Posted on March 01, 2012 Brother   Binyam T. Alemayehu

 

የያዕቆብ   መልእክት 5

  

Jas 5

19 ወንድሞቼ ሆይ፥ ከእናንተ ማንም ከእውነት ቢስት አንዱም ቢመልሰው፥ 19 Brethren, if any of you do err from the truth,   and one convert him;
20 ኃጢአተኛን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልሰው ነፍሱን ከሞት እንዲያድን፥ የኃጢአትንም ብዛት እንዲሸፍን ይወቅ። 20 Let him know, that he which converteth the   sinner from the error of his way shall save a soul from death, and shall hide   a multitude of sins.

 

ከቃሉ እንዳስተዋልነው የኃጢያትን ብዛት ሊሸፍን የሚችል ሃይል እንዳለ በዚህም ሃይል ጉልበት ሰው ሃጢያተኛውን ከተሳሳተበት መንገድ በመታደግ መልሶ ነፍሱን ከሞት ሊታደገው እንደሚችል ያስረዳናል።

 

ተመሳሳይ ሃሳብም በጴጥሮስ ላይ ያነሳል።“1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4፡8 ትጸልዩም ዘንድ በመጠን ኑሩ፤ ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናልና ከሁሉ በፊት እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።1Pet 4፡8 And above all things have fervent charity among yourselves: for charity shall cover the multitude of sins.”

በምሳሌ ደግሞ ክልሉን ሰፋ አድርጎ ሁሉን ይሸፍናል ይለናል።

“መጽሐፈ ምሳሌ 10፡12 ጥል ክርክርን ታስነሣለች ፍቅር ግን ኃጢአትን ሁሉ ትከድናለች።

KJV Prov 10፡12 Hatred stirreth up strifes: but love covereth all sins.” ፍቅር ሁሉን ይሸፍናል ይለናል። ፍቅር የሃላፊውን ጊዜ ቆፍሮ አያጋልጥም ሃጢያትም በሃላፊ ጊዜ በዛ ሰው ህይወ ላይ ይገዛ እንደ ነበር ብሎ በማስታወስ አያጠቃም  ፍቅር ግን ሁሉን ይሸፍናል ። ፍቅር እዳያሸንፍ አቅም ሊያሳጣው የሚችል የሃጢያት ትልቅ ያለም። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፡8 ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም ና 1Cor 13፡8 Charity (LOVE) never faileth:”

መቼም ኃጢአተኛው ከመንገዱ ተመልሶ በሕይወት ይኖር ዘንድ እንጂ ኃጢአተኛው ይሞት ዘንድ እ/ር እራሱ እንደማይፈቅድ ግልጽ ነው።

 KJV Ezek 18፡23 Have I any pleasure at all that the wicked should die? saith the Lord God: and not that he should return from his ways, and live?”

“ትንቢተ ሕዝቅኤል 18፡23 በውኑ ኃጢአተኛ ይሞት ዘንድ እፈቅዳለሁን? ይላል ጌታ እግዚአብሔር ከመንገዱስ ይመለስና በሕይወት ይኖር ዘንድ አይደለምን?

“ትንቢተ ሕዝቅኤል 33፡11 እኔ ሕያው ነኝና ኃጢአተኛው ከመንገዱ ተመልሶ በሕይወት ይኖር ዘንድ እንጂ ኃጢአተኛው ይሞት ዘንድ አልፈቅድም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ተመለሱ፥ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ ስለ ምንስ ትሞታላችሁ? በላቸው።

KJV Ezek 33፡11 Say unto them, As I live, saith the Lord God, I have no pleasure in the death of the wicked; but that the wicked turn from his way and live: turn ye, turn ye from your evil ways; for why will ye die, O house of Israel?”

በአረጌው አስተዳደር ህግ አከታትሎ የሚያገለግለው ኩነኔን ነበር፡ ሰው በህጉ በተደበደበ ቁጥር ከህጉ ጋር ሊመጥን እንደማይችል እየተሰማው ይመጣል። ከአሮጌው ስርአት ወደ አዲሱ ኪዳን የሙልአት ስርአት ሽግግር ላይ በመሆናችን  ብዙዎች እስከአሁን በህግ አገልግሎት ላይ ተቆናጠው

ትንቢተ ኢሳይያስ 58 Isa 58
1 በኃይልህ ጩኽ፥ አትቈጥብ፥ ድምፅህን እንደ መለከት አንሣ፥ ለሕዝቤ መተላለፋቸውን ለያዕቆብ ቤትም   ኃጢአታቸውን ንገር። 1 Cry aloud, spare not, lift up thy voice like a   trumpet, and shew my people their transgression, and the house of Jacob their   sins.

 

በእርግጥም ይህንን እ/ር ሰዎች ወደታች ወደጥፋት ጎዳና አቆልቁለው እዳይወርዱና ፈጽመው እንዳይጠፉ ለመገደብ  ይጠቀምበታል። በእርግጥም

መጽሐፈ ምሳሌ 27 Prov 27
5 የተገለጠ ዘለፋ ከተሰወረ ፍቅር ይሻላል። 5     Open rebuke is better than secret love.
6 የወዳጅ ማቍሰል የታመነ ነው የጠላት መሳም ግን የበዛ ነው። 6     Faithful are the wounds of a friend; but the kisses of an enemy are     deceitful.

አብዛኛውን ጊዜ ሁላችንም ሊያነቃንና እደቃሉጌታ ህያው ሊያደርገን ያስፈልጋል ሊያጠራንና ወዳየልን የክርስቶስ መልክ ሊያሳድገን ማለት ነው።

ግን ሌላም አዲስ አገልግሎት አለ ያም አስደናቂው ፍቅሩነው።

“2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡19 እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ ።

2Cor 5፡19 To wit, that God was in Christ, reconciling the world unto himself, not imputing their trespasses unto them.” በጥፋተኝነት በመኮነን ሳይሆን በፍቅር የከበረውን ለሰው ፊት ሳያደላ ከአባታችን ለሁሉ ሰው በነጻ የተሰጠውን ደህንነት መመስከር ይገባናል።

አዎን ፍቅር ሁሉን ይሸፍናል። ከማጋለጥ ይልቅ በስውር ይተዋል። ከመኮነን ይልቅ ያስታርቃል። የማይወደድቱንም ለፍቅር እዲለወጡና እጃቸእን እስኪሰጡ ደግሞም ከፍቅር ጋር እስኪዋሃዱ በፍቅር ይቀጥላል። እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ አሜን!

Posted on March 01, 2012

Brother Binyam T. Alemayehu