አባትን Theon Θεὸν ልጅን Theos Θεὸς ,


ከውይይት የተጠቀሰ፤ Binyam TA Fitsum Abraham ሰላም ወንድም ፉጹሜ፤ አይዞህ አልተናደድኩም ከመሰለ ይቅርታ። ያነሳከው ሃሳብ ይሄ ግልጽ ነው ብራዘር። የአባትነትና የልጅነት ክብር የሚገለጸው ለክብሩ በተገባ ቃል ነው። በየዮሐንስ ወንጌል 1፡1 ሳያሻማ አባትን Theon Θεὸν ልጅን Theos Θεὸς , ብሎ ይጠራዋል። እነዚህን ሁለት ቃላቶች ያዝልኝና በትግስት የተወሰኑ እውነቶችን በነዚህ Theon Θεὸν እና Theos Θεὸς , እናስተውል። ባለፈው እንደተባለው ግን ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፦ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ የተባለው ለአባት ነው እንጂ ልጅ ሌላ ነው የሚለው ትክክል አይደለም። እራሱ ልጅ ነው ወይም Theos Θεὸς ተብሎ የተጠራው ነው አልፋው ኦሜጋውም የተባለው ቃል በቃል እየው።
(Rev 1:8 ) “I am the Alpha and the Omega,” says the Lord[Kyrios Κύριος] God[Theos Θεός ,] , “He who is and was and evermore will be— the Almighty [the Ruler of all.]”
በብሉይም ብትሄድ “ያህዌ Yhovah yeh-ho-vaw’ አዶናይን ‘adown aw-done’ ጠላቶችህን ለእግርህ መቀመጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው። መዝሙረ ዳዊት 110፡1” ተመልከት በብሉይ ያህዌ ነው ለአዶናይ በትንቢት መልክ በቀኜ ተቀመጥ ያለው እንዳትረሳ በቀኝ ይህ ልጅነትን ሲጠቁም ነው። አራሱ አዶናይ ማለትም እግዚአብሔርን[አዶናይ ’ă•ḏō•nāy אֲדֹנָ֛י] በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት ሲባልለት ታያለኅ ። ትንቢተ ኢሳይያስ 6፡1 ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርንእግዚአብሔርን[አዶናይ ’ă•ḏō•nāy אֲדֹנָ֛י] በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፥ የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት ነበር። በራእይ ላይም እራሱ በብሉይ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የተባለው የእብራይስጥ መጠርያው አዶናይ በግሪክ [ Theos Θεός] የተባለው ተቀምጦ በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ታየዋለህ አሁንም ቃል በቃል እየው። የዮሐንስ ራእይ 4፡8 አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሉአቸው፥ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዓይኖች ሞልተውባቸዋል፤ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ[ Theos Θεός] እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም።
የዮሐንስ ራእይ 4፟፡10-11 ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ፦ ጌታችንና አምላካችን[ Theos Θεὸς] ሆይ፥ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ።
አባትም በTheon Θεὸν ፈንታ ልጁ በተጠራበት Theos Θεὸς ተብሎ እየተፈራረቀ ሲጠራ ታያለሕ። ወደ ዕብራውያን 1 :8 ስለ ልጁ ግን፦ አምላክ[ Theos Θεός , God] ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው። 9 ጽድቅን ወደድህ ዓመፅንም ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር [Theos Θεός , God] አምላክህ [Theos Θεός , God ]ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ ይላል። ወንድም ቢኒ።

ተጨማሪ ሌላ።

ከውይይት የተጠቀሰ፡ Fitsum Abraham ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ! the Word was God! ቃልም (ሎጎስም: የእ/ር ሐሳቡም) በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። የወንድማችን ሃሳቡም ከከወንድማችን ጋር ነበረ ከተባለ ሃሳቡ ሌላ ወንድማችን ሌላ ነው ማለትህ ነው? ወይስ ሃሳብህ የወንድማችን hybrid human clone genetically identical copy ኮፒየ ነው ኮፕየ ነው ዘራፍ ሃሳቤ ከኔ ተቀብቶ የተላከ ነው። ሃሳቤን ፈትጥሬዋለሁ በስልጣን በመለኮት አንድ ነን? ወዘተ…. ያስቃል። ቃልም (ሎጎስም: የእ/ር ሐሳቡም) በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። የሚለውን ሌላ አምላክ እንዳለ አድርገህ መረዳትህ ይደንቃል። ቃሉ ላይ ቆይ። ምዕራፍ 1: 1. በመጀመሪያው ቃል (The Word ፡logos ሎጎስ ማለት የእ/ር ሀሳብ አስተሳሰቦች ስብስብ፤ ምክንያት፤ ንግግር የኮሙኒኬሽን፤ የቃላት መግለጫ ሐሳብ ሎጎስ) ነበረ። ቃልም (ሎጎስ: የእ/ር ሐሳቡ) በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። ቃልም (ሎጎስ: የእ/ር ሐሳቡም) እግዚአብሔር እራሱ ነበረ።
John 1:1. Within a beginning there was The Word (logos: The Thought; The Collection of Thoughts; The Idea; The Reason; The Discourse; The Communication; The Verbal Expression). And the Word (logos: the thought; the expression) was (and continued being) facing, directed and moving toward (or: with) God. And the Word (logos: the thought; the idea; the reason; the expression) continued being God. [or: Originally the Word was existing and continued to be, and the Word was being {projected} toward God. And the Word, It was existing being God (idiomatically: And the Word was just what God was; And the Expression was {an extension of} Deity).] ልጨምርልህ እየሱስ ክርስቶስ ቃል እ/ር ብቻ ሳይሆን እየሱስ ክርስቶስ እራሱ ጳራቂላጦስ አጽናኙ ነው በእ/ር ቃል እንየው። ጌታ ምን እንዳለ አስተውል። ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም ወደ እናንተ እመጣለሁ። መጣ እሺ ከዛስ በኋላስ መንፈስ ስለሆነ ምን አለ? ዓለም አያየኝም እናንተ ግን ታዩኛላችሁ በዚያን ግዜ ምን ይከሰታል? ማወቅ ይከሰታል። ‘እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ .’ ሃይሉ ያለው ማወቁ ላይ ነው ዓለም አያየኝም እናንተ ግን ታዩኛላችሁ። ‘ቅኔውን ሲፈታው ስለራሱ እንጂ ስሌላ እያወራ እንዳልሆነ አስተውል? .
የዮሐንስ ወንጌል 14/18 ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ. 19 ገና ጥቂት ዘመን አለ ከዚህም በኋላ ዓለም አያየኝም እናንተ ግን ታዩኛላችሁ። እኔ ሕያው ነኝና እናንተ ደግሞ ሕያዋን ትሆናላችሁ. 20 እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ . John 14፡18 I will not leave you #comfortless: I will come to you. ወንድም ዮሐ 14:18 ጌታችን ምን እንዳለ በግማሽ ሳይሆ በሙሉ ትኩረትህ አሁን አስተውል። መንፈስ ማን እንደሆነ መንፈስ ቅዱስ ምን እንደሆነ ግልጽ ያደርግልናል . የስላሴ 3 ኛ አካል ነው? ጌታ እራሱ ይናገር። የዮሐንስ ወንጌል 14/28 #እኔ#እሄዳለሁ#ወደ#እናንተም#እመጣለሁ እንዳልኋችሁ ሰማችሁ[ሄዶ በመንፈስ ክብሩ ተመልሶ የሚመጣው ማነው? እየሱስ እራሱ አጽናኝ ሆኖ]. “#ወደ #እናንተ #እመጣለሁ[እኔ] አስተዋላችሁ ጌታ ምን አለ? እኔ እሄዳለሁ: እኔም ወደ አንተ እመጣለሁ! ወደ እናንተ እመጣለሁ[ማ ይመጣል እየሱስ] 20 እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን [አጽናኙ በሚመጣበት ቀን] ታውቃላችሁ. ( “በዚያም ቀን እናንተ እኔ በአባቴ እንዳለሁ ታውቃላችሁ እናንተም በእኔ ውስጥ [መቼ ቀን? አጽናኝ ሲመጣ]” የዮሐንስ ወንጌል 14/28 #እኔ #እሄዳለሁ #ወደ #እናንተም #እመጣለሁ እንዳልኋችሁ ሰማችሁ[ሄዶ በመንፈስ ክብሩ ተመልሶ የሚመጣው ማነው? እየሱስ እራሱ አጽናኝ ሆኖ]. “#ወደ #እናንተ #እመጣለሁ[እኔ] አስተዋላችሁ ጌታ ምን አለ? እኔ እሄዳለሁ: እኔም ወደ አንተ እመጣለሁ! እኔ እሄዳለሁ ወደ እናንተም እመጣለሁ! አሁን እየሱስ ክርስቶስ እራሱ ጳራቂላጦስ ተብሎ መጠራቱን በእ / ር ቃል እናረጋግጥ. አፅናኝ [ጳራቂላጦስ] ሌላ አጽናኝ [ጳራቂላጦስ] ይሰጣችኋል ያለው ጳራቂላጦሱ ማን እንደሆነ እናያለን።
የዮሐንስ ወንጌል 14 / 15-16 ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ. እኔም አብን እለምናለሁ [ጸልዩ] ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ [ጳራቂላጦስ; parakletos አጽናኝ፤ አማላጅ, consoler:. Advocate, አጽናኝ] ይሰጣችኋል። ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ዘንድ።
1 ኛ የዮሐንስ መልእክት 2 ፡1 ልጆቼ ሆይ: ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ. ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ #ጠበቃ [ጳራቂላጦስ; parakletos አጽናኝ፤ አማላጅ, consoler: -advocate, ጠበቃ አጽናኝ] አለን #እርሱም#ጻድቅ#የሆነ#ኢየሱስ#ክርስቶስ#ነው። አመለጠህ? ልድገምልህ #ጠበቃ [ጳራቂላጦስ; parakletos አጽናኝ፤ አማላጅ, consoler: -advocate, ጠበቃ አጽናኝ] አለን #እርሱም #ጻድቅ #የሆነ #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ነው። ፡) ….ክፍል 2 ወንድም ቢኒ።
ክፍል 2፤ በተፈጥራዊው አእምሮ እንደምታስበው የሰው ልጅ እየሱስ ክርስቶስ አባት ማን ይመስልሀል? ጌታ እየሱስ ክርስቶስ በብፅዕት ድንግል ማርያም ማህፀን # የተረገዘው በመንፈስ ቅዱስ መፅለል ነበር.
እንደምናስተውለው መንፈስ ቅዱስ ለእርግዝናዋ ምክንያት ነው። እየሱስም ተወለደ ያስረገዛት መንፈስ ቅዱስ ቢሆንም የመንፈስ ቅዱስ ልጅ ግን አልተባለም አልነበረምም ነገር ግን የአባት (አብ) ልጅ ነው “የአብ ልጅ” ኛ ዮሐንስ 2: 3 አስተውል ያስረገዛት #መንፈስ ቅዱስ #የእግዚአብሔር #መንፈስ #ነው እንጂ ከ 3 ቱ ስላሴዋች አንዱ አይደለም ቢሆን ኖሮ እርሱ ባስረገዘ ሌላ አባት ባልተባለ ነበረ። እንደ የስላሴ አፈ ታሪክ ቲፎዞዋች አባባል መንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ ስብእና ለብቻው ያለው ቢሆን ኖሮ ወይም ከ2ቱ ወይም 3 ቱ ስላሴዋች አንዱ ቢሆን ኖሮ መንፈስ ቅዱስ አባቱ በተባለ ነበር እ ንጂ ሌላ የእንጀራ አባት ጣልቃ የገባ መለኮት አብ የተባለ በጉልበት አባቱ ባልሆነ።
እንኳን አስተዋይ ሰው ማንኛውም ቀላል አስተሳሰብ ያለው ሰው ማንም አንዲት እናት ማኅፀን ውስጥ አንድ ሕፃን ከመወለዱ ጊዜ ልጁ ወላጅ አባት አባት ይባላል እንጂ ሌላ መጤ አባት አይባልምም ሌላ ሰው ወይም ሥላሴ አባል እንደሆነ መረዳት እንችላለን። አስተውል ያስረገዛት #መንፈስ ቅዱስ #የእግዚአብሔር #መንፈስ #ነው።
ብዙ ሰው የመጀመሪያውን ትእዛዝ ጥሶ ይመላለሳል ቃሉ ጌታ እግዚአብሔር አንድ ነው ሲለው ሰው ግን በህይወቱ የእግዚአብሔርን ቃል ከንቱ ለማስቀረት ወጥመድ ሆኖበት 3 እግዚአብሔሮችን የነ ዳቪንቼ የፈረንጅ ምስል ስእል ያስባል ይኖራል። እግዚአብሔር መንፈስ ነው አንድ ነው። የሚቀጥለው ትእዛዝ የሚጀምረው እግዚአብሔር አንድ እንደሆነ በማወቅ ሳይሆን ለማወቅ መጀመሪያ ስማ ! ሰማና! ሰማና! ያልሰማ ብዥ ብሎበት አንድየን 3 ሆኖ ያየዋል። እስራኤል ሆይ: ሰማ የማርቆስ 12:29 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው: ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ እስራኤል ሆይ: #ስማ ፤ጌታ አምላካችን #አንድ ነው። በተረፈ በጌታ ፍቅር ሰላም ለአንተ ይሁን። ወንድም ቢኒ።

ተጨማሪ 3

ከውይይት የተጠቀሰ፤ Fitsum Abraham ሰላም ብራዘር፤ ክፍል1፡ 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 6:14 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስኪገለጥ ድረስ ያለ እድፍና ያለ ነቀፋ ሆነህ ትእዛዙን ጠብቅ፤15 ያንም መገለጡን በራሱ ጊዜ ብፁዕና #ብቻውን #የሆነ ገዥ፥ #የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ፥ ያሳያል። 16 እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን፤ አሜን። our Lord Jesus Christ (the Anointed One), 15 Which [appearing] will be shown forth in His own proper time by the blessed, only Sovereign (Ruler), the King of kings and the Lord of lords, 16 Who alone has immortality [in the sense of exemption from every kind of death] and lives in unapproachable light, Whom no man has ever seen or can see. Unto Him be honor and everlasting power and dominion. Amen (so be it).AMP
#ብቻውን #ገዥ #የሆነው #የነገሥታት #ንጉሥ#የጌቶችም #ጌታ እርሱ #ብቻ #ኢመዋቲ ነው፤ #ሊቀረብ #በማይቻል #ብርሃን #ውስጥ ይኖራል፤ የተባለው #የነገሥታት #ንጉሥ፣ #የጌቶችም #ጌታ ማነው? እንየዋ ቃሉ እንዲህ ይለናል #በጉም #የጌቶች #ጌታና #የነገሥታት #ንጉሥ #ስለ #ሆነ
የዮሐንስ ራእይ 17፥14 እነዚህ #በጉን ይወጋሉ፤ በጉም #የጌቶች #ጌታና #የነገሥታት #ንጉሥ #ስለ #ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፥ ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ።
19፥16 በልብሱና በጭኑም የተጻፈበት፦ #የነገሥታት #ንጉሥና #የጌታዎች #ጌታ የሚል ስም አለው።
#ሊቀረብ #በማይቻል #ብርሃን #ውስጥ ይኖራል እውነት ነው ልጅነትን ለማስተማር ግ ን በስጋ መጋረጃ ሸፍኖታል ብርሃን መሆኑን metamorphoo አሳይተዋል። ከሰው ክብር ወደ መለኮት የብርሃን ክብር ተለወጠ። የማቴዎስ ወንጌል 17፡2 በፊታቸውም #ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ #ፀሐይ #በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። And was transfigured[metamorphoo] before them: and his face did shine as the sun, and his raiment was white as the light. ለዚህ የቀረበ ለውጥ ምሳሌ አንዲገባን ወደ ልጅነታችን ልመልሳችሁ Metamorphosis በተፈጥሮ the most clasick example in nature is የቢራቢሮ ለውጥ ነው። ከኧባ ጨጋሬነት በምድር ላይ ተስቦ ከሚሄድ ማንነት ወደ የሚበር ፍጥረት የመቀየርዋ ሂደት ነው። የተጠቀመበት from catrepiler to buterfly Metamorphosis እደሆነ 7ኛ ከፍል ተምረናል። cocoon እጭ ውስጥ ኧባ ጨጋሬ አካሉን ይከትና ጭንቅላቱ ወደ ውጪ ያስቀራል ጭንቅላቱ ይወድቅና የቀረ አካሉ ሲወጣ በተአምር በሚመስል ቢራቢሮ ሆኖ ይወጣል ይቀየራል። ያለውጥ transformion ከኧባ ጨጋሬ በምድር ላይ ተስቦ ከሚሄድ ወደ ሚበር ፍጥረት የመቀየርዋ ሂደት የሚገርም ነው። ከአንድ ፎርም(ቅርፅ) ወደ ሌላ ፎርም ያለው ለውጥ ነው። ምንም እንካን ለሙሴ ኦሪት ዘጸአት 33፡20 ደግሞም፦ ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልህም ብሎ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን መሆኑን ነግሮ ጀርባውን ቢያሳየውም ስጋ ለብሶ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ዮሐንስንም ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው ሚዛኑን በጠበቀ መልኩ ብርሃን መሆኑን ገለጠ እንደዛም ሆኖ እነ ጴጥሮስ ብርሃኑ ትንሽ አጡዝዋቸው ነበር። የማርቆስ ወንጌል 9፡5-6 ጴጥሮስም….የሚለውን አያውቅም ነበር። በፊታቸውም #ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ #ፀሐይ #በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ።….2 ወንድም ቢኒ

ክፍል 2፡ እየሱስ ህግን የሰጠውና ስጋ የለበሰው ያህዌ ነው! ጌታ እየሱስ በምን ስልጣን ነበር የተራራው ስብከት ተብሎ በሚታወቀው በማቲዮስ 5-7 ትምህርቱላይ የፍቺውን ትክክለኛ ትርጉም ሲያርም የነበረው?
ሐዋርያው ጳውሎስ ሲነግረን ስለዚህ በፊት ክርስቶስን በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም፡ ከዚህ ቡሃላ መንፈስ ሆነዋልና። ብሎ ናል ።“ኋለኛው አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ።1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15/45” “ ጌታ ግን መንፈስ ነው[ Now the Lord is that Spirit:]፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ።2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3/17” [2Cor 3/17 Now the Lord is that Spirit: and where the Spirit of the Lord is, there is liberty.]
እየሱስ ህግን የሰጠውና ስጋ የለበሰው ያህዌ ነው! ጌታ እየሱስ ክርስቶስ በስጋ የመጣው ወደ መንፈስ ሊመራን ነው። በመጀመሪያው ቃል እንደ ነበረ፥ ዘንድም ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር እንደነበረ። ቃልም ሥጋ ሆኖ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ እንደመጣ የማያምን ሁሉ ሃሰተኛ መንፈስ ነው የክርስቶስ ተቃዋሚውም መንፈስ ነው፤ ። ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ግን ከእግዚአብሔር ነው።
“1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4/2 የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፥3 ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ እንደ መጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ይህም የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው፤ ይህም እንዲመጣ ሰምታችኋል፥ አሁንም እንኳ በዓለም አለ።”
*እየሱስ ፈጣሪም ነው ህግን የሰጠውና ስጋ የለበሰውም ያህዌ እሱ ነው! ይህንን እውነት ለማስተዋል በቀደሙት ክፍሎች በብዙ አይተነዋል እንዲሁም እያንዳንዱን መጽሐፍት ብትመረምሩ ጌታን በዛ ውስጥ ታገኙታላችሁ። የእብራይስጥ ቋንቋ እራሱ ይህንን እውነት ያረጋግጠዋል። አንድ የእብራይስጥና የግሪክ ቋንቋ ማንም መረዳቱ የተሰጠውና ቃሉን የሚያጠና ሊቅ ሁሉ ሊያውቀው የተገባ ነው። “የእብራይስጥ ቋንቋ በአብዛኛው የአንድ ቃል ፍቺ ሃብታም ከመሆኑ የተነሳ ከአንድ በላይ ደራርቦ ሃሳብን ሊያሳይ ይችላል። የእብራይስጥ ቋንቋ ቃላት ስእላዊ ገላጭ ያለውና የድምጽ ገላጭም አጣምሮ የያዘ ሊሆንም ይችላል፡፡
ለምሳሌ ሁሉም ፈደሎች ቁጥርም ናቸው ቃላትም ናቸው። ለምሳሌ “alef” የመጀመርያው ፊደል ነው ያው ፊደል የመጀመርያው ቁጥር አንድ ማለትም ነው። “alef” የሚለው ያው ቃል በሬ ማለት ሲሆን ስእላዊ ገላጩም ጥንካሬን፤ ብርታትን [ymbolizes, strength] የሚያመለክት ነው። ሁለተኛው “beth” ቁጥር ሁለት ነው። “beth” የሚለው ቃል እራሱ ቤት ፤ቤተ ሰዎችና ፤ቤተሰቦችን [house or household] ያካተተ ፍቺ አለው።
በእብራይስጥ ቋንቋ ህግ ማለት Torah ነው። በእብራይስጥና ቋንቋ ቶራ[ Torah] ሲፃፍ tav-vav-resh-hey ሆኖ ይፃፋል። ይህ ከተያያዛበት ለየብቻው ቃሉ ሲተረጎም Tav ማለት ምልክት ወይም መስቀል ማለት “a mark or sign” [of the cross] ሲሆን። በዋናው በመጀመርያው ጥናታዊ ያልተበረዘ በእብራይስጥ ቋንቋ “መስቀል” ተብሎ ነበር የተፃፈው። በዘመናይ በእብራይስጥና ቋንቋ ተለይቶ ይገኛን። ይህም የሆነው በባቢሎን 70 አመት ምርኮ ጊዜ የባህል ወረራ ስለደረሰ ከአረሚክ ቋንቋ ጋር ተዳቅሎ ተበረዘ።
ሁለተኛው “vav” የሚለው በግልጽ ትርጉሙ እንደ አገባቡ የተሰቀለው፤በሚስማር ፤የተጠረቀመው፤የተቸከለው “a nail or peg.” ሲሆን ሶስተኛው “resh” የሚለው በግልጽ መሪ ወይም ራስ “a head, or leader.” ማለት ነው። በመጨረሻም “hey” በቃሉ መጨረሻ ሲቀመት ትርጉሙ ከሱ ወይ ከዛ የወጣ የተገኘ ማለት ነው። “what comes from.”
በእብራይስጥና ቋንቋ ህግ ማለትም Torah ከሚለው ቃል ፍቺ እምናስተውለው በመስቀል ላይ ከተሰቀለው መሪ ወይም ራስ የተገኘ “what – comes – from – the – Leader- nailed- to- the – Cross” ማለት ነው ። በሌላ አነጋገር እየሱስ ህግን የሰጠውና በመስቀል ላይ የተሰቀለው መሪ ወይም ራስ እሱ መሆኑን በዚህ ታላቅ ሚስጥር ውስጥ የእ/ር ድንቅ ስራ ይስተዋላል። “…that they may be #ONE, even as #WE [The Lord Jesus AND His Father(His divine origin, His Spirit or his source)] ARE O-N- E”!!! HOW many Persons? Jesus & Father–TWO. HOW many GODS?–O-N-E G-O-D!!! it is uncompromised spiritual principle as a #husband and #wife ARE #ONE, and #Jesus and #His #Church, ARE also #ONE, so also “#Jesus and #His #Father,” ARE #ONE. Amen (so be it).ቢኒ።

ተጨማሪ ተመሳሳይ 4

ከውይይት የተጠቀሰ፡ ἐγὼ εἰμί ἀμὴν ሰላም ብራዘር እንደዚህ አይነት ነገር ይዘህ ስትቀርብ በአማርኛ ትርጉሞች ብቻ ባትደገፍ ጥሩ ነው በዋናው ላይ አያያዥ እና የሚል የለውም። Rev 21፡22. And I did not see an inner sanctuary [= the holy place, or places, of the Temple] within her, for the LORD [=Yahweh], Almighty (All‑Strong) God, even the little Lamb, is her inner sanctuary (lit.: dwelling place). ከሶስት ኑባሬዎች ብሎ ነገር የለም አማርኛ ስላሳመርክ አይደለም እነሆ ዘንዳ ወዘተ የ1960 አማርኛ ጥሩ ነው ሆኖም በማስተዋል አንብበው። ተባረክ። Rev 14. John, to the Seven Churches (congregations; called‑out assemblies) within Asia: Grace and Peace to you (for you; in you) folks, from the One continuously existing (or: unceasingly being; Who continuously IS), even the One Who was, and continued being, and the One Who is continuously (repeatedly; habitually) coming ‑‑ even from the Seven Spirits in front of His throne ‑‑የዮሐንስ ራእይ 21፡6 አለኝም፦ ተፈጽሞአል። #አልፋና#ዖሜጋ#መጀመሪያውና#መጨረሻው#እኔ ነኝ። ለተጠማ ከሕይወት ውኃ ምንጭ እንዲያው እኔ እሰጣለሁ። ለተጠማ ከሕይወት ውኃ ምንጭ የሚሰጠው ከሆነ #አልፋና #ዖሜጋ፥ #መጀመሪያውና #መጨረሻው #እኔ ነኝ ያለው ማነው እሱ ይህን ቃል ተናግሮ እኔ ነኝ ያለው? የዮሐንስ ወንጌል 4፡14 እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ አላት። የዮሐንስ ወንጌል 5:39 እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፤ የዮሐንስ ወንጌል 7:15 አይሁድም፦ ይህ ሰው ሳይማር መጻሕፍትን እንዴት ያውቃል? ብለው ይደነቁ ነበር።
ጌታ እንዳለው ከሙሴ ዘንድ ስለሱ ተጽፈዋል እስቲ ይህን የሚደንቅ ምጢር እንመልከት። ‘ እግዚአብሔር (ያህዌ) ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም[ደህንነቴም yashua: እያሱ በእብራይስጥ እየሱስ በግሪክ] ሆነልኝ፤ እርሱ አምላኬ ነው፤ አመሰግነዋለሁ፤ የአባቴ አምላክ (ኤሎሂም) ነው፤ እኔም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ። እግዚአብሔር (ያህዌ) ተዋጊ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር (ያህዌ) ነው። ‘ ዘፀአት 15:2-3 አስተዋላችሁትን ቢቱን እግዚአብሔር (በያህዌ) ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም[ደህንነቴም yashua: እያሱ በእብራይስጥ እየሱሴም በግሪክ] ሆነልኝ። እንዲገባን በግልጽ አማርኛ እንየው “ያህዌ ደህንነቴ ወይም እየሱሴ ሆነልኝ[“ያህዌ እየሱሴ ሆነልኝ”]”
ይህ የእየሱስ ስጋ የመልበሱ ትንቢት ነው። የአሮጌው ኪዳን እ/ር በአዲስ ኪዳን ሰው ሆኖ ስለመገለጡ ነው። ይህም በኢሳያስ 12:2-3 ‘እነሆ፣ እግዚአብሔር ድነቴ[እየሱሴ] ነው፤ እታመናለሁ፣ ደግሞም አልፈራም፤ ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም [እየሱሴም]ሆኖአል።” ከድነቴ[እየሱሴ] ምንጮች ውሃ በደስታ ትቀዳላችሁ። ‘ ኢሳይያስ 12:2-3 እንደምናስተውለው ኢሳያስ በሙሴ መጽሐፍ በዘፅአት የተፃፈውን ደግሞ ሲጠቅስ እናስተውላለን። በዚህ አያበቃም እየሱስ ይህን በመጥቀስ አጽንቶታል።
ጌታ እየሱስ ይህን ትንቢት ግልጽ አድርጎ ፈቶታል። ‘የበዓሉ መጨረሻ በሆነው በታላቁ ቀን፣ ኢየሱስ ቆሞ ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ አለ፤ “ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ፤ በእኔ የሚያምን፣ መጽሐፍ እንዳለ የሕይወት ውሃ ምንጭ ከውስጡ ይፈልቃል።” ‘ ዮሐንስ 7:37-38 በሌላ የእንግሊዝኛ ትርጉም ማንም ከተጠማ ከደህንነት ምንጭ ዉሃ ይጣጣ ይላል።
ይህ ግልጽ ቃል የሚያስረዳን በአሮጌው ኪዳን እየሱስ [በእብራይስጥ እያሱ] ስለ ድነት ወይም ደህንነት ተደብቆ የነበረው ሚስጥር እንደሆነ ነው። ጌታ እየሱስ ስጋ የለበሰው ያህዌ ነው። “ያህዌ እየሱሴ ሆነልኝ” በቀድሞው ኤልሻዳይ ብሎ እራሱን የጠራው በራእይ[በእየሱስ ክርስቶስ መገለጥ መጽሐፍ] እራሱን በድጋሚ ሲያረጋግጥ ሁሉን ቻይ ብለዋል። ጌታ እየሱስ ክርስቶስ በአዲስ ኪዳን አስር ቦታ ላይ (ኤልሻዳይ ‘el ale Shadday shad-dah’-ee) ተብሎ ተጠርተዋል። ልናየው ያልቻልነው ተርጋሚዎቹ ኤልሻዳይ እንደማለት ፈንታ በአማርኛችን ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ በእንግሊዝኛ Almighty ብለው ስለተረጎሙት ነው ። የፃድቅ ሃብቱ ትጋቱ ነውና ማጥናት ትችላላችሁ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:18 , የዮሐንስ ራእይ 1:8, 4:8, 11:17, 15:3, 16:7, 16:14, 19:6, 19:15, 21:22 ወንድም ቢኒ።

ተጨማሪ 5

ከውይይት የተጠቀሰ፡ Fitsum Abraham ክፍል 1፡ ስሙም ነው የሚለው ስም በመጽሓፍ ማንነትን ተፈጥሮን ባህርይን ወዘተ የሚገልጽ ነው። ስሙም ኃያል አምላክ ነው! የዘላለም አባት ነው! አብ ነው Almighty ሁሉን ቻይ ኤልሻዳይ ላልከው ጌታ እየሱስ ክርስቶስ በአዲስ ኪዳን አስር ቦታ ላይ (ኤልሻዳይ ‘el ale Shadday shad-dah’-ee) ተብሎ ተጠርተዋል። ልናየው ያልቻልነው ተርጋሚዎቹ ኤልሻዳይ እንደማለት ፈንታ በአማርኛችን ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ በእንግሊዝኛ Almighty ብለው ስለተረጎሙት ነው ። የፃድቅ ሃብቱ ትጋቱ ነውና ማጥናት ትችላላችሁ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:18 , የዮሐንስ ራእይ 1:8, 4:8, 11:17, 15:3, 16:7, 16:14, 19:6, 19:15, 21:22
አንዱ እ/ር ኤልሻዳይ፤ያህዌ ብሎ እራሱን ገለጠ ሁለት እግዚአብሔሮች አይደሉም ቡሃላ ነገሩን ስለምናያይዘው ማስተዋሉመልካም ነው። የህግ ሰጪው ማንነት በዘፀ፤20:2 አስርሩን ትእዛዛት ሲሰጥ በህግ መቅድሙ ላይ ሲናገር ‘“ከግብፅ ከባርነት ምድር ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ (ያህዌ self-Existent በራሱ የሚኖር ። በራሱ ህልውና ያለው) እኔ ነኝ።” “ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይኑሩህ። ‘ ዘፀአት 20:2-3”
ለአብርሃም ሲገለጥ እንደ ኤልሻዳይ አወቀው ‘አብራም ዕድሜው 99 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ተገልጦለት እንዲህ አለው፤ “እኔ ኤልሻዳይ” ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ፤ ነቀፋም አይኑርብህ፤ ‘ ዘፍጥረት 17:1 ከዘፍጥረት እስከ ዘዳግም የፃፈው ሙሴ ነው። ይህም ማለት እነ አብርሃም ያልበራለቻው ያህዌ የሚለው የእ/ር ስም ከገባው ቡሃላ የፃፈው ስለሆነ ያህዌ እያለ በእብራይስጥ ተጠቅሞበታል ኤልሻዳይ እና ያህዌ አንድ አምላክ እንደሆነ እናያለን ። “እኔ እግዚአብሔር (Hebrew፣ያህዌ Yhovah yeh-ho-vaw’) ነኝ። ሁሉን የሚችል አምላክ (ኤልሻዳይ ‘el ale Shadday shad-dah’-ee) ሆኜ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ ተገለጥሁላቸው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር (Hebrew፣ያህዌ Yhovah yeh-ho-vaw’) በተባለው ስሜ ራሴን አልገለጥሁላቸውም። ‘ ዘፀአት 6:2-3
ከዚህ የምንረዳው እ/ር እራሱን በተለያየ ስምና መልክ[ስም በመጽሓፍ ቅዱስ የሚያሳየው የአንድን ነገር ባህርዩ ን ወይም ተፈጥሮዉን ነው] እራሱን እንዴት እንደሚገልጥ እናስተውላለን። በአዲስ ኪዳን ቃል የነበረው እ/ር ስጋ ሆኖ በክርስቶስ እየሱስ ተገለጠ የእብራይስጥ ስሙ “እያሱ [yashua or Joshua]” ነው። ትርጉሙም “ደህንነት፤አዳኝ [እ/ር ያድናል ]” ማለት ነው። ይከውም በግሪክ ቋንቋ “እየሱስ” ይባላል ትርጉሙም “አዳኝ” ማለት ነው።…..ክፍል 2 ቢኒ።

ክፍል 2፡ ጌታ በሉቃስ ወንጌል 24:27 ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጐመላቸው። እንደ ምናስተውለው ጌታ ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ላይ የተፃፈው ስለሱ መሆኑንና ለመረዳት ግን ጌታ በመንፈሱ ካልተረጎመልና መጻሕፍትን እናስተውል ዘንድ አእምራችን ካልከፈተልን በትዮሎጂ እውቀት ከማበጥ ውጪ እውነትን ለመረዳት ይከብደናል። የሉቃስ ወንጌል 24/45 በዚያን ጊዜም መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው፤
የዮሐንስ ወንጌል 5:39 እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፤ የዮሐንስ ወንጌል 7:15 አይሁድም፦ ይህ ሰው ሳይማር መጻሕፍትን እንዴት ያውቃል? ብለው ይደነቁ ነበር።
ጌታ እንዳለው ከሙሴ ዘንድ ስለሱ ተጽፈዋል እስቲ ይህን የሚደንቅ ምጢር እንመልከት። ‘ እግዚአብሔር (ያህዌ) ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም[ደህንነቴም yashua: እያሱ በእብራይስጥ እየሱስ በግሪክ] ሆነልኝ፤ እርሱ አምላኬ ነው፤ አመሰግነዋለሁ፤ የአባቴ አምላክ (ኤሎሂም) ነው፤ እኔም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ። እግዚአብሔር (ያህዌ) ተዋጊ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር (ያህዌ) ነው። ‘ ዘፀአት 15:2-3 አስተዋላችሁትን ቢቱን እግዚአብሔር (በያህዌ) ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም[ደህንነቴም yashua: እያሱ በእብራይስጥ እየሱሴም በግሪክ] ሆነልኝ። እንዲገባን በግልጽ አማርኛ እንየው “ያህዌ ደህንነቴ ወይም እየሱሴ ሆነልኝ[“ያህዌ እየሱሴ ሆነልኝ”]”
ይህ የእየሱስ ስጋ የመልበሱ ትንቢት ነው። የአሮጌው ኪዳን እ/ር በአዲስ ኪዳን ሰው ሆኖ ስለመገለጡ ነው። ይህም በኢሳያስ 12:2-3 ‘እነሆ፣ እግዚአብሔር ድነቴ[እየሱሴ] ነው፤ እታመናለሁ፣ ደግሞም አልፈራም፤ ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም [እየሱሴም]ሆኖአል።” ከድነቴ[እየሱሴ] ምንጮች ውሃ በደስታ ትቀዳላችሁ። ‘ ኢሳይያስ 12:2-3 እንደምናስተውለው ኢሳያስ በሙሴ መጽሐፍ በዘፅአት የተፃፈውን ደግሞ ሲጠቅስ እናስተውላለን። በዚህ አያበቃም እየሱስ ይህን በመጥቀስ አጽንቶታል።
ጌታ እየሱስ ይህን ትንቢት ግልጽ አድርጎ ፈቶታል። ‘የበዓሉ መጨረሻ በሆነው በታላቁ ቀን፣ ኢየሱስ ቆሞ ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ አለ፤ “ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ፤ በእኔ የሚያምን፣ መጽሐፍ እንዳለ የሕይወት ውሃ ምንጭ ከውስጡ ይፈልቃል።” ‘ ዮሐንስ 7:37-38 በሌላ የእንግሊዝኛ ትርጉም ማንም ከተጠማ ከደህንነት ምንጭ ዉሃ ይጣጣ ይላል።
ይህ ግልጽ ቃል የሚያስረዳን በአሮጌው ኪዳን እየሱስ [በእብራይስጥ እያሱ] ስለ ድነት ወይም ደህንነት ተደብቆ የነበረው ሚስጥር እንደሆነ ነው። ጌታ እየሱስ ስጋ የለበሰው ያህዌ ነው። “ያህዌ እየሱሴ ሆነልኝ” በቀድሞው ኤልሻዳይ ብሎ እራሱን የጠራው በራእይ[በእየሱስ ክርስቶስ መገለጥ መጽሐፍ] እራሱን በድጋሚ ሲያረጋግጥ ሁሉን ቻይ ብለዋል። ጌታ እየሱስ ክርስቶስ በአዲስ ኪዳን አስር ቦታ ላይ (ኤልሻዳይ ‘el ale Shadday shad-dah’-ee) ተብሎ ተጠርተዋል። ልናየው ያልቻልነው ተርጋሚዎቹ ኤልሻዳይ እንደማለት ፈንታ በአማርኛችን ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ በእንግሊዝኛ Almighty ብለው ስለተረጎሙት ነው ። የፃድቅ ሃብቱ ትጋቱ ነውና ማጥናት ትችላላችሁ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:18 , የዮሐንስ ራእይ 1:8, 4:8, 11:17, 15:3, 16:7, 16:14, 19:6, 19:15, 21:22 …..3 ወንድም ቢኒ።

ክፍል 3፡ በአሮጌው ኪዳን ለአብ የተነገሩት በአዲስ ኪዳን ለጌታ እየሱስ ክርስቶስ ስለመነገራቸው የሚያሳዩ ጥቂቶችን ለመጥቀስ ያህል
የዮሐንስ ራእይ 1/8 ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ(በእብራይስጥ ኤልሻዳይ ‘el ale Shadday shad-dah’-ee በግሪክ pantokrator pan-tok-rat’-ore፤ the all-ruling, i.e. God (as absolute and universal sovereign):–Almighty, Omnipotent.)፦ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።
Rev 1/8 I am Alpha and Omega, the beginning and the ending, saith the Lord, which is, and which was, and which is to come, the Almighty. (በእብራይስጥ ኤልሻዳይ ‘el ale Shadday shad-dah’-ee በግሪክ pantokrator pan-tok-rat’-ore፤ the all-ruling, i.e. God (as absolute and universal sovereign):–Almighty, Omnipotent.)
የዮሐንስ ራእይ 4:8 አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሉአቸው፥ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዓይኖች ሞልተውባቸዋል፤ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም።
Rev 4:8Open in Logos Bible Software (if available) And the four beasts had each of them six wings about him; and they were full of eyes within: and they rest not day and night, saying, Holy, holy, holy, Lord God Almighty, which was, and is, and is to come.ወንድም ቢኒ።

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal