ከወንድም ካሳሁን ጋር ረጅም ውይይት በእ/ር ቃል …..


ከውይይት የተጠቀሰ፤ Binyam TA ወንድም Kasahun Zewde አትፍራው ቃሉን ማባበል ተገቢ አይደለም። የቃሉ ፍቺ ያበራል። “እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፡ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፡ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ።”
እንደምናስተውለው የእግዚአብሔር መልክ አምሳል እና አምሳያ በዚህ ቃል መሰረት የወንድን እና የሴትን ገጽታ ያካትታል። በዘፍጥረት ያህዌ ከማን ጋራ ነበር የሚናገረው”በምስላችን ሰው እንፍጠር “ቡሃላም” አዳም አንድ እንደኛ ሁነዋልና”ይላል ከተሳሳተ በሃላ፡ይህ ቃል ከድሮ የስላሴ መገለጫ ስንጠቀምበት የነበረ ቀዳሚ ቃል ነው፡፡ በእርግጥ የሰሶት መገለጫ ኣይደለም፡ብዙነት ስለሚናገር ግን ካለው የሶስትነት የጣኦት ምስል ልምምዶች ጋር ኣገናኝተን ይዘንዋል፡፡ ዘፍጥረት 1:26 እኛ ሲል ስላሴን አያሳይም ። የቃሉ ፍቺ ለተፈጥራዊው አእምሮ ስሜት ስለማይሰጠው አይቀበለውም ስሜቱን ያለመኮርኮሩ ትክክል ነው ይህ መንፈሳዊ እንጂ 5ቱ የስሜት ህዋሳት ሰፈር ዘንድ ስፍራ የለውምና። መንፈሳዊውን ነገር በመንፈስ ይምንረዳው ነውና። ብዙ ሰዎች በመቆጣትም በድንጋጤም እኛ ሲል ስላሴን አይደል እንዴ የሚያሳየው ብለውኛል እንደ ደረሱበት ነው እንግዲህ? ጥሩ ጥያቄ ነው እኛ የሚለው ቃል 3ቱ ሥላሴን እግዚያብሄሮች ለማሳየቱ በምን እርግጠኛ ይኮናል ትሆናለህ/ሽ? እኛ 2ለትም 3ትም 4ትም 5ትም ከዛም በላይ የሚያሳይ ሊሆን ይችላልና።
በቤተክርስቲያን ውስጥ ስለ ሥላሴ በአብያተ-ክርስቲያናት ክርክር ውስጥ ዋናው ነጥቡ ተደርጎ ይነሳል። አንድ ጊዜ አምላክ ሥላሴ እንደሆነ አድርገው ከተረዱና ካወቁ በኋላ እንደገና በእግ/ር ቃል ለመታረም ለብዙዎች ጭንቅ ነው። በውኑ በትክክል 3 እግዚአብሔር ስትል እንደ ቃሉ ተረድተዋልን? ለራስህ/ሽ ቃሉን መመርመር መልካም ነው።
ምን ታባብለዋለህ መንፈስ ጾታ የለውም ከየት አመጣከው? ከቲዮሌጃን? ይልቁኑ ይህ ቃል የእግዚአብሔርን ሙሉነት የሚያስረዳ በድርብ ክብሩ እራሱን የገለጠበት ነው ። የእግዚአብሔር አምሳያ ጣእም ድርብ ስለሆነ ወንዶችና ሴቶች መፍጠሩ የሱ መልክ ነው። የጥንት የስነ-መለኮት ምሁራን በስላሴ ላይ በጣም ትኩረት ስላደረጉበት በዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ለይ የእግዚአብሔርን ቃልን ዋናን ሃሳብ ሳያስተውሉት ቀርተዋል። “ከዚያም እግዚአብሔር አለ ሰውን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር አለ. እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፡ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፡ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ። ሀይማኖት ያጔሯ : የእግዚአብሔር መንፈሳዊ መልክ ወንድና ሴት ነው ማለትም ማንም ሳያግዘው በራሱ ሊያዘጋጅ ይችላል። ይህን ለማለት ለሰው የሚቸግረው የሰው አእምሮ ከሥጋ ፍትወት ጋር የተቆራኘ ስለሆነ ግልፅ ነው። እግዚአብሔርን መንፈስ እንጂ ስጋ ስላልሆነ ፍትወተ ሥጋ አይመለከተውም። እርሱ ልእለ ተፈጥሮና ልእለ ፍጡራን ነውና ። የእግዚአብሔር ክብር ሌላ ነው የሰው ክብር ሌላ ነው የመንፈስ ክብር ሌላ ነው የሥጋ ክብር ሌላ ነው።
የቃሉ ፍቺ ያበራል። “እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፡ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፡ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ።”
እንደምናስተውለው የእግዚአብሔር መልክ አምሳል እና አምሳያ በዚህ ቃል መሰረት የወንድን እና የሴትን ገጽታ ያካትታል። ይህ ባይሆን ኖሮ ምድራዊው የእግዚአብሔር አምሳያ ተብሎ የፈጠረው ሰው አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት የያዘ ባለ አንድ ፆታ ብቻ ሆኖ ይፈጥረው ነበረ። ሲፈጥራቸው ግን በአንድ አዳም ውስጥ ሁለት ፆታ ነበር እግዚአብሔር ግን ቡሃላ ለሁለት ከፈላቸው።
እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፡ በመልኩ? በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፡ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ;;
በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፡ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ? ግልጽ ነው። ።Gen 1 verse 27, “And God created man in His own image, in the image of God He created him; male and female He created them.” The #image and #likeness of #God, then, #includes#male and #female#aspects of #God. If this were not so, then the #earthly #image of God would #express just #one#sex, either male or female.
በእርግጥ የጥንት የነገረ-መለኮት ምሁራኑ አምላክን በአዎንታዊነት ለመግለጽ እውነትን ለማሳየት አልቻሉም። እግዚአብሔር በራሱ ሙሉ ስለሆነ ማንም ሳያግዘው መለኮታዊ ሙልአቱን ተጠቅሞ ማዘጋጀት እንደሚችል ከገለፁት እየተገዘቱ መገለል እንዳይደርስባቸው እውነትን መቅበር ይመረጣሉ።ሌላው ችግር ብዙዎቹ የጣዖት አምልኮ አምላኪዎችና አማልክቶች የሴት አገላለጾች ስለሚጨምሩ ሁሉ እርስ በራሱ እየተፈራራ ችግር ነበረ። ወንድም ቢኒ።

Hailegiorgis Tefera …እልልልልልልል…
ቢኒዬ የተባረከው ተባረክ ።

2 ሳሙኤል 23 (2 Samuel)
2፤ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ተናገረ፤ ቃሉም በአንደበቴ ላይ ነበረ።
3፤ የእስራኤል አምላክ ተናገረኝ፤ የእስራኤል ጠባቂ እንዲህ አለ፡— በሰው ላይ በጽድቅ የሚሠለጥን፥ በእግዚአብሔርም ፍርሃት የሚነግሥ፥
4፤ እርሱ እንደ ማለዳ ብርሃን እንደ ፀሐይ አወጣጥ፥ በጥዋትም ያለ ደመና እንደሚደምቅ፥ ከዝናብ በኋላ ከምድር እንደሚበቅል ልምላሜ ይሆናል።
5፤ በውኑ ቤቴ በእግዚአብሔር ዘንድ እንዲሁ አይደለምን? ከእኔም ጋር በሁሉ ነገር ቅንና ጽኑ የሆነውን የዘላለም ቃል ኪዳን አድርጎአል፤ መድኃኒቴንና ፈቃዴን ሁሉ ያበቅላል። …እልልልልልልል…

Ashenafi Akele ቢን ሰው ብቻ እኮ አይደለም ተቀላቅሎ ተፈጥሮ ( ዘፍ 5 ላይ በፈጠራቸው ቀን አዳም ብሎ ጠራቸው)በኋላ ከሁለት የተከፈለው መጀመሪያ ራሱ ሰማይና ምድርን ፈጠረ(ተቀላቅሎ) ከዛ በኋላ ነው የለያያቸው።

ከውይይት የተጠቀሰ፤ Binyam TA ወንድም Kasahun Zewde መንፈሳዊው ነገር ልናስተውለው ከምንችለው በላይ ልእለ ተፈጥሮ ነው ታዲያ ጌታ እንዴት ያስረዳን ? መንፈሳዊውን የቃል አለም እነጳውሎስ ሲያዩ ያልተገባ ከማለት በቀር ቋንቋ አጡለት። [ወደ ገነት ተነጠቀ፥ ሰውም ሊናገር የማይገባውን የማይነገረውን ቃል ሰማ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12/4 ]
‘እኔን ብታውቁኝ ኖሮ አባቴንም[መንፈሴንም(ከአብ[ከመንፈስ] ወጥቼ መጥቻለሁ)] ባወቃችሁት ነበር። ከአሁን ጀምሮ ግን ታውቁታላችሁ፤ አ-ይ-ታ-ች-ሁ-ታ-ል-ም።” ፊልጶስም፣ “ጌታ ሆይ፤ አብን አሳየንና ይበቃናል” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “አንተ ፊልጶስ! ይህን ያህል ጊዜ ከእናንተ ጋር ስ-ኖ-ር አ-ታ-ው-ቀ-ኝ-ም-ን? እኔን ያየ አብን[መንፈሴንም] አይቶአል፤ እንዴትስ፣ ‘አብን[መንፈስን] አሳየን’ ትላለህ? እኔ በአብ [በመንፈሴ] እንዳለሁ፣ አብም[መንፈሴም] በእኔ እንዳለ አ-ታ-ም-ን-ም-ን? የምነግራችሁ ቃል ከራሴ አይደለም፤ ነገር ግን ሥራውን የሚሠራው በእኔ የሚኖረው አብ[መንፈሴ] ነው። እ-ኔ በ-አ-ብ እ-ን-ዳ-ለሁ አ-ብ-ም[መንፈሴም] በ-እ-ኔ እ-ን-ዳ-ለ ስ-ነ-ግ-ራ-ች-ሁ እ-መ-ኑ-ኝ፤ ሌላው ቢቀር ስለ ድንቅ ሥራዎቹ እንኳ እመኑ። ‘ ዮሐንስ 14:7-11
ግልጽ ቋንቋ የሚገባው ብሩክ ነው። ክርስቶስ እውነት ነው። ሌላ ሊሆን አይችልም።
ምክንያቱም እ/ር[መንፈስ] እውነት ነው ። እርሱም በእ/ር[መንፈስ] ውስጥ ያድራል። እርሱ ሌላ ሊሆን አይችልም እውነት እንጂ፤ ምክንያቱም እ/ር እውነት ነው እርሱም በእ/ር ውስጥ ያድራል፤ እርሱ ሌላ ነገር ሊሆን አይችልም ህይወት እንጂ እ/ር[መንፈስ] ህይወት ነውና እርሱም በእ/ር ውስጥ ያድራል። በውኑ የአባቱ[መንፈሱ] ሁለንተና በልጁ አድሮ የለምን? ጌታ እየሱስ ክርስቶስ የእ/ር ሙሉ ፈቃድ ነው። የራሱን ፈቃድ ሊያደርግ አልመጣም ነገር ግን የላከውና በእርሱ ውስጥ ያደረው የአባቱን ፈቃድ እንጂ። የሰራቸው ድንቆች ሁሉ “ስራውን የሰራው በእኔ ውስጥ ያለው አባቴ [መንፈሴ] ነው” ይላቸው ነበር። “የዮሐንስ ወንጌል 4/24 እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥” ለዚህም ነው ወጥቼ ወደ መጣሁበት ወደ አባቴ[መንፈሴ] እመለሳለሁ ሲል ወደ መንፈሴ ክብር እመለሳለሁ እያላቸው ነው። የተናገራቸው ታላላቅ የህይወትና የጥበብ ቃላቶችና አባባሎች የአባቱ[የመንፈሱ] ቃሎች ነበሩ። እርሱ እራሱ የእ/ር[መንፈስ] ቃል ነበረ። ብሩኩ እየሱስ ክርስቶስ የእ/ር[መንፈስ] ቃል ሰባኪ ብቻ አልነበረም እራሱ የእ/ር[መንፈስ] ቃል ነበረ እንጂ።
ይህን የዘልአለም የእ/ር ሚስጥር ከሚገልጡልን ቃላቶች አንዱ አስደናቂ ቃል በየሃ1/18 የሚገኜው ነው። “የዮሐንስ ወንጌል 1/18 መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን[መንፈስን] ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ[በመንፈሱ] እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው።” የህያው ቃል ትርጉም እንዲህ ያስቀምጠዋል። “እ/ር[መንፈስን] መቼም ቢሆን ያየው ሰው የለም። ነገር ግን ከአብ[ከመንፈስ] ጋር ፍፁም አንድ የሆነው አንድ ልጁ እየሱስ ክርስቶስ መጥቶ ለአለም ገለጠው። ” ይህን ቃል Amplifid Bible“በየትኛውም ጊዜ እ/ርን[መንፈስን] ያየው ሰው በፍፁም የለም። ብቻውን ልዩ የሆነው ልጁ በእቅፉ የነበው እርሱ አወጀው።
እርሱ ገለጠው። ሊታይበት ወደ ሚችለው አወጣው። እርሱ እንዲታወቅ አደረገው።” RHM የተባለው ትርጉም ደግሞ “እርሱ ገለጠው አስተረጎመው” ይላል። እንዲህ ትርጉም ጽህፈት ቤት ሰው የሚሄደው በሚገባው ወይም በተፈለገው ቋንቋ ተተርጉም ነገሩን ለመረዳት ነው። ጌታ እ/ርንም[መንፈስንም] በሚገባን በሰው ቋንቋ ተርጉሞ አሳየን። ሌላ ትርጉም ሙልአት ወዳለው መገለጥ አመጣው ይላል። እንግዲህ እየሱስ ክርስቶስ በእርሱ ውስጥ የሚኖረው የማይታየው አምላክና አባት ሙሉ መገለጥ ነው። እ/ር በሙልአት እራሱን በልጁ አስቀመጠ ወይም አደረ የማይታይ የዘልአለም ባህርዩን ለሰው ይገልጥ ዘንድ። ወንድም ቢኒ።

Hailegiorgis Tefera …እልልልልልልል… ወንድምዬ ቢኒዬ ብሩክ ነህ ደስ አለኝ ።
…እልልልልልልል…

ከውይይት የተጠቀሰ፤ Binyam TA Kasahun Zewde ክፍል 1፡ ወንድም ካሳሁን አንተ የምትላቸው ለአንተ ስል በቆየ ጹሁፍ ላይ አስተያየት ስለሰጠህ እንጂ ይህ የምከራከርበት ትልቅ አረስት አይደልም ለኔ ይህ ኤለመንተሪ ነው። ካንተ ተቀርፍፎ የወደቀውን ገለባ ገለባውን የስጋ ትምክትህን አልቆጥርብህም ስንዴ ስንዴውን የእ/ር ቃሉን ብቻ በማየት እዛ ላይ ለመቆየት እጥራለሁ። ተባረክ። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5/21 ልጆች ሆይ፥ ከጣዖታት[የእግዚአብሔር የውሸት ምስል] ራሳችሁን ጠብቁ። ይላል ጣዖታት ማለት የውሸት የአምላክ ምስል ማለት ነው።
እውነተኛውን የአምላክ ምስል ለማስተማል መጀመርያ የአዲስ ኪዳን እስራኤል በመስማት፤ መጀመር አለበት ።ኦሪት ዘዳግም 6:4 እስራኤል ሆይ፥ #ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር #አንድ እግዚአብሔር ነው፤ አንዳንዱን ሰው እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አጋንንት በማመን ይቀድመዋል። የያዕቆብ መልእክት 2፡19 እግዚአብሔር #አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ #አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል።
እ/ርን “ማን ላከኝ ልበላቸው?” ብሎ ጠየቀ የዚህን ጊዜ ነበር እ/ር እንዲህ ብሎ በጊዜ ተፈትነው በማይበሰብሱ ቃላቶቹ የመለሰለት “ያለውና የሚኖረው እኔ ነኝ… እኔ እኔ ነኝ ላከኝ በላቸው” [I AM that I AM, tell the pepople that I AM hath sent you] ለመጀመርያ ግዜ ለሰሙት እንግዳ ስም እንደ ሚሆንባቸውና ግራ ሊያጋባቸው ይችላል። ነገር ግን በዚህ አስደናቂ ስም ውስጥ ታምቆ የያዘው ፍቺ ብዛትና የተጠቀሰው እውነት በብዙ ትውልዶች ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም።
ከብዙ ምእተ አመታት ቡሃላ ፈሪሳውያን ከአዳኙ ጋር ስለ ስልጣኑና ስለ መለኮታዊ ምንጩ (about his authority & divine origin) ሲከራከሩት በመለሰው መልስ በቁጣ ተሞልተው የልባቸው ምሳሌ የሆነውን ዲንጋይ አንስተው ቢቻላቸው ሊወግሩትና ሊገድሉት ተመኝተው ነበር እርሱ ግን ተሰወረባቸው ማለትም ከስጋ ወደ መንፈስ ተቀየረባቸው። ያበገናቸው መልሱ ነበር “…ከአብርሃም በፊት “እኔ ነኝ” (before Abraham was “I AM” )የቀድሞ ትርጉም ተርጋሚዎች እዚህ ላይ ስላልገባቸው ከJOV (Jusus opinonative versions ኪኪኪ…)ብናየው የተሻለ ነት ልጆቹ የእ/ር መልኮታዊ እይታ[Divine Perspectiv of GOD) ልንይዝ የግዴታ ነውና ዋናውን ተናጋሪ ልናስተውል የግድ ነው። ያቃጠላቸው በዋናው ቌንቋ “…ከአብርሃም በፊት ነበርኩ ሳይሆን ያላቸው “ከአብርሃም በፊት እኔ ነኝ! I was ሳይሆን I AM ነው ያላቸው። “እኔ ነኝ“ ማን እደሆነ ስለሚያውቁ አጓሩ።
ይውጣላቸው ብሎ ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን ለራስህ አዘጋጀህ የካህናት አለቆችና ጻፎች ዳዊት ለብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር በበገና ሲያቀነቅን የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችን ባየሁ ጊዜ፥ ጨረቃንና ከዋክብትን አንተ የሠራሃቸውን፥ ወዘተ… እያለ መንፈሳዊ ቅኔ ሲደረድር ቃሉ ለማን እንደሆነ የተነገረው ያውቁታል ጌታ እየሱስ ክርስቶስ በአይናቸው ፊት ሌላ ቅኔ ደገመላቸው የአሮጌው ኪዳን እግዚአብሔር እኔ ነኝ ዳዊት የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችን ባየሁ ጊዜ፥ ጨረቃንና ከዋክብትን አንተ የሠራሃቸውን፥ ብሎ በመንፈስ ቅዱስ ያዜመው ለኔ ነው ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን ለራሴ ያዘጋጀሁት እኔው ለራሴ ነው ብልዋቸው ቁጭ። የካህናት አለቆችና ጻፎች ያደረገውን ድንቃ ድንቅ በመቅደስም፦ ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ እያሉ የሚጮኹትን ልጆች ባዩ ጊዜ፥ ተቈጥተው፦16 እነዚህ የሚሉትን አትሰማምን? አሉት። ኢየሱስም፦ እሰማለሁ፤ ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን ለራሴ ያዘጋጀሁት እኔው ለራሴ ነው ብልዋቸው እርፍ። ሃይማኖት ዞረበት። ኪኪኪ….
“መዝሙረ ዳዊት 8:1 አቤቱ ጌታችን፥ ስምህ በምድር ሁሉ እጅግ ተመሰገነ፥ ምስጋናህ በሰማዮች ላይ ከፍ ከፍ ብሎአልና።2 ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ ስለ ጠላትህ፥ ጠላትንና ቂመኛን ለማጥፋት።3 የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችን ባየሁ ጊዜ፥ ጨረቃንና ከዋክብትን አንተ የሠራሃቸውን፥4 ታስበው ዘንድ ሰው ምንድር ነው? ትጐበኘውም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድር ነው?”
“የማቴዎስ ወንጌል 21:15 ነገር ግን የካህናት አለቆችና ጻፎች ያደረገውን ድንቃ ድንቅ በመቅደስም፦ ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ እያሉ የሚጮኹትን ልጆች ባዩ ጊዜ፥ ተቈጥተው፦16 እነዚህ የሚሉትን አትሰማምን? አሉት። ኢየሱስም፦ እሰማለሁ፤ ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን ለራስህ አዘጋጀህ የሚለውን ቃል ከቶ አላነበባችሁምን? አላቸው።”….2 ወንድም ቢኒ።
ክፍል 2፡ እየሱስ ህግን የሰጠውና ስጋ የለበሰው ያህዌ ነው! ጌታ እየሱስ ክርስቶስ በስጋ የመጣው ወደ መንፈስ ሊመራን ነው። በመጀመሪያው ቃል እንደ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር እንደነበረ። ቃልም ሥጋ ሆኖ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ እንደመጣ የማያምን ሁሉ ሃሰተኛ መንፈስ ነው የክርስቶስ ተቃዋሚውም መንፈስ ነው፤ ። ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ግን ከእግዚአብሔር ነው።
“1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4/2 የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፥3 ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ እንደ መጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ይህም የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው፤ ይህም እንዲመጣ ሰምታችኋል፥ አሁንም እንኳ በዓለም አለ።”
*እየሱስ ፈጣሪም ነው ህግን የሰጠውና ስጋ የለበሰውም ያህዌ እሱ ነው! ይህንን እውነት ለማስተዋል በቀደሙት ክፍሎች በብዙ አይተነዋል እንዲሁም እያንዳንዱን መጽሐፍት ብትመረምሩ ጌታን በዛ ውስጥ ታገኙታላችሁ። የእብራይስጥ ቋንቋ እራሱ ይህንን እውነት ያረጋግጠዋል። አንድ የእብራይስጥና የግሪክ ቋንቋ ማንም መረዳቱ የተሰጠውና ቃሉን የሚያጠና ሊቅ ሁሉ ሊያውቀው የተገባ ነው። “የእብራይስጥ ቋንቋ በአብዛኛው የአንድ ቃል ፍቺ ሃብታም ከመሆኑ የተነሳ ከአንድ በላይ ደራርቦ ሃሳብን ሊያሳይ ይችላል። የእብራይስጥ ቋንቋ ቃላት ስእላዊ ገላጭ ያለውና የድምጽ ገላጭም አጣምሮ የያዘ ሊሆንም ይችላል፡፡
ለምሳሌ ሁሉም ፈደሎች ቁጥርም ናቸው ቃላትም ናቸው። ለምሳሌ “alef” የመጀመርያው ፊደል ነው ያው ፊደል የመጀመርያው ቁጥር አንድ ማለትም ነው። “alef” የሚለው ያው ቃል በሬ ማለት ሲሆን ስእላዊ ገላጩም ጥንካሬን፤ ብርታትን [ymbolizes, strength] የሚያመለክት ነው። ሁለተኛው “beth” ቁጥር ሁለት ነው። “beth” የሚለው ቃል እራሱ ቤት ፤ቤተ ሰዎችና ፤ቤተሰቦችን [house or household] ያካተተ ፍቺ አለው።
በእብራይስጥ ቋንቋ ህግ ማለት Torah ነው። በእብራይስጥና ቋንቋ ቶራ[ Torah] ሲፃፍ tav-vav-resh-hey ሆኖ ይፃፋል። ይህ ከተያያዛበት ለየብቻው ቃሉ ሲተረጎም Tav ማለት ምልክት ወይም መስቀል ማለት “a mark or sign” [of the cross] ሲሆን። በዋናው በመጀመርያው ጥናታዊ ያልተበረዘ በእብራይስጥ ቋንቋ “መስቀል” ተብሎ ነበር የተፃፈው። በዘመናይ በእብራይስጥና ቋንቋ ተለይቶ ይገኛን። ይህም የሆነው በባቢሎን 70 አመት ምርኮ ጊዜ የባህል ወረራ ስለደረሰ ከአረሚክ ቋንቋ ጋር ተዳቅሎ ተበረዘ። ሁለተኛው “vav” የሚለው በግልጽ ትርጉሙ እንደ አገባቡ የተሰቀለው፤በሚስማር፤ የተጠረቀመው፤የተቸከለው “a nail or peg.” ሲሆን ሶስተኛው “resh” የሚለው በግልጽ መሪ ወይም ራስ “a head, or leader.” ማለት ነው። በመጨረሻም “hey” በቃሉ መጨረሻ ሲቀመት ትርጉሙ ከሱ ወይ ከዛ የወጣ የተገኘ ማለት ነው። “what comes from.” በእብራይስጥና ቋንቋ ህግ ማለትም Torah ከሚለው ቃል ፍቺ እምናስተውለው በመስቀል ላይ ከተሰቀለው መሪ ወይም ራስ የተገኘ “what – comes – from – the – Leader- nailed- to- the – Cross” ማለት ነው ። በሌላ አነጋገር እየሱስ ህግን የሰጠውና በመስቀል ላይ የተሰቀለው መሪ ወይም ራስ እሱ መሆኑን በዚህ ታላቅ ሚስጥር ውስጥ የእ/ር ድንቅ ስራ ይስተዋላል።
ጌታ እየሱስ ከስጋ ወደ መንፈስ ሊመራን ነው የመጣው። “2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡16 … ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም።” አዎን አሁን 33 ½ አመት በስጋ ውስጥ ተዎስኖ እደነበረው አይደለም ህይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነዋል:: “1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15፡45 …ኋለኛው አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ።” ደግሞም ከሰማያት ሁሉ በላይ አልፎ ሁሉን ሞልቶታል በስጋ ተወስኖ ሁሉ መሙላት አይችልም ወደ መንፈስ ክብሩ ተመልሶ እንጂ። “ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡10 ይህ የወረደው ሁሉን ይሞላ ዘንድ ከሰማያት ሁሉ በላይ የወጣው ደግሞ ያው ነው። Eph 4፡10 He that descended is the same also that ascended up far above all heavens, that he might fill all things.)” ወንድም ቢኒ።

Mulugeta Shiferaw አሜን

Hailegiorgis Tefera ወንድምዬ ቢኒዬ ጽሑፍህ ድንቅ ነው ።

ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን ለራስህ አዘጋጀህ
የካህናት አለቆችና ጻፎች ዳዊት ለብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር በበገና ሲያቀነቅን የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችን ባየሁ ጊዜ፥ ጨረቃንና ከዋክብትን አንተ የሠራሃቸውን፥ ወዘተ… እያለ መንፈሳዊ ቅኔ ሲደረድር ቃሉ ለማን እንደሆነ የተነገረው ያውቁታል ጌታ እየሱስ ክርስቶስ በአይናቸው ፊት ሌላ መንፈሳዊ ቅኔ ደገመላቸው የአሮጌው ኪዳን እግዚአብሔር እኔ ነኝ ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን ለራሴ ነው ያዘጋጀሁት ብልዋቸው እርፍ። ዳዊት የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችን ባየሁ ጊዜ፥ ጨረቃንና ከዋክብትን አንተ የሠራሃቸውን፥ ብሎ በመንፈስ ቅዱስ ያዜመው ለኔ ነው ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን ለራሴ ያዘጋጀሁት እኔው ለራሴ ነው ብልዋቸው ቁጭ። የካህናት አለቆችና ጻፎች ያደረገውን ድንቃ ድንቅ በመቅደስም፦ ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ እያሉ የሚጮኹትን ልጆች ባዩ ጊዜ፥ ተቈጥተው፦16 እነዚህ የሚሉትን አትሰማምን? አሉት። ኢየሱስም፦ እሰማለሁ፤ ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን ለራሴ ያዘጋጀሁት እኔው ለራሴ ነው ብልዋቸው እርፍ። ሃይማኖት ዞረበት። ኪኪኪ….
“መዝሙረ ዳዊት 8:1 አቤቱ ጌታችን፥ ስምህ በምድር ሁሉ እጅግ ተመሰገነ፥ ምስጋናህ በሰማዮች ላይ ከፍ ከፍ ብሎአልና።2 ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ ስለ ጠላትህ፥ ጠላትንና ቂመኛን ለማጥፋት።3 የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችን ባየሁ ጊዜ፥ ጨረቃንና ከዋክብትን አንተ የሠራሃቸውን፥4 ታስበው ዘንድ ሰው ምንድር ነው? ትጐበኘውም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድር ነው?”
“የማቴዎስ ወንጌል 21:15 ነገር ግን የካህናት አለቆችና ጻፎች ያደረገውን ድንቃ ድንቅ በመቅደስም፦ ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ እያሉ የሚጮኹትን ልጆች ባዩ ጊዜ፥ ተቈጥተው፦16 እነዚህ የሚሉትን አትሰማምን? አሉት። ኢየሱስም፦ እሰማለሁ፤ ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ #ምስጋናን#ለራስህ#አዘጋጀህ የሚለውን ቃል ከቶ አላነበባችሁምን? አላቸው።” ወንድም ቢኒ።

ከውይይት የተጠቀሰ፤ Binyam TA Kasahun Zewde ክፍል 1፤ በቅድሚያ እውነትን በፍቅር መግለጥ የተሻለ ነው ብራዘር። ትልቅ መገለጥ እንደያዘ ሰው መታበይህ ሳያስቀኝ እንዳልቀረ ሳልነግርህ ማለፍ አልቻልኩም። ቃልም (ሎጎስም: የእ/ር ሐሳቡም) በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። የካሳሁን ሃሳቡም ከካሳሁን ጋር ነበረ ከተባለ ሃሳቡ ሌላ ካሳሁን ነው ማለትህ ነው ወይስ ሃሳብህ የወንድም ካሳሁን hybrid human clone genetically identical copy ኮፒየ ነው ኮፕየ ነው በስልጣን በመለኮት አንድ ነን? ያስቃል። ቃልም (ሎጎስም: የእ/ር ሐሳቡም) በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። የሚለውን ሌላ አምላክ እንዳለ አድርገህ መረዳትህ ታስቃለህ። የሚገርመው በተደጋጋሚ ሃሳብህን በቃሉ እንደመግለጽ ተሽቀዳድመህ ዳንኪራ መጨፈር በባዶ ሜዳ አላስፈላጊ ነው። ቃሉ ላይ ቆይ። ምዕራፍ 1: 1. በመጀመሪያው ቃል (The Word ፡logos ሎጎስ ማለት የእ/ር ሀሳብ አስተሳሰቦች ስብስብ፤ ምክንያት፤ ንግግር የኮሙኒኬሽን፤ የቃላት መግለጫ ሐሳብ ሎጎስ) ነበረ። ቃልም (ሎጎስ: የእ/ር ሐሳቡ) በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። ቃልም (ሎጎስ: የእ/ር ሐሳቡም) እግዚአብሔር እራሱ ነበረ።
John 1:1. Within a beginning there was The Word (logos: The Thought; The Collection of Thoughts; The Idea; The Reason; The Discourse; The Communication; The Verbal Expression). And the Word (logos: the thought; the expression) was (and continued being) facing, directed and moving toward (or: with) God. And the Word (logos: the thought; the idea; the reason; the expression) continued being God. [or: Originally the Word was existing and continued to be, and the Word was being {projected} toward God. And the Word, It was existing being God (idiomatically: And the Word was just what God was; And the Expression was {an extension of} Deity).] ልጨምርልህ እየሱስ ክርስቶስ ቃል እ/ር ብቻ ሳይሆን እየሱስ ክርስቶስ እራሱ ጳራቂላጦስ አጽናኙ ነው በእ/ር ቃል እንየው። ጌታ ምን እንዳለ አስተውል። ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም ወደ እናንተ እመጣለሁ። መጣ እሺ ከዛስ በኋላስ መንፈስ ስለሆነ ምን አለ? ዓለም አያየኝም እናንተ ግን ታዩኛላችሁ በዚያን ግዜ ምን ይከሰታል? ማወቅ ይከሰታል። ‘እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ .’ ሃይሉ ያለው ማወቁ ላይ ነው ዓለም አያየኝም እናንተ ግን ታዩኛላችሁ። ‘ቅኔውን ሲፈታው ስለራሱ እንጂ ስሌላ እያወራ እንዳልሆነ አስተውል? .
የዮሐንስ ወንጌል 14/18 ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ. 19 ገና ጥቂት ዘመን አለ ከዚህም በኋላ ዓለም አያየኝም እናንተ ግን ታዩኛላችሁ። እኔ ሕያው ነኝና እናንተ ደግሞ ሕያዋን ትሆናላችሁ. 20 እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ . John 14፡18 I will not leave you #comfortless: I will come to you. ወንድም ካስሽ ዮሐ 14:18 ጌታችን ምን እንዳለ በግማሽ ሳይሆ በሙሉ ትኩረትህ አሁን አስተውል። መንፈስ ማን እንደሆነ መንፈስ ቅዱስ ምን እንደሆነ ግልጽ ያደርግልናል . የስላሴ 3 ኛ አካል ነው? ጌታ እራሱ ይናገር። የዮሐንስ ወንጌል 14/28 #እኔ #እሄዳለሁ #ወደ #እናንተም #እመጣለሁ እንዳልኋችሁ ሰማችሁ[ሄዶ በመንፈስ ክብሩ ተመልሶ የሚመጣው ማነው? እየሱስ እራሱ አጽናኝ ሆኖ]. “#ወደ #እናንተ #እመጣለሁ[እኔ] አስተዋላችሁ ጌታ ምን አለ? እኔ እሄዳለሁ: እኔም ወደ አንተ እመጣለሁ! ወደ እናንተ እመጣለሁ[ማ ይመጣል እየሱስ] 20 እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን [አጽናኙ በሚመጣበት ቀን] ታውቃላችሁ. ( “በዚያም ቀን እናንተ እኔ በአባቴ እንዳለሁ ታውቃላችሁ እናንተም በእኔ ውስጥ [መቼ ቀን? አጽናኝ ሲመጣ]” የዮሐንስ ወንጌል 14/28 #እኔ #እሄዳለሁ #ወደ #እናንተም #እመጣለሁ እንዳልኋችሁ ሰማችሁ[ሄዶ በመንፈስ ክብሩ ተመልሶ የሚመጣው ማነው? እየሱስ እራሱ አጽናኝ ሆኖ]. “#ወደ #እናንተ #እመጣለሁ[እኔ] አስተዋላችሁ ጌታ ምን አለ? እኔ እሄዳለሁ: እኔም ወደ አንተ እመጣለሁ! እኔ እሄዳለሁ ወደ እናንተም እመጣለሁ! አሁን እየሱስ ክርስቶስ እራሱ ጳራቂላጦስ ተብሎ መጠራቱን በእ / ር ቃል እናረጋግጥ. አፅናኝ [ጳራቂላጦስ] ሌላ አጽናኝ [ጳራቂላጦስ] ይሰጣችኋል ያለው ጳራቂላጦሱ ማን እንደሆነ እናያለን።
የዮሐንስ ወንጌል 14 / 15-16 ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ. እኔም አብን እለምናለሁ [ጸልዩ] ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ [ጳራቂላጦስ; parakletos አጽናኝ፤ አማላጅ, consoler:. Advocate, አጽናኝ] ይሰጣችኋል። ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ዘንድ።
1 ኛ የዮሐንስ መልእክት 2 ፡1 ልጆቼ ሆይ: ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ. ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ #ጠበቃ [ጳራቂላጦስ; parakletos አጽናኝ፤ አማላጅ, consoler: -advocate, ጠበቃ አጽናኝ] አለን #እርሱም #ጻድቅ #የሆነ #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ነው። አመለጠህ? ልድገምልህ #ጠበቃ [ጳራቂላጦስ; parakletos አጽናኝ፤ አማላጅ, consoler: -advocate, ጠበቃ አጽናኝ] አለን #እርሱም #ጻድቅ #የሆነ #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ነው። ፡) ….ክፍል 2 ወንድም ቢኒ።

ክፍል 2፤ በተፈጥራዊው አእምሮ እንደምታስበው የሰው ልጅ እየሱስ ክርስቶስ አባት ማን ይመስልሀል? ጌታ እየሱስ ክርስቶስ በብፅዕት ድንግል ማርያም ማህፀን # የተረገዘው በመንፈስ ቅዱስ መፅለል ነበር.
እንደምናስተውለው መንፈስ ቅዱስ ለእርግዝናዋ ምክንያት ነው። እየሱስም ተወለደ ያስረገዛት መንፈስ ቅዱስ ቢሆንም የመንፈስ ቅዱስ ልጅ ግን አልተባለም አልነበረምም ነገር ግን የአባት (አብ) ልጅ ነው “የአብ ልጅ” ኛ ዮሐንስ 2: 3 አስተውል ያስረገዛት #መንፈስ ቅዱስ #የእግዚአብሔር #መንፈስ #ነው እንጂ ከ 3 ቱ ስላሴዋች አንዱ አይደለም ቢሆን ኖሮ እርሱ ባስረገዘ ሌላ አባት ባልተባለ ነበረ። እንደ የስላሴ አፈ ታሪክ ቲፎዞዋች አባባል መንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ ስብእና ለብቻው ያለው ቢሆን ኖሮ ወይም ከ 3 ቱ ስላሴዋች አንዱ ቢሆን ኖሮ መንፈስ ቅዱስ አባቱ በተባለ ነበር እ ንጂ ሌላ የእንጀራ አባት ጣልቃ የገባ መለኮት አብ የተባለ በጉልበት አባቱ ባልሆነ።
እንኳን አስተዋይ ሰው ማንኛውም ቀላል አስተሳሰብ ያለው ሰው ማንም አንዲት እናት ማኅፀን ውስጥ አንድ ሕፃን ከመወለዱ ጊዜ ልጁ ወላጅ አባት አባት ይባላል እንጂ ሌላ መጤ አባት አይባልምም ሌላ ሰው ወይም ሥላሴ አባል እንደሆነ መረዳት እንችላለን። አስተውል ያስረገዛት #መንፈስ ቅዱስ #የእግዚአብሔር #መንፈስ #ነው።
ብዙ ሰው የመጀመሪያውን ትእዛዝ ጥሶ ይመላለሳል ቃሉ ጌታ እግዚአብሔር አንድ ነው ሲለው ሰው ግን በህይወቱ የእግዚአብሔርን ቃል ከንቱ ለማስቀረት ወጥመድ ሆኖበት 3 እግዚአብሔሮችን የነ ዳቪንቼ የፈረንጅ ምስል ስእል ያስባል ይኖራል። እግዚአብሔር መንፈስ ነው አንድ ነው። የሚቀጥለው ትእዛዝ የሚጀምረው እግዚአብሔር አንድ እንደሆነ በማወቅ ሳይሆን ለማወቅ መጀመሪያ ስማ ! ሰማና! ሰማና! ያልሰማ ብዥ ብሎበት አንድየን 3 ሆኖ ያየዋል። እስራኤል ሆይ: ሰማ የማርቆስ 12:29 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው: ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ እስራኤል ሆይ: #ስማ ፤ጌታ አምላካችን #አንድ ነው። በተረፈ በጌታ ፍቅር ሰላም ለአንተ ይሁን። ወንድም ቢኒ።

ከውይይት የተጠቀሰ፤ Kasahun Zewde ወንድም ካሳሁን ማሪያም የዳዊት ዘር አንዳልሆነች እወቅ። በወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ ሲል ምን ማለቱ አንደሆነ በእ/ር አሳይካለሁ። ሆኖም ከዛ በፊት ለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ለማድረግ አንችልምና ጌታ በጣም አገኘህ ማለት ነው ብሎክ ላደርጋችሁ ነው ብለህ አረፍከው። ተባረክ። የመሰናበቻ ይህን ልበልህ ካስሽ ስወድህ ቅናትህ ደስ ይለኛል ሆኖም አንተ ስትናገር ሰውን ቅቤ የምትቀባ ይመስልካል በመሃል ጨምረህ ለምትናገረው ሰው ከተናገረክ ትሰናከላለህ ይህ ተገቢ አይደለም ተረጋጋ። ጳውሎስ የተባለው ሳውል ግን ለማለት ያብቃን ወንድማችንን አስታወስከኝ ሳኦል ሳለ አይነካም ነበረ ጳውሎስ ከሆነ ቡሃላ ግን……. በ”የሐዋርያት ሥራ 13 2 እነዚህም ጌታን ሲያመልኩና ሲጦሙ መንፈስ ቅዱስ. በርናባስንና #ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ አለ. “ከዚያም በቁ .9” ጳውሎስ የተባለው ሳውል ግን “ይለዋል. ጳውሎስ በክርስቶስ አዲስ ማንነቱ ሲሆን ሳኦል የስጋዊ ማንነቱ ስም ነው። ከዚህ ቁጥር ቡሃላ ሃኪሙ ሉቃስ በአዲስ ማንነቱ ስም ጳውሎስ እያለ ብቻ ይጠራዋል. በሮሜ 7 ላይ ጳውሎስ ስለ ሁለት ማንነቱ ያለውን ትግል ያስረዳናል። Please Bro. don’t take it personal, taking something like this personally to get upset by the things other people say or do, b/c you think that their remarks or behaviour are directed at you in particular Don’t take it personally it’s all about the truth Bro. ። ሮሜ1፡”3-4 ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው ;. እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” ይህምወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ተወለደ

ትንቢተ ኢሳይያስ 11 ፡1 ከእሴይ (ከዳዊት አባት) ግንድ በትር ይወጣል: ከሥሩም ቍጥቋጥ ያፈራል.2 የእግዚአብሔር መንፈስ: የጥበብና የማስተዋል መንፈስ: የምክርና የኃይል መንፈስ: የእውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል. 3 እግዚአብሔርን በመፍራት ደስታውን ያያል. ዓይኑም እንደምታይ አይፈርድም: ጆሮውም እንደምትሰማ አይበይንም 4 ነገር ግን ለድሆች በጽድቅ ይፈርዳል: ለምድርም የዋሆች በቅንነት ይበይናል በአፉም በትር ምድርን ይመታል: በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል. 5 የወገቡ መታጠቂያ ጽድቅ: የጎኑም መቀነት ታማኝነት ይሆናል.
በትረ መንግሥቱ ከይሁዳ እንደ ሚመትጣ ከዳዊት ዘርም እንደሆነ ከኦሪት ጀምሮ እ / ር ሲናገር ነበረ :: “ኦሪት ዘፍጥረት 49 10 በትረ መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም: የገዥም ዘንግ ከእግሮቹ መካከል:. ገዥ የሆነው እስኪመጣ ድረስ የአሕዛብ መታዘዝም ለእርሱ ይሆናል” ከዳዊት ግንድ እንደ ሚመጣ ደግሞ “መዝሙ 89 29 ዘሩንም ለዓለምና ለዘላለም:. ዙፋኑንም እንደ ሰማይ ዘመን አደርጋለሁ “ሲል ለባሪያው ለዳዊት ቃል ገብቶለት ነበረ :: የጌታ እየሱስ እናት ማሪያም በዮሴፍ በኩል በጋብቻ የዳዊት ዘር አድርጎ እ / ር ይቆጥራታል :: መጽሐፍ ዮሴፍ የዳዊት ዘር እደሆነ ያስረዳናል ::” ሉቃ 1 27 ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ:. የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ “ስለ የጌታ እየሱስ እናት ማሪያም ትውልድ ከይሁዳ ነገድ መሆንዋን ምንም አይናገርም ::” ሉቃ 1 27 ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ: የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ. “ሲል ብቻ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ብሎ በእጮኛዋን ነገድ ብቻ ያስተዋውቃታል ::
ከየት ነገድ እንደ ሆነች ፍንጭ የምናገኘው መላኩ ገብርኤል ለማሪያም የእ / ርን ቃል ሲያቀብላት ከአሮን ወገን የሆነችውን ኤልሳቤጥን ዘመድሽ ብሎ የጠራትን እናስተውላለን :: የመጥምቁ ዮሃንስ እናትን ከከአሮን ወገን እንደሆነች መጽሐፍ ይናገራል በዚህም የጌታ እየሱስ እናት ማሪያም እንደ ዘመድዋ ኤልሳቤት ከአሮን ወገን እንደሆነች ግልጽ ነው :: “ሉቃ 1 36 እነሆም ዘመድሽ ኤልሳቤጥ: እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች: ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው; “መላኩ ገብርኤል ለማሪም የእ / ርን ቃል ሲያቀብላት ዘመድሽ ኤልሳቤጥ ብሎ ያረጋግጣል ከዛም ማሪያም ለወራት ከኤልሳቤት ዘመድዋ ዘን ተጠልላለች “ሉቃ 1 5 በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ; ሚስቱም ከአሮን ልጆች ነበረች: ስምዋም ኤልሳቤጥ ነበረ.” ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ; ሲል ሚስቱም ከአሮን ልጆች ነበረች:. ስምዋም ኤልሳቤጥ ነበረ “ይለናል እንደ ምናስተውለው የማሪም ዘመድ ከአሮን ወገን መሆንዋ ብቻ ሳይሆን ከተለያየ ነገድ ጋብቻ ያደርጉ እንደ ነበር እናስተውላለን :: ዘካሪያስ ከአብያ ክፍል ሲሆን ሚስቱም ኤልሳቤጥ ከአሮን ልጆች ነበረች ::
በዚህም ከይሁዳ ነገድ የሆነው የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ከአሮን ነገድ የሆነችውን የጌታ እየሱስ እናት ማሪያም መታጨቱ በዛ ዘመን እንግዳ ነገር እንዳልሆነ እናስተውላለን :: ስለዚህ ጌታ ከይሁዳ ነገድ የዳዊት ዘር የተባለው በዮሴፍ በኩል ነው የዳዊት ልጅ የተባለው እንጂ ከአሮን ወገን ከሆነችው ከናቱ ከማሪም በኩል እይደለም :: ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ ብሎ እንደ ተነገረ እ / ር ዮሴፍንና ማሪያምን አንድ ስጋ አድርጎ ስለ ሚቆጥር ከይሁዳ ነገድ አድርጎ ይቆጥራታል በዚህም ጌታ የዳዊት ልጅ ተብሎ ተጠራ :: በጋብቻ ያለው ውህደት በጌታ ፊት ምንኛ ክቡር እንደሆነ ስናስተውል ትህትናን ያስይዛል በአመለካከታችንም ንስሃ ያመጣብናል :: እዚህ ላይ እ / ር ስለ ጋብቻ ያለው አመለካከት እጅግ ጥብቅና ሰማይ ከምድር እንደ ሚርቅ ከሰው እመለካከት የራቀ እደሆነ እንረዳለን ::….2 ወንድም ቢኒ።

ሌላ ተጨማሪ።

ክርስቶስ ለብዙ ነገር የበላይ ራስም ነው። የአሕዛብም ራስ፤ የሕይወትንም ራስ ፤ የማዕዘን ራስ፤ የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ፤ የቤተ ክርስቲያን ራስ፤ የመዳንንም ራስ፤ ብዙ ልጆችን ወደ ክብር ያመጣ የመዳናችን ራስ፤ የጥበብና የእውቀት ራስ፤ እርሱ የሁሉ ራስ ነው አካሉ የሆነችው የቤተ ክርስቲያን ራስ የመሆኑ ሚስጥር ግን ታላቅ ነው፤ የአንድ አካል ! “ ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፥ እኔ ግን ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እላለሁ።
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5/32” ወደ ሮሜ ሰዎች 12/5 እንዲሁ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥ እርስ በርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው ብልቶች ነን።1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6/17 ከጌታ ጋር የሚተባበር ግን አንድ መንፈስ ነው።1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12/12 አካልም አንድ እንደ ሆነ ብዙም ብልቶች እንዳሉበት ነገር ግን የአካል ብልቶች ሁሉ ብዙዎች ሳሉ አንድ አካል እንደ ሆኑ፥ ክርስቶስ ደግሞ እንዲሁ ነው፤ወደ ገላትያ ሰዎች 3/28 አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።ወደ ገላትያ ሰዎች 3/27 ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና።
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1/18 እርሱም የአካሉ ማለት የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው፤ እርሱም በሁሉ ፊተኛ ይሆን ዘንድ፥ መጀመሪያ ከሙታንም በኵር ነው። የራሱ አካል ለሆነችው የቤተክርስቲያን ማለትም የክርስቶስ አካል [በእርሱ ሙሉ ሆናችኋል! ye are complete in him!] ይላታል። ራስ በሆነው በእሱ የመሎኮት ሙልአት ሁሉ በእርሱ ውስጥ ቲፍ ብሎ ተሞልቶዋል ማለት አካል ማለት ከአንገት በላይ ካለው የጭንቅላት የአካል ክፍል ብቻ ሳይሆን ይሄ በንፈሳዊ የክርስቶስ አካል ልጅነት በጥቅሉ ልጆችን ሁሉ የሚጨምር ነው የአካሉ ሙልአት ናችሁና። የጭንቅላት ብቻውን ብታዩ ሙሉ አካል ነው ልትሉ አትችሉም። ራስ በሆነ በእርሱ ሆናችሁ በውስጣችሁ ተሞልታችኋል። ለአለቅነትና ለሥልጣንም ሁሉ ራስ በሆነ በእርሱ ሆናችሁ ተሞልታችኋል።
ያለመፈንዳታችንም ሚስጥር ነው። የመንፈሱ ሙልአት የማንነቱ መያዣ አርጎ የሰራን እርሱ ነው። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5/ 4 በእውነትም የሚሞተው በሕይወት ይዋጥ ዘንድ ልንለብስ እንጂ ልንገፈፍ የማንወድ ስለ ሆነ፥ በድንኳኑ ያለን እኛ ከብዶን እንቃትታለን።5ነገር ግን ለዚሁ የሠራን እግዚአብሔር ነው እርሱም የመንፈሱን መያዣ ሰጠን።
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3/2 ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን። እርፍ እሰይ!!! ወንድም ቢኒ።

ክፍል 2 ፡ጌታ በ “ዘፍ 2 24 ጠቅሶ ሲናገር በ” ማቲ 19 5 አለም. ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል: ከሚስቱም ጋር ይተባበራል:? ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ የሚለውን ቃል አላነበባችሁምን 6 ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም. እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው “ለዚህም ነው ጌታ ፈሪሳውያንን እንዴት የዳዊት ልጅ ልሆን እችላለሁ ሲል መለኮታዊ ምንጩን እንዲያስተውሉ በማድረግ ዝም ያሰኛቸው ::” የማቴዎስ ወንጌል 22 41-42 ፈሪሳውያንም ተሰብስበው ሳሉ:. ኢየሱስ: ስለ ክርስቶስ ምን ይመስላችኋል? የማንስ ልጅ ነው? ብሎ ጠየቃቸው. የዳዊት ልጅ ነው አሉት.43-44 እርሱም: እንኪያስ ዳዊት: ጌታ ጌታዬን. ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው ሲል እንዴት በመንፈስ ጌታ ብሎ ይጠራዋል 45 ዳዊትስ ጌታ ብሎ ከጠራው:? #እንዴት #ልጁ #ይሆናል? አላቸው .46 አንድም ቃል ስንኳ ይመልስለት ዘንድ የተቻለው የለም:. ከዚያ ቀንም ጀምሮ ወደ ፊት ማንም ሊጠይቀው አልደፈረም “አሜን. ሰላም ለአንተ ይሁን። ወንድም ቢኒ።

ከውይይት የተጠቀሰ፤ Binyam TA Kasahun Zewde ብራዘር እኔ በዚያ መልኩ ነው የምረዳው ያልገባኝ ካለ እኔም ለመማር ዝግጁ ነኝ ሁላችን ከእውቀት ከፍለን የምናውቅ ነን በእውቀት ፍጹም የሆነው ሲገልጥልን የምንማር ነንና አንተም በዚህ ጉዳይ ላይ የገባህ ካለ አካፍለኝ።ግብዝ አልሆንም ከአምና ጀምረን መሰለኝ በእ/ር ቃል ብዙ መነጋገር የጀመርነው ከአንተም የቀረለኝ መልካም ነገር አለ። እንካን የእ/ር ቃል እየተነጋገርን ዛሬ ጌታን የተቀበለ ሰው ቢመጣ በሱ ውስጥ እዚያብሄር ሊናገር እንደሚችል አምናለሁ። ስለዚህ ሁላችንም የክርስቶስ ነን በአድነት አይሰማህ ። ተባረክ። ሁሉም እያንዳንዱ ይጻፍ ዘንድ ወደ ከተማው ሄደ #ዮሴፍም ደግሞ #ከዳዊት#ቤትና#ወገን እንደነበር ይነግረናል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ ብሎ እ/ር የተናገረውን ቃሉን እያከበረ ነው እላለሁ በሰው አይን እንጂ በእ/ር አይን ዮሴፍና ማርያም አንድ ናቸው። መንፈሳዊ ነገር እንግዲህ አንዳንዴ እንዲህ ነው ። ምን ይህ ብቻ እዛ ጋር በስጋ ከዳዊት ወገን ብሎት ጌታ እየሱስ ሲያፈርሰው ዳዊትስ ጌታ ብሎ ከጠራው:? ክርስቶስ #እንዴት#ልጁ#ይሆናል? አላለም? የሉቃስ ወንጌል 2፡4-5 #ዮሴፍም ደግሞ #ከዳዊት #ቤትና #ወገን ስለ ነበረ ከገሊላ ከናዝሬት ከተማ ተነሥቶ ቤተ ልሔም ወደምትባል ወደ ዳዊት ከተማ ወደ ይሁዳ፥ ፀንሳ ከነበረች ከእጮኛው ከማርያም ጋር ይጻፍ ዘንድ ወጣ።
ሌላው ” እጮኛሞች ” የሚለው ሃሳብም ሊታይ ይችላል። ሉቃስ ወንጌል 2፡4-5 #ዮሴፍም ደግሞ #ከዳዊት #ቤትና #ወገን ስለ ነበረ ከገሊላ ከናዝሬት ከተማ ተነሥቶ ቤተ ልሔም ወደምትባል ወደ ዳዊት ከተማ ወደ ይሁዳ፥ ፀንሳ ከነበረች #ከእጮኛው ከማርያም ጋር ይጻፍ ዘንድ ወጣ።
ዮሴፍ እና ማርያም ገና አልተጋቡም ምክንያቱም ሉቃስ እነሱ ” እጮኛሞች ” እንደሆኑ ነግሮናል ። ይህም በህጋቸው እጮኛሞች አንድ ላይ ሊኖሩ አይፈቀድም። ማርያም በእጮኝነት ዘመንዋ ከወላጆቿ ጋር በናዝሬት እየኖረች እንደነበረ ያመለክታል። ዮሴፍ ከሱ ጋር ከጋብቻ በፊት በማርገዝዋ ከመንፈስ መጸለል መረገዙን ታሪኩን የሚያምን ስለማይኖር ከምላስ ጅራፍ ብሎም በድንጋይ ከመወገር ሊጠብቃት ተጣድፎ ያወጣም ሊሆን ይችላል። ማርያም እርጉዝ ናት እንደአሁኑ ዘመን ዘመናዊ መጋጋዣ ያልነበረበት መሆኑ ግልጽ ነው። ታዲያ ዮሴፍ በዚያ ሁኔታ 80 ኪሎ ሜትር ርቀት በእግር የ3 ቀን ገደማ ጉዞ ወደ ቤተልሔም ያመጣት ለምን ነበር? ማርያም በእጮኝነት ዘመንዋ ከወላጆቿ ጋር በናዝሬት እየኖረች ከነበረ ማርያም ከዳዊት ቤት ከሆነች አባቷ ከእነርሱ ጋር ጉዞውን ያላደረገው ለምንድን ነው? ከይሁዳ ወገን ቢሆን ኖሮ ምናልባትም ሊያደርግ ይችል ነበር። ሌላው ይቅርና ተጓዦች ለደህነንት ሲባል ቢሆኑም እንኳ ብቻውን አይጓዙም ነበር ። ቅድም እንደገለጽኩት ከየት ነገድ እንደ ሆነች ፍንጭ የምናገኘው መላኩ ገብርኤል ለማሪያም የእ / ርን ቃል ሲያቀብላት ከአሮን ወገን የሆነችውን ኤልሳቤጥን ዘመድሽ ብሎ የጠራትን እናስተውላለን :: የመጥምቁ ዮሃንስ እናትን ከከአሮን ወገን እንደሆነች መጽሐፍ ይናገራል በዚህም የጌታ እየሱስ እናት ማሪያም እንደ ዘመድዋ ኤልሳቤት ከአሮን ወገን እንደሆነች ግልጽ ነው :: “ሉቃ 1 36 እነሆም ዘመድሽ ኤልሳቤጥ: እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች: ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው; “መላኩ ገብርኤል ለማሪም የእ / ርን ቃል ሲያቀብላት ዘመድሽ ኤልሳቤጥ ብሎ ያረጋግጣል ከዛም ማሪያም ለወራት ከኤልሳቤት ዘመድዋ ዘን ተጠልላለች “ሉቃ 1 5 በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ; ሚስቱም ከአሮን ልጆች ነበረች: ስምዋም ኤልሳቤጥ ነበረ.” ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ; ሲል ሚስቱም ከአሮን ልጆች ነበረች:. ስምዋም ኤልሳቤጥ ነበረ “ይለናል እንደ ምናስተውለው የማሪም ዘመድ ከአሮን ወገን መሆንዋ ብቻ ሳይሆን ከተለያየ ነገድ ጋብቻ ያደርጉ እንደ ነበር እናስተውላለን :: ዘካሪያስ ከአብያ ክፍል ሲሆን ሚስቱም ኤልሳቤጥ ከአሮን ልጆች ነበረች ::
በዚህም ከይሁዳ ነገድ የሆነው የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ከአሮን ነገድ የሆነችውን የጌታ እየሱስ እናት ማሪያም መታጨቱ በዛ ዘመን እንግዳ ነገር እንዳልሆነ እናስተውላለን :: ስለዚህ ጌታ ከይሁዳ ነገድ የዳዊት ዘር የተባለው በዮሴፍ በኩል ነው የዳዊት ልጅ የተባለው እንጂ ከአሮን ወገን ከሆነችው ከናቱ ከማሪም በኩል እይደለም :: ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ ብሎ እንደ ተነገረ እ / ር ዮሴፍንና ማሪያምን አንድ ስጋ አድርጎ ስለ ሚቆጥር ከይሁዳ ነገድ አድርጎ ይቆጥራታል በዚህም ጌታ የዳዊት ልጅ ተብሎ ተጠራ :: በጋብቻ ያለው ውህደት በጌታ ፊት ምንኛ ክቡር እንደሆነ ስናስተውል ትህትናን ያስይዛል በአመለካከታችንም ንስሃ ያመጣብናል :: እዚህ ላይ እ / ር ስለ ጋብቻ ያለው አመለካከት እጅግ ጥብቅና ሰማይ ከምድር እንደ ሚርቅ ከሰው እመለካከት የራቀ እደሆነ እንረዳለን።
ጌታ ኢየሱስ እንደ 77 ኛው ትውልድ ሆኖ ከመወለዱ በፊት 76 ትውልዶችን እስከ ዮሴፍ ወስደዋል ያንንም በዝርዝር ያስቀምጠዋል።የማቴዎስ ወንጌል 1:1 #የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ።… 6 #እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ። 15 ኤልዩድም አልዓዛርን ወለደ፤ አልዓዛርም ማታንን ወለደ፤ ማታንም ያዕቆብን ወለደ፤ 16 ያዕቆብም ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደች የማርያምን #እጮኛ#ዮሴፍን ወለደ። ቢኒ። ተባረክ።

ከውይይት የተጠቀሰ፤ Binyam TA ፤ Kasahun Zewde አዶናይና ያህዌ አንድ እግዚአብሔር መሆኑን ብናውቅ በረከት ነው። መዝሙረ ዳዊት 110:1 እግዚአብሔር ጌታዬን፦…Ps 110:1 The Lord said unto my Lord, …. በመዝሙር 110 :1 አገላለጹን ከዋናው ከእብራይስጥ እንየው። ” ያህዌ አዶናይን፦ ጠላቶችህን ለእግርህ መቀመጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው።” Psalm 110:1 In Hebrew words it literally reads, “Yahweh said to my Adonai, Sit at My right hand, until I make thine enemies thy footstool.”
ዳዊት በእግዚአብሔር መንፈስ ሆኖ በጥሬው ቃል በግልጽ #ያህዌና እና #አዶናይ ብሎ በዚህ ጥቅስ ላይ አጽፏል። በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ አዶናይ ክርስቶስን የሚያመልክቱ ሆነው በመጽሃፍ ጠቅሶታል። Adonai refers to Christ እንዲያውም ነብዩ ሕዝቅኤል ብዙውን ጊዜ ሁለቱን እየለዋወጠ አዶናይን ያህዌ እያለ እያእዋወጠ በሁለቱም ስሞች ጌታን ይጠራዋል። በብሉይ ኪዳን ለእግዚአብሔር የሚሠራበት ሌላ ስም አዶናይ ነው። እሱ የአድኖ ቅርጽ plural – የብዙ ቁጥር ሲሆን “አለቃ” ወይም “ጌታ” ማለት ነው። እሱም የሉአላዊነት አገዛዝን ወይም የበላይነትን ያመለክታል። “Adonai[Adonai is the plural of Adon, meaning “Lord, Lord, LORD, master, or owner” (the word Adon derives from a Ugaritic word meaning “lord” or “father”).] ፤ Yahweh[self-Existent or Eternal” እያለ ብዙውን ጊዜ አዶናይን ያህዌ እያፈራራቀ አንዱን ጌታ በሁለቱም ስሞች አባትን ይጠራዋል። ” ጌታ እግዚአብሔር the Lord God.” ተብሎ ተተርጎማዋል ። ለምሳሌ ያህል ከአብርሃም እንጀምር። አብርሃምን የባረከው ማን እንደሆነ ከእብራይስጡ እናስተውል።
ዘፍጥ 15፡2 አብራምም፣ “አዶናይ ያህዌ ሆይ፤ ያለ ልጅ የቀረሁ ስለ ሆንሁ፣ የቤቴ ወራሽ የደማስቆ ሰው ኤሊዔዘር ነው፤ ታዲያ ምን ትሰጠኛለህ?” አለው። 3“አንተ ልጆች ስላልሰጠኸኝ፣ ከቤቴ አገልጋይ አንዱ ወራሼ መሆኑ አይቀርም።” 4በዚህ ጊዜ የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል መጣለት፤ “ይህ ሰው ወራሽህ አይሆንም፤ ነገር ግን ከአብራክህ የሚከፈል ልጅ ወራሽህ ይሆናል።” 5ወደ ውጪም አውጥቶ፣ “ቀና ብለህ ወደ ሰማይ ተመልከት፤ እስቲ መቊጠር ከቻልህ፣ ከዋክብቱን ቊጠራቸው፤ ዘርህም እንዲሁ ይበዛል” አለው። Gen 15፡2 And Abram said, Lord አዶናይ God ያህዌ what wilt thou give me, seeing I go childless, and the steward of my house is this Eliezer of Damascus?
መዝሙረ ዳዊት 97፡5 ተራሮች በያህዌ ፊት፣ በምድርም ሁሉ አዶናይ ፊት እንደ ሰም ቀለጡ። Ps 97፡5 The hills melted like wax at the presence of the Lord[Yahweh[self-Existent or Eternal], at the presence of the Lord[Adonai] of the whole earth. ወንድም ቢኒ።
• 3068 Yhovah yeh-ho-vaw’
from 1961; (the) self-Existent or Eternal; Jehovah, Jewish
national name of God:–Jehovah, the Lord. Compare 3050, 3069.
see HEBREW for 1961
see HEBREW for 3050
see HEBREW for 3069
• 113 ‘adown aw-done’ or (shortened) adon {aw-done’}; from an unused root (meaning
to rule); sovereign, i.e. controller (human or divine):–lord, master, owner. Compare also names beginning with “Adoni-“.

Hailegiorgis Tefera …እልልልልልልል… የአብርሃም ዘር ክርስቶስ ነው ክርስቶስም የክርስቶስ ዘርም አይቆጠርም ብቻ አንድ እና አንድ ሆ አንድ ነው ።
እግዚአብሔር እግዚአብሔር ነው ።
…እልልልልልልል…

ከውይይት የተጠቀሰ፤ Kasahun Zewde ክፍል 1 ፡ ሰላም፤ መቼም ቁጣህን ሃጥህ ከሚያባብለኝ ጻድቅ ይገስጸኝ በሚል በበጎ ህሊና ልየው ልዝለለው አዳምን ሳይሆን በንተ ያለውን የእ/ር ዘር ክርስቶስን በማየት በቀጥታ ወደ እ/ር ቃል እገባለሁ። በእብራይስጡ ያህዌ አዶናይን፦ጠላቶችህን ለእግርህ መረመጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው። በማለቱ በብሉይ ኪዳን አልቀበልም መንፈሳዊ አይደለም ስጋዊ ነው ብለክ ከእውነት ለመሸሽህ ትንሽ አሳከኝ ብራዘር። ስማ ወንድም አዲስ ኪዳን ለፍጥረት ያለውን መልክት ለመረዳት የፍጥረት ውድቀትና የፍጥረት መታደስን ሁሉን በተገቢው ለማስተዋል ከአሮጌው ኪዳን ምንጩን ማንበብ ተገቢ ነው። አዲስ ኪዳን ዘፍጥረት ከሌለ መሰረት የሌለው ቤት ማለት ነው። እራስክን የማን ደቀ መዝሙር ታደርጋለህ? የመንግሥተ ሰማያት ደቀ መዝሙር የሆነ ጻፊ ሁሉ #ከመዝገቡ #አዲሱንና #አሮጌውን #የሚያወጣ ነው ካልሆነ ከስረካል እውነትን ግዛት እንጂ አትሽጣት ። የማቴዎስ ወንጌል 13፡52 እርሱም፦ ስለዚህ #የመንግሥተ #ሰማያት ደቀ መዝሙር የሆነ ጻፊ ሁሉ #ከመዝገቡ #አዲሱንና #አሮጌውን #የሚያወጣ #ባለቤትን #ይመስላል አላቸው። ገናለገና እውነት ዶክትሪንህን ስለናደብህ ብሉይ ኪዳን የስጋ ጹሁፍ ነው ብለህ ብለህ ቃሉን መካድ ጀመርክ? ዜና አለኝ ለአንተ አሮጌው ኪዳን መንፈሳዊ ነው በእ/ር መንፈስ ተነድተው የጻፉት ነው ስለ በሙሴ ሕግና በነቢያት በመዝሙራትም ስለ ስላሴ የሚናገሩ አይደሉም ሁሉም ስለ እየሱስ ክርስቶስ የሚመሰክሩ ናቸው። የሉቃስ ወንጌል 24፡44 እርሱም፦ ከእናንተ ጋር ሳለሁ #በሙሴ #ሕግና #በነቢያት #በመዝሙራትም #ስለ #እኔ #የተጻፈው #ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይገባል ብዬ የነገርኋችሁ ቃሌ ይህ ነው አላቸው። የዮሐንስ ወንጌል 5/39 እናንተ #በመጻሕፍት የዘላለም #ሕይወት እንዳላችሁ #ይመስላችኋልና እነርሱን #ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ስለ #እኔ #የሚመሰክሩ ናቸው፤ ትንሽ ላስታውስህ ከዘፍጥረት እስከ ሚልክያስ የአሮጌው ኪዳን መፅሀፍት ሆኑ ከማቲዮስ ወንጌል እስከ የሀንስ ራእይ አዲስ ኪዳን ያለ እ/ር ፈቃድ አልተጻፉም። ቅዱሳት መፅሀፍት ሁሉ የእ/ር መንፈስ ያለባቸው ናቸው። ለማስተማር ለመገሰፅ ለማቅናት በፅድቅም መንገድ ለመምከር ይጠቅማሉ። ይሀውም የእ/ር ሰው ለመልካም ስራ ሁሉ ብቁ ሆኖ እንዲገኝ ነው። 2ኛጢሞ3/1617 መፅሀፍ ቅዱስ የተቀደሰ ወይም የተለየ ማለት ነው። ይሀውም የቅዱሳት መፅሀፍ መዝገብ ነው። መፅሀፉ የአርጌው {የብሉይ} ኪዳን እና የአዲስ ኪዳን ጥምር ነው። እነዚህ እ/ር እራሱ የመረጣቸውን በመንፈሱ እየነዳ ያፃፋቸው ናቸው።2ኛ ዮሀ1/2021.ተመልከት። “ የአዲስ ኪዳን ፁሁፎች ከአሮጌው ኪዳን ፁሁፎች ውስጥ ከእ/ር ዘንድ በመጣ መጠነ ሰፊ መገለጥ የተመሰረቱ ፅሁፎች ናቸው። አዲስ ኪዳን ለፍጥረት ያለውን መልክት ለመረዳት የፍጥረት ውድቀትና የፍጥረት መታደስን ሁሉን በተገቢው ለማስተዋል ከአሮጌው ኪዳን ምንጩን ማንበብ ተገቢ ነው። አዲስ ኪዳን የተፃፈው በታወቀው የቀድሞው ጊዜ የአውሮጳ ቋንቋ በግሪክ ዘየ ነው። የኣሮጌው ኪዳን የተፃፈው ሴማዊ ቋንቋ በሆነው እብራይስጥና አረሚክ ነው። Bro. J. Preston Eby, Ones He share this marvelous understanding with his anointed pen “The Book of Genesis is probably the most important book ever written. The Bible is unquestionably the one Book that has exerted the greatest influence on history of any book ever produced. The Bible, however, is actually a compilation of sixty-six books, and the Book of Genesis is the foundation of them all. If the Book of Genesis were somehow removed, the Bible would appear absurd and incomprehensible. It would be like a building without a foundation, or a bridge with no support. The books of the Old Testament, narrating God’s dealings with His ancient people of Israel, would be bigoted and racist, were they not set in the context of the progressive development of God’s wise and gracious purposes for all mankind as laid down in the early chapters of Genesis. The New Testament is, if anything, even more dependent on Genesis than the Old. There are at least 165 passages in Genesis that are either directly quoted or clearly referred to in the New Testament by Jesus and the apostles, having to do with the redemptive purposes of God and the principles of His Kingdom. I do not hesitate to say that the writings of the New Testament, describing the execution and implementation of God’s wonderful redemptive purposes in Jesus Christ, is completely unintelligible except in the light of the magnificent revelation of God’s great and glorious plan of the ages, as established in the record of man’s beginnings, recorded only in Genesis.

The word “genesis” of course means “origin” or “beginning,” and the Book of Genesis gives the only true and reliable account of the basic entities and conditions of the universe and of life. Genesis yields vital information concerning the origin of ALL THINGS – and therefore the meaning of ALL THINGS! Let every man know that in the whole of the universe there is no greater truth than this one sublime truth that THE FUTURE IS BOUND UP IN THE PAST. A man’s belief concerning his origin will inevitably determine his belief about his purpose on earth and his eternal destiny.” ….2 ወንድም ቢኒ።

ክፍል 2፡ ዐሥራ ሁለቱ ነገዶች ከያዕቆብ ተወለዱ እግዚአብሔር ለእስራኤልን የሰጠው ልጆች ሮቤል፤ ስምዖን፤ ይሁዳ፤ ይሳኮር፤ ዛብሎን፤ ቢንያም፤ ዳን፤ ንፍታሌሉ፤ ጋድ፤ አሴር፤ ኤፍሬም እና ምናሴ ናቸው። ሆኖም ሌዊም በእ/ር አይን ነገድ ነበረ። ለምሳሌ ለመጥቀስ ያክል።
ኦሪት ዘኍልቍ 18፡1 እግዚአብሔርም አሮንን አለው፦ …. 2 ደግሞም የአባትህን #የሌዊን #ነገድ ወንድሞችህን ከአንተ ጋር አቅርብ፤ ከአንተም ጋር በአንድነት ይሁኑ፥ ያገልግሉህም፤ አንተ ግን ከአንተም ጋር ልጆችህ በምስክሩ ድንኳን ፊት ትሆናላችሁ። የዮሐንስ ራእይ 7፡7 ከምናሴ ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥ ከስምዖን ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥ #ከሌዊ #ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥ ከይሳኮር ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥
“እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው” የተሳሳተ ትርጉም ነው። የኃጢአት መስዋዕት አደረገው ተብሎ መተርጎም ነበረበት።
በብሉይ የእግዚአብሔር እሳት የሚወክለው የእ/ርን ህግ ነው። [ኦሪት ዘዳግም 33፡2 በስተ ቀኙም የእሳት ሕግ ነበረላቸው። ወደ ሮሜ ሰዎች 7:14 ሕግ መንፈሳዊ እንደ ሆነ እናውቃለንና፤ ] እንደምናውቀው የጌታ አሠራሩ ልዩ ልዩ ነው፥ ሁሉን በሁሉ የሚያደርግ እግዚአብሔር ግን #አንድ ነው። ይህ እግዚያብሔር ልዩ ልዩ የእሳት አይነቶችን ይጠቀማል ለሙሴ ቁጥቃጦው ስር ሲገለጥለት የነበረው እሳትና መስዋእትን የሚበላው እሳት ወይም ሶደምና ጎመራን ያቃጠለው እሳት ልዩ ልዩ ባህርይ ነበራቸው። ለሙሴ የእግዚአብሔርም መልአክ በእሳት ነበልባል በእሾህ ቍጥቋጦ መካከል ታየው፤ እነሆም ቍጥቋጦው በእሳት ሲነድድ ቍጥቋጦውም ሳይቃጠል አየ። በእዮብ ላይም የሰይጣን ሳይሆን #የእግዚአብሔር #እሳት ከሰማይ ወደቀች፥ በጎቹንም አቃጠለች፥ ጠባቂዎችንም በላች። መጽሐፈ ኢዮብ 1፡16 በሌላ በኩል ወደ የኃጢአት ስርየት መሰዊያ ወይም ወደ አምልኮ መሰዊያ የሚላከው እሳት በአንጻሩ የእግዚአብሔር እሳቱ የተገኘውን “የኃጢአት መስዋዕት khattaw, “sin offering,” ምንም ሳያስቀር ፍጽሞ ይልሰዋል። በጥላው የኃጢአት መስዋዕት መስዋእት እንጂ መስዋዕቱ ኃጢአት አልሆነም በአካሉም በክርስቶስ እንዲሁ ነው።
‘The priest who is making atonement or offers it for sin [khattaw, “sin” or “የኃጢአት መስዋዕት “sin offering”] with it doth eat it, in the holy place it is eaten, in the court of the tent of meeting; (Lev 6:26 [YLT]) ወንድም ቢኒ። ለጥቅማችን የተወሰኑ ከአንድ አንድ ወንድሞች ላካፍል።
Dr. Jones Ones shear his study on this matter. God as it consumes the khattaw, “sin offering,” transforming it from substance to vapor that dissipates. The word khattaw literally means “sin,” but it also refers to a “sin offering,” because the offering represents the sin itself and is its substitute. The word khattaw is referenced in Greek terms in 2 Cor. 5:21, 21 He made Him who knew no sin to be sin [i.e., sin offering] on our behalf, that we might become the righteousness of God in Him.
Here we must understand Paul’s statement, not with a Greek mindset, but with Hebrew understanding. Jesus was sinless, but He became a sin offering (khattaw) on our behalf. Strictly speaking, He did not become “sin” for us, except insofar as the sin offering was identified with the sin of the one needing atonement or reconciliation.
Dear Bro. Ray also shear :is a horrible translation. God never treated His Son “AS IF” He were a sinner, seeing that He NEVER DID SIN! “Sin OFFERING” is the proper translation, not based on the singular word “sin” from which it is taken, but based on the KNOWLEDGE OF HOWS LANGUAGE IS USED. We have a plethora of proof from the Old Testament that “sin” MUST be translated “sin OFFERING,” in many Scriptures, and that is why it was translated “sin offering” in many Scriptures. But in II Cor. 5:20, the Translators dropped the ball and did not do what they surely knew was the proper way to translate it, but since they were working with Greek rather than Hebrew, they let it slide. ወንድም ቢኒ።

ከመዝጊያ ውይይት የተወሰደ፣ Kasahun Zewde ውንድም ካሳሁን ሸክላ ሰሪው እንደወደደ ሰርቶናል በደረስንበት እንመላለስ። ስለአንተ እ/ርን አከብራለሁ ለእያንዳንዳችን የሰጠን መረዳት ቢለያይም አንድ ቢሆንም እ/ር አዋቂ ነው። ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት እስክንመጣ የእ/ር ፈቃድ ይሁንብን ከቀጠልን ማቆምያ የለውም። ሃዋርያው እንዳለ ያለማቃረጥ የእውነት መንፈስ ወደ እውነት ሁሉ እየመራን፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ። እንዳለ በጌታ በርታ እኔም እበረታለሁ። በተረፈ ታምነህ ተሰማራ ። እ/ር በልብህ ያስቀመጠውን ሸክም ውደቅበት ። መጽሐፈ ምሳሌ 11፡30 የጻድቅ ፍሬ የሕይወት ዛፍ ናት፥ ነፍሶችንም የሚሰበስብ እርሱ ጠቢብ ነው። ወንድም ቢኒ።

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal