
ሰላም ይሁን። ከወድድም ቢኒ። ዛሬ ወንድማችን ሻሎም ሻሎም “ሄኖክና ኤልያስ ወደ ሰማይ አልተነጠቁም ። በሥጋ ሞተዋል ።” በሚለው አርእስት የኤሊያስን ባልጠራጠርም የሄኖክ ነገር ለማስተዋል በእ/ር ቃል ውስጥ ብዙ ሳሰላስል ነበረ። በመጨረሻም የእ/ርን ቃል እያነበብኩ እየተማርኩ ሳለ ጌታ እነዚህን ሚስጥራት እንዳስተውል መራኝ። ጌታ እንደ ረዳኝ መጠን ላካፍላችሁ ወደድኩ ክብር ለክብር አባቴና አምላኬ ይሁን።
ሄኖክና ኤልያስ ወደ ሰማይ እንደተነጠቁ እንደ ሰው ሁሉ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተምሬ ነበር እንደ ሰው ሁሉም በዚህ መልኩ አምን ነበረ ።
ኦሪት ዘፍጥረት 5/24 ሄኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ አልተገኘም፤ እግዚአብሔር ወስዶታልና።
እንደሚታወቀው ይህ ጥቅስ እግዚአብሔር ሄኖክን ወደ ሰማይ እንደ ተወሰደው የሚያሳይ ጥቅሶች አንዱና ዋንኛው ነበረ።
በዕብራውያን ምዕራፍ 11 ስለ ታላቅ የእምነት ግዙፎች ሰዎች ሁሉ በዝርዝር ይናገራል። ሄኖክም አንዱ ነው። በቁጥር 13 ላይ ወደ ዕብራውያን 11/13 እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ፥ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል አላገኙምና፤ ዳሩ ግን ከሩቅ ሆነው አዩትና ተሳለሙት፥…” አስተውሉ እነዚህ የእምነት ታላላቅ ሰዎች አንዳቸውም የትንሣኤን የክርስቶስ ሕይወት አልተቀበሉም እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ፥ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል አላገኙምና ሄኖክና ኤልያስም የእምነት ታላላቅ ሰዎች መካከል ናቸው።ትንሳኤ የሆነው ክርስቶስ እየሱስ ገና ስላልመጣ የትንሣኤ ሥራ አልተቀበሉም ተስፋዎቹን ከሩቅ አይተው ሞቱ። ምክንያቱም ከሙታን መካከል በኩር የሆነውን የኢየሱስን መቅድም አይችሉም።
ይህም የውስንነት እውነት ሄኖክንም ሆነ ኤልያስን ይጨምራል። ነገር ግን ቃል እንዳይጋጭ ተጨማሪ ማስረጃዎችን መመርመር ያስፈልገናል።
ወደ ዕብራውያን 11/5 ሄኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ተወሰደ፥ እግዚአብሔርም ስለ ወሰደው አልተገኘም። ሳይወሰድ እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘ ተመስክሮለታልና፤
Heb 11/5 By faith Enoch was translated that he should not see death; and was not found, because God had translated him: for before his translation he had this testimony, that he pleased God.”
መጽሐፍ ቅዱስ በማንኛውም መንገድ እርስ በርሱ እንደማይጋጭ እናውቃለን። ሄኖክ ከጌታ እየሱስ ቀድም እንዶነሮ እናውቃለን። ይህ ቃል በተተረጎመበት ሃሳብ ከላይ ካለው ሃሳብ ጋር ብቻ ሳይሆን የሚጋጨው። ከጌታ እየሱስ ቃል ጋርም ይጋጫል። የዮሐንስ ወንጌል 3/13 ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው።
በዚህ ተቃራኒ የሚመስለው በርግጥም በተተረጎመበት ሃሳብ ላይ ስተት ተሰርተዋል።
በዕብራውያን ምዕራፍ 11 ቁጥር 5 ውስጥ እያንዳንዱን ቃል ስናነብብ አማርኛ ትርጉም ደብቆታል እንጂ “translated” በግሪክ ውስጥ ያለው ቃል የመጣው “METATITHEMI” “ሜቲትቲሚ” ነው። እሱም ከሁለት ሥርወ ቃላቶች “ሜቲ” እና “ታምሚ” (“ሜቲ”).”META” and “TITHEMI.” የተገኘ ሲሆን “ሜታ” ማለት “አብሮ ማጀብ” [accompany] ሲሆን “ቲሆሚ” ማለት በፀጥታ ለመቀመጥ፤ መጋደም [place in repose, to lay down] ማለት ነው። በአጭሩ የሞተን ሰው ማጋደም እንደ ማለት ነው። ግልጽ ነው ከሰማይም ከወረደ እየሱስ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው። ከእየሱስ መክበር በፊት እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ፥ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል ገና አላገኙም።
ዕብራውያን ምዕራፍ 11 ቁጥር 13 ይወስናቸዋል። ኤልያስ ታላቅ የእምነት ሰዎች መካከል ነበሩ። ከእየሱስ መክበር በፊት እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ፥ ኤልያስም የተሰጠውን የተስፋ ቃል ገና አላገም ነበር። እንደዚያ ከሆነ እሱም ከሌሎቹ ጋር አብሮ ሞቷል። ኢየሱስ ከሙታን መካከል በኩር የሆነውን ሊቀድሙት አይችሉም።
ጴጥሮስ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ የታዩአቸው አማርኛው ትርጉም ቆርጦታል እንጂ ራእይ ነበረ በአካል አልመጡም።Matt 17:9: “..Tell the VISION[ራእይ] to no man, until the Son of Man be risen again from the dead.” መተርጎም የነበረበት “የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ያያችሁትን “ራእይ” ለማንም አትንገሩ ብሎ አዘዛቸው።” ነበር።
የማቴዎስ ወንጌል 17/9 ከተራራውም በወረዱ ጊዜ ኢየሱስ፦ የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ያያችሁትን ለማንም አትንገሩ ብሎ አዘዛቸው።
Matt 17/9 And as they came down from the mountain, Jesus charged them, saying, Tell the vision to no man, until the Son of man be risen again from the dead.
Jos 1:1 Now after the DEATH of Moses the servant of the LORD it came to pass, that the LORD spake unto Joshua the son of Nun, Moses’ minister, saying, Jos 1:2 Moses My servant is DEAD…”
Well there you have from God Almighty Himself. When a person DIES, he is DEAD.
ሌላው ኤልያስ የእግዚአብሔር መንፈስ ወደ ሰማይ አንሥቶ ወደ ሌላው ስፍራ እንደወሰደው ከእ/ር ቃል ማስተዋል ይቻላል። ኤልያስ ተነጠቀ እንጂ አልሞተም የሚለውን አስተምህሮ ይህ ቃል ያመክነዋል።
በ መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 2/1 እንዲህም ሆነ፤ እግዚአብሔር ኤልያስን በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ሊያወጣው በወደደ ጊዜ ኤልያስ ከኤልሳዕ ጋር ከጌልገላ ተነሣ።…..11 ሲሄዱም፦ እያዘገሙም ሲጫወቱ፥ እነሆ፥ የእሳት ሰረገላና የእሳት ፈረሶች በመካከላቸው ገብተው ከፈሉአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ወጣ።
አሁን ይህ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ወጣ ማለት የእግዚአብሔር መንፈስ አንሥቶ ወደ ሌላው ስፍራ ይውሰደው ወደ ሰማያት በዛው ይውሰደው የሚገላግለን የእ/ር ቃል ነው።
አሁን በጣም ጠቃሚ የሆነ እውነትን እንመለከታለን። በ 2 ነገስት 1 ውስጥ አክዓብም ከሞተ በኋላ ሞዓብ በእስራኤል ላይ ዐመፀ። የአክዓብ ልጅ አካዝያስ ከእስራኤል ዙፋን ተቀመጠ።、እሱም ለጥቂት ዓመታት ገዛ። እዚህ ላይ ግን ጠቀሜታው ኤልያስ በእርሱ የንግስና ጊዜ ውስጥ “መነጠቁ” ነው። የትኛው ዓመት እንደሆነ አናውቅም ሆኖም በእሱ ዘመነ መንግስት እንደነበረ እናውቃለን። የሚገርም ነገር ኤልያስ ከተነጠቀ በኋላ በሌላ በኢዮራም ዘመነ መንግስት ትንቢት ሲናገር እናስተውላለን።
የቤተ ክርስቲያን ትውፊት ኤልያስ ወደ ሰማይ ተወስዶ ሞቶን እንዳልሞተ ሲያስተምሩ ኖረዋል እኛንም አስተምረውናል። አስታውሱ “ከዕብራውያን 11:13 ከእየሱስ መክበር በፊት እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ፥ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል ገና አላገኙም።” የሚለው እውነት ነው።
የሚገርም ነገር ስሙ ኤልያስ ከተነጠቀ በኋላ በ 2 ኛ ዜና 21:12 ውስጥ ኤልያስ ለኢዮራም ንጉሥ የይሁዳ ንጉሥ ቃል መናገሩን እናገኛለን። መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 21/12 ከነቢዩም ከኤልያስ እንዲህ የሚል ጽሕፈት መጣበት፦ የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በአባትህ በኢዮሣፍጥ መንገድ በይሁዳም ንጉሥ በአሳ መንገድ አልሄድህምና፥
2Chr 21/12 And there came a writing to him from Elijah the prophet, saying, Thus saith the Lord God of David thy father, Because thou hast not walked in the ways of Jehoshaphat thy father, nor in the ways of Asa king of Judah,
በዚህ ክፍል ላይ “ጽሑፍ” ከኤልያስ ወደ ኢዮራም መጣ። ይህ “ጽሁፍ” ቢያንስ ከሁለት ዓመት በኋላ ኤልያስ ከተነጠቀ በኋላ ማለት ነው “መጣጥፉ” እንደመጣ እናናስተውላለን ። ይሁን እንጂ በዚህ ወቅት ኤልያስ “ወደ ሰማይ ተነጠቅዋል” ኢዮራም ደብዳቤውን እንዴት እንዳገኘ ያስገርማል።
ይህ መነጠቅ አዲስ ልምምድ አልነበረም ይሄኛው ለየት ያደረገው እነኤልሳ ዳግም ያለማየታቸው እንጂ ሊነጠቁ እና የቦታ ለውጥ ሊያካሂዱ እንደሚችሉ ግልጽ ነው።
ለምሳሌ፦ መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 18/12 እኔም ከአንተ ጥቂት ራቅ ስል የእግዚአብሔር መንፈስ አንሥቶ ወደማላውቀው ስፍራ ይወስድሃል፤ እኔም ገብቼ ለአክዓብ ስናገር፥ ባያገኝህ ይገድለኛል እኔም ባሪያህ ከትንሽነቴ ጀምሬ እግዚአብሔርን እፈራ ነበር።
እስራኤል ከይሁዳ ተቆርጦ መሄዱ አይዘነጋም።
በ 2 ኛ ነገሥት ምዕራፍ 1 ቁጥር 1 መሠረት ኤልያስ በአካዝያስ ንግሥና ዘመን “ተነጠቀ” ነበር። ከንጉሱ ሞት ቡሃላ ኤልያስ ለኢዮራም የደብዳቤው ቃል ወደ የኢየሩሳሌም ከተማ ላከ ይህም የይሁዳ መንግሥት እንጂ የእስራኤል መንግሥት ግዛት አይደለም በ 2 Chር. 21:12
ወደ ዕብራውያን 11/39-40 እነዚህም ሁሉ በእምነታቸው ተመስክሮላቸው ሳሉ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አላገኙም፥ ያለ እኛ ፍጹማን እንዳይሆኑ እግዚአብሔር ስ