ፍቅር ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል ! Love rejoiceth with the truth!
“1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፡6 ፍቅር… ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤ 1Cor 13፡6 Love…Rejoiceth not in iniquity, but rejoiceth in the truth;” ሐዋርያው ፍቅር ደስ የሚለው በእውነት እንደ ሆነና በአመጽ ደስ እንደ ማይለው የፍቅር የሃሴት ሰፈር ከእውነት ጋር እንደሆነ ይነግረናል። የጌታ ቃል ከእውነት ጋር እንድንጣመር በተለያየ መልኩ ያስተምረናል። “ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6፡14-15 እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ” ወገብ በአብዛኛው በመጽሐፍ እጅግ ጠቃሚ ለሰው የሐይል ክልል ተምሳሌት አድርጎ ይጠቀምበታል። በጥቂት ቦታም “ከወገብህ የሚወጣውን ዘርህን” በነዚህና በመሳሰሉ ቃላት ከዘር ጋር ሲያይዘው በተቀረው ከሐይል ጋር ይመስለዋል። ለምሳሌ “ወገብህን አጽና፥ ኃይልህንም እጅግ አበርታ፤ አንተ ግን ወገብህን ታጠቅ፥ ተነሥም፤ ወገብዋን በኃይል ትታጠቃለች፥ ክንድዋንም ታበረታለች፤ አሕዛብንም በፊቱ አስገዛ ዘንድ የነገሥታትንም ወገብ እፈታ ዘንድ፥” “ የዮሐንስ ወንጌል 21፡18 እውነት እውነት እልሃለሁ፥ አንተ ጐልማሳ ሳለህ ወገብህን በገዛ ራስህ ታጥቀህ ወደምትወደው ትሄድ ነበር፤ ነገር ግን በሸመገልህ ጊዜ እጆችህን ትዘረጋለህ፥ ሌላውም ያስታጥቅሃል ወደማትወደውም ይወስድሃል አለው”

“1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1፡13 ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኖራችሁ” 1Pet 1፡13 Wherefore gird up the loins of your mind የአይምራችን ወገብ ወይም ሐይል መታጠቅ ወይም መጽናት ያለበት በእውነት ነው። በዚህም ከእ/ር ፈቃዱም ጋር እንስማማለን። “የዮሐንስ ወንጌል 17፡17 በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው።” ማሰብ ያለብንም እውነት የሆነውን ነገር ብቻ ነው። “እኔ እውነት ነኝ” እንዳለ እውነትን በማሰብም ጌታን ሁሌ በአይናችን ፊት እናየዋለን ማለት ነው። እርሱን ስናየው ደግም ከከብር ወደ ክብር እርሱን እንመስል ድረስ መለወጥ አለ። “ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፡8 በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤” አዎን ማሰብ ያለብንም እውነት የሆነውን ነገር ብቻ ነው። “ የጌታ ቃል ከእውነት ጋር እንድንጣመር በተለያየ መልኩ ያስተምረናል። ይህ ሊሆን የሚችለው ግን ከእውነት ጋር በድቅር ደስ ሲለን ነው ። ፍቅር ከእውነት ጋር ደስ ይለዋልና ! እ/ር አባታችን ፍቅር ነው እኛም የፍቅር ልጆች ፍቅሮች ነን በእውነትም ሁሉ ደስ ይለናል ። ለእውነት ፍቅር ከሌለን ግን እንፍራ እ/ር ብርቱ ነውና ከእርሱ ቁጣ አናመልጥም።


“2ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 2፡11-12 ስለዚህም ምክንያት፥ በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዓመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ ፍርድን እንዲቀበሉ፥ ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል።” 2Thess 2፡11 And for this cause God shall send them strong delusion, that they should believe a lie: 12 That they all might be damned who believed not the truth, but had pleasure in unrighteousness.” በፊታችን ሁለት መንገዶች እ/ር አስተካክሎ አስቀምጠዋል። ወይ በውስጣችን ደህንነትን ይሰራ ዘንድ እውነትን በፍቅር እንቀበላለን አሊያ በውጣችን ብዥታን ይልክብንና ስህተትን እናምናለን። አስተውሉ የሚገርመው ይህን ሁሉ የሚሰራው ሌላ ሳይሆን እራሱ እ/ር ነው። በዚህም የክብርና የመአቱ መግለጫዎችን ያዘጋጃል።

በዓመፅ ደስ ለሚላቸውና የእውነት ፍቅር ለማይቀበሉት በምላሹ በውስጣቸው የስህተት አሰራር ይሰራባቸዋል። ከዛም ለፍርድ አልፈው ይሰጡና በእሳቱ ከስተቱ በማንጻት ጽድቅን ይማራሉ። በኢሳ 29/10 ለኃጢአተኛ ሞገስ ቢደረግለት ጽድቅን አይማርም ብታባብሉት ብትሸልሙት ጽድቅን አይማርም የሚማረው የእ/ር ፍርድ ሲገለጥ ብቻ ነው። በኢሳ 29/9 ፍርድህን በምድር ባደረግህ ጊዜ በዓለም የሚኖሩት ጽድቅን ይማራሉና:when thy judgments are in the earth , the inhabitants of the WORLD will learn righteousness .[uprightness & right standing with GOD.] Isaiah 26/9 አስተዋላቹሁን ፍርዱ በአለም ሲገለጥ ምንን ይማራሉ ይላል? ጽድቅን! ሃሌሉያ! እንግድህ እነዚህ በአስቸጋሪ መንገድ እውነትን ይማራሉ የእውነትን ፍቅር መቀበል ምንኛ የተሻለ እንደሆነ በብርቱ አሰራሩ አልፈው ይማራሉ። እንደዚህም ሆኖ እ/ር በዚህ ሁሉ ሂደት የበላይ እንደሆነ ሁሉ በቁጥጥሩ ስር እንዳለ ፈቃዱ ይፈጸማል።
“ትንቢተ ኢሳይያስ 66፡4 እኔ ደግሞ የተሳለቀባቸውን እመርጣለሁ፥ የፈሩትንም ነገር አመጣባቸዋለሁ በፊቴ ክፉ ነገርን አደረጉ፥ ያልወደድሁትንም መረጡ እንጂ በጠራሁ ጊዜ አልመለሱልኝምና፥ በተናገርሁም ጊዜ አልሰሙኝምና። Isa 66፡4 I also will choose their delusions, and will bring their fears upon them; because when I called, none did answer; when I spake, they did not hear: but they did evil before mine eyes, and chose that in which I delighted not.”

እ/ር የትኛውን ብዥታ ተጠቅሞ ጉልበት ሁሉ ለእርሱ ክብር ወደ መስጠት እደሚያመጣው ያውቃል። ይህንም የጌታን ፈቃድ መጋፋት ክፉን በራስ ላይ ማምጣት እደሆነ አስተምሮ እርሱ ሰብሮ እርሱ ይጠግናል። ትንቢተ ሆሴዕ 6፡1 ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ እርሱ ሰብሮናልና፥ እርሱም ይፈውሰናል እርሱ መትቶናል፥ እርሱም ይጠግነናል።ከእውነት ጋር ፍቅር አብረን እንቀበላለን እውቀት ብቻውን ከሁሉ ከሚበልጠው ፍቅር ውጪ አያጸናንምና ። በ1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13 ላይ 16 የፍቅር ባህሪያቶች አሉ ። በአሮጌው ኪዳን የእ/ር ህልውና ማደርያው ድንካን በ16 ከብር በተሰሩ ችካሎች ጸንቶ የቆመ ነበረ የአዲስ ኪዳን ማደሪያ ድንካኖቹም ስር መሰረታችን ጸንቶ የሚያቆመን 16 ባህርያት ያሉት ፍቅር ነው። “ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 3፡16-17 በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድት ጠነክሩ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር እንደ ክብሩ ባለ ጠግነት መጠን ይስጣችሁ፤ የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ፥”

“ትንቢተ ዳንኤል 11:14 …ከሕዝብህም መካከል የዓመፅ ልጆች ራእዩን ያጸኑ ዘንድ ይነሣሉ ነገር ግን ይወድቃሉ። Dan 11:14 the robbers of thy people shall exalt themselves to establish the vision; but they shall fall.” ለእውነት ፍቅር የሌላቸው እራሳቸውን ከፍ ያደርጉና ያልቃሉ ራእይንም ሊያጸኑ እዲችሉ ሁሉ ነገር ግን ይወድቃሉ። ለእውነት ፍቅር ሲኖራቹሁ ግን በራስ ጥረት ራእይ እዲጸና አትታገሉም በነጠላ እይታ ጌታቹ ላይ እየጠበቃቹሁ ቃሉ ሙልአትን ሲሰጠው ታያላቹሁ። “መዝሙረ ዳዊት 119፡165 ሕግህን ለሚወድዱ ብዙ ሰላም ነው፥ ዕንቅፋትም የለባቸውም። Ps 119፡165 Great peace have they which love thy law: and nothing shall offend them.” አሜን!