Let the unselfish Christ Jesus mind be in you
Let the unselfish Christ Jesus mind be in you! PDF
Posted on 09/01/ 2011 by wongelradio
Brother Binyam T. Alemayehu http://wongelradio.com/
Let the unselfish
Christ Jesus mind be in you
እራስ ወዳድ ያልሆነው የክርስቶስ እየሱስ አይምሮ በእናንተ
ዘንድ ደግሞ ይሁን።
“ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2፡3 እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤ 4 እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥ ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ። 5 በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን።”
“Phil 2፡3
Let nothing be done through strife or vainglory; but in lowliness of mind let
each esteem other better than themselves. 4 Look not every man on his own
things, but every man also on the things of others. 5 Let this mind be in you,
which was also in Christ Jesus:”
እንዳስተዋልነው እራስ ወዳድ ያልሆነው የክርስቶስ እየሱስ አይምሮ በእኛ ዘንድ ደግሞ ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው ይለናል? አዎን
እየአንድአንዳችን ባልንጀራችን ከእኛ ይልቅ የተሻለ እንደሆነ በትህትና በውሳኔ በመቁጠር ደግሞም በተግባርም ቢሆን እየአንድአንዳችን
ለራሳችን የሚጠቅመንን ብቻ ሳይሆን ለባልንጀራችን በማሰብ እራስ ወዳድ ያልሆነው የክርስቶስ እየሱስ አይምሮ በእኛ ዘንድ ህያው እንደሚሆን
ያስተምረናል።
ጌታ እየሱስ ባል እንጀራህን መውደድ ሁለተኛይቱ ታላቅ ትእዛዝ እንደሆነች ነግሮናል።
የማቴዎስ ወንጌል 22፡36 መምህር ሆይ፥ ከሕግ ማናቸይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት? ብሎ
ጠየቀው። 37 ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ። 38 ታላቂቱና
ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት። 39 ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፥ እርስዋም፦ ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ የምትለው ናት።
40 በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕጉም ሁሉ ነቢያትም ተሰቅለዋል።
መዝሙረ ዳዊት 119፡130 የቃልህ ፍቺ ያበራል፥ ሕፃናትንም አስተዋዮች ያደርጋል።The entrance of thy words giveth light; it giveth
understanding unto the simple ተብሎ እንደተጻፈ ትዝ ይለኛል የዚህ ቃል ፍቺ በውስጤ ብርሃን ሲለቅ ሁኔታውን አልዘነገውም ያን ቀን
በአገራችን አትክልትና ፍራፍሬን በጉጠት ደራርበው በደጅ አንጠልጥለው በሚሸጡበት ሱቅ ነበርኲ። በብረት ጉጠት ደራርበው ባንጠለጠሉት
አትክልትና ፍራፍሬን በተመስጦ እያየሁ ነበረ።
ጌታ እየሱስ የተናገረው ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ ደግሞም ባልንጀራህን
እንደ ነፍስህ ውደድ በሚሉት ። በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕጉም ሁሉ ነቢያትም ተንጠጥለዋል። የሚለው ሃሳብ በብረት ጉጠት ተደራርበው አትክልትና ፍራፍሬዎቹ
ተንጠልጥለው እንዳሉና ብረቱ ቢሰበር ግን አትክልትና ፍራፍሬዎቹ እንደሚወድቁ ወደ ማስተዋሌ መጣ። በዚህ ምሳሌም በእነዚህ በሁለቱ
ማለትም አምላክህን እና ባልንጀራህን መውደድ ላይ ትእዛዛትም ሁሉ ሕጉም ሁሉ ነቢያትም በመውደድ (በፍቅር) ላይ ተንጠጥለው እንዳሉ አስተዋልኩ። ፍቅር የህግ ፍጻሜ
(ግብ) ነውና።
ጌታ እየሱስ አንድ ሕግ አዋቂ ሊፈትነው ተነሥቶ ወዳጄ ማነው ብሎ ጠይቆት ነበረ ጌታም የወዳጅን ትርጉም ከተለመደው በላይ
ከፍ ያለ የፍችውን ደረጃ ነገረው።
“የሉቃስ ወንጌል 10፡29 እርሱ ግን ራሱን ሊያጸድቅ ወድዶ ኢየሱስን። ባልንጀራዬስ
ማን ነው? አለው። 30 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ፦ አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ወረደ በወንበዴዎችም እጅ ወደቀ፤ እነርሱም
ደግሞ ገፈፉት ደበደቡትም በሕይወትና በሞት መካከልም ትተውት ሄዱ። 31 ድንገትም አንድ ካህን በዚያ መንገድ ወረደ አይቶትም ገለል
ብሎ አለፈ። 32 እንዲሁም ደግሞ አንድ ሌዋዊ ወደዚያ ስፍራ መጣና አይቶት ገለል ብሎ አለፈ። 33 አንድ ሳምራዊ ግን ሲሄድ ወደ
እርሱ መጣ አይቶትም አዘነለት፥ 34 ቀርቦም ዘይትና የወይን ጠጅ በቍስሎቹ ላይ አፍስሶ አሰራቸው፥ በራሱ አህያም ላይ አስቀምጦት
ወደ እንግዶች ማደርያ ወሰደው ጠበቀውም። 35 በማግሥቱም ሁለት ዲናር አውጥቶ ለባለቤቱ ሰጠና። ጠብቀው፥ ከዚህም በላይ የምትከስረውን
ሁሉ እኔ ስመለስ እከፍልሃለሁ አለው። 36 እንግዲህ ከነዚህ ከሦስቱ በወንበዴዎች እጅ ለወደቀው ባልንጀራ የሆነው ማንኛው ይመስልሃል?
37 እርሱም፦ ምሕረት ያደረገለት አለ። ኢየሱስም፦ ሂድ አንተም እንዲሁ አድርግ አለው።” እንደአስተዋልነው መልእክቱ “ኢየሱስም፦ ሂድ አንተም እንዲሁ አድርግ አለው።” ነው።
Posted on 09/01/ 2011 by wongelradio
Brother Binyam T. Alemayehu
“እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤ 4 እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥ ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ።” መቼም እራስ ወዳድነት የዚህ ትውልድ ገጸ-ባህሪ ዋንኛው ገላጭ ቃል እንደሆነ የአደባባይ ምስጢር ነው። መቸም ይህ ሃሳብ የሚያወራው ያለው እ/ር በተቀበለን ማንነታችን መቀበል በሚለው ጣእም እንዳልሆነ ግልጽ
ነው። ጌታ ማንነታችን በመቀበል በክርስቶስ አክብሮን እስከ መጨረሻውም የወደደን እ/ር የወደደውን እንወዳለንና የተቀበለውን ማንነታችን እንቀበላዋለን።
የስጋ ስራ የሆነው ከራስ ወዳድነት ግን የእኔነት እራስን የማስቀደም ስግብግብነት የሚያሳይ ነው። ከዚህም የተነሳ በዚህ ዘመንም እ/ር ያጣመራቸው ጋብቻዎች ሰው ሊለያቸው በራስ ወዳድነት አፋፍ ላይ ደርሰው ሲናወጡ ይስተዋላሉ። እያንዳዱ የራሱ መንገድ እዲፈጸም ይሰባበራልና። ሁሉ የራሱን ደስታ ያስቀድማል የራሱን ስሜትና
ጥቅም ለመጠበቅ ይጋደላል። እያአንዳዱ ግን ለአንዱ ቅድሚያ ሰጥቶ ሲያስብ ሁሉ ሚዛኑን ይጠብቃል ለሁለቱም የተትረፈረፈ በረከት ይሆንላቸዋል። የክርስቶስ አይምሮ ለራሱ አይጋደልም ፍቅን ይሰጣል ደጋግሞም አብዝቶ ይሰጣልና ። ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን የወደደበትን ፍቅር ስናይም ፍጽምናውን አይተን እንኮነናለን። ፈለጉን በጸጋው ታግዘን ለመከተልም አይናችን እርሱን እርሱን ያያሉ። በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእኛ ዘንድ ደግሞ እንዲሆን ጌታ ሆይ ጸጋህ ያስችለን ብለን በትህትና ከጌታ እግር ስርም እንደፋለን።
ሐዋሪያው ጳውሎስ ዘንድም እራስ ወዳድ ያልሆነው የክርስቶስ እየሱስ አይምሮ ሲገልጥ
እናያለን። “2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12፡15 እኔ ግን ስለ ነፍሳችሁ በብዙ ደስታ ገንዘቤን እከፍላለሁ፥ ራሴን እንኳ እከፍላለሁ።
ከመጠን ይልቅ ብወዳችሁ በዚህ ልክ ፍቅራችሁ የሚያንስ ነውን? 2Cor 12፡15 And I will very gladly spend
and be spent for you; though the more abundantly I love you, the less I be loved.”
ሐዋሪያው ጳውሎስ እንደምናስተውለው ምላሽን ሳይጠብቅ በደስታ ዋጋ ይከፍላል እራሱን ይሰጣል ከመጠን ይልቅ ይወዳል ። ለመስጠት መቻሉ ብቻ ለሱ የተበረከ ባእሪ እንደተሰጠው
ይቆጥራል ያመሰግናልም። ሰው ከላይ ካልተሰጠው በቀር አንዳች ነገር ሊያደርግ አይችልምና ። ደግሞም በነገር ሁሉ ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ አብቶ የተባረከ ነው። ይሄ ነው የፍቅር ልጅ ፍቅር ለታይታ የድራማ ህይወት ሳይሆን በፍቅር የሚመላለስ የክርስቶስ ህይወት በስጋው ተገልጦ የሚኖር። እርሱ እያነሰ ክርስቶስ እየላቀ በሂወቱ የሚሄድ ብቻ ሳይሆን ከዚያም ባሻገር እኔ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ህያው ሆኖ ይኖራል not I, but Christ ወደሚል የበሰለ የልጅነት ክብር የደረሰ ሆኖ እናገጀዋልን። ታዲያ ይህ ሰው ፍቅርን
እደዚህ ብሎ ሲተነትነው የተግባር ሰው መሆኑን እናስተውላለን።
| 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13 | 1Cor 13 |
| 1 በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ። |
1 Though I speak with the tongues of men and of angels, and have not charity, I am become as sounding brass, or a tinkling cymbal. |
| 2 ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። |
2 And though I have the gift of prophecy, and understand all mysteries, and all knowledge; and though I have all faith, so that I could remove mountains, and have not charity, I am nothing. |
| 3 ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። |
3 And though I bestow all my goods to feed the poor, and though I give my body to be burned, and have not charity, it profiteth me nothing. |
| 4 ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤ | 4 Charity suffereth long, and is kind; charity envieth not; charity vaunteth not itself, is not puffed up, |
| 5 የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤ | 5 Doth not behave itself unseemly, seeketh not her own, is not easily provoked, thinketh no evil; |
| 6 ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤ | 6 Rejoiceth not in iniquity, but rejoiceth in the truth; |
| 7 ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል። | 7 Beareth all things, believeth all things, hopeth all things, endureth all things. |
| 8 ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን ይሻራል። |
8 Charity never faileth: but whether there be prophecies, they shall fail; whether there be tongues, they shall cease; whether there be knowledge, it shall vanish away. |
| 9 ከእውቀት ከፍለን እናውቃለንና፥ ከትንቢትም ከፍለን እንናገራለንና፤ | 9 For we know in part, and we prophesy in part. |
| 10 ፍጹም የሆነ ሲመጣ ግን ተከፍሎ የነበረው ይሻራል። | 10 But when that which is perfect is come, then that which is in part shall be done away. |
| 11 ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፥ እንደ ልጅም አስብ ነበር፥ እንደ ልጅም እቈጥር ነበር፤ ጎልማሳ ሆኜ ግን የልጅነትን ጠባይ ሽሬአለሁ። |
11 When I was a child, I spake as a child, I understood as a child, I thought as a child: but when I became a man, I put away childish things. |
| 12 ዛሬስ በመስተዋት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፤ ዛሬስ ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ በዚያን ጊዜ ግን እኔ ደግሞ እንደ ታወቅሁ አውቃለሁ። |
12 For now we see through a glass, darkly; but then face to face: now I know in part; but then shall I know even as also I am known. |
| 13 እንዲህም ከሆነ፥ እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው። |
13 And now abideth faith, hope, charity, these three; but the greatest of these is charity. |
ሐዋሪያው ለጢሞትዮስ በመጨረሻው ዘመን እራስ ወዳድነት የሚያስጨንቅ ቀኖችን እደሚያመጣ እንዲህ ብሎ ያስረዳዋል።
“ 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3፡1 ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ
ይህን እወቅ። 2Tim 3፡1 This know also, that in the last days perilous times shall
come.” በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንደመጣ በዙሩያቹ ያሉትን ሚድያ ስሙ የምትሰሙት እየባሰበት የሚሄድ የሚያስጨንቅ ዜናን ነው። ባለንበት ዘመን እራስ ወዳድነት
የሚያስጨንቅ ቀኖችን እደዳመጣ በቁጥር 2 እናስተውላለን ያስረዳናልም። “2 ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና 2 For men shall be lovers of their own selves” ይህም ለእ/ር ፍቅር ተቃራኒ ነው። እስቲ አስጠሊታው እራስ ወዳድነት በሰው ማንነት ወስጥ ምንን እንደ ሚያዘጋጅ እንመልከት። እራሳችን የምንወድ ከሆነ ያለጥርጥር እነዚህን እንሆናለን
| “2 …ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥ |
| 3 ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥ |
| 4 ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤ |
| 5 የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ።” |
ምን አይነት አስቀያሚ ዝርዝር ነው? እራስ ወዳድነት ምንን እንደ ሚያዘጋጅ አስተዋላችሁ? መልሱ ታዲያ ምንድ ነው?
መልሱ ለእራስ እይወት መሞት ነው THE DEATH OF THE SELF-LIFE ይህ ለራስ ወዳድነት ፈጽሞ ተቃራኒ ነውና። እራስ ወዳድነት አስጨናቂ ዘመን
የሚያዘጋጅ ከሆነ እራስ ወዳድነት ከሂወታችን ሲሞት የሰላም ጊዜን ያዘጋጃል። የእ/ር ፍጥ ረት በዚህ መንገድ ድል ሲነሱ ያሳያል ለሳጋ ፈቃድ መሞት ለመንፈስ ህይወ ህያው መሆን ነውና።
“የዮሐንስ ራእይ 12፡11 እነርሱም ከበጉ ደም የተነሣ ከምስክራቸውም ቃል የተነሣ ድል ነሡት(ሰይጣንን)፥ ነፍሳቸውንም እስከ ሞት ድረስ አልወደዱም። Rev 12፡11 And they overcame him by the blood of the Lamb, and by the word of their testimony; and they loved not their lives unto the death.KJV.”
“Rev 12:11 But they overcame him( Satan ) by the blood of the Lamb and by the word of their testimony, and they did not love their lives so much that they were afraid to die.(NET)”
መልእክቱን በጌታ እየሱስ ቃል እንፈጽማለን
የማቴዎስ ወንጌል 16 Matt 16
| 25 ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፤ ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል። |
25 For whosoever will save his life shall lose it: and whosoever will lose his life for my sake shall find it. |
| 26 ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል? |
26 For what is a man profited, if he shall gain the whole world, and lose his own soul? or what shall a man give in exchange for his soul? |
አሜን!
Posted on 09/01/ 2011 by
wongelradio
Brother Binyam T. Alemayehu
Let the unselfish Christ Jesus mind be in you!