ትጋት diligence 1
ትጋት
diligence
መጽሐፈ ምሳሌ 12፡11 ምድሩን የሚሠራ ሰው እንጀራ ይጠግባል ለከንቱ ነገር የሚሮጥ ግን አእምሮ የጐደለው ነው። አዎን ትጋትን የሚተካ የለም!
መጽሐፈ ምሳሌ 19፡15 ተግባርን መፍታት እንቅልፍን ታመጣለች፥ የታካችም ነፍስ ትራባለች። አዎን ስራን መናቅ ስትጀምር አስቸጋሪ ህይወት ለመኖር መርጥሃል ማለት ነው::
መጽሐፈ ምሳሌ 10፡4 የታካች እጅ ችግረኛ ታደርጋለች የትጉ እጅ ግን ባለጠጋ ታደርጋለች። ተግተህ ከመስራት ውጪ መክበር የለም ተግተህ ካልሰራህ ምንም ክፍያ አታገኝምና::
መጽሐፈ ምሳሌ 13፡4 የታካች ሰው ነፍስ ትመኛለች አንዳችም አታገኝም የትጉ ነፍስ ግን ትጠግባለች። በትጋት ሳትሰራ መኖር ሳታውቅ መሞት ነው::
መጽሐፈ ምሳሌ 19፡24 ታካች ሰው እጁን በወጭቱ ያጠልቃታል፥ ወደ አፉ ስንኳ አይመልሳትም።ታካች የስንፍናው ብዛት እጁን ሰዶ ከመአዱ ለመብላት እንኻን ትጋት ያንሰዋል::
መጽሐፈ ምሳሌ 12፡11 ምድሩን የሚሠራ ሰው እንጀራ ይጠግባል ለከንቱ ነገር የሚሮጥ ግን አእምሮ የጐደለው ነው። ከንቱ ነገርን አታስብ እውነት የሆነውን ነገር አስብና ምድርህን እረስ እንጀራን ትጠግባለህ::
መጽሐፈ ኢዮብ 28:9 ሰው ወደ ቡላድ ድንጋይ እጁን ይዘረጋል፥ ተራራውንም ከመሠረቱ ይገለብጣል።
10 ከድንጋይ ውስጥ መንዶልዶያ ይወቅራል ዓይኑም ዕንቍን ሁሉ ታያለች።
11 ፈሳሹም እንዳይንጠባጠብ ይገድባል የተሰወረውንም ነገር ወደ ብርሃን ያወጣል። ትጉ ሰው የተገባር ሰው ነው ከድካሙም ፍሪ ይጠግባል: