ጥያቄ/መልስ ዘፍጥረት 1:26 እኛ ሲል ስላሴን አይደል እንዴ የሚያሳየው?


ጥያቄ/መልስ ዘፍጥረት 1:26 እኛ ሲል ስላሴን አይደል እንዴ የሚያሳየው?  ሰላም ይሁን ወንድም። ጥሩ ጥያቄ ነው እኛ የሚለው ቃል 3ቱ ሥላሴን እግዚያብሄሮች ለማሳየቱ በምን እርግጠኛ ትሆናለህ? እኛ 2ለትም 3ትም 4ትም 5ትም ከዛም በላይ የሚያሳይ ሊሆን ይችላልና።

በቤተክርስቲያን ውስጥ ስለ ሥላሴ በአብያተ-ክርስቲያናት ክርክር ውስጥ ዋናው ነጥቡ ተደርጎ ይነሳል።  አንድ ጊዜ አምላክ ሥላሴ እንደሆነ አድርገው ከተረዱና ካወቁ በኋላ እንደገና በእግ/ር ቃል ለመታረም ለብዙዎች ጭንቅ ነው። በውኑ እነሱ በትክክል 3 እግዚአብሔር  ሲሉ እንደ ቃሉ ተረድተዋልን?  ለራስህ ቃሉን መመርመር መልካም ነው።

ይልቁኑ ይህ ቃል የእግዚአብሔርን ሙሉነት የሚያስረዳ በድርብ ክብሩ እራሱን የገለጠበት ነው እላለሁ።

የእግዚአብሔር አምሳያ ድርብ ስለሆነ ወንዶችና ሴቶች መፍጠሩ የሱ መልክ ነው። የጥንት የስነ-መለኮት ምሁራን በስላሴ ላይ በጣም ትኩረት ስላደረጉበትት በዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ቁጥር 1 የመጀመሪያ ምዕራፍ ውስጥ የእግዚአብሔርን ቃል ላይ ዋናን ሃሳብ ሳያስተውሉት ቀርተዋል። ” ከዚያም እግዚአብሔር ” ሰው ሰውን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር “አለ. ” እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፡ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፡ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ።

እንደምናስተውለው የእግዚአብሔር መልክ አምሳል እና አምሳያ በዚህ ቃል መሰረት የወንድን እና የሴትን ገጽታ ያካትታል።  ይህ ባይሆን ኖሮ ምድራዊው የእግዚአብሔር አምሳያ ተብሎ የፈጠረው ሰው አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት የያዘ ባለ አንድ ፆታ ብቻ ሆኖ ይፈጥረው ነበረ። እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፡ በመልኩ? በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፡ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ;;

በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፡ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ? ግልጽ ነው። ።Gen 1 verse 27, “And God created man in His own image, in the image of God He created him; male and female He created them.” The image and likeness of God, then, includes male and female aspects of God. If this were not so, then the earthly image of God would express just one sex, either male or female.

በእርግጥ የጥንት የነገረ-መለኮት ምሁራኑ አምላክን በአዎንታዊነት ለመግለጽ እውነትን ለማሳየት አልቻሉም።  እግዚአብሔር በራሱ ሙሉ ስለሆነ ማንም ሳያግዘው መለኮታዊ ሙልአቱን ተጠቅሞ ማዘጋጀት እንደሚችል ከገለፁት እየተገዘቱ መገለል እንዳይደርስባቸው  እውነትን መቅበር ይመረጣሉ።ሌላው ችግር ብዙዎቹ የጣዖት አምልኮ አምላኪዎችና አማልክቶች የሴት አገላለጾች ስለሚጨምሩ ሁሉ እርስ በራሱ እየተፈራራ ችግር ነበረ።

በቁጥር 28 እግዚአብሔርም ባረካቸው ብሎ እንደ አንድ መልሶ ይጣረዋል።

28 እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።

በስሞቹ ላይ ጥናት ብታደርግ ከመጀመርያው የተናገረውና ለሙሴ ህግ የሰጠው ማነው? ህግን ለሙሴ የሰጠው እራሱን “ያህዌ (Yahweh)” ብሎ በሚነደው ቁጥቋጦ ጠርተዋል። “ያህዌ” የሚለው የፈጣሪ ስም እ/ር መጀመርያና መጨረሻ የሌለው ዘልአለማዊና እራሱን በራሱ ህላዌ(ህልውና) [self-existent] ያለው መሆኑን የሚያመለክት ነው። ይህ በአባትነት ባህርይ እ/ር እራሱን ለፍጥረት የገለጠበት 10ቱን ትእዛዛት በመስጠት ስነ-ስርአት ያወጀበት ባህርዩ ነው። ይህ ያህዌ አዲስ ስም ነበር ሲያስተዋውቃቸው። በዚህ ስም ለአብርሃም ለይሳቅ ለያቆብ አልተገለጣላቸውም ነበር። “’እግዚአብሔርም (Hebrew፣ ኤሎሂም elohiym el-o-heem) ሙሴን አለው፤ “እኔ እግዚአብሔር (Hebrew፣ያህዌ Yhovah yeh-ho-vaw’) ነኝ። ሁሉን የሚችል አምላክ (ኤልሻዳይ ‘el ale Shadday shad-dah’-ee) ሆኜ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ ተገለጥሁላቸው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር (Hebrew፣ያህዌ Yhovah yeh-ho-vaw’) በተባለው ስሜ ራሴን አልገለጥሁላቸውም። ‘ ዘፀአት 6:2-3 አዲሱ መደበኛ ትርጉም። ፍጥረት ገና መፈጠሩ ስለነበር በእናታዊ የአመራር ዘየ እራሱን ሲገልጥ ይታያል። ኦሪት ዘፍጥረት መላት፤እንደአገባቡ፡ የፍጥረት ህግ፤ የፍጥረት ስር፤ የፍጥረት ምንጭ፤የፍጥረት መገኛ፤የፍጥረት ውልደት፤ የፍጥረት ልደት ማለት ነው።

 

እንዳትረሳ አንዱ እ/ር ኤልሻዳይ፤ያህዌ ብሎ እራሱን ገለጠ ሁለት እግዚአብሔሮች አይደሉም አንድ እ/ር መሆኑን ማስተዋሉ መልካም ነው።

የህግ ሰጪው ማንነት በዘፀ፤20:2 አስርሩን ትእዛዛት ሲሰጥ በህግ መቅድሙ ላይ ሲናገር ‘“ከግብፅ ከባርነት ምድር ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ (ያህዌ self-Existent በራሱ የሚኖር ። በራሱ ህልውና ያለው) እኔ ነኝ።” “ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይኑሩህ። ‘ ዘፀአት 20:2-3”

ለአብርሃም ሲገለጥ እንደ ኤልሻዳይ አወቀው ‘አብራም ዕድሜው 99 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ተገልጦለት እንዲህ አለው፤ “እኔ ኤልሻዳይ” ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ፤ ነቀፋም አይኑርብህ፤ ‘ ዘፍጥረት 17:1 ከዘፍጥረት እስከ ዘዳግም የፃፈው ሙሴ ነው። ይህም ማለት እነ አብርሃም ያልበራለቻው ያህዌ የሚለው የእ/ር ስም ከገባው ቡሃላ የፃፈው ስለሆነ ያህዌ እያለ በእብራይስጥ ተጠቅሞበታል ኤልሻዳይ እና ያህዌ አንድ አምላክ እንደሆነ እናያለን ። “እኔ እግዚአብሔር (Hebrew፣ያህዌ Yhovah yeh-ho-vaw’) ነኝ። ሁሉን የሚችል አምላክ (ኤልሻዳይ ‘el ale Shadday shad-dah’-ee) ሆኜ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ ተገለጥሁላቸው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር (Hebrew፣ያህዌ Yhovah yeh-ho-vaw’) በተባለው ስሜ ራሴን አልገለጥሁላቸውም። ‘ ዘፀአት 6:2-3 አዲሱ መደበኛ ትርጉም። ወንድም ቢኒ።

  • http://stream.zenolive.com/u3ebzsedgceuv
  • ወንጌል ራድዮ በወንድም ቢያንም Bro. Bini TRUTH IN LOVE, RECONCILIATION OF ALL MANKIND UNDERSTANDING AND BEYOND
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/umhzr6hq7yzuv?zs=oRSj43vJRBK7sKie97UJlg
  • Glorious Harvest Worship Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/wsat39ewmd0uv?zs=Em3pukmTTbelFhx1TL3lTg
  • Wongel FM The Cloud of Glory International Church and Prayer Center (CGIC)
  • Pentecostal
  • http://stream.zenolive.com/gpsmxgas3vduv
  • ህያው ተስፋ ራድዮ Hiyaw Tesfa Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-162.zeno.fm/pfaho9uockwuv?zs=Aahd31R7T86lNKGGJUJbZQ
  • Orthodox Radio Ethiopian Orthodox Church Mezmur
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-152.zeno.fm/xbpzacbw298uv?zs=CC35I_UPS6WxAa7xMo7ArA
  • Bete Meskel Ethiopian Orthodox
  • Ethiopian Orthodox Radio
  • https://stream-151.zeno.fm/qt90skpqp0hvv?zs=MWJISXawTyWTYWk8M2NR5w&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Birhan Gospel Radio
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/074mnuw3sfeuv?zs=HAJmne4CTamoHCdyYE-irg
  • Yenigat Kokeb
  • Pentecostal
  • https://stream-152.zeno.fm/q6zt1xhvcd5tv?zs=sBLthcwlSbaiBEsYZ3yBaw&aw_0_req_lsid=0ccd358e002df8f6b4c02dc73f5596cc
  • Heaven Radio-Medan Radio በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳን ሬዲዮ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አየር ላይ ነበር ፡፡
  • Pentecostal
  • https://stream-153.zeno.fm/7x9ztyvaqxhvv?zs=4lJgENOLTgSasoQNoGylfA
  • Berhan Protestant mezmur ድንቅ የአምልኮ መዝሙሮች Amazing Worship songs
  • Pentecostal
  • http://stream-149.zeno.fm/k1yczycy49duv?zs=cQyBKF5CSxWQ2edXJhSUiA&_=1
  • Kingdom Resources Radio
  • RECONCILIATION
  • https://stream-153.zeno.fm/ogarxmw0gm7uv?zs=SKZ3MkSnQIGJPNRScd6xgw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • Christ our pass over international church
  • Pentecostal
  • https://stream-151.zeno.fm/bbnz36ojnrktv?zs=C3yJLoPvTmKMXSSZ_aFbuw&aw_0_req_lsid=3bb4bc98aeab911e46be71b281542fb0
  • የፀጋ ድምፅ ራድዮ Christian teaching,prayer,worship song....
  • Pentecostal
  • https://stream-150.zeno.fm/1zkgshv99e9uv?zs=G10XtIGRR9iYWQ0GEBITRA&aw_0_req_lsid=af514e8404312f69a7e6630a4157e1f0
  • Good News for Nation (GNN) የምስራች አገልግሎት
  • Pentecostal