
ለተወደድ አንድ ውንድማችን ከተሰጠ ምላሽ የተወሰደ። ከወንድም ቢኒ። Yep, you are off the base brother. ባነሳከው ሀሳብ ላይ ብዙ ማስተካከያ ልነግርህ እችላለሁ የሚጠቅምህ ግን እይታህ መስተካከሉ ነው። ለተፈጥራዊ ሰው ሁሉ ነገር ተፈጥራዊ ነው። በአንፃሩ ለመንፈሳዊ ሰው ሁሉ ነገር መንፈሳዊ ነው። እየሱስ መንፈሳዊ እይታ ነበረው።
“እ/ር መንፈስ ነው። ዮሃ 4/24” መንፈሳዊውን ነገር ለቁሳዊው አለም ለማስረዳት በአካላዊ ቋንቋ መስሎ ያስረዳናል። የብዙ አማኞች ችግር ይሄ ነው። ለዚህም ነው በመንፈስ መገለጥ እንድንረዳቸው በተምሳሌነት የተጠቀመባቸው ምልክቶች፣ SYMBOLS ቀጥታ ከመተርጎም የመጡ ብዙ ችግሮች የተከሰቱት። መጽሐፍ ቅዱስ መንፈሳዊ መጽሐፍ ነው።
“ቶሎ መሆን የሚገባውን ነገር ለአገልጋዮቹ እንዲያሳይ፣ እግዚአብሔር ለእርሱ የሰጠው የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ይህ ነው፤ ኢየሱስም መልአኩን ልኮ ለአገልጋዩ ለዮሐንስ በምልክት ገለጠለት፤ ራእይ 1:1” JOV (Jusus opinonative versions )
[JMT]AN UNVEILING OF JESUS CHRIST (REVELATION)CHAPTER 1:1. An unveiling of Jesus Christ which God gave by Him (in Him; for Him; to Him) to point out to His bond‑servants (love‑slaves) that which is necessary to come to be (to be birthed) in swiftness. And sending as an apostle, through means of the agent (messenger), He indicated by signs (symbols) to (in; for) His bond‑servant John
ስለዚህም የዚህ መጽሓፍ መሰረታዊ እይታችን ትክክል ካልሆነ የመረዳት ግንባታውም ምን እንደሚሆን የታወቀ ነውና መሰረታዊ እይታችን ላይ ሚዛኑን የጠበቀ አቅም እንዲኖረን መሰረት ሊሆን የሚገባውን እውነት[ኢየሱስ ክርስቶስ እውነት ነው] ከቃሉ እውነት በቅድሚያ እናስተውል። ከተመሠረተው መንፈሳዊ መሰረት በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። መንፈሳዊ ነገር እንደ ቱባ ክር ነው እውነተኛውን ጫፍ ከያዛቹሁት ቀሪው ዝም ብሎ ይተረተርላችሃልና።
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ መንፈስ ክብሩ ተመልሶ ከሰማያት ሁሉ በላይ ከመውጣቱና ሁ-ሉ-ን ከ-ሞ-ም-ላ-ቱ ከመክበሩ በፊት [ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4/10] ማለትም በስጋ አገልግሎት ወራቱ ለሕዝቡ ይህን ሁሉ በምሳሌ ተናገረ፤ በነቢዩም፦ በምሳሌ አፌን እከፍታለሁ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውንም እናገራለሁ የተባለው ይፈጸም ዘንድ ያለ ምሳሌ አልተናገራቸው የታወቀ ነው።[የማቴዎስ ወንጌል 13/34-35] ሃኪሙ ዶ/ር ሉቃስ ሲነግረን “ኢየሱስ ያደርገውና ያስተምረው ዘንድ ስለጀመረው” ያደርገውና ያስተምረው ዘንድ ስለ ጀመረው?እደሆነ ያስረዳናል ይህም የጀመረውን ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውንም በምሳሌ የማስረዳት ጥበቡ በራእይ መፅሐፍም ቀጥሎበታል።
“ ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ኢየሱስ የመረጣቸውን ሐዋርያትንበመንፈስ ቅዱስ ካዘዛቸው በኋላ እስከ ዐረገበት ቀን ድረስ፥ያደርገውና ያስተምረው ዘንድ ስለ ጀመረው ሁሉመጀመሪያውን ነገር ጻፍሁ፤የሐዋርያት ሥራ 1/1-2”
ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውንም በምሳሌ አፌን እከፍታለሁ፥እናገራለሁ የሚለው ጌታ ትላንትም ዛሬም ነገው ያው ነው።
ብርሃን ሲገለጥ ጨለማን ያጋልጣልና በብርሃን ማንነቱ ሁሉን ይሞላዋል። ብርሃን ለጨለማ እሳቱ ነው ይበላዋል። መጽሐፉ አዎንታዊና የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥን መንፈሳዊ እውነታዎችን የመገለጡ ረቂቅ ታክቲክ ወይም ዘየ የሚተርክ በምልክት በተምሳሌት እንዲገባን የሆነ መንፈሳዊ መጽሐፍ ነው። እ/ር በምልክት ላከው “sent and signified it, Rve 1:1” እነዚህ ገላጭ ምልክቶች በራሳቸው እውን አይደሉም ኢየሱስ ክርስቶስ ግን እውን ነው። በገላጭ ምልክት signs and symbols ያሳያቸው ናቸውና። ምልክት ወይም ተምሳሌት የሚነገረው በጥሬው ካለው ትርጉሙ ውጪ ሌላ ነገርን የሚወክል ምስል፤ ቃል ወይም ሃረግ ነው። እውነታው ፍፃሜው የክርስቶስ መገለጥ ነው። የሌሎቹ መገለጥ በራሳቸው ፍፃሜ አይደሉም ወደ ፍፃሜ የሚያቻኩሉና ታይተው ለመዋጣቸውና አንድአንዶቹም ለመጥፋታቸው የተመደቡ ናቸው ይህም እሱ በሙሉክብሩይገለጥ ዘንድ ነው።
Signified signs and symbols are not literal, HE IS THE REALITY! It’s is the An unveiling of REALITY of Jesus Christ. Revelation 1:1[jmt]
መጽሐፉ ስለ አንድ ፀረ ክርስቶስ ሰው መገለጥ አላማ ይዞ የተፃፈ አይደለም። ወይም ያለፉ ታሪካዊ ትውፊቶችን ክስተቶችን ወይም የወደፊት ጥፋት መገለጥ ለማሳየት የተፃፈ አይደለም። እያንዳንዱ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የሚጋለጥ ኢየሱስ ክርስቶስ ከተሸፈነበት በምልክት የተመሰሉ አግልሎ እንዴት ድል እንደሚነሳቸው የሚያሳይ ነው።
በቀላል ቋንቋ የቀሩት የዚህ የእ/ር ብርሃን ክርስቶስ መገለጥ ገመናቸውን ያጋለጣቸው ትእይንቶች ናቸው። ልክ ማታ ውሃ ጠምቶህ/ሽ ወደ ወጥ ቤት ትሄድና መብራቱን ስታበራ በረሮው ይሁን ሌላው ነገር ሁሉ ግልጥ ብሎ ሲተራመስ እንደሚታይ በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ፤ የቀሩ ሁሉ ወደ መታየት መጥተው ሲተራመሱ ይስተዋላል ። በምስል በምልክት ያፃፋቸው ሁሉ የነገሮች ገፀ-ባህርይ አመልካች ወካይ ምልክቶች እና አመልካቾች ናቸው። እያንዳንዱ ዋይታ፤ እያንዳንዱ ነጎድጓድ፤አርሜገዶን፤ እንስሶች፤ ምስሎች,፤ምልክቶች፤ ባቢሎን፤ዘንዶ፤ወዘተ… ከብርሃኑ መከሰት የተነሳ በምልክት መንፈሳዊውን ሚስጥር ወክለው የተጋለጡ የነገሮች ገፀ-ባህርይ አመልካች ወካይ ምልክቶች እና አመልካቾች ናቸው። ። በአጭሩ በክብር መገለጡ የኢየሱስ ክርስቶስ እንጂ የመከራዎች ወይም የክርስቶስ ተቃዋሚን መገለጥ ለማሳየት አይደለም። እነሱ የጎንዮሽ ትእይንት ናቸው እንጂ ዋናው የእ/ር ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ነው። ተባረክ። ወንድም ቢኒ።