
ከስላሴ ጥያቄና መልስ የተወስደ። ክፍል አንድ። ከወንድም ቢኒ ። ሰላም ወገኖች። በዚህ መልኩ ለመማማር እንዲጠቅም የእናንተን ጨምሮ የወንድማችንም የወገኖችም ሃሳብ ሊያንሸራሽር ይችላል በሚል መለጠፌ ትክክል ነበርኩ። መቼም የእ/ርን ቃል እጅ ያሻቹሁን ያእል እጁን ብትጠመዝዙት ስላሴ የሚለው ቃል በእ/ር ቃል ውስጥ አንድም የለም ይህ በራሱ በቂ ነው። ቀጥተኛ ቃሉ ቢኖር ኖሮ የነገር ፍጻሜ በሆነ ነበር ነገር ግን ቃሉ በፍጥረቱ የበረሀ፤ የአለም የነበረ ወደ ቤተ ክርስቲያን ተደቅሎ የገባ እስኮሆነ ድረስ በእ/ር ቃል የሚያረጋግጥ አንድም የ3ቱ ስላሴዎች ምስል አምላኪ ቃሉን ማረጋገጥ እንዳይችል የአደባባይ ምስጢር ነው። ይህ አመለካከት እንደ ናዝሬት ፈረሶች እይታ ብቻ ሳይሆን ልክ የጋቭሮቮች ፈረስ አረንጋዴ መነጽር ካጠለቅላቸው የከረመውን የበሰበሰውን ድርቆሽ ሳር አረንጋዴ ነው ብለው ግጥም አርገው እያመነዠኩ ያጣጥሙታል። የስላሴ መንጽር ያጠለቀ ሰውም እይታው 3 ከሆነ ዘንዳ የካሉን ፊደል እንጂ የቃሉን መንፈስ ማየት አይችልም ማትዮስ 28፤19 ሆነ ሌላ ቦታ ሶስት ነገሮች ከተጠቀሱ ለአሪፉ ባለመንጽር የሚታየው በአረንጋዴ መብራት ወስጥ 3ቱ ስላሴ ነው።
እኔ እንደማስተውለው የእ/ር መገለጦች አንድ ቦታ መጠቀሳቸው ወይም መፃፋቸው በቀር ሶስት እግዚአብሔሮችን ወይም ስላሴን አያረጋግጡም። እኔ እንዳውም ሐውርያት በስላሴዎች እንዲያጠምቁ አዝዋቸው ከነበረ ባስላሴዎች ስም ባጠመቁ ነበር ። በእየሱስ ስም ብቻ ማጥመቃቸው ለራሱ ግን ከበቂ በላይ ማስረጃ ነው ለኔ። ለባለ አእምሮ ሰው ግን በመገለጥ ሳይሆን በሎጂክ የሚንቀሳቀስ እስከሆነ ድረስ ለማጥናት ፍላጎቱ ላለው ሁሉ እውነትን ወደማወቅ እንዲደርስ እ/ር ቢፈቅድ ከታሪክ መዛግብት ጭምር ማስረጃዎችን ለማቅረብ እሞክራለሁ። ብዙ የቀድሞ እውነቶችን ለማጥናት ስሞክር ይህ ቃል በተጽኖ ስር ሆንው ሊቃውንቱ እስክ ጨመሩት ቃል ድረስ ይህ ቃል እንዳልነበር ያሳያል።
የወጣው የመጀመርያውን የቤተ ክርስቲያን ታሪክ የፃፈው ” ሂስቶሪያ ኤክሊሲሲሳካ” “Historia Ecclesiastica,” Church History (Eusebius) ጳጳስ ሲዘርያ ዩሲቢየስ የተወለደው 260 – 339 ዓመትም ሞተ። መጽሐፉ በ 325 ታትሞ የወጣው ነው። ” ሂስቶሪያ ኤክሊሲሲሳካ” የእሱ መጽሐፍ የቤተክርስቲያን ታሪክ ተብሎ የሚታወቀው የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ በይፋ ከመፅደቁ ከሰባ ሁለት ዓመታት በፊት ነበር። ይህ የቀድሞ ቤተክርስቲያን ታሪክ በጥልቀት ለመገንዘብ ለዘመናዩም የክርስትና አካሄድ ቅርጽ ሰጥቶአል። ማትዮስ28፡19 ሲጠቅስ 17 ግዜ ህዝብን ሁሉ በስሜ አጥምቁ ብሎ ከእ/ር ቃል እየጠቀሰ ጽፎታል “Go disciple ye all the nations in my name” (17 times) ይህ ማለት ምን ማለት እንደሆነ በማስተዋሉ ፈጣን ለሆነ የቃል ግማሽ ይበቃዋልን ለመመርመር ሊያነሳሳው ይገባል። ይህን መጽሐፍ ሊንክ ከስር አስቀምጣዋለሁ ዳውንሎድ በማድረግ አውርዱትና አንቡቡት እኔ ያገንኘሁት ይሂብሩና የግሪክ ስኮላር ከሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት መስራች የትምርት ቤቱ የመጀመርያ ተማሪዎች ስለነነበር የሰጡን ነው ምናልባት ኦንላይን ይገኝ ይሁን አላውቅም ጥራዝ መጽሐፉ ግን በአሳታሚዎች እንደሚሸጥ አውቃለሁ።
https://www.dropbox.com/s/tusjj2nk76ma6vh/Church_History_Complete.pdf?dl=1
ይቀጥላል…….2 ከወንድም ቢኒ።
ክፍል 2። ስም በእ/ር ቃል ወስጥ የሚያመለክተው ባህርይን ተፈጥሮን ስልጣንን ማንነትን ወክሎ እንደሆነ ግልጽ ነው። በተፈጥራዊው እይታ በከፊል ተመሳሳይነት አለው። ስም[ስ፤ስም] ለማንኛውም ሰው፤ ነገር፤ ቦታ፤ ወዘተ …. የሚሰጥ መጠርያ ነው። [ሰዋ፤ሰዋሰው] ለግሱ እንደ ባለቤት ወይም ተሳቢ ሆኖ ሊያገለግል የሚችል የሰው፤ የነገር፤ የቦታ፤ መጠርያ ቃል መሆኑ ና ተግባሩም የተሰያሚው አካሄድ ይወስነዋል።
ትንቢተ ሚልክያስ 3/6 እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም፤ ….። Mal 3/6 For I am the Lord, I change not; … . እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም እ/ር ለአንድ ሚሊ ሰከንድ እንካ ማንነቱ ከተለወጠ እ/ር በእውነት እግዚአብሔር ነቱ ከአንድ ማንነቱ ተለውጦ 3 ከሆነ ተለወጠ ጠፋ ማለት ነው እ/ር ግን አይለወጥም።
ኦሪት ዘጸአት 33/19እግዚአብሔርም፦ እኔ መልካምነቴን ሁሉ በፊትህ አሳልፋለሁ፤ የእግዚአብሔርንም{ያህዌ G፤ Yhovah yeh-ho-vaw’ self-Existent } ስም[G፤ shem shame፣ authority, character] በፊትህ አውጃለሁ፤ ይቅርም የምለውን ይቅር እላለሁ፥ የምምረውንም እምራለሁ አለ።
20ደግሞም፦ ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልህም አለ።
21እግዚአብሔርም አለ፦ እነሆ ስፍራ በእኔ ዘንድ አለ፥ በዓለቱም ላይ ትቆማለህ፤
22ክብሬም ባለፈ ጊዜ በሰንጣቃው ዓለት አኖርሃለሁ፥ እስካልፍ ድረስ እጄን በላይህ እጋርዳለሁ፤
23እጄንም ፈቀቅ አደርጋለሁ፥ ጀርባዬንም ታያለህ፤ ፊቴ ግን አይታይም።
34/5 እግዚአብሔርም በደመናው ውስጥ ወረደ፥ በዚያም ከእርሱ ጋር ቆመ፥ የእግዚአብሔርንም ስም አወጀ።6 እግዚአብሔርም በፊቱ አልፎ፦ እግዚአብሔር፥ እግዚአብሔር መሐሪ፥ ሞገስ ያለው፥ ታጋሽም፥ ባለ ብዙ ቸርነትና እውነት፥7እስከ ሺህ ትውልድም ቸርነትን የሚጠብቅ፥ አበሳንና መተላለፍን ኃጢአትንም ይቅር የሚል፥ በደለኛውንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችንም ኃጢአት በልጆች እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድም በልጅ ልጆች የሚያመጣ አምላክ ነው ሲል አወጀ።
ጌታ በአሮጌው ኪዳን እኔ ፊተኛ ነኝ እኔም ኋለኛ ነኝ፥ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም እኔ ማንንም አላውቅም አለ። በአዲስ ኪዳን ደገመ አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።
ትንቢተ ኢሳይያስ 44/6የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር፥ የሚቤዥም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ፊተኛ ነኝ እኔም ኋለኛ ነኝ፥ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም። 7 እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ይነሣና ይጥራ ይናገርም፤ ከጥንት የፈጠርሁትን ሕዝብ ያዘጋጅልኝ፥ የሚመጣውም ነገር ሳይደርስ ይንገሩኝ። 8አትፍሩ አትደንግጡም፤ ከጥንቱ ጀምሬ አልነገርኋችሁምን? ወይስ አላሳየኋችሁምን? እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ። ከእኔ ሌላ አምላክ አለን? አምባ የለም ማንንም አላውቅም።
የዮሐንስ ራእይ 22/13 አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።
እርሱ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው ብቻ ሳይሆን አልፋና[Hebrew origin; the first letter of the alphabet ። a al’-fah] ዖሜጋ፥[omega o’-meg-ah/ the last letter of the Greek alphabet, i.e. the finality:–Omega.] ይቀጥላል…….3 ከወንድም ቢኒ።
ክፍል 3 ። መጽሃፍት ትመረምራላችሁ መጽሓፍት ሁሉ ግን ስለኔ ይናገራሉ ህይወት እንዲሆንላችሁ ግን ወደኔ ልትመጡ አትወዱም። ምን ምን? መጽሓፍት ሁሉ ግን ስለኔ ይናገራሉ ? ሁሉ ስለኔ የሁሉ ትርጉም ሁሉ ነው። “እኔ ነኝ” “I am” መጨረሻ የለውም የወይኑ ግንዱ እኔ ነኝ፤ በሩእኔ ነኝ፤ መልካም እረኛ እኔ ነኝ፤ የአለም ብርሃን እኔ ነኝ ፤ አልፋ እኔ ነኝ ፤ ኦሜጋ እኔ ነኝ ፤ የመጀመርያው እኔ ነኝ፤ የመጨረሻው እኔ ነኝ፤ የምዋጀው እኔ ነኝ ፤ ብርታትህ እኔ ነኝ ፤ የሚኖረው እኔ ነኝ ፤ ሞቶ የነበረው እኔ ነኝ ፤ ትንሳኤው እኔ ነኝ ፤ የዘጋሁትን ማንም የማይከፍተው የከፈትኩትን ማንም የማይዘጋው እኔ ነኝ ፤ የዳዊት ስርና እኔ ነኝ ፤ የንጋት ኮከብ እኔ ነኝ፤ ስሙም ድንቅ መካር እኔ ነኝ ፥ ኃያል አምላክ እኔ ነኝ ፥ የዘላለም አባት እኔ ነኝ ፥ የሰላም አለቃ እኔ ነኝ “ያለውና የሚኖረው እኔ ነኝ:
እኔ ነኝ፤ እኔ ነኝ፤ እኔ ነኝ፤ እኔ ነኝ… እኔ እኔ ነኝ በላቸው” [I AM that I AM, tell the pepople that I AM hath sent you] እነሆ ለስነቱ መጨረሻ የለውም ። “ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2/9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤የዮሐንስ ራእይ 1/8 ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፦ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።” አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ ያለኝ እኔ እኔ፤ የታመነውና እውነተኛው ምስክር እኔ ነኝ፥።የዮሐንስ ራእይ 4/10-11 ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ፦ ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም[ለደስታህ ተፈጥረውማልና for thy pleasure they are and were created.] ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ። ከወንድም ቢኒ።
ማቴዎስ ወንጌል 28/19-20፡ የሚገርመው ጌታ ሲያዛቸው በማቴዎስ ወንጌል 28/19-20 ትክክለኛው በእ/ር ቃል ውስጥ በማስረጃ እንየው። “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በስሜ እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።” ነበር ያላቸው ቡሃላ ሲተረጉሙን የስላሴን ትምህርት እጅ ጠምዝዘው ለማሰራጨት በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም ተብሎ እንዲጨመርበት ተገደደ። ሆናም ይህን እውነት የሚፈታላችሁ የእ/ር ቃል እራሱ ነው። ሃዋርያት የታዘዙትን ብቻ እንዳደረጉ ግልጽ ነው። “ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው” በስሜ አንጂ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም ብሎ አዝዋቸው ቢሆን ከቃሉ ፈቀቅ አይሉም ነበር። አስተውሉ እነሱ ለአንዴም እንካን በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም አላጠመቁም አልታዘዙምና ባዘዛቸው በእየሱስ ስም ብቻ ግን አጠመቁ።
የሐዋርያት ሥራ 2/38 ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።
የሐዋርያት ሥራ 8/16 በጌታ በኢየሱስ ስም ብቻ ተጠምቀው ነበር እንጂ ከእነርሱ በአንዱ ላይ ስንኳ ገና አልወረደም ነበርና።
የሐዋርያት ሥራ 10/48 በኢየሱስ ክርስቶስ ስምም ይጠመቁ ዘንድ አዘዛቸው። ከዚህ በኋላ ጥቂት ቀን እንዲቀመጥ ለመኑት።
የሐዋርያት ሥራ 19/5 ይህንም በሰሙ ጊዜ በጌታ በኢየሱስ ስም ተጠመቁ፤
የሐዋርያት ሥራ 19/4 ጳውሎስም፦ ዮሐንስስ ከእርሱ በኋላ በሚመጣው በኢየሱስ ክርስቶስ ያምኑ ዘንድ ለሕዝብ እየተናገረ በንስሐ ጥምቀት አጠመቀ አላቸው። ወንድም ቢኒ።
ተጨማሪ https://www.facebook.com/permalink.php?story_fbid=1723674467718504&id=100002279031400
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1722736544478963&id=100002279031400
http://www.godglorified.com/matthew_2819.htm
Analysis of Matthew 28:19 by Randall Duane Hughes
http://www.godglorified.com/various_quotes.htm
Various Quotes from Books, Commentaries, and Dictionaries relating to Matthew 28:19
http://www.godglorified.com/eusebius.htm
The Writings of Eusebius
The Eusebian Form of the Text of Matthew 28:19
http://www.godglorified.com/Conybeare_1901.htm
A Collection of Evidence
For and Against the Traditional Wording
of the Baptismal Phrase in Matthew 28:19
http://www.godglorified.com/collection_of_evidence.htm