
“አስተምሮትህ ምንድን ነው?” በጌታ ለምወዳት እህቴ ጌታ አብዝቶ ይባርክሽ። “ስተሃል ይሄ ከእ/ር አይደለም ንስሃ ግባ” ላልሽው በቤተክርስቲያን በሰው የተለመደ እውነት ትምርት አይደለም ለማለት እንደሆነ ይገባኛል። ከእ/ር እንደሆነስ እርሱ ይመሰክራልና የስጋና የደም ማረጋገጫ አያስፈልገኝም። ከእ/ር የሆነ የእ/ርን ነገር ያስተውላልና። የቀድመውን መረዳት እስክ ኮሌጅ ድረስ ተምሬዋለሁ።
ለማንኛውም እኔም እንደ አንቺ መጀመርያ ላይ የጌታ መንፈስ ወደ እውነት ሁሉ ሲመራኝ ተቃውሜው ነበረ ግን መሪው መሪ ነውና ከፊት ይቀድማል ተብሎ እንደ ተፃፈ እሱ ቀድሞኝ እንደሄደ ሳስተውል እረኛው ይምራኝ አልኩ። ጌታ ይብዛልሽ። የሌላም ሰው ጥያቄ ሊሆን ስለሚችል ይህ ብለጥፈው መልካም ነው። ” (2Cor 1:17. ‘ይህን ሳቅድ በሚገባ ሳላስብ ያደረግሁት ይመስላችኋልን? ወይስ በዓለማዊ ልማድ አንዴ፣ “አዎን፣ አዎን” ወዲያው ደግሞ፣ “አይደለም፣ አይደለም” የምል ይመስላችኋልን? ‘2 ቆሮንቶስ 1:17
በጌታ ፍቅር ሰላም ይሁን!
እንግዲህ ይህን ስለ አንዳንድ ወገኖች ስል እጽፋለሁ እንጂ በእግዚያብሄር ልጅነት ውስጥ ይሄ ነው የሚባል ቃሚ የእምነት ድንጋጌ የለም ። አጠቃላይ ስእሉን በጥቂቱ ለመግለፅ ነው።
ማስጠንቀቂያ! እርሱ የእውነት መንፈስ ወደ እውነት ሁሉ በመራን ጊዜ ወደ ሚሄድበት እኛም በጉን እንከተለዋለን !
መንፈሳዊው ነገር ልናስተውለ ከምንችለው በላይ ታላቅና ግዙፍ ነው። እ/ር የገለጠልን ብቻ እናስተውላለንና ። የእግዚያብሄር፡ሚስጥር ማብቂያው ገናም ነውና። ‘ነገር ግን ሰባተኛው መልአክ መለከቱን በሚነፋባቸው ቀኖች፣ ለአገልጋዮቹ ለነቢያት በገለጠላቸው መሠረት የእግዚአብሔር ምስጢር ይፈጸማል።” ‘ራእይ 10:7
አሁን ከዛ ለማለፍ ምንም ብንተጋ ከውቅያኖስ በጭልፋ እንደ መቅዳት ያህል ነው። አላማችን እግዚያብሄር መሆኑን ብቻ ግን እናውቃለን።
በተረፈ በግሌ አሁን ልንሸከመው የማንችለው ነገር እንዳለ አስተውያለሁ። ጌታ ብዙ እውነት እየገለጠ በለፉት 22 አመታት ከምነት ወደ እምነት ከክብር ወደ ክብር ከአንድ የመረዳት ሰማይ ከፍ ወዳለ ሰማይ ሲያሳየኝ የቀድመውን ሲያስረጅብኝ ሲያስደነግጠኝ አስተውያለሁ ለዚህም እኔ ለራሴ ህያው ምስክር ነኝ። መጽሐፍ እንደሚል “እቃሪ ውሃ አይፈወስም” ወራጅ ውሃ ግን ስለ ሚንቀሳቀስ ይፈወሳልና። እ/ር ሲመራን ስጋና ደም አናማክርም ጌታን መከተል ብቻ ነው። ”ሄኖክ አካሄዱን ከእግዚአብሄር ጋር አደረገ ስለዚህም አልተገኘም“ አንተም እንዲሁ አድርግ አትገኝም።
ለሁሉም ሰዎች የእግዚአብሔር ፍቅር ይሰበካል ይታወጃል። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፤ የእውነትን ቃል በቅንነት ማስተዋልና መለየት፤ እውነትን በፍቅር ማስተማር፤ በክርስቶስ ተቀባይነትን፤ እና ይቅርታን ለማድረስ እንጥራለን!
* በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን ስለ ቅዱሳን መጻሕፍት ስናስብ ከአምላክ ለሰው ልጆች መገለጥ የያዘ እንደሆነ እንደ ቃሉ እናምናለን።
* እኛ አንድ አምላክ አብ ሁሉን ቻይ ሰማይንና ምድርን በፈጠረው እናምናለን በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ገላጭ የመለኮት ክብሩ ፍጽም ነፀብራቅ መገለጥ እንደሆነ እና የዓለም ሁሉ አዳኝ እንደሆነ በመንፈስ ቅዱስ አፅናኝነቱ ውስጥ በሱ በኩል ሁሉም የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት አንድ መንፈሳዊ አካል አንድነት እዳገኙ እናስተውላለን ።
* በኃጢአት ይቅርታ ውስጥ ና በመንፈሱ ሃይል የግል የመታደስ(ዳግም ውልደትን) አስፈላጊነት እናምናለን
* የእግዚአብሄር አራሚ ፍርድ በምድር ባደረገ ጊዜ በዓለም የሚኖሩ ሁሉ ጽድቅን እንደሚማሩ እናምናለን። ኢሳያስ.26:8/9
በመጨረሻም የሰው ልጆች ቅድስናና ዳስታ የእግዚአብሔር የዘላለም አጀንዳው ውስጥ እንዳካተተ እናምናለን ።
‘በዘመን ፍጻሜ ይሆን ዘንድ ያለውሐሳቡ በሰማይም በምድርም ያሉትን ነገሮች ሁሉ ራስ በሆነው በክርስቶስ ሥር ለመጠቅለል ነው።
ኤፌሶን 1:10
*ሁሉ በአዳም እንደሞቱ እንደዲሁ ሁሉም በክርስቶስ ሕያዋን ይሆናሉ።ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው በራሱ ተራ ይሆናል። 1ቆሮ 15/22
አዳም ሁሉን ወደ ሃጥያት ይዞ ለመውደቅ አቅም እንደ ነበረው ሁሉ ክርስቶስ ይበልጡኑ ሁሉን ወደ ጽድቅ ይዞ ሊነሳ የበለጠ ሃይል አለው። ብለን እናምናለን። ‘እኔ ግንከምድር ከፍ ከፍ ባልሁ ጊዜ ሰውን ሁሉ ወደ ራሴ እስባለሁ።” ዮሐንስ12:32
* እግዚአብሔር የሰዎች ሁሉ አዳኝ ነው። 1 ጢሞቴዎስ 4:10
* የእግዚአብሄር ትግስት ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃ እንደሆነ እናምናለን። ‘አንዳንድ ሰዎች የዘገየ እንደሚመስላቸው ጌታ የተስፋ ቃሉን ለመፈጸም አይዘገይም፤ ነገር ግን ማንም እንዳይጠፋ ፈልጎ፣ ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃ ስለ እናንተ ይታገሣል።’2 ጴጥሮስ 3:9
* ጌታ ኢየሱስ የዓለምን ኃጢአት ያስወገደ የእግዚአብሔር በግ ነው.(ዮሐንስ 1:29)
* ‘እግዚአብሔር በክርስቶስ ዓለምን ከራሱ ጋር ሲያስታርቅ የሰዎችን በደል አይቈጥርባቸውም ነበር፤ ለእኛም ደግሞ የማስታረቅ ቃል ሰጠን። ‘2 ቆሮንቶስ 5:19
* እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ, ‘እግዚአብሔር በክርስቶስ ዓለምን ከራሱ ጋር ሲያስታርቅ የሰዎችንበደል አይቈጥርባቸውም ነበር፤ ለእኛም ደግሞ የማስታረቅ ቃልሰጠን። እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንድንሆን፣ ኀጢአትየሌለበትን እርሱን እግዚአብሔር ስለ እኛ ኀጢአት አደረገው።’ 2ቆሮንቶስ 5:19,21
* ‘ወንጌል’ ይህ ጥሩ ዜና ነው። ‘ወንጌል’ እውነትም መልካም ዜና ነው እንጂ ክፉ ዜና አይደለም። እናም ምንም መጥፎ ዜና የለበትም! በግሪኩ ‘ወንጌል’ የሚለው ቃል የተተረጉሞ የተፃፈው
(በግሪክኛ ከ« evangel») ከሚለው ድብልቅ ቃል ነው. (‘eu’ – good, መልካም ወይም ጥሩ, እና ‘angelion’ – message መልዕክት) ስለዚህ ወንጌል ማለት መልካም ዜና ነው። ወንጌሉም የመዳናችን የምስራች መስማታችን ነው። ኤፌ1:13 እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል ይከውም የመዳናችሁን ወንጌል ሰምታችሃል።
* እግዚአብሔር አምላክ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይወዳችኋል። እሱ ዓለምን ከመፍጠሩ በፊት እርሱ ወደድኋችሁ.(ኤፌሶን 1/3-14) ይህም የእርሱ ጠላት ሳለን ወደ ራሱ ለማስታረቅ ወስኖ እርምጃ የወሰደው እግዚአብሔር እራሱ ነበር.(ሮሜ 5/8-11)
* ምንም እንካ በእግዚአብሔርን ሕግ መኖር የማንችል ቢሆንም, እግዚአብሔር በልጁ ኢየሱስ ክርስቶስን ሞትና ትንሳኤ አማካኝነት
በአይኑ ፊት በክርስቶስ ትክክል አደረገን። (ሮሜ 5/8-11)
* አንተ/ቺ አሁን ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም ሊኖርህ/ሽ ይችላል(ሮሜ 5: 1).
* አንተ/ቺ አሁን በክርስቶስ ሕይወት ሊበዛላችሁ በብዛትም ሊኖራችሁ ይችላል። በደስታም ከህይወት ውሃ መቅዳት ትችላላችሁ። ‘ሌባውሊሰርቅ፣ ሊገድልና ሊያጠፋ ብቻ ይመጣል፤ እኔ ግን ሕይወት እንዲኖራቸውና እንዲትረፈረፍላቸው መጥቻለሁ።” ‘ዮሐንስ 10:10’
እንዲህም አለኝ፤ “ተፈጸመ፤ አልፋና ዖሜጋ፣ የመጀመሪያውናየመጨረሻው እኔ ነኝ፤ ለተጠማ ከሕይወት ውሃ ምንጭ ያለ ዋጋ እሰጣለሁ። ‘ራእይ 21:6
* የእግዚአብሔርን ይቅርታ አሁን ማወቅ ይችላሉ። ኤፌሶን 1/7:8
* የዚህ ሁሉ ምክንያቱም የኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ ነው. ተፈጸመ! (ዮሐንስ 19:30) ተፈጸመ!
