
ጥያቄና/መልስ ክፍል 2 በሃብታሙ ሰው እና አልአዛር ምሳሌ
ክፍል ሰባት Brother Binyam T. Alemayehu 02/22/2018
በጌታ ፍቅር ሰላም ይሁን በጌታ ወንድሜ ካሳሁን ዘውዱ የጌታ ፀጋ ከመንፈስህ ጋር ይሁን። ብራዘር እኛ ከእንግዲህ ወዲህ የአባትን ፈቃድ እንጂ ምንም ነገር ማድረግ እንፈልጋለን አቅሙም የለንም። እኛንም ሆነ ማንንም ስጋ ለባሽ መንፈስ ለማስደሰት ፍላጎት የለንም ወይም በግድም አናሳምንም።[ስጋ ለባሽ መንፈስ ስል ቅር እንዳይልህ ከእ/ር መንፈስ የተወለደ መንፈስ ነውና። ሰው እንደ መረዳቱ ነው ምንም ችግር የለበትም። ነፍስ ነኝ ካለም መልካም፤ ስጋ ነኝ ካለም መልካም ፤መንፈስ ነፍስ ስጋ ነኝ ካለም ሁሉም መልካም ነው፤ በሰው ሁለንተና ውስጥ ሁሉም ድርሻ አላቸው ለሁሉም መረዳት ጊዜ አለውና ስጋ ለባሽ ካለ ግን ፤ ስጋን ልብስ ነው ካለው የስጋ ወይም የልብስ ክብር ለብቻው ነው። ልብሱን የለበሰው እውነተኛ ማንነት ማነው ምንድ ነው? የነፍስ ክብርም ሌላ ነው፤ የመንፈስም ክብር ሌላ ነው።] ማንንም የማሳመን ስራ አልያዝንም ህይወትን ከማካፈል አንፃር እንጂ ማሳመን የኔ የአንተ የእህቴም ስራ አይደለም ማሳመን የእ/ር የራሱ ስራ ነው የእምነትን መጠን የሚያካፍል እ/ር ነው። ለቅዱሳን አንዴ እምነትን ያደለ እሱነው። የእ/ርን ለእ/ር ነው ነገሩ። “የዮሐንስ ወንጌል 6/29 ኢየሱስ መልሶ፦ ይህ የእግዚአብሔር ሥራ እርሱ በላከው እንድታምኑ ነው አላቸው። John 6/29 Jesus answered and said unto them, This is the work of God, that ye believe on him whom he hath sent.”
ወገኖች ለምን እ/ር ሁሉን አዲስ እንደ ያደርግ ቢያቁም አዲስ ነገር ለምን ያስበረግጋቸዋል? ይገባኛል ሰው ያለውን ለመጠበቅ ይተጋል የእ/ር ሰአት እስኪደርስ ድረስ ኖርማል ሪያክሽን ነው። አንድ ብርጭቆ በነገሮች ከተሞላ ሌላ ነገር ልሙላው ቢባል ቦታ የለውም የእ/ር ቃልም ሲመጣም እንዲሁ ነው የሞላው ነገሮች ላይ የቃሉን ዉሃ ያለማቃረጥ ከሞላህበት ግን የሚፀናው ይፀናል የማይፀናው አይፀናም።
ባለፉት ትውልዶች ሁሉ የደረሰባቸው ለትምህርታችን ተጽፈዋልና ከነሱ ብዙ መማር እንችላለን። ሁሉ ወገኖች በዚህ ያሉት ቢሆኑ ከእግዚአብሔር አባት ቃሉ የተጎናጸፈውን የእውነት ብርሃን በመፈለግ ወደ እውነት ሁሉ እንደመራቸው መጠን በጉ ወደ ሄደበት የሚከተሉት ናቸው። ከወገኖች ጋርም መንፈሳዊ እውነቶች ለማካፈል ለመተናነጽ የሚፈልጉ ናቸው እንጂ እንደ ባቢሎን ነገስታት ትንንሽ የራሳቸው መንግስት መስርተው ቸርቼ ግዛቴ እንደሚሉት ትርፍን በማስላት ለጥቅም የሚራራጥ ከዚህ የለም። ያንን ግዛት እ/ር አስረጅቶታል። ቤተ ክርስቲያኔ?”የማቴዎስ ወንጌል 16/18 … ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።” ቤተክርስትያን የክርስቶስ ናት የክርስቶስም መቅደስ ናት እንጂ የወንበዶች ዋሻ አይደለችም። “ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ ተጽፎአል፥ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት አላቸው።” ዛሬ ጌታ ወደ መቅደስ ሲገባ መቅደሱ ቤቱ የጸሎት ቤት ሆኖ ያገኘዋል? ወይስ በሚያርም ፍርድ ይነሳበታል? ጅራፍ ሰርቶ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሁሉ ያስወጣል፥? የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጮችንም ወንበሮች ይገለብጣል? መልሱን ለጌታ።
ክፍል ስምንት
እኔ እስከሚገባኝ ፍቅር ግድ ስለ ሚለን እንጂ ቲፎዞ የሚፈልግ ማንም የለም። ሁሉ የእ/ር ነው። በጌታ ያለ ህብረት ግን ከህይወት እንጀራ ክርስቶስ ከተቆረሰልን አብሮ ለመቋደስ ይጠቅማል። በአጭሩ ወደ እውነት ሁሉ በመራን ጊዜ ወደ ሚሄድበት እኛም በጉን እንከተለዋለን ! ለሁሉም ሰዎች የእግዚአብሔር ፍቅር ይሰበካል ይታወጃል። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፤ የእውነትን ቃል በቅንነት ማስተዋልና መለየት፤ እውነትን በፍቅር ማስተማር፤ በክርስቶስ ተቀባይነትን፤ እና ይቅርታን ለሁሉ ለማድረስ እንጥራለን!
“እቋሪ ዉሃ አይፈወስም” “ወራጅ ዉሃ ግን ይፈወሳል” ወራጅ ውሃ ለምን እንደሚፈወስ ግልጽ ነው ስለ ሚንቀሳቀስ ነው። ስለዚህ እ/ር ወደ እውነት ሁሉ እንደመራን መጠን በጉ ወደ ሄደበት መሄዳችን የታወቀ ነው። እኛ ከእንግዲህ ወዲህ የአባት ፈቃድ ይሁንብን እንጂ ለማንም ዶክትሪን ተጎጂ ሆነን ከጌታ ህይወት መዘግየት አንሻም ምንም ነገር ማድረግ እንፈልም የአባትን ፈቃድ ግን ይሁንብን ።
‘ወንጌል’ ይህ ጥሩ ዜና ነው። ‘ወንጌል’ እውነትም መልካም ዜና ነው እንጂ ክፉ ዜና አይደለም። እናም ምንም መጥፎ ዜና የለበትም! በግሪኩ ‘ወንጌል’ የሚለው ቃል የተተረጉሞ የተፃፈው (በግሪክኛ ከ« evangel») ከሚለው ድብልቅ ቃል ነው. (‘eu’ – good, መልካም ወይም ጥሩ, እና ‘angelion’ – message መልዕክት) ስለዚህ ወንጌል ማለት መልካም ዜና ነው።
ወንጌሉም የመዳናችን የምስራች መስማታችን ነው። ኤፌ1:13 እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል ይከውም የመዳናችሁን ወንጌል ሰምታችሃል።
‘በዘመን ፍጻሜ ይሆን ዘንድ ያለውሐሳቡ በሰማይም በምድርም ያሉትን ነገሮች ሁሉ ራስ በሆነው በክርስቶስ ሥር ለመጠቅለል ነው።
ኤፌሶን 1:10
* የእግዚአብሄር አራሚ ፍርድ በምድር ባደረገ ጊዜ በዓለም የሚኖሩ ሁሉ ጽድቅን እንደሚማሩ እናምናለን። ኢሳያስ.26:8/9
በመጨረሻም የሰው ልጆች ቅድስናና ዳስታ የእግዚአብሔር የዘላለም አጀንዳው ውስጥ እንዳካተተ እናምናለን ።
ሁሉ በአዳም እንደሞቱ እንደዲሁ ሁሉም በክርስቶስ ሕያዋን ይሆናሉ።ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው በራሱ ተራ ይሆናል። 1ቆሮ 15/22
አዳም ሁሉን ወደ ሃጥያት ይዞ ለመውደቅ አቅም እንደ ነበረው ሁሉ ክርስቶስ ይበልጡኑ ሁሉን ወደ ጽድቅ ይዞ ሊነሳ የበለጠ ሃይል አለው። ብለን እናምናለን። ‘እኔ ግን ከምድር ከፍ ከፍ ባልሁ ጊዜ ሰውን ሁሉ ወደ ራሴ እስባለሁ።” ዮሐንስ12:32
እግዚአብሔር የሰዎች ሁሉ አዳኝ ነው። 1 ጢሞቴዎስ 4:10
የእግዚአብሄር ትግስት ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃ እንደሆነ እናምናለን። ‘አንዳንድ ሰዎች የዘገየ እንደሚመስላቸው ጌታ የተስፋ ቃሉን ለመፈጸም አይዘገይም፤ ነገር ግን ማንም እንዳይጠፋ ፈልጎ፣ ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃ ስለ እናንተ ይታገሣል።’2 ጴጥሮስ 3:9
ጌታ ኢየሱስ የዓለምን ኃጢአት ያስወገደ የእግዚአብሔር በግ ነው.(ዮሐንስ 1:29)
ክፍል ዘጠኝ
ወደ ወንድማችን ካሳሁን ጥያቄ ልሂድ ጥያቄህ እንዲህ የሚል ነበር። ”ከሙታን አንዱ ይሂድልንና ወይንም አልአዛር ይሂድልንና ለውንድሞቻችን ይንገርልን የሚለውን ቃል ትተኸዋልና ዋናውም ይህንን ሁሉ የፃፍክበትም ጉዳይ እርሱ ነውና ለዚህም መልስ ስጥበት” እሱን በመሃል እመልሰዋሉ ምሳሌው ላይ ብዙ ፍቺ ልናይበት ብንችልም ሁሉን ለማቅረብ ግን ይበዛል ጥቂቶችን እነካካለሁ።
1, የአብርሃም እቅፍ
እንግዲህ በሃብታሙ ሰው እና አልአዛር ምሳሌ ውስጥ ሃብታሙ ሰው የሚወክለው የአይሁድ ህዝብን ነው ብለናል። በወቅቱ በእ/ር ሞገስና በረከት ከማንም የምድር ህዝብ ለብቻው ተነጥሎ እየተደሰተ የሚኖር የነበረ ህዝብ ነው። አልአዛር በሌላ እጅ የሚወክለው አህዛብን ሲሆን ይህም በአይሁድ ደጅ የተጣለው ምንም አይነት መንፈሳዊ በረከት የማያገኝ ከእ/ር ቃል ኪዳን የልተሰጠው ህዝብ እራሱን በውሾች ደረጃ ወርዶ ያገኘው በአይሁድ ህዝብም ዘንድ እንደ ውሾች የሚቆጠሩት አህዛብን ይወክላል ብለናል።
ምሳሌው የሚያሳያው የአይሁድ ህዝብና አህዛብ ቦታ ሊቀያየሩ በማኮብከብ ላይ እንዳሉ የሚያሳይ መንፈሳዊ ትእይንት ነው። የሆነውም እሱ ነው። ሃብታሙ ሰው በፍርድ ስር እራሱን ሲያገኘው አልአዛር እራሱን በአብርሃም እቅፍ አግኝቶታል። ”አሻቅቦ አብርሃምን በሩቅ አየ አልዓዛርንም በእቅፉ።” የክብር ስፍራ ከአብርሃም ጋር የሞገስ የበረከት የቀረበ ወዳጅነት ተሰጠው። ለአብርሃም የተሰጠውን የመንፈስ ተስፋ በክርስቶስ አገኘ።
“ወደ ገላትያ ሰዎች 3/8 መጽሐፍም እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነት እንዲያጸድቅ አስቀድሞ አይቶ፦ በአንተ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ ሰበከ።”
ቋንቋው symbolic ምሳሌያዊ ወይም ምልክታዊ ነው። የሁለቱን ሞታቸውን ብታስተውሉ አልአዛር ተቀበረ አይልም አልአዛር ወደ አብርሃም እቅፍ ተወሰደ ሲል ሃብታሙ ሰው ግን ተቀበረ ይለዋል። ያም ማለት በክርስቶስ ካልሆነ በቀር በራሳቸው መብት የእ/ር ልዩ ህዝብ ተወዳጅ ህዝብ ላይሆኑ የእ/ር ህዝብ ሆነው ላይታዩ ተቀበሩ ወደ ማይታዩበት አወረዳቸው። እንደድሮ በአለም ሁሉ ገነው ዳግም ላይታዩ በትረ መንግስቱ ከዩሁዳ በተቃወሙት ክርስቶስ ተወስደ።
የሉቃስ ወንጌል 16/25 አብርሃም ግን፦ ልጄ ሆይ፥ ምን? ምን? አዎን የአብርሃም ልጅ በሲኦል ሲሰቃይ።
በ ቁጥር 23 በሲኦልም በሥቃይ ሳለ አሻቅቦ አብርሃምን በሩቅ አየ አልዓዛርንም በእቅፉ።
የግሪኩ ሲኦል Greek “hell” is HADES. ቃሉ የማይታይ unseen ማለት ነው። በእንግሊዝ አገር አንዳንድ ሰዎች እስካሁን “I hell my potatoes,” ይላሉ ያም ማለታቸው ድንቼን በጉድጋድ ቀበርኩ ለማለት ነው። ከእይታ ልሰውረው ነው፤ ልሸፍነው፡ነው። እንደ ማለታቸው ነው። ስለዚህ ሃብታሙ ሰው ከተሸፈነበት ከተሰወረበት ሆኖ በሥቃይ ሳለ አሻቅቦ አብርሃምን በሩቅ አየ አህዛብም[አልዓዛርንም] በእቅፉ አየው። የመንፈስ በረከት ተቀብሎ ሲያይ ሲሰቃይ ይታያል። ማንም አይሁዳዊ ሆነ ደጋፊዎቻቸው የመንፈስን ተስፋ በእምነት አህዛብ እንደተቀበሉ፥ የአብርሃም በረከት ወደ አሕዛብ በኢየሱስ ክርስቶስ እንደደረሰላቸው ሲያይ ስለክርስቶስ ሲነሳ በቅናት የማይቃጠል የማይሰቃይ የለም። በሲኦልም በሥቃይ ሳለ አሻቅቦ አብርሃምን ብቻ ሳይሆን በሩቅ ያየው አልዓዛርንም በእቅፉ አይቶታል።
ጌታም አስቀድሞ ተናግራቸው ነበር “የሉቃስ ወንጌል 13/28 አብርሃምንና ይስሐቅን ያዕቆብንም ነቢያትንም ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ባያችሁ ጊዜ፥ እናንተ ግን ወደ ውጭ ተጥላችሁ ስትቀሩ፥ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።”
”ወደ ገላትያ ሰዎች 3/14 የመንፈስን ተስፋ በእምነት እንድንቀበል፥ የአብርሃም በረከት ወደ አሕዛብ በኢየሱስ ክርስቶስ ይደርስላቸው ዘንድ።“
የማቴዎስ ወንጌል 21/43 ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት ከእናንተ ትወሰዳለች ፍሬዋንም ለሚያደርግ ሕዝብ ትሰጣለች።
44 በዚህም ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ይቀጠቀጣል፤ ድንጋዩ ግን የሚወድቅበትን ሁሉ ይፈጨዋል።
45 የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ምሳሌዎቹን ሰምተው ስለ እነርሱ እንደ ተናገረ አስተዋሉ፤
ክፍል አስር
የሃብታሙ ሰው ሥቃይ ፤
የሉቃስ ወንጌል 16/23 በሲኦልም በሥቃይ ሳለ አሻቅቦ አብርሃምን በሩቅ አየ አልዓዛርንም በእቅፉ።24 እርሱም እየጮኸ፦ አብርሃም አባት ሆይ፥ ማረኝ፥ በዚህ ነበልባል እሣቀያለሁና የጣቱን ጫፍ በውኃ ነክሮ መላሴን እንዲያበርድልኝ አልዓዛርን ስደድልኝ አለ።
Luke 16/23 And in hell he lift up his eyes, being in torments, and seeth Abraham afar off, and Lazarus in his bosom. 24 And he cried and said, Father Abraham, have mercy on me, and send Lazarus, that he may dip the tip of his finger in water, and cool my tongue; for I am tormented in this flame.
ምን ምን? ይህ አካላዊ ተፈጥራዊ እሳት ቢሆን ኖሮ ለውይይት ጊዜ ይሰጠው ነበርን? እሳት ሲቃጠል ቢሆን ኖሮ ለውይይት ጊዜ አይኖሮውም ፀጉሩ ይቃጠላል ስጋው ይቃጠላል አጥንቱ ሳይቀር ቅሪቱ ይከስላል እንጂ ማውራት አይችሉም በህይወት እስካለ ድረስ እስትንፋሱ እስከምታልፍ ዋዮ ከማለት ውጪ።
ታዲያ የስቃዩ ምክንያት ምንድ ነው? “አየ” ይላል አስተውሉ “lift up his EYES…” “አሻቅቦ በሩቅ አየ” what he SEES! IS TORMENTING the rich man. “ቅንዓትም እንደ ሲኦል የጨከነች ናትና። ፍንጣሪዋ እንደ እሳት ፍንጣሪ፥ እንደ እግዚአብሔር ነበልባል ነው።” የጌታ እየሱስ የተነገረው የእሳት ቃል ታያላቹሁ እንዳለቸው ያዩት ያሰቃያቸዋል ያበግናቸዋል። “በውኑ ቃሌ እንደ እሳት፥ ድንጋዩንም እንደሚያደቅቅ መዶሻ አይደለችምን?” ”አብርሃምንና ይስሐቅን ያዕቆብንም ነቢያትንም ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ባያችሁ ጊዜ፥ እናንተ ግን ወደ ውጭ ተጥላችሁ ስትቀሩ፥ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል“ እነ አብራህምን ማየቱ ብቻ ሳይሆን ያሰቃየው አልአዛር በእቅፉ ሆኖ ሲያይ ለኔ የተገባ ክብር ነበረ ብሎ እርር ድብን ብሎ የሚያሰቃየው የስቃዩ ዋናው ምንጭ ግን እሳቱ ነው። እሳቱም ፦የእሳት ረመጥ የሆነው ቃል የሆነው የስልጣን የእ/ር ቃል ነው፤ ‘ነገር ግን፣ …. ቃሉ በልቤ እንደ እሳት፣ በዐጥንቴም ውስጥ እንደ ረመጥ ሆነብኝ፤ ዐፍኜ መያዝ አቃተኝ፤ ጨርሶ መቋቋም አልቻልሁም። ‘ ኤርምያስ 20:9 አዲሱ መደበኛ ትርጉም።” ደግሞም ከሁሉ በላይ እ/ር የሚባለ እሳት ነው ከመጀመርያው ይሄ እ/ር ደግሞ ቃል ነው። ቃሉ እሳት ነው የሚሰጠውም ህግ እሳታዊ ህግ። ኦሪት ዘዳግም 33/2 …በስተ ቀኙም የእሳት ሕግ ነበረላቸው።
ትንቢተ ኤርምያስ 23/29 በውኑ ቃሌ እንደ እሳት፥ ድንጋዩንም እንደሚያደቅቅ መዶሻ አይደለችምን? ይላል እግዚአብሔር፡
“መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 8/6 … ቅንዓትም እንደ ሲኦል የጨከነች ናትና። ፍንጣሪዋ እንደ እሳት ፍንጣሪ፥ እንደ እግዚአብሔር ነበልባል ነው።”
በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ አይነት እሳት አለ። አስተውሉት እስቲ “በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና።” ሲል እሳቱ ምን አይነት ነው ተፈጥራዊ ወይስ መንፈሳዊ እሳት?ወደ ሮሜ ሰዎች 12/20 ጠላትህ ግን ቢራብ አብላው፤ ቢጠማ አጠጣው፤ ይህን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና።
አዎን ብዙ አይነት እሳት አለ። ሙሴ የየው የሚነድ ቁጥቃጦስ? በእሳት ነበልባል በእሾህ ቍጥቋጦ መካከል ታየው፤ እነሆም ቍጥቋጦው በእሳት ሲነድድ ቍጥቋጦውም ሳይቃጠል አየ።
ወደ አባቴ ቤት አምስት ወንድሞች አሉኝና፤
የሉቃስ ወንጌል 16/27 እርሱም፦ እንኪያስ፥ አባት ሆይ፥ ወደ አባቴ ቤት እንድትሰደው እለምንሃለሁ፤ አምስት ወንድሞች አሉኝና፤
28 እነርሱ ደግሞ ወደዚህ ሥቃይ ስፍራ እንዳይመጡ ይመስክርላቸው አለ።
29 አብርሃም ግን፦ ሙሴና ነቢያት አሉአቸው፤ እነርሱን ይስሙ አለው።
30 እርሱም፦ አይደለም፥ አብርሃም አባት ሆይ፥ ነገር ግን ከሙታን አንዱ ቢሄድላቸው ንስሐ ይገባሉ አለ።
31 ሙሴንና ነቢያትንም የማይሰሙ ከሆነ፥ ከሙታንም እንኳ አንድ ቢነሣ አያምኑም አለው።
ሃብታሙ ሰው[ይሁዳ] አምስት ወንድሞች አሉኝና፤ ለምን? አምስት አለ? በእርግጥም በትረ መንግስት የተሰጠው የይሁዳ ነገድ እራሱ ይሁዳ አምስት ወንድሞች አሉት ይህን ከእ/ር ቃል በማየት ማረጋገጥ ነው። ሃብታሙ ሰው የአብርሃም ልጅ የይሳቅ ልጅ የያቆብ ልጅ ነው።
“ኦሪት ዘፍጥረት 35/22 እስራኤልም በዚያች አገር በተቀመጠ ጊዜ ሮቤል ሄደ የአባቱንም ቁባት ባላን ተገናኛት፤ እስራኤልም ሰማ። የያዕቆብም ልጆች አሥራ ሁለት ናቸው
23 የልያ ልጆች፤ የያዕቆብ በኵር ልጅ ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዛብሎን፤
24-25 የራሔል ልጆች፤ ዮሴፍ፥ ብንያም፤ የራሔል ባርያ የባላ ልጆችም፤ ዳን፥ ንፍታሌም፤
26 የልያ ባሪያ የዘለፋ ልጆችም፤ ጋድ፥ አሴር፤ እነዚህ በሁለቱ ወንዞች መካከል በሶርያ የተወለዱለት የያዕቆብ ልጆች ናቸው።”
ይህ ስፍራ ካስተዋላችሁት የይሁዳ ሙሉ ወንድሞቹ በአባትም በእናትም የሚገናኙት አምስት ወንድሞች እንዳሉት ታያላችሁ። የያቆብ የመጀመርያ ሚስቱ የልያ ልጆች፤ [የያዕቆብ በኵር ልጅ ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዛብሎን፤] ይሁዳ ስድስተኛ ሆኖ ተጠቅሰዋል። ለዘመናይ ሰው ይህ ትርጉሙ እብዛም ሊመስለው ይችላል ጌታ ምሳሌውን ሲናገር ለነበሩት ግን ትልቅ ትርጉም ነበረው ስለ ነሱ እንደ ሚናገር እያወቁ ሊገድሉት ይፈልጉ ነበር።
ክፍል አስራ አንድ [የመጨረሻው]
ከሙታንም እንኳ አንድ ቢነሣ አያምኑም
በዛው በሃብታሙ ሰውና አልአዛር ምሳሌ መጨረሻ ላይ ጌታ አይናቸው ፊት ስለራሱ ትንሳኤ ትንቢት ነገራቸው። እንደ ተናገረው ከልባቸው ድንዳኔ የተነሳ እየሱስ ከሙታን አንዱና ቀዳሚው ሆኖ ቢነሳም አላመኑም። የሉቃስ ወንጌል 16/31 … ከሙታንም እንኳ አንድ ቢነሣ አያምኑም አለው።
እስራኤል ሁሉ ይድናል፤
*እስራኤል አሁን በታላቅ መንፈሳዊ ድንዛዜ ላይ ናቸው እ/ር ግን ያነቃቸዋል እስራኤል ሁሉም ይድናል፤ እግዚአብሔር ሁሉን ይምር ዘንድ ሁሉን በአለመታዘዝ ዘግቶታልና። ሃብታሙ ሰው ሊያድነው ወደማይችል አብርሃም አባት ሆይ አድነኝ ብሎ ተማፀነ እርሱ አላዳነውም ሌላ ግን ሊያድ ነው የሚችል በሰማይ በምድር ከምድር በታች ስልጣን ያለው አለ። የዮሐንስ ራእይ 1/18 …የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ። የዮሐንስ ራእይ 3/7 … የዳዊት መክፈቻ ያለው፤ የሚከፍት፥ የሚዘጋም የሌለ፤ የሚዘጋ፥ የሚከፍትም የሌለ፤ ቅዱስና እውነተኛ የሆነው እርሱ እንዲህ ይላል። ጌታ በሱ ብቻ እንደሚድኑስለሚያውቅ ተስፋቸው የጨለመ አይደለም “የማቴዎስ ወንጌል 23/39 እላችኋለሁና፥ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩኝም።” በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው ማለት ሲጀምሩ ጌታን ያዩታል። አይናቸው አዳኙን ታያለች ድነውም ይቀራሉ። አሜን።
ወደ ሮሜ ሰዎች 11/25 ወንድሞች ሆይ፥ ልባሞች የሆናችሁ እንዳይመስላችሁ ይህን ምሥጢር ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፤ የአሕዛብ ሙላት እስኪገባ ድረስ ድንዛዜ በእስራኤል በአንዳንድ በኩል ሆነባቸው፤
26 እንደዚሁም እስራኤል ሁሉ ይድናል፤ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፦ መድኃኒት ከጽዮን ይወጣል ከያዕቆብም ኃጢአተኛነትን ያስወግዳል። 27 ኃጢአታቸውንም ስወስድላቸው ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው።28 በወንጌልስ በኩል ስለ እናንተ ጠላቶች ናቸው፥ በምርጫ በኩል ግን ስለ አባቶች ተወዳጆች ናቸው፤ 29 እግዚአብሔር በጸጋው ስጦታና በመጥራቱ አይጸጸትምና።30 እናንተም ቀድሞ ለእግዚአብሔር እንዳልታዘዛችሁ፥ አሁን ግን ከአለመታዘዛቸው የተነሣ ምሕረት እንዳገኛችሁ፥ 31 እንዲሁ በተማራችሁበት ምሕረት እነርሱ ደግሞ ምሕረትን ያገኙ ዘንድ እነዚህ ደግሞ አሁን አልታዘዙም። 32 እግዚአብሔር ሁሉን ይምር ዘንድ ሁሉን በአለመታዘዝ ዘግቶታልና። 33 የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው፤ ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፥ ለመንገዱም ፍለጋ የለውም።34 የጌታን ልብ ያወቀው ማን ነው?35 ወይስ አማካሪው ማን ነበር? ወይስ ብድራቱን ይመልስ ዘንድ ለእርሱ አስቀድሞ የሰጠው ማን ነው? አሜን። ወንድም ቢኒ