 4 እነዚህ ሴቶች እንደ ሁለቱ ኪዳኖች ናቸውና። ከደብረ ሲና የሆነችው አንዲቱ ለባርነት ልጆችን ትወልዳለች፥ እርስዋም አጋር ናት።25 ይህችም አጋር በዓረብ ምድር ያለችው ደብረ ሲና ናት፤ አሁንም ያለችውን ኢየሩሳሌምን ትመስላለች፥ ከልጆችዋ ጋር በባርነት ናትና። ባሪያ በመሆንዋም ለባልዋ መታዘዝ ግዴታዋ ነው።[እየሱስ ቃል የነበረው እ/ር ስጋ ከመልበሱ በፊት በነበረው ቅርጽ]የሰጣት ተስፋ አሁንም ቃሌን በእውነት ብትሰሙ ኪዳኔንም ብትጠብቁ፥ የሚል በሁኔታዎች የተደገፈ ቃል ኪዳን ነበረ። ኦሪት ዘጸአት 19/5 አሁንም ቃሌን በእውነት ብትሰሙ ኪዳኔንም ብትጠብቁ፥ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአሕዛብ ሁሉ የተመረጠ ርስት ትሆኑልኛላችሁ፤6 እናንተም የካህናት መንግሥት የተቀደሰም ሕዝብ ትሆኑልኛላችሁ። ለእስራኤል ልጆች የምትነግራቸው ቃል ይህ ነው።

ይህ የአጋር አይነት የጋብቻ ግኑኝነት ነው። እስራኤል ከእ/ር ጋራ በሲና ተራራ በቃል ኪዳኑ በጋብቻ በተሳሰሩ ጊዜ ያለውንም ያሳያል። ይሄ የአሮጌው ኪዳን ጋብቻ ነው። በዘፅአት 19/5 እስራኤል ለባልዋ ለመታዘዝ መማል ነበረባት። እስራኤልም የእ/ር አገልጋይ ሚስቱ ሆነች። ይሄ መጥፎ አይደለም በዛው አንጻርም እ/ር ከህዝቡጋር ሙሉ ለሙሉ የሚፈልገው ጋብቻ አይደለም። የተሻለ ህብረትን ይሻልና ለዚህም ነበር በአጀንዳው ውስጥ እስራኤልን ሊፈታት እቅዱን ያስቀመጠው።

እስራኤል ለብዙ ክፍለዘመን ታማኝ ሳትሆን ዘማዊሆና አስቸግራው ጌታ በመጨረሻ የፍቺ ወረቀትዋን ሰጣት “ትንቢተ ኤርምያስ 3፡8 ከዳተኛይቱም እስራኤል ስላመነዘረች ስለዚህ ፈትቻታለሁ የፍችዋንም ወረቀት ሰጥቻታለሁ አታላይ እኅትዋ ይሁዳ ግን እንዳልፈራች እርስዋም ደግሞ ሄዳ እንደ ጋለሞተች አየሁ።

Jer 3፡8 And I saw, when for all the causes whereby backsliding Israel committed adultery I had put her away, and given her a bill of divorce; yet her treacherous sister Judah feared not, but went and played the harlot also.” ከዛም በተሻለ ነገር ላይ የተመሰረተውን አዲሱን ኪዳን አደረገ።

ጌታ እስራኤልን አግብቷት ባይሆን ኖሮ ፈፍቺ ወረቀት መስጠት ባላስፈለገው ነበር። ይህን ሲያደርግ እራሱ በሙሴ በኩል የሰጠውን የጋብቻ ህግ እያከበረ ነበር፡

‘አንድ ሰው አንዲት ሴት ካገባ በኋላ፣ አሳፋሪ ነገር አግኝቶባት ባይደሰትባት፣ የፍቺ ወረቀት ጽፎ በመስጠት ከቤቱ አስወጥቶ ይስደዳት። ከቤቱ ከወጣች በኋላ ሌላ ባል ብታገባ፣ ሁለተኛ ባሏም እንደዚሁ ጠልቷት የፍቺ ወረቀት በመስጠት ከቤቱ አስወጥቶ ቢሰዳት ወይም ቢሞት፣ ከዚያ በኋላ የፈታት የመጀመሪያ ባሏ፣ የረከሰች በመሆኗ እንደ ገና መልሶ ሊያገባት አይችልም፤ ይህ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት አስጸያፊ ነው። አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ላይ ኀጢአት አታምጣ። ‘ዘዳግም 24:1-4

ይህ ህግ ትንቢታዊ እንደነበር እ/ር ከህዝቦች ጋር እንዴት እንደሚሰራም በእስራኤል ጋብቻ ላይ ያሳየናል።

እምናወራው ያለው ስለ መንፈሳዊ ነገር እደሆነ እንደ ተሰመረበት ይሁንና መንፈሳዊውን ጋብቻ በምሳሌ የሚያስስረዱ ሁለት አይነት የጋብቻ ግንኝነቶች እንዳሉ ሳይወሳ መታለፍ የሌለበት ነው። በገላቲያ4: 22/31-22 አንዱ ከባሪያይቱ አንዱም ከጨዋይቱ የሆኑ ሁለት ልጆች ለአብርሃም እንደ ነበሩት ተጽፎአልና። 23 ነገር ግን የባሪያይቱ ልጅ እንደ ሥጋ ተወልዶአል፥ የጨዋይቱ ግን በተስፋው ቃል ተወልዶአል። 24 ይህም ነገር ምሳሌ ነው፤ እነዚህ ሴቶች እንደ ሁለቱ ኪዳኖች ናቸውና። ከደብረ ሲና የሆነችው አንዲቱ ለባርነት ልጆችን ትወልዳለች፥ እርስዋም አጋር ናት። 25 ይህችም አጋር በዓረብ ምድር ያለችው ደብረ ሲና ናት፤ አሁንም ያለችውን ኢየሩሳሌምን ትመስላለች፥ ከልጆችዋ ጋር በባርነት ናትና። 26 ላይኛይቱ ኢየሩሳሌም ግን በነጻነት የምትኖር ናት እርስዋም እናታችን ናት።

27 አንቺ የማትወልጅ መካን፥ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ፥ እልል በዪና ጩኺ፤ ባል ካላቱ ይልቅ የብቸኛይቱ ልጆች በዝተዋልና ተብሎ ተጽፎአል። 28 እኛም፥ ወንድሞች ሆይ፥ እንደ ይስሐቅ የተስፋ ቃል ልጆች ነን። 29 ነገር ግን እንደ ሥጋ የተወለደው እንደ መንፈስ የተወለደውን በዚያን ጊዜ እንዳሳደደው ዛሬም እንዲሁ ነው። 30 ነገር ግን መጽሐፍ ምን ይላል? የባሪያይቱ ልጅ ከጨዋይቱ ልጅ ጋር አይወርስምና ባሪያይቱን ከልጅዋ ጋር አውጣት። 31 ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ የጨዋይቱ ልጆች ነን እንጂ የባሪያይቱ አይደለንም።”

ሐዋሪያው ስለ ሁለት ኪዳኖች በሁለቱ ሚስቶች እንደ ሚመሰሉ ነግሮናል ማለትም አጋርና ሳራ ባሪያይቱና (bondwoman) ነጻ ያልሆነችው ሴትና ጨዋይቱ (freewoman) ነጻይቱ ሴት ማለት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ሁለት የተለያዩ የጋብቻ አይነቶች ነበሩ። ሰውየው ባሪያይቱን ካገባ ያላቸው ግንኝነት የጌታና የባሪያ ነው። እዲህ አይነትዋ ሚስትም ያላት መብት ውስን ሲሆን በቤተሰብ ውሳኔ ውስጥ ምንም ድምጽ የላትም። ባልዋ እድሉን ሊያቀርብ ይችላል ነገር ግን እደዛ እዳያደርግ የተወሰነ ነበረ።

ይህ የአጋር አይነት የጋብቻ ግኑነት ነው። እስራኤል ከእ/ር ጋራ በሲና ተራራ በቃል ኪዳኑ በጋብቻ በተሳሰሩ ጊዜ ያለውንም ያሳያል። ይሄ የአሮጌው ኪዳን ጋብቻ ነው። በዘፅአት 19/5 እስራኤል ለባልዋ ለመታዘዝ መማል ነበረባት። እስራኤልም የእ/ር አገልጋይ ሚስቱ ሆነች። ይሄ መጥፎ አይደለም በዛው አንጻርም እ/ር ከህዝቡጋር ሙሉ ለሙሉ የሚፈልገው ጋብቻ አይደለም። የተሻለ ህብረትን ይሻልና ለዚህም ነበር የነገርን መጀመርያውን ብቻ ሳይሆን ፍጻሚውን በሚያውቅ ማንነቱ በመለኮት አጀንዳው ውስጥ እስራኤልን ሊፈታት እቅዱን ያስቀመጠው።

“ትንቢተ ኤርምያስ 3፡8 ከዳተኛይቱም እስራኤል ስላመነዘረች ስለዚህ ፈትቻታለሁ የፍችዋንም ወረቀት ሰጥቻታለሁ አታላይ እኅትዋ ይሁዳ ግን እንዳልፈራች እርስዋም ደግሞ ሄዳ እንደ ጋለሞተች አየሁ።

Jer 3፡8 And I saw, when for all the causes whereby backsliding Israel committed adultery I had put her away, and given her a bill of divorce; yet her treacherous sister Judah feared not, but went and played the harlot also.” ከዛም በተሻለ ነገር ላይ የተመሰረተውን አዲሱን ኪዳን አደረገ።

አዲሱ ኪዳን የተመሰለው በነጻይቱ ሴት በሳራ ነው። በአዲሱ ኪዳን የተመሰረተው ጋብቻ መታዘዝ በሚለው ሃሳብ ላይ የተመሰረተ አይዳለም። ሁለት የተጋቡ ወንድና ሴት ከተስማሙ እዲታዘዙ መናገር የሚያስፈልግ አይደለም። አንዳቸው አንዳቸው አንድን ነገር እንዲያርጉ በስልጠን የሚያዙበት ምክንያት የለም ስምምነቱ አለና ። የቤተሰብ ስልጣን የሚገለጠው የስምምነት እጥረት በመካከላቸው ካለ ነው።

በዚህ ምንያት እ/ር ድል ነሺ ካልሆኑበቀር ለማግባት ሃሳቡም የለውም። ድል ነሺነው ከእ/ር ጋር ወይም ከጌታ እየሱስ ክርስቶስ ጋር የሚስማማው። ድል ነሺ የጌታን አይምሮ ያውቃል አሊያም እንዲያውቀው ይሻል። የእ/ርን ፈቃድ ሲያገኘውም ከፈቃዱ ጋር ተስማምቶ እራሱን ያገኘዋል። አልያም ከፈቃዱ ጋር ፍጹም አንድ እስኪ ሆን መረዳትን ለመቀበል እስከ መጨረሻው ይሻል። በመንፈሳዊ እድገት የመማር ሂደት ወስጥ በእርግጥም ድል ነሺው የእ/ርን ሃሳብ ቶሎ ላያስተውል ይችላል:: እንደ እ/ር አገልጋይ እ/ርን ይታዘዛል። ሙሉ ግንዛቤን ገና ስላላገኘ ፈቃዱን በማድረግ ብቻ ገና አልረካም የእ/ርን አይምሮ እስኪ ያገኘውና ገብቶት በሙሉ ስምምነት እራሱን እስኪ ያገኘው ወደ ፊት ይዘረጋል።

ከእ/ር ጋር አለመስማማት ምክንያቱ የመረዳት እጥረት ነው። መላው አለምን እ/ር እንደሚያየው ብናየው እ/ር የሚያደርገውን ሁሉ ለምን እደሚያደረገው ያለመስማማት ባልኖረ ነበር። ችግሩ አለም ሁሉ መለኮት ከሚያየው አካያ አናየውም። ይህ አብ አንድን ሰው ወደ ጌታ እንደ ሳበው በጌታ እንደሆነ የሚገኝ ለውጥ አይደለም። በመንፈስ ሲሞላም በነገር ሁሉ ከእ/ር ፈቃድ ጋር ሙሉ ለሙሉ መስማማቱ ወድያው አይመጣም። ከእ/ር ጋር አብሮ መጔዝን ይጠይቃል አንድ ሰው ከመሬት ተነስቶ የእ/ርን ባህርይ አይበዘብዝም አብሮ ጊዜ ማሳለፍን ይጠይቃል ደቀ መዛሙርቱ ሰዎች ከንግግራቸው የተነሳ ከእየሱስ ጋር እደነበሩ ያወቁት ለሰዎስት አመት ተኩል አብረው በመውጣት በመግባት ባህርዩን በከፊል ስለ ተካፈሉ ነው። ወንድም ቢኒ። BROTHER BINYAM T. ALEMAYEHU WRITINGS

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal