ወንጌል የሚሰበከው መልካም የምስራች ስለ ሆነ ነው። እንደ ዮናስ ነነዌን ለምን አልገለበጥካትም አንተ ድሮውንም ብዮ ነበር መሀሪ መሆንህን እውቅ ነበር ብሎ እንደተቆጣ እና እንደኮበለለው ዮናስ ልንሆን አይገባም።


Discussion Quotes፡ Binyam TA Samson Ayele ወንድማችን ሳሚ። ወንጌል የሚሰበከው መልካም የምስራች ስለ ሆነ ነው። እንደ ዮናስ ነነዌን ለምን አልገለበጥካትም አንተ ድሮውንም ብዮ ነበር መሀሪ መሆንህን እውቅ ነበር ብሎ እንደተቆጣ እና እንደኮበለለው ዮናስ ልንሆን አይገባም። ዮናስ እውነተኛ ነብይ ነበረ። ቃል ስለመጣለት ጥፋትን ያዘለ ፍርድ ለህዝቡ ሁሉ ተነበየ በዛው አንደበቱ ምህረትን ትሰብካታለህ ሲባል እምቢ ቡራ ከረዮ አለ። ከውቅያኖስ መካከል ከባህር አውሬ አሳ ነብሪ ሆድ ወስዶ ዘጋው። ከሲኦል ሆኜ እፀልያለሁ እስኪያስብለው ድረስ ከእግዚአብሔር ሀሳብ ጋር ለመታረቅ ጭንቅ ሆነበት ነበርና። ወደርሱ የመጣችው ፍርድ ግን ፅድቅን ተማረባት። እግዚአብሔር አጠፉለሁ ሲል እምራለሁ ፅድቅን አስተምራለሁ ማለቱን አስተውለዋልና ነፍሱ እኔን ሀሰተኛ ነብይ ሊያስብል ምህረትን አውጅ ይለኛልን? ብሎ ተቆጣ። እኛም በዮናስ ዱካ እንዳንገኝ እግዚአብሔርን እንፍራ።

እግዚአብሔር እውነት ነው ፍቅር ነው። ፍቅርን ብታሰቃዮት ግን በእውነት አምላካችን የሚባል እሳት ነው። ደግሜም ሰልሼም እላለሁ ወንጌል የሚሰበከው ለነፃነት መልካም የምስራች ስለ ሆነ ነው እንጂ የሆረር ፊልም ይመስል ለፍርሀት ባርነት አይደለም። አብ ለሳባቸው ሁሉ መዳናቸውን ለሚሰሙት መልካም ነውና። ምሳሌ25:25 የቀዘቀዘ ውኃ ለተጠማች ነፍስ ደስ እንደሚያሰኝ፥ ከሩቅ አገር የመጣ #መልካም #ምስራች እንዲሁ ነው።
ወንጌል ከመሰረቱ መልካም ዜና ነው። ምንም ኩፉ ዜና የለበትም!ወንጌል ‘gospel’ የሚለው ቃል ኢቫንጀል ከግሪክ (‘evangel’ from the Greek) ቃል የተተሮገመ ሲሆን፡ ይህም ከሁለት የቃላት ውህድ የተገኘ ነው። መልካም እና መልእክት(‘eu’ – good, and ‘angelion’ – message). ስለዚህ ወንጌሉ በቀላል ቋንቋ መልካም መልእክት ማለት ነው። እንግዲህ ነገሩ እንዲህ ሆኖ ሳለ የባቢሎን ነገስታቶችዋ ክፉ መልእክቱን ከየት አመጡት? የታወቀ ነው ሰው የአከባቢው ውጤት ነውና ግልጽ ነው። ባቢሎን ማለት በእብራይስጥ ግራ መጋባት፤መደናገር፤ትርምስምስ confusion ነውና። Strong- 894 Babel baw-bel’ from 1101; confusion; Babel (i.e. Babylon), including Babylonia and the Babylonian empire:–Babel, Babylon. ሁላችንም ከምርኮ ያስለቀቀን እ/ር ምስጉን ነው።
መልእክተኛውም ሁሉ ትውልዶችን ወይን ጠጅ ያጠጣችው ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፥ ወደቀች እያለ ነው። የዮሐንስ ራእይ 14/8 , የዮሐንስ ራእይ 18/2 ብዙ ትውልዶችን በተቀላቀለ ትምህርትዋ እንዳሰከረች እግዚአብሔር በተራዋ በመልክተኞቹ የብርቱ ቍጣውን ወይን ጠጅ የሞላበትን ጽዋ እንዲሰጣት አዘዋልና። የዮሐንስ ራእይ 16/19. እ/ር ሲሰራ ሁሉ ለመልካም ነውና ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ ጀምረዋል። “1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4/17 ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና…”
ለመሆኑ የምስራቹ ምንድ ነው? ወንጌሉስ ምንድ ነው? በኤፌሶን ላሉት ቅዱሳን የምስራቹን ከሰሙ ቡሃላ ሳይሆን በክርስቶስ ኢየሱስም ቁዱሳን ሳይባሉ ገና ሃጥአን፡ ሳሉ የተነገራቸው የሰሙት የምስራቹ ወንጌል ወይም መልካም ዜናው የተባለው ይሄ ነው “የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የ-መ-ዳ-ና-ች-ሁ-ን ወ-ን-ጌ-ል” ነው። አስተውሉ በአላፊ ጊዜ (past tense) የተቀመጠ ነው። ገና ትድናላችሁ እያላቸው ሳይሆን የተፈፀመውን መዳናቸውን ነው የነገራቸው። የተነገረው በአይሁዳዊ ሆነ እንጂ ይህ የምስራች የተነገረው በኛ አገር እናቶች ቢሆን ኖሮ ይህንን የምስራች የሚነግሩት በዚህ መልኩ ነበር ብየ አስባለሁ። የባህል ልብሳቸውን እንደለበሱ ሁለት እጆቻቸውን ወደ ሰማይ ዘርግተው ወደ ሃጥአኑ እየሮጡ እልልልልልልልል…. እ/ር በክርስቶስ አዳናቹሁ እኮ! እሰይ! እሰይ! እሰይ! እያሉ በደስታ ተቃቅፈፍ ይሳሳሙ ነበር ። “ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1-13 እናንተም ደግሞ “የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፤” “(Eph 1:13 [KJV]) In whom ye also trusted, after that ye heard the word of truth, the gospel of your salvation: in whom also after that ye believed, ye were sealed with that holy Spirit of promise,” ድነት ወይም ደህንነት ማለት ከሃጥያትና ከሞት ሃይል ነፃ መውጣት ማለት ነው። ይህም ማለት ለሚያምንቱ የሆነ የእ/ር የነፃ ስጦታ ነው። “የማቴዎስ ወንጌል 1-21 ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።” ሕዝቡ መዳን ያስፈለጋቸው ከኃጢአታቸው ነው እንጂ ከሲኦል አይደለም።
“ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2/8 ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤9 ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።” ይሄ ደህንነት ቀድሞ ጊዜ ወደ ሰው ዘሮች ሁሉ የተላለፈው በአዳም ላይ የተነገረው የመርገም ቃልን በእዮሱስ የመስቀሉ ስራ ወደ በረከት ገልብጦታል። ሁሉ ማንፈሳዊ፤ ሃሳባዊ፤ አካላዊ፤ ለሰው ዘሮች ሁሉ ተቃዋሚ ኅይላት የሆኑት ኅይል ኧልባ ተደርገዋል። ይህም ለሃጥያት ተገዥነትን አላቀዋል። ሮሜ 6/6,14 ከዲያብሎስ ስራ ነፃነትን 1ኛ ዮሃ3/5-11 ከሞት ፍርሃትና ባርነት ነፃነትን። ዕብ 2/14-15 አውጥቶ በምትካቸው ፅድቅን፤ ሰላም፤ደስታ የሂወታቸው መሃከለኛ ሆኖ እንዲ ለማመዱት የሚያደርግ ሆነዋል። አሜን! ወንድም ቢኒ።

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal