
ጥያቄና/መልስ፤ ጥያቄ፡ የሰው ዘር ያለባቸው ሌሎች ምድሮች ፕላኔቶች አሉ ብለህ ታስባለሕ? የሰውን ሕይወት ሳስብ ብቸኛ ፍጡራናን ምድር ላይ ያለነው እኛ ብቻ ነን ብዮ ማመን ከበደኝ ፡፡ እግዚአብሔር ለኛ ብቻ ብሎ እንደዚህ ያለ ወሰን የሌለው ሰፊ ህዋ ወይም አጽናፈ፟ አለማትን ለኛ ብቻ ገድቦ ስርቶት ይሆን ወይስ ሌሎች አለማት ላይ እኛን የሚመስሉ ፍጡራ ይኖራሉ ብለህ ታስባለህ? ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የአንተን አስተያየት ለመስማት ፈልጌ ነበር መልሱን በጉጉት እጠብቃለሁ፡፡ አመሰግናለሁ።
መልስ፡ ውድ ወንድም በክርስቶስ። በቅድሚያ እግዚአብሔር ሊያደርገው #ከፈጠረው#ሥራ#ሁሉ በእርሱ #ዐርፎአል ኦሪት ዘፍጥረት 2፡3 ታየኝ እኮ እ/ር ዳግማዊ የአፈጣተር ስራት ሊፈጥር ካረፈበት ተነስቶ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር ብሎ ዳግም ሲፈጥር ወይም ከእኛ በፊት የሰራውን ሲደግመው። አንተ አይኖሩም ብየ ማመን ከበደኝ ነው ያልከው እኔ ደግሞ ልክ እንደ እኛ በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር ብሎ የፈጠራቸው ሌሎች ሰዎች ከእኛ ዓለማት ተጨማሪ ሊኖሩ ይችላሉ ብሎ ማመን ይከብደኛል ፡፡ ይህ ነገሩ በሰባዊ ስሌትና ቀመር ስታስቲክሳዊ በመረጃ የተደገፈ የመሆኑ ጉዳይ አደለም ነገሩ። እግዚአብሔር እዚህ እኛ በስጋ ድንኻን አድረን ባለንባት በፕላኔቷ ምድራችን ምን እያደረገ እንደሆነ የማስተዋል ጉዳይ ነው። ሃሳቡን አንሳታው የክርስቶስ እንጂ የአዳም አእምሮ የለንምና። በአሳቹ በስጋዊ አእምሮ ተይዘን በመላ ምት በሌላ ቦታ ተመሳሳይ ፍጥረታት ሊኖር ይችላል ካልን ለምን ግብና ዓላማ ሊሆን ይችላል? ይህ ቃል ትዝ ይልሃል? እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ #የሰውን ወገኖች #ሁሉ #ከአንድ ፈጠረ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ ሲል ግን ብዙ ምድሮችን ሳይሆን አንድ ምድርን ነው የሚያመለክተን። በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ። አንድ ምድር። “እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ፥ የተወሰኑትንም ዘመኖችና ለሚኖሩበት ስፍራ ዳርቻ መደበላቸው። ቢሆንም #ከእያንዳንዳችን#የራቀ#አይደለም።፡
እግዚአብሔር #ከአንተ#ጋር ነው። ወንድም ቢኒ።
Alem Wenji ሌሎች ፕላኔቶች እግዚያብሔር አልፈጠርንም ? ኬት መጡ?
Binyam TA ሰላም፤ ሌሎች ፕላኔቶችን ፈጥረዋል ያ ማለት ግን ሌሎች የሰዎች ዘሮችንም አብሮ በውስጣቸው ፈጥረዋል ማለት አይደለም። ካነሳነው አይቀር ትንሽ ለማከል ያህል። Mount Palomar in California, astronomers ስለ አጽናፈ ሰማይ ሰፊነት የተወሰነ ሀሳብ ለማግኘት … “አልፋ ሄርኩለስ” የሚባለው ኮከብ ከ 2,400,000,000,000 ማይሎች በላይ ስፋት አለው። እጅግ በጣም ግዙፍ ከመሆኑ የተነሳ የእኛ ፀሐይና ምድር (የመሬት ርቀት ከፀሐይ ወደ 93 ሚሊየን ያህል ርቀት ባለው ርቀት) በዚህ እጅግ ግዙፍ ግዙፍ ኮከብ መካከል ተቀጻጽለው ቢደረደሩ 25 ጊዜ በውስጡ መቀመጥ ይችላሉ ፡፡ ከአንድ ኮኮብ ወደ ሌላው ጫፍ ለመብረር ቢታሰብ(ቢቻል ኖሮ!) በሰዓት 25,000 ማይሎች ፈጣን በተባለው ሮኬታቸው ቢወነጨፉ 11 ዓመታት ይወስዳል! እንዴት ያለ ርቀቶች! እንዴት ያለ ታላቅ አምላክ ነው ያለን! መዝሙር 19 “ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ” ይላል ፡፡ ለፍጡራኑ ይህን ያህል ታላቅ ክብር ከሰጡ የሱ ክብር ምን ያህል ይሆን?መዝሙረ ዳዊት 8፡
3 የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችን ባየሁ ጊዜ፥ ጨረቃንና ከዋክብትን አንተ የሠራሃቸውን፥ ትንቢተ አሞጽ 5፡
8 ሰባቱን ከዋክብትና ኦሪዮን የተባለውን ኮከብ የፈጠረውን፥ መዝሙረ ዳዊት 147፡4 የከዋክብትንም ብዛት ይቈጥራል፥ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል።ትንቢተ ኤርምያስ 31፡35 ስሙ የሠራዊት ጌታ የሚባል፥ ፀሐይን በቀን የጨረቃንና የከዋክብትን ሥርዓት በሌሊት ብርሃን አድርጎ የሚሰጥ፥ እንዲተምሙም የባሕርን ሞገዶች የሚያናውጥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ መጽሐፈ ኢዮብ 9፡
7 ፀሐይን ያዝዛታል፥ አትወጣምም፤
ከዋክብትንም ያትማል። መጽሐፈ ኢዮብ 9፡
9 ድብ የሚባለውን ኮከብና ኦሪዮን የሚባለውን ኮከብ፥ ሰባቱንም ከዋክብት፥
በደቡብም በኩል ያሉትን የከዋክብት ማደርያዎች ሠርቶአል።
መጽሐፈ ኢዮብ 38፡31 በውኑ የሰባቱን ከዋክብት ዘለላ ታስር ዘንድ፥
ወይስ ኦሪዮን የሚባለውን ኮከብ ትፈታ ዘንድ ትችላለህን?
32 ወይስ ማዛሮት የሚባሉትን ከዋክብት በጊዜያቸው ታወጣ ዘንድ፥
ወይስ ድብ የሚባለውን ኮከብ ከልጆቹ ጋር ትመራ ዘንድ ትችላለህን?
33 የሰማይን ሥርዓት ታውቃለህን?
በምድርስ ለይ እንዲሠለጥን ልታደርግ ትችላለህን?
34 የውኆች ብዛት ይሸፍንህ ዘንድ
ቃልህን ወደ ደመናት ታነሣ ዘንድ ትችላለህን?
35 መብረቆች ሄደው፦ እነሆ፥ እዚህ አለን ይሉህ ዘንድ
ልትልካቸው ትችላለህን? ቢኒ።
Alem Wenji ተባረክ
Mesfin Assefa Excellen