Posted on 8/25/ 2011

Brother Binyam T. Alemayehu

what do we mean when we pray deliver us from evil?

ከክፉው አድነን ብለን ስንጸልይ ምን ማለታችን ነው?

መቼም ጌታ ስለተናገራቸው ቃላቶች ስናስብ እርሱ በትንቢተ ኢሳይያስ 11፡3 እደሚናገረን “ ዓይኑም እንደምታይ አይፈርድም፥ ጆሮውም እንደምትሰማ አይበይንም”  ተብሎ እንደ ተጻፈ የሚፈርደው ከአይንና ከጆሮ ከሚያገኘው መረጃ ተነስቶ ሳይሆን የነገሮችን እውነተኛ ተፈጥሮ ስለ ሚገነዘብ ይበይናለ በዚህም ምክንያት በፍርዱም አይስትም እንዲያውም ወደ እውነት መርቶ ያድናል። “ትንቢተ ኢሳይያስ 53፡11 ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፥”  “Isa 53:11 by His knowledge of Himself [whichHe possesses and imparts to others] shall My [uncompromisingly] righteous One,
My Servant, justify many and make many righteous (upright and in right standing
with God),”  እንደ ምናስተውለው ጌታ በእውቀቱ ነው ቡዙዎችን ያጸደቀው(በእ/ር ፊት ትክክል)
ሆነው እዲቆሙ ያደረገው።

ታዲያ ይህ ጌታ ከክፉው አድነን ብለን እንድንጸልይ ሲነግረን ምን ነበር በአይምሮው የነበረው ? በክፉው እንዳንሸነፍ ጌታ ሊያድነን እደሚገባ የማያሻማ እውነት ነው። በጌታም አይምሮ ከክፉው መዳን እንዳለብን እውቀቱን ገልጾልናል። ክፉ ማለት ለጌታ እኛ ክፉ እንደ ምንለው አይደለም ። ክፉው ሃዘን፤ ጥፋት፤ ጦርነት፤ በሽታ፤ አደጋ፤ ወንጀል፤ እጽ፤ ጥላቻ፤  ስደት፤ መለየት፤
ትእቢት፤ ወዘተ… አለም ክፉ ብሎ በዘልማድ የሚጠራው ለእርሱ የክፉው ስራ ውጤቶች እንጂ በራሳቸው ምንጮች አይደሉም። የምንፈራውና ነጻ መውጣት ያስፈለገን ኩፉው የተበላሸው የሰው ልብ ነው።

“ኦሪትዘፍጥረት 6፡5 እግዚአብሔርም የሰው ክፉት በምድር ላይ እንደ በዛ፥ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደ ሆነ አየ።

Gen 6፡5 And God saw that the wickedness of man was great in the earth,
and that every imagination of the thoughts of his heart was only evil
continually.” “ትንቢተ ኤርምያስ 17፡9 የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ እጅግም ክፉ ነው ማንስ ያውቀዋል? Jer 17፡9 The heart is deceitful above all things, and desperately wicked: who can know it?”

“የማቴዎስወንጌል 15፡19 ከልብ ክፉ አሳብ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት መመስከር፥ ስድብ ይወጣልና።20 ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው። Matt 15፡19 For out of the heart proceed evil thoughts, murders, adulteries, fornications, thefts, false witness, blasphemies: 20 These are the things which defile a man” ያውላቹሁ እንግዲህ ክፉው ያለው በሰው ልብ ውስጥ ነው። ለዚህ እውነት መንቃት አለብን። ሰዎች ኩፉውን እዛማዶ ነው ብለው ያዩ ታል። እጃቸውንም በተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ይቀስራሉ። ያም በራሱ የተወሰነ እውነታ አለው የክፉው ስር እና መነሻው ግን የሰው ልብ ነው መዳን ያስፈለገንም ክፉው እሱ ነው ።

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2 Eph 21-2 በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው። 1 And you hath he quickened, who were dead in trespasses and sins; 2
Wherein in time past ye walked according to the course of this world, according
to the prince of the power of the air, the spirit that now worketh in the children of disobedience:

3 በእነዚህም ልጆች መካከል እኛ ሁላችን ደግሞ፥ የሥጋችንንና የልቡናችንን ፈቃድ እያደረግን፥ በሥጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበርን እንደ ሌሎቹም ደግሞ ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን።3 Among whom also we all had our conversation in times past in the lusts of our flesh, fulfilling the desires of the flesh and of the mind; and were by nature the children of wrath, even as others. ከፍጥረታችንየቁጣልጆች were by nature the children of wrath

በዚህ አለም ኩፉው ተገልጦ የሚታየው የክፉ የማምረቻ ፋብሪካው የሰው ልብ ስለሆነ ነው። ሰው ከዚህ ልቡ ካለው ክፉ ተፈጥሮ ሲድን የክፉ መገለጦች ይጠፋሉ። ሐዋሪያው ወደ ዚህ መረዳ ደርሶ ነበር። ታማኝሆኖም እውነቱን ነግሮናል። “ወደ ሮሜ ሰዎች 7፡18 በእኔ ማለት በሥጋዬ በጎ ነገር እንዳይኖር አውቃለሁና፤ … 24 እኔ ምንኛ ጎስቋላ ሰው ነኝ! ለዚህ ሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን ያድነኛል?” ክፉውና ከክፉው መዳን እየተካሄደ ያለው በልባችን ውስጥ ነው።

Posted on 8/25/ 2011

Brother Binyam T. Alemayehu

2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፡18 እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን።  THAT IS DELIVERANCE! መዳን ማለት ያ ነው። እ/ር ደረጃ በደረጃ ወደ መልኩ ሊለውጠን ቃል ገብተዋል። እ/ር ተናገረ ማለት ደግሞ ሆነ ማለት ነው። “2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1/2-3 የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። 4 ስለ ክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድትሆኑ፥ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን።” ከክፉ የመዳናችን ሚስጥር በፍጻሜው በባህሪው እንገኝ ዘንድ ነው። ባለፈው ጊዜ ካየነው በዚህ ላይ ይጠቅመናል ልጥቀሰው።

እ/ር የሰው ልጆችን ማዳን ወይም መዋጀት ያስፈለገው ከሲኦል አድኖ ወደ መንግስተ ሰማያት ለማሻገር አይደለም። በልምድ የሚነገር ካልሆነ በስተቀር የእ/ር ቃል በቀጥታ እደዛ የሚል በተወዳጁ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም። ከራሳቸው ሃጢያትና በውስጣቸው ከሚሰራው የአመጻ ሚስጥር በማንጻት አላቆ ወደ እ/ር መለኮታዊ ተፈጥሮና ባህሪ ለማምጣት ነው እንጂ። “የማቴዎስ ወንጌል 1፡21 ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።” አስተዋላችሁ ህዝቡ መዳን ያስፈለጋቸው ከገዛ ሃጢያታቸው እንጂ ከሲኦል አይደለም።

“የሐዋርያት ሥራ 3፡26 ለእናንተ አስቀድሞ እግዚአብሔር ብላቴናውን አስነሥቶ፥ እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ እየመለሰ ይባርካችሁ ዘንድ፥ ሰደደው።” Acts 3፡26 Unto you first God, having raised up his Son Jesus, sent him to bless you, in turning away every one of you from his iniquities. ደግሞም ወደ ቲቶ 2፡14 መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።

“ የእንግሊዝኛው ግልጽ መልእክቱን ስለሚያሳይ እንመልከተው “that hemight redeem us from all iniquity, and purify unto himself” ከቃሉ እንደምናስተውለው የተዋጀነው ከአንድ ማንነት ወደ ሌላ ማንነት ነው። ይህም ከአመጻ ሁሉ from all iniquity, አጥርቶ ወይም አንጽቶ ወደ ራሱ purify unto himself ነው እንጂ። የተዋጀነው ከቦታ ወደ ቦታ የጂኦግራፊ ወይም የካርታ ለውጥ ከሲኦል ወደሆነ ሩቅ ጠፈር ላይ የሚገኝ ገነት የተባለ ቦታ ወይም ፕላኔት ሰፈር ለመቀየር አይደለም። የተዋጀነው አመጻ ከተሞላ ማንነት ወደ ራሱ መልክና አምሳል ለማምጣት ነው። የመንጻሩም ሂደት በእሳቱ በማሳለፍ አመጻውን ሁሉ በመብላት ወደ መልኩ  ማምጣት ነው።

Mal 3፡2 But who may abide the day of his coming? and who shall stand when he appeareth? for he is like a refiner’s fire, and like fullers’ soap: 3 And he shall sit as a refiner and purifier of silver: and he shall purify the sons of Levi, and purge them as gold and silver, that they may offer unto the Lord an offering in righteousness.

ትንቢተ ሚልክያስ 3፡2 ነገር ግን እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳትና እንደ አጣቢ ሳሙና ነውና የሚመጣበትን ቀን መታገሥ የሚችል ማን ነው? እርሱስ በተገለጠ ጊዜ የሚቆም ማን ነው? 3 እርሱም ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያጠራ ሰው ይቀመጣል፥ የሌዊንም ልጆች ያጠራል፥ እንደ ወርቅና እንደ ብርም ያነጥራቸዋል እነርሱም ለእግዚአብሔር በጽድቅ ቍርባንን የሚያቀርቡ ይሆናሉ። የእሳቱአላማ ማንጠር ነው። አሜን!” “ከየኖኅ ዘመን እንደ ነበረ! ክፍል 2 የተጠቀሰው ተፈጸመ።”

ዳዊት መዝሙረ ዳዊት 51፡10 አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ። Ps 51፡10 Create in me a
clean heart, O God; and renew a right spirit within me. የገባው ነገር ስላለ ነው።  በእርግጠኝነት ከክርስቶስ የህይወት ውሃ  እየቀዳን የምንጠጣ ከሆነ ንጹህ ልብ ሊኖረን ግዴታ ነው። መዝሙረ ዳዊት 103፡1 ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ፥ አጥንቶቼም ሁሉ፥ የተቀደሰ ስሙን። Ps 103፡1 Bless the Lord, O my soul: and all that is within me, bless his holy name. በኛ ውስጥ ሁለንተናችን ቅዱስ ስሙን ሉያመሰግን የተገባው ነው።

ነብዩ ህዝቄል ከራእዮቹ በአንዱ እ/ር ወደ ግንቡ አመጣው ግንቡን ንደለውና የማሳይህ ነገር አለ አለው “ የቀደሙት እስራኤል በጨለማ የሚያደርጉትን በሃሳብ አደባባያቸው የሚያደርጉትን አሳየው።” ሕዝቄኤል8/1፡16 የሰው ልጅ ሆይ፥ የሚያደርጉትን፥ ከመቅደሴ ያርቁኝ ዘንድ የእስራኤል ቤት በዚህ የሚያደርጉትን ታላቁን ርኵሰት ታያለህን? ነብዩ ባየው ነገር ክው ብሎ ደንግጦ ነበር።  የተንቀሳቃሾችና የርኩሳን አራዊት ምሳሌ የእስራኤልንም ቤት ጣዖታት ሁሉ ተስለው በሃሳባቸው ግድግዶች ተለጥፈው ነበር። እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች በጨለማ እያንዳንዱ በስዕሉ ቤት የሚያደርጉትን አይተሃልን? እነርሱ። እግዚአብሔር አያየንም እግዚአብሔር ምድሪቱን ትቶአታል ይላሉና አለኝ። እርሱም፦ ደግሞ ተመልሰህ ከዚህ የበለጠውን የሚያደርጉትን ታላቅ ርኵሰት ታያለህ አለኝ። እነዚህ በእ/ር በተመረጠ ህዝብ መካከል ሽማግሌዎች ናቸው በልባቸው ከሚካሄደው ቢስትሊ ኔቸር አውሪያዊ ተፈጥሮ ግን ሲገለጥባቸው እናያለን። መጽሐፈ ምሳሌ 23፡7 ሰው በልቡ እንዳሰበ እንዲሁ ነው፡

በትክክል የውስጥ አደባባዮቻችን ሊነጹና ሊጸዱ ይገባል። እ/ር ይመስገን የእ/ር ቃል ፈጣንና የሚሰራ ሁለት አፍ ካለው ሰይፍ ይልቅ የተሳለና መለየት ያለበትን ሃሳብ ሁሉ የሚለይ ነው። ወደ ዕብራውያን 4፡12 የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤Heb 4፡12 For the word of God is quick, and powerful, and sharper than any twoedged sword, piercing even to the dividing asunder of soul and spirit, and of the joints and marrow, and is a discerner of the thoughts and intents of the heart.

ስለ  የልብ ጣዖቶች ጌታ ተናግሮት ነበረ ፥ ትንቢተ ሕዝቅኤል 14:4-5 ስለዚህ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሁሉም በጣዖቶቻቸው ከእኔ ተለይተዋልና የእስራኤልን ቤት በልባቸው እይዝ ዘንድ ከእስራኤል ቤት ጣዖቶቹን በልቡ የሚያኖር፥ የበደሉንም መቅሠፍት በፊቱ የሚያቆም ሰው ሁሉ ወደ ነቢዩ በመጣ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ጣዖታቱ ብዛት እመልስለታለሁ ብለህ ንገራቸው።

Ezek 14:4 Therefore speak unto them, and say unto them, Thus
saith the Lord God; Every man of the house of Israel that setteth up his idols
in his heart, and putteth the stumblingblock of his iniquity before his face,
and cometh to the prophet; I the Lord will answer him that cometh according to
the multitude of his idols; 5 That I may take the house of Israel in their own
heart, because they are all estranged from me through their idols. በ1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5፡21 ልጆች ሆይ፥ ከጣዖታት ራሳችሁን ጠብቁ። ይላል ጣዖታት ማለት የውሸት አምላ ምስል ማለት ነው።

የማርቆስ ወንጌል 9፥49 ሰው ሁሉ በእሳት ይቀመማልና፥ መሥዋዕትም ሁሉ በጨው ይቀመማል። ጌታ እውነት ነኝ ብለዋል ሰው ሁሉ በመንፈሳዊ እሳት ይቀመማል ካለ አሰራሩ ይለያይ እንጂ ማንም ከእ/ር እሳት የሚያመልጥ የለም ። ሁሉን በእሳት የሚያሳልፍ ጌታ እየሱስ እራሱ ነው። “የማቴዎስ ወንጌል 3፡11 እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤” ደግሞም Heb 12፡29 For our God is a consuming fire.  ወደ ዕብራውያን 12፡29 አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ( consuming የሚባላ) እሳት ነውና። በመገለጡ ወይም በመምጣቱ ሃጢያታችንና አመጻችን ከልባችን ይበላዋል። ከክፉውም ያድነናል። ብርሃን ለጨለማ እሳቱ ነውና ይበላዋል ጨለማ በብርሃን ፊት ህልውና የለውም።  “ኦሪት ዘዳግም 33፡2 እንዲህም አለ፦ እግዚአብሔር ከሲና መጣ፥ .. ከአእላፋትም ቅዱሳኑ መጣ፤ በስተ ቀኙም የእሳትሕግ ነበረላቸው። Deut 33፡2 And he said, The Lord came from Sinai, …and he came with ten thousands of saints: from hisright hand went a fiery law for them. ቃሉ እሳት ነው።

አምላካችን ድንገት ወደ መቅደሱ በእሳታዊ ባህርዩ ይመጣል ፍርድንም ከእ/ር ቤት ይጀምራል። በተመሰረትንበት መንፈሳዊ መሰረት ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የእሳቱ(የመለኮቱ ፤የመንፈሱ) ወጤቶች በሆኑ የመለኮት ባህሪያት ተምሳሌቶች በሆኑት በወርቁ በብር በከበረ ድንዳይ ሰርተን እንደሆነ እሳቱን ያልፋሉ እንዲያውም በክብር ይደምቃሉ ወይም የሰው ክብር ተምሳሌት በሆኑ በእንጨት በሳርም በአገዳም ካነጽን አገዳው ተረረረር እያለ ይነድልናል ሳሩም እየተንጣጣ ይነዳል ስራችን እሳቱ ሲገልጠው ከበላው ያማል መሰረታችን ግን ክርስቶስ ጽኑ ነውና አየየይ እያልን በሲቃ እንድናለን። የማንም ሥራ የተቃጠለበት ቢሆን ይጎዳበታል፥ እርሱ ራሱ ግን ይድናል ነገር ግን በእሳት እንደሚድን ይሆናል ። ማንም በእርሱ ላይ ያነጸው ሥራ ቢጸናለት ግን ደመወዙን ይቀበላል።

ትንቢተ ሚልክያስ 3                                            Mal3

2 ነገር ግን እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳትና እንደ አጣቢ ሳሙና ነውና የሚመጣበትን ቀን መታገሥ የሚችል ማን ነው? እርሱስ በተገለጠ ጊዜ የሚቆም ማን ነው?  2 But who may abide the day of his coming? and who shall stand when he appeareth? for he is like a refiner’s fire, and like fullers’ soap:

3 እርሱም ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያጠራ ሰው ይቀመጣል፥ .. ልጆችን ያጠራል፥ እንደ ወርቅና እንደ ብርም ያነጥራቸዋል እነርሱም ለእግዚአብሔር በጽድቅ ቍርባንን የሚያቀርቡ ይሆናሉ።     3 And he shall sit as a refiner
and purifier of silver: and he shall purify the sons…, and purge them as gold and silver, that they may offer unto the Lord an offering in righteousness. አሜን ጌታ ሆይ ከክፉው አድነን:: የማርቆስ ወንጌል 9፥49 ሰው ሁሉ በእሳት ይቀመማልና፥ መሥዋዕትም ሁሉ በጨው ይቀመማል። አንተን እንመስል ዘንድ በባህርይህ ቀምመን! አሜን! ተፈጸመ።

Posted on 8/25/ 2011

Brother Binyam T. Alemayehu