
ከጥያቄና/መልስ የተወሰደ፤ Mesfinee Z Messenger በዘፍጥረት ያህዌ ከማን ጋራ ነበር የሚናገረው”ብምስላችን ሰው እንፍጠር”ብሃላም” ኣዳም ኣንድ እንደኛ ሁነዋልና”ይላል ክተሳሳተ በሃላ፡ይህ ቃል ከድሮ የስላሴ መገለጫ ስንጠቀምበት የነበረ ቀዳሚ ቃል ነው፡፡በእርግጥ የሰሶት መገለጫ ኣይደለም፡ብዙነት ስለሚናገር ግን ካለው ሶስትነት ልምምዶች ጋር ኣገናኝተን ይዘንዋል፡፡ለዚህ ሃሳብህ ምን ይሆናል?ተባርከሃል
ዘፍጥረት 1:26 እኛ ሲል ስላሴን አያሳይም ባይ ነኝ። የቃሉ ፍቺ ለተፈጥራዊው አእምሮ ስሜት ስለማይሰጠው አይቀበለውም ስሜቱን ያለመኮርኮሩ ትክክል ነው ይህ መንፈሳዊ እንጂ 5ቱ የስሜት ህዋሳት ሰፈር ዘንድ ስፍራ የለውምና። መንፈሳዊውን ነገር በመንፈስ ይምንረዳው ነውና። ብዙ ሰዎች በመቆጣትም በድንጋጤም እኛ ሲል ስላሴን አይደል እንዴ የሚያሳየው ብለውኛል እንደደረሱበት ነው እንግዲህ? ጥሩ ጥያቄ ነው እኛ የሚለው ቃል 3ቱ ሥላሴን እግዚያብሄሮች ለማሳየቱ በምን እርግጠኛ ይኮናል ትሆናለህ/ሽ? እኛ 2ለትም 3ትም 4ትም 5ትም ከዛም በላይ የሚያሳይ ሊሆን ይችላልና።
በቤተክርስቲያን ውስጥ ስለ ሥላሴ በአብያተ-ክርስቲያናት ክርክር ውስጥ ዋናው ነጥቡ ተደርጎ ይነሳል። አንድ ጊዜ አምላክ ሥላሴ እንደሆነ አድርገው ከተረዱና ካወቁ በኋላ እንደገና በእግ/ር ቃል ለመታረም ለብዙዎች ጭንቅ ነው። በውኑ እነሱ በትክክል 3 እግዚአብሔር ሲሉ እንደ ቃሉ ተረድተዋልን? ለራስህ/ሽ ቃሉን መመርመር መልካም ነው።
ይልቁኑ ይህ ቃል የእግዚአብሔርን ሙሉነት የሚያስረዳ በድርብ ክብሩ እራሱን የገለጠበት ነው እላለሁ። የእግዚአብሔር አምሳያ ጣእም ድርብ ስለሆነ ወንዶችና ሴቶች መፍጠሩ የሱ መልክ ነው። የጥንት የስነ-መለኮት ምሁራን በስላሴ ላይ በጣም ትኩረት ስላደረጉበት በዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ለይ የእግዚአብሔርን ቃልን ዋናን ሃሳብ ሳያስተውሉት ቀርተዋል። “ከዚያም እግዚአብሔር አለ ሰውን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር አለ. እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፡ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፡ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ።
ሀይማኖት ያጔሯ : የእግዚአብሔር መንፈሳዊ መልክ ወንድና ሴት ነው ማለትም ማንም ሳያግዘው በራሱ ሊያዘጋጅ ይችላል። ይህን ለማለት ለሰው የሚቸግረው የሰው አእምሮ ከሥጋ ፍትወት ጋር የተቆራኘ ስለሆነ ግልፅ ነው። እግዚአብሔርን መንፈስ እንጂ ስጋ ስላልሆነ ፍትወተ ሥጋ አይመለከተውም። እርሱ ልእለ ተፈጥሮና ልእለ ፍጡራን ነውና ። የእግዚአብሔር ክብር ሌላ ነው የሰው ክብር ሌላ ነው የመንፈስ ክብር ሌላ ነው የሥጋ ክብር ሌላ ነው።
የቃሉ ፍቺ ያበራል።
“እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፡ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፡ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ።” እንደምናስተውለው የእግዚአብሔር መልክ አምሳል እና አምሳያ በዚህ ቃል መሰረት የወንድን እና የሴትን ገጽታ ያካትታል። ይህ ባይሆን ኖሮ ምድራዊው የእግዚአብሔር አምሳያ ተብሎ የፈጠረው ሰው አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት የያዘ ባለ አንድ ፆታ ብቻ ሆኖ ይፈጥረው ነበረ። ሲፈጥራቸው ግን በአንድ አዳም ውስጥ ሁለት ፆታ ነበር እግዚአብሔር ግን ቡሃላ ለሁለት ከፈላቸው።
እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፡ በመልኩ? በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፡ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ;; በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፡ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ? ግልጽ ነው። ።Gen 1 verse 27, “And God created man in His own image, in the image of God He created him; male and female He created them.” The #image and #likeness of #God, then, #includes#male and #female#aspects of #God. If this were not so, then the #earthly #image of God would #express just #one#sex, either male or female.
በእርግጥ የጥንት የነገረ-መለኮት ምሁራኑ አምላክን በአዎንታዊነት ለመግለጽ እውነትን ለማሳየት አልቻሉም። እግዚአብሔር በራሱ ሙሉ ስለሆነ ማንም ሳያግዘው መለኮታዊ ሙልአቱን ተጠቅሞ ማዘጋጀት እንደሚችል ከገለፁት እየተገዘቱ መገለል እንዳይደርስባቸው እውነትን መቅበር ይመረጣሉ።ሌላው ችግር ብዙዎቹ የጣዖት አምልኮ አምላኪዎችና አማልክቶች የሴት አገላለጾች ስለሚጨምሩ ሁሉ እርስ በራሱ እየተፈራራ ችግር ነበረ። ወንድም ቢኒ።
ተጨማሪ 2
ጥያቄና/መልስ፤Mesfinee Z Messenger ፡ ማቴዎስ ወንጌል 28/19-20፡ የሚገርመው ጌታ ሲያዛቸው በማቴዎስ ወንጌል 28/19-20 ትክክለኛው በእ/ር ቃል ውስጥ በማስረጃ እንየው። “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በስሜ እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።” ነበር ያላቸው ቡሃላ ሲተረጉሙን የስላሴን ትምህርት እጅ ጠምዝዘው ለማሰራጨት በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም ተብሎ እንዲጨመርበት ተገደደ። ሆናም ይህን እውነት የሚፈታላችሁ የእ/ር ቃል እራሱ ነው። ሃዋርያት የታዘዙትን ብቻ እንዳደረጉ ግልጽ ነው። “ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው” በስሜ አንጂ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም ብሎ አዝዋቸው ቢሆን ከቃሉ ፈቀቅ አይሉም ነበር። አስተውሉ እነሱ ለአንዴም እንካን በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም አላጠመቁም አልታዘዙምና ባዘዛቸው በእየሱስ ስም ብቻ ግን አጠመቁ።
የሐዋርያት ሥራ 2/38 ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።
የሐዋርያት ሥራ 8/16 በጌታ በኢየሱስ ስም ብቻ ተጠምቀው ነበር እንጂ ከእነርሱ በአንዱ ላይ ስንኳ ገና አልወረደም ነበርና።
የሐዋርያት ሥራ 10/48 በኢየሱስ ክርስቶስ ስምም ይጠመቁ ዘንድ አዘዛቸው። ከዚህ በኋላ ጥቂት ቀን እንዲቀመጥ ለመኑት።
የሐዋርያት ሥራ 19/5 ይህንም በሰሙ ጊዜ በጌታ በኢየሱስ ስም ተጠመቁ፤
የሐዋርያት ሥራ 19/4 ጳውሎስም፦ ዮሐንስስ ከእርሱ በኋላ በሚመጣው በኢየሱስ ክርስቶስ ያምኑ ዘንድ ለሕዝብ እየተናገረ በንስሐ ጥምቀት አጠመቀ አላቸው። መቼም የእ/ርን ቃል እጅ ያሻቹሁን ያእል እጁን ብትጠመዝዙት ስላሴ የሚለው ቃል በእ/ር ቃል ውስጥ አንድም የለም ይህ በራሱ በቂ ነው። ቀጥተኛ ቃሉ ቢኖር ኖሮ የነገር ፍጻሜ በሆነ ነበር ነገር ግን ቃሉ በፍጥረቱ የበረሀ፤ የአለም የነበረ ወደ ቤተ ክርስቲያን ተደቅሎ የገባ እስኮሆነ ድረስ በእ/ር ቃል የሚያረጋግጥ አንድም የ3ቱ ስላሴዎች ምስል አምላኪ ቃሉን ማረጋገጥ እንዳይችል የአደባባይ ምስጢር ነው። ይህ አመለካከት እንደ ናዝሬት ፈረሶች እይታ ብቻ ሳይሆን ልክ የጋቭሮቮች ፈረስ አረንጋዴ መነጽር ካጠለቅላቸው የከረመውን የበሰበሰውን ድርቆሽ ሳር አረንጋዴ ነው ብለው ግጥም አርገው እያመነዠኩ ያጣጥሙታል። የስላሴ መንጽር ያጠለቀ ሰውም እይታው 3 ከሆነ ዘንዳ የቃሉን ፊደል እንጂ የቃሉን መንፈስ ማየት አይችልም ማትዮስ 28፤19 ሆነ ሌላ ቦታ ሶስት ነገሮች ከተጠቀሱ ለአሪፉ ባለመንጽር የሚታየው በአረንጋዴ መብራት ወስጥ 3ቱ ስላሴ ነው።
እኔ እንደማስተውለው መንፈስ የሆነው የአንዱ እ/ር በተለያየ ክብር መገለጦች ናቸው። አንድ ቦታ መጠቀሳቸው ወይም መፃፋቸው በቀር ሶስት እግዚአብሔሮችን ወይም ስላሴን አያረጋግጡም። እኔ እንዳውም ሐውርያት በስላሴዎች እንዲያጠምቁ አዝዋቸው ከነበረ ባስላሴዎች ስም ባጠመቁ ነበር ። በእየሱስ ስም ብቻ ማጥመቃቸው ለራሱ ግን ከበቂ በላይ ማስረጃ ነው ለኔ። ለባለ አእምሮ ሰው ግን በመገለጥ ሳይሆን በሎጂክ የሚንቀሳቀስ እስከሆነ ድረስ ለማጥናት ፍላጎቱ ላለው ሁሉ እውነትን ወደማወቅ እንዲደርስ እ/ር ቢፈቅድ ከታሪክ መዛግብት ጭምር ማስረጃዎችን ለማቅረብ እሞክራለሁ። ብዙ የቀድሞ እውነቶችን ለማጥናት ስሞክር ይህ ቃል በተጽኖ ስር ሆንው ሊቃውንቱ እስክ ጨመሩት ቃል ድረስ ይህ ቃል እንዳልነበር ያሳያል።
የወጣው የመጀመርያውን የቤተ ክርስቲያን ታሪክ የፃፈው ” ሂስቶሪያ ኤክሊሲሲሳካ” “Historia Ecclesiastica,” Church History (Eusebius) ጳጳስ ሲዘርያ ዩሲቢየስ የተወለደው 260 – 339 ዓመትም ሞተ። መጽሐፉ በ 325 ታትሞ የወጣው ነው። ” ሂስቶሪያ ኤክሊሲሲሳካ” የእሱ መጽሐፍ የቤተክርስቲያን ታሪክ ተብሎ የሚታወቀው የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ በይፋ ከመፅደቁ ከሰባ ሁለት ዓመታት በፊት ነበር። ይህ የቀድሞ ቤተክርስቲያን ታሪክ በጥልቀት ለመገንዘብ ለዘመናዩም የክርስትና አካሄድ ቅርጽ ሰጥቶአል። ማትዮስ28፡19 ሲጠቅስ 17 ግዜ ህዝብን ሁሉ በስሜ አጥምቁ ብሎ ከእ/ር ቃል እየጠቀሰ ጽፎታል “Go disciple ye all the nations in my name” (17 times) ይህ ማለት ምን ማለት እንደሆነ በማስተዋሉ ፈጣን ለሆነ የቃል ግማሽ ይበቃዋል። ለመመርመር ሊያነሳሳው ይገባል። ይህን መጽሐፍ ሊንክ ከስር አስቀምጣዋለሁ ዳውንሎድ በማድረግ አውርዱትና አንቡቡት እኔ ያገንኘሁት ይሂብሩና የግሪክ ስኮላር ከሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት መስራች የትምርት ቤቱ የመጀመርያ ተማሪዎች ስለነነበር የሰጡን ነው ምናልባት ኦንላይን ይገኝ ይሁን አላውቅም ጥራዝ መጽሐፉ ግን በአሳታሚዎች እንደሚሸጥ አውቃለሁ። ወንድም ቢኒ።
https://www.dropbox.com/s/tusj…/Church_History_Complete.pdf… ወንድም ቢኒ።
Éÿù Ÿè Âpô Lj Bra ተባረክ! ግን
ማለት?? አንተ የአሁኑን(1962 እትም) bible አትቀበለውም??Delete or hide this
Binyam TAÉÿù Ÿè Âpô Lj ሰላም ላንተ ይሁን ብራዘር። ከማስተዋል ጋር እቀበለዋለሁ ሆኖም ሲተረጎም ጥቃቅን ስተቶች እንዳሉት በመገንዘብ ጭምር ነው። በጣም የሚያሳዝነው አብዛኛዎቹ የእንግሊዝኛም ሆነ የአመርኛ ትርጉሞች ብዙ የሚመሰገኑበት ቢኖርም ለምሳሌ ያህል ዘመንን በተመለከተ ሲተረጉሙ ግድ የለሽ ሆነው ዘልአለም እያሉ በመተርጎማቸው በእ/ር ህዝብ ላይ ለዘመናት ትልቅ ግራ መጋባትን አስከትለዋል። ይህም ብዙ ትውልዶችን ለአያሌ ዘመናት የተዛባ መረዳት ውስጥ ቆልፎ አስቀምጠዋቸዋል። ለመጥቀስ ያህል የእንግሊዝኛም ሆነ የአመርኛ ትርጉሞች KJV ላይ እዲሁም በዚህ መጽሐፍ ተጽኖ ስር የተተረጎሙ ሁሉ ላይ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ቅዱስን ስለሚሳደብ ሰው የተናገረውን ቃል እንዲህ ያስቀምጡታል። እግዚያብሄር ያሳያችሁ አንዱ ቃል ወደ ስንት ተበታትኖ እንደ ተተረጎመ age {2 ጊዜ beginning of the World {2} ጊዜ, for ever and ever,(8) course{1}ጊዜ World {32} ጊዜ eternal {42}ጊዜ, world began{1}ጊዜ forever{27}, for evermore{2}, እነዚህ ሁሉ ዘመን ወይም እንደ አገባቡ ከዘመን ዘመን፤ ለዘመናት፤ ለዘመኑ፤ ወዛተ ተብሎ በቀላሉ በዚህ መልክ መተርጎም ነበረበት። “ማርቆ3/29 መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ ሁሉ ግን “የዘልአለም” ሃጥያት ይሆንበታል እንጂ አይሰረይለትም” ከዚህ የተሳሳተ ትርጉም የተነሳ የተሳሳተ ጽንሰ ሃሳብ ተወልደዋል። ለዘልአለም ይቅር የማይባል ሃጥያት አለ ብለን እንድናስብ አድርጎን ነበር። ነገር ግን የቃሉ ፍቺ በትክክል እንዲያቀብል አድርገው ከተረጎሙት ከጥቂት የእንግሊዝኛም ትርጉሞች መካከል Emp hatic Diaglott የተባለው ትርጉም ትክክለኛውን ትርጉምi እዲህ ያስቀምጠዋል። “Whoever may blasphemy the Holy Spirit no forgiveness to the age but is exposed to anian lasting judgment mar3/29” “መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ ሁሉ “ለዘመኑ” ይቅር አይባልም። ነገር ግን ”ለዘመኑ“ ፍርድ ይጋለጣል።“ እንደ ምናስተውለው ይቅር የማይባለው ለፍርድ የሚጋለጠው ለዘመኑ ፍርድ እንጂ ለዘልአለም ፍርድ አይደለም። በማትዮስ 12/32 ያለው ደግሞ እንዲህ ተብሎ ተተርጉመዋል ”በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚናገር ሁሉ በዚህ ”አለም“ ቢሆን በሚመጣው አይሰረይለትም። አለም የሚለው ቃል ከግሪኩaion ማለትም ዘመን age ተብሎ መተርጎም ከነበረበት ቃል የመጣ ነው። ቃሉ መተርጎም የነበረበት “መንፈስ ቅዱስ ላይ የሚናገር ሁሉ በዚህ “ዘመን” ቢሆን በሚመጣው አይሰረይለትም” ነው። ጌታ እየሱስ የተወለደው በህግ ዘመን ስለ ነበር በዚህ ዘመንም ቢሆን ማለቱ የህግን ዘመን ለማሳየት ሲሆን በሚመጣው ዘመን ቢሆን ሲል ደግሞ አሁን እኛ ያለንበትን የፀጋውን ዘመን ማለቱ ነው። ይህን ካስተዋልን ስለ ዘመንና ስለ ዘልአለም ያለውን ብዥታ ያጠራልናል። በግሪክ aion(ሰዋሰው noun) በግልጽ “ዘመን ወይም ያልተወሰነ ክፍለ ጊዜ ነው an age or an indefinite period of time, Young’s Concordance” BROTHER BINYAM
Binyam TAÉÿù Ÿè Âpô Lj ይህን አንብበው የከበረ ነገር ይቀርልካል። የመፅሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን ታሪክ መረዳት። Understanding Bible Translations History http://wongelradio.org/archives/2114